Logo
Getu Temesgen
🎭 የአንጋፋው አርቲስት ግዮን ዓለምሰገድ የክብር ምሽት! 🌟
#ethiopia | ​ከ"ፍቅር መጨረሻ" እስከ "ገዳይ"፤ ከመድረክ ቴአትር እስከ ቴሌቪዥን መስኮት... በገጸ-ባህሪያት ውስጥ ሕይወት እየዘራ ጥበብን ያከበረው ጉምቱው ባለሙያ አርቲስት ግዮን ዓለምሰገድ ሊመሰገን ነው!
​ብዙዎች "የሞተ ገጸ-ባህሪ ቢሰጡትም ከሞት ቀስቅሶ አላዘር ያደርገዋል" የሚሉለት ይህ ድንቅ ተዋናይ፣ ለሀገራችን ጥበብ ላበረከተው ድንቅ አስተዋጽኦ የሚገባውን ክብርና ምስጋና ይቸረው ዘንድ የጥበብ ወዳጆቹና ጓዶቹ ጥሪ አቅርበዋል።

​በዕለቱ ምን ይጠበቃል?

​🎬 ዘጋቢ ፊልም፦
ከታላቁ ጌትነት እንየው እስከ ሱራፌል ተካ ምስክርነት የተሰጠበትና የአርቲስቱን የሕይወትና የጥበብ ጉዞ የሚዘክር ድንቅ ፊልም ይቀርባል።

​🏆 የክብር ሽልማት፦
ለአርቲስቱ የሥራ አሻራ እውቅና የሚሰጥ የክብር ሽልማት ይበረከታል።

​🎁 የስጦታ መርሐ-ግብር፦
ከሀገር ውስጥ እስከ ባህር ማዶ ያላችሁ ወዳጆቹ በአይነትም ሆነ በገንዘብ ስጦታችሁን በማበርከት ምስጋናችሁን መግለጽ ትችላላችሁ።

​የዝግጅቱ ዝርዝር፦
​📅 እሁድ የካቲት 15 ቀን 2018 ዓ.ም.
​📍 ዩኒሰን ሆቴል (Unison Hotel)
​🕒 ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ

​ለበለጠ መረጃና ስጦታ ለማበርከት የኮሚቴ አባላትን ያነጋግሩ፦

📞 ስንታየሁ ገብሩ፡ 0910206765
📞 አበባው ደረበ (ኒቆ)፡ 0913504087
📞 ደሳለኝ ድረስ (መረዋ)፡ 0912491788
📞 ቻሌ ማረው (ቻቻ)፡ 0918766188

​ኑ!
የአስከበሩንን እናክብር፤ የሰሩልንን እናመስግን።

​#gyionalemseged #ethiopianart #theatre #cinema #recognition #ethiopia #artisthonor #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.