8 months ago
በግብር ህጉ መሰረት ኪሳራን ስንት ግዜ ማሸጋገር ይፈቀዳል ❓
(Loss carry forward)
#ethiopia | ግብር ከፋይ ሁልግዜ ትርፍ ሊያተርፍ አይችልም አንዳንድ ግዜ ኪሳራም ያጋጥመዋል ፡፡ እዚህ ጋር በጥንቃቄ መታየት ያለበት ነገር ቢኖር የግብር ህግ የኪሳራ ትርጉም የተለየ መሆኑን ነው ፡፡
በግብር ህጉ የኪሳራ ትርጉም ❓
በገቢ ግብር አዋጁ አንቀጽ 26(1) መሰረት ለግብር ዓመቱ ተቀናሽ የሚደረገው ወጪ ግብር ከፋዩ በግብር ዓመቱ ካገኘው ጠቅላላ ገቢ ከበለጠ በብልጫ የታየው የገንዘብ መጠን ግብር ከፋዩ የደረሰበት ኪሳራ ይሆናል፡፡ በመሆኑም ኪሳራን ለማስላት ከግምት የምናስገባው ሁሉንም ነጋዴው ያወጣውን ወጪ ሳይሆን በግብር ህጉ መሰረት የተፈቀዱ ወጪዎች ብቻ ናቸው ፡፡
ግብር ከፋይ በአንድ ግብር አመት ኪሳራ ካጋጠመው ይህንኑ ኪሳራ ከሚቀጠለው የግብር አመት ከሚገኝ ገቢ ላይ እንደወጪ በመያዝ ሊቀንስ ይችላል ፡፡ የዚህ አመት ኪሳራ የሚቀጥለው አመት ተቀናሽ ይሆናል ማለት ነው ፡፡
በአንድ አመት ያጋጠመ ኪሳራ እየተሸጋገረ ለተከታታይ ለአምስት አመታት ከሚገኝ ገቢ ላይ እየተቀነሰ ሊሄድ ይችላል ፡፡ ይህም ማለት ኪሳራው ተቀንሶ እስከሚያልቅ ድረስ ግብር ከፋዩ የገቢ ግብር አይከፍልም፡፡
ኪሳራ የሚየሳይ ግብር ከፋይ ቀደም ብሎ ሂሳቡን በገለልተኛ ❗የውጪ ኦዲተር ❗በማስመርመር ይህንኑ ሰነድ ለግብር ባለስጣኑ ማቅረብ አለበት ፡፡ ይህም ማለት በራሱ የሂሳብ ባለሙያ ተሰርቶ የሚቀርብ የሂሳብ መዝግብ ለኪሳራ ማሸጋገር ተቀባይነት የለውም፡፡
በአንቀጽ 26(4) እንደተቀመጠው ግብር ከፋዩ በግብር እድሜው( በምስረታ እና ስራ በሚያቆምበት ሰአት) ኪሳራውን ሊያሸጋገር የሚችለው ለሁለት ግዜያት ወይንም ተከታታይ አስር አመታት ብቻ ነው ፡፡
አንድ ነጋዴ ከሁለት ግዜ በላይ ሊከስር እንደሚችል ይገመታል ነገር ግን የግብር ህጉ እያለ ያለው ስንት ግዜም ብትከስር እኔ የማይልህ የሁለት ግዜ ብቻ ነው እያለ ነው ፡፡ በነገራችን ላይ ሁለት ግዜ ኪሳራ ማለት ለተከታታይ አስር አመታት ግብር ከፋዩ ግብር አይከፍልም ማለት ነው ፡፡
ከተፈቀደው ግዜ ውጪ የሚመጣን ኪሳራ በተመለከተ ኪሳራ ያሳየበት መዝገብ ውድቅ እየተደረገ የግብር ከፋዩ ግብር በግምት እንዲከፍል ይገደዳል ፡፡
#taxawareness #taxeducation #taxcompliance
በህግ ባለሙያ ዮሴፍ አለሙ (LLB,LLM) የተዘጋጀ
ከጠበቃ እና የህግ አማካሪ ፋንታሁን ደለለው
ለ Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

Comments