Logo
Getu Temesgen
⚽️ የፍቅር ስጦታ ከሜዳው ባለውለታ፦
አሸናፊ ግርማ (ሳቪዮላ) ተተኪዎችን አበረታታ! 🇪🇹✨

​በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ስሙ በደማቁ የተጻፈው፣ የኢትዮጵያ ቡና እና የዋሊያዎቹ ድንቅ ኮከብ አሸናፊ ግርማ ዛሬ ማምሻውን በመስቀል ፍላወር 35 ሜዳ በመገኘት ለተስፋ ለስፖርት ቡድን አባላት የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል። አያይዞም ስፖርታዊ ልምዱን፤ ምክሩን አካፍሏል።

​ስለ አሸናፊ ግርማ (ሳቪዮላ) በጥቂቱ፦

​🏆 ድርብ ኮከብ፦
ሁለት ጊዜ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ የተመረጠ የጥበብ ተምሳሌት።

​🥇 የዋንጫ ባለቤት፦
ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የጥሎ ማለፍና የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫን ያነሳ።

​🇪🇹 ብሔራዊ ጀግና፦
በዋሊያዎቹ ማሊያ ሦስት የሴካፋ ዋንጫዎችን የሳመ ባለታሪክ።

​📚 ባለታሪክ፦
የሕይወት ጉዞው "ከአሸዋ ሜዳ እስከ አርጀንቲና" በተሰኘው መጽሐፉ በሰፊው ተተርኳል።

​አሁኑኑ ኑሮውን በቶሮንቶ፣ ካናዳ 🇨🇦 ያደረገው አሹ፣ ወደ ሀገሩ ሲመጣ የወጣቶቹን ስፖርተኞች ተስፋ ለማለምለም ኳሶችና የተለያዩ የመለማመጃ ትጥቆችን በስጦታ አበርክቷል።

እናንት ያገሬ ልጆች
​"መሥራት ጀግንነት ነው፤ ማድነቅ ደግሞ መሰልጠን ነው!" ለዚህ ድንቅ ባለሙያ ምስጋና ይገባዋል።

​#ashenafigirma #saviola #ethiopianfootball #ethiopiancoffee #walias #sportsupport #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.