ዮናስ አብርሀም : በሬዲዮ ድራማ
ዕዝራ እጅጉ ( ተወዳጅ ሚድያ)
#ethiopia | ዮናስ አብርሃምን ሳውቀው በትክክል 28 ዓመት ከ7 ወር ይሆነዋል። ያስተዋወቀችኝም የሀይስኩል ጓደኛዬ እርቀሠላም በለጠ ናት። ያኔ 12ኛ ጨርሼ ፋና ስመላለስ ዮኒ ስመጥር ጋዜጠኛ ነበር። ከ11 ዓመት በኃላ በ2000 ሐምሌ ስቀጠር ደግሞ የመዝናኛ ክፍል ዐለቃዬ ሆኖ ተከሰተ። 2014 ላይ ደግሞ የዮኒን ታሪክ ከ180 ጋዜጠኞች ጋር የአማርኛ ኢንሳይክሎፒዲያ ( መዝገበ አእምሮ ),ላይ ሰነድኩት።
ዮናስ ከወርቅ ፀባዩ ጋር ለሁላችንም የሚመች ምርጥ ሰው መሆኑን በሙሉ አንደበት እመሰክራለሁ ። የሥራ ትጋቱና ለሙያው ያለው መሰጠትም የተለየ ነው። አንድ ቀን በአደባባይ ስናመሰግነው ዝርዝሩን አወራለሁ። አሁን ግን ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ላቅና።
ዛሬ ታህሳስ 24 2018 ዮናስ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ተማሪዎች በሬድዮ ድራማ አሠራር ዙሪያ ልምዱን አካፍሎ ነበር።
ተወዳጁ የሬድዮ ጋዜጠኛ፣ ደራሲና አዘጋጁ ዮናስ አብርሃም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር እና ፊልም ጥበባት ት/ቤት በመገኘት በማታው መርኃ - ግብር (Extension) ለሚማሩ የ4ኛ ዓመት የቴአትር ተማሪዎች በተግባር የታገዘ የልምድ ልውውጥ ስልጠና እና ልምዱን በማካፈሉ ብዙዎች ርካታና ደስታቸውን ገልፀዋል።
የሬድዮ ድራማ ከቴአትር እና ፊልም ትወና [Acting for different media (theatre, film, TV, voiceover, digital) ] የሚለይበትን ይህንኑ ስልጠናም የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች እንዲሁም በእለቱ ለተገኙ ታዳሚያን በባሕል ማዕከል አዳራሽ በመገኘት ስልጠናውን በተሳካ ሁኔታ ሰጥቷል፡፡
የቴአትር እና የፊልም ጥበባት ትምህርት ቤቱም ስልጠናውን ለሰጠላቸው ለተወዳጁ የሬዲዮ ጋዜጠኛ እና ደራሲ ዮናስ አብርሃም ያለውን አክብሮት እና ምስጋና ገልጿል። ለወደፊትም ተመሳሳይ ፕሮግራሞችን ከሌሎች እውቅ የዘርፉ ባለሙያዎች እና ምሁራን ጋር በመተባበር ባለሙያዎቹ ልምዳቸውን ለተማሪዎቻችን የሚያካፍሉበት ሁኔታ እንደሚቀጥል የትምህርት ክፍሉ ያምናል።
ዮናስ ምርጥ ጊዜ እንደነበረው ነግሮኛል። ተማሪዎቹም ሁሉም ተደስተዋል። በድጋሚ እንዲመጣም ጠይቀዋል።
▸ ስለ ሬድዮ ድራማ ስክሪፕት አፃፃፍ/Voice Theatre/
▸ ስለ ሬድዮ ተዋናይነት ልዩ ባህሪ /Sound Acters/
▸ ስለ ሬድዮ ድራማ ዓይነቶች፣
▸ ከሌላው ዘርፍ ጋር ያላቸው ልዩነት እና አንድነት፣
▸ የሬድዮ ድራማ ዓላማ፣ ግብ፣ ሥነምግባር... ላይ ዕውቀቱን አካፍሏል።
▸ የ31 አመት የመፃፍና የማዘጋጀት ሠፊ የሥራ ልምዱን ተሞክሮ ማጋራቱ ይበል ያሰኛል።
የዮናስ አብርሃም ሥራዎች በቁጥር ሲገለፁ:-
● ፅሑፍ/script
▸ በየቀኑ - በአማካይ 20 ገፅ ይፅፋል፣
▸ በወር - 600 ገፅ፣
▸ በአመት - 7,200 ገፅ፣
▸ በ31 አመት - 223,200 ገፅ አየር ላይ አውሏል።
▸ ድራማ - 1/4ኛውን ይይዛል፤ 56 ሺ ገፅ ፅፏል፤
▸ ሬድዮ ፋና ላይ ብቻ ከ42 በላይ ድራማዎች፣ "ትንንሽ ፀሐዮች" (እማማ ጨቤ) እና "የጨረቃ ውል" ድራማን ሳይጨምር። እነሱ ብቻቸውን 5 አመት ተኩል እና 2 አመት ተኩል ተላልፈዋል።
▸ ዋዜማ፣ የበዓል ቀን ጠዋትና ማታ የተላለፉ ባለ 3 ክፍሎችን የበዓል ልዩ ድራማዎች አልቆጠረም።
➙ ከ124 በዓላት በላይ ፅፏል = 372 ክፍሎች ይሆናሉ።
➙ ሃምሣ ስድስት ሺህ ገፅ ወደ ባለ 250 ገፅ መፅሐፍ ቢመነዘር = 223 መፅሐፍ ይሆናል።
● ቅንብር/production
▸ ቢያንስ በሣምንት 2 = በ52 ሣምንት 104፣
▸ በ1612 ሣምንት (31አመት) = 3,224 ቅንብር።
● ግጥም
▸ በወር በአማካይ ከ 7 > በላይ = በአመት በአማካይ 50 =1600 አካባቢ የግጥም ሥራዎች።
● ጭውውት
▸ የሺና ስለሺን ጨምሮ = በአማካይ 1,200 ዓይነት ጭውውቶች ፅፏል።
● ማሥታወቂያ
▸ ድሮ ለሬድዮ ፋና ከፃፈው ጀምሮ አሁንም በገቢ ምንጭነት ለኤጀንቶች የያዘጋጃቸው ስክሪፕቶች በጠቅላላ ከ6ሺ በላይ ይሆናሉ።
● በድምፅ
▸ አየር ላይ የዋለበት ጊዜ ቢቆጠር... ከግማሽ በላይ ዕድሜውን ሬድዮ ውስጥ የኖረ ነው። ዮናስን እጅግ የማደንቀው በምክንያት ነው።

5 months ago