2 months ago
ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ከቭላድሚር ፑቲን ጋር በአካል ለመወያየት ጥሪ አቀረቡ
#ethiopia | ዩክሬንና ሩሲያ በቀጥታ በመገናኘት ጦርነቱን እንዲያቆሙ የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ (ቪዲዮ) ለሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በጻፉት ግልጽ ደብዳቤ በአካል ለመገናኘት ጥሪ ማቅረባቸው ተሰማ።
የአሜሪካ ትኩረት ሙሉ በሙሉ ወደ ኢራን ጉዳይ በዞረበት በዚህ ወቅት፣ ጦርነቱ እንደገና የአሜሪካ ቀዳሚ አጀንዳ እስኪሆን ድረስ ዝም ብሎ መጠበቅ ስህተት መሆኑን እና ሰላም ሊመጣ የሚችለው በሁለቱ አገራት ቀጥተኛ ንግግር ብቻ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል።
ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ለሚካሄደው ድርድር እንዲረዳ ሙሉ የተኩስ አቁም እንዲታወጅ የጠየቁ ቢሆንም፣ ቭላድሚር ፑቲን ግን ከዚህ ቀደም የተኩስ አቁም ጥያቄውን ውድቅ አድርገውታል።
የክሬምሊን ቤተ መንግሥት ደብዳቤው እንደደረሰውና ለፑቲን ገለጻ እንደሚደረግላቸው ያረጋገጠ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም ሩሲያ ዘለንስኪ ወደ ሞስኮ መጥተው መወያየት እንደሚችሉ ገልጻ ነበር።
ቭላድሚር ፑቲን ስምምነት ለማድረግ ፈቃደኛ መሆናቸውን ቢናገሩም፣ ዩክሬን ዶኔትስክ፣ ሉሃንስክ፣ ኬርሰን እና ዛፖሪዢያ ከተባሉ አራት ክልሎች እንድትወጣ እና የኔቶ አባል የመሆን ጥረቷን እንድታቆም የሚሉትን ጠንካራ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጠዋል፡፡
ዩክሬን ግን ይህንን ግዛቶቿን አሳልፋ መስጠት የሩሲያን ዳግም ወረራ የሚያበረታታ መሆኑን በመግለጽ የሩሲያን ቅድመ ሁኔታዎች ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርጋለች።
በሌላ በኩል የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሁለቱ መሪዎች መገናኘት "በጣም ጥሩ ነገር ነው" ሲሉ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጋዜጣ + #russian #uk #peace #nowar

4 months ago
አብዛኛው አሜሪካዊ ከኢራን ጋር የሚደረገው ጦርነት በአስቸኳይ እንዲቆም መጠየቁ ተገለጠ
#ethiopia | አዲስ የሕዝብ አስተያየት መለኪያ እንደሚያመለክተው፣ አብዛኛው የአሜሪካ ሕዝብ ሀገሪቱ ከኢራን ጋር ከምትሰነዝረው ወታደራዊ ጥቃት እንድትወጣና ግጭቱ በአስቸኳይ እንዲቆም እንደሚፈልግ አመልክቷል።
66% የሚሆኑ አሜሪካውያን ውጤቱ ሽንፈት ቢሆን እንኳ አሜሪካ ከኢራን ጋር ከሚደረግ ማንኛውም ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንድትወጣ ይፈልጋሉ።
60% የሚሆኑት ዜጎች አሜሪካ በኢራን ላይ የምታካሂደውን ወታደራዊ ጥቃት እንደማይቀበሉ ገልጸዋል።
40% የሚሆኑት የሪፐብሊካን ደጋፊዎችም ጥቃቱ በአስቸኳይ እንዲቆም ፍላጎታቸውን ገልጸዋል፤ ይህም በሀገሪቱ የፖለቲካ ውሳኔ ሰጪዎች ላይ ከፍተኛ ጫና ሊፈጥር እንደሚችል ተገምቷል።
ይህ የሕዝብ ስሜት አሜሪካውያን ከቀድሞዎቹ የኢራቅና አፍጋኒስታን ጦርነቶች በመነሳት ለዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ ቅድሚያ እየሰጡ መሆኑን ያሳያል ተብሏል።
#usa #iran #breakingnews #peace #reuters #ipsos #getutemesgen #ethiopianjournalist #warpost #globalnews #addisababa #ethiopia #nowar #foreignpolicy

ሁሉም ቆም ብሎ ያስብ! — አገር እንደ ዕንቁላል ናት
#ethiopia | የዓለማችን ሁኔታ በተለይም በመካከለኛው ምስራቅ (ቴህራንና ቴል አቪቭ) የሚታየው እልቂትና ውድመት ተስፋ አስቆራጭ እየሆነ መጥቷል።
ለዘመናት የተገነቡ የቴክኖሎጂ ማምረቻዎች፣ የጥበብ ውጤቶችና ውብ ከተሞች በአንድ ጀምበር ወደ አመድነት ሲቀየሩ ማየት "ማውደም እንዴት ቀላል ነው?" ያስብላል።
የዓለምን ጥፋት ቆመን የምንመለከት ኢትዮጵያውያን ሁሉ፣ ዛሬ ከትንንሽ የሴራና የመጠፋፋት አዙሪቶች የምንወጣበት ጊዜ አሁን ነው።
ከግጭትና ከጦርነት አሸናፊ/ተሸናፊነት ትምክህት ወጥተን አገርን በንቃት እንጠብቅ።
ቂም፣ ጥላቻና መገፋፋት አገርን አያጸኑም፤ ይልቁንም ያፈርሳሉ። አገር እንደ ዕንቁላል ናትና ከወደቀች መጠገን እንደማይቻል ከታሪክ እንማር።
"እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል" እና "እኔ ምን አገባኝ" የሚሉ አጥፊ አስተሳሰቦች እሳት ታቅፎ እንደ መተኛት አደገኛ ናቸው።
መንግስትም ሆነ መሪ ያልፋሉ፤ ቀሪዋ ግን አገር ናት። ለትውልድ የምትተርፍ አገር እንድትኖረን መተሳሰብና መከባበር ምርጫ የሌለው መንገድ ነው።
"አረረም መረረም ለአገር ሰላምና ደህንነት፣ ለህዝቦች ሉአላዊ ክብርና ማህበራዊ እሴቶች ሁሉም ዘብ ይቁም!"
🙏 የጋራ ጸሎታችን፡
አምላክ ከምድር ጥፋት ሁሉ ይጠብቀን! አገራችንንና ሕዝባችንን በሰላም ያቆይልን። አሜን!
(ንጉሥ ወዳጅ ነው)
#getu #getutemesgen #ጌጡ #ethiopia #peace #nationalunity #humanity #nowar #ኢትዮጵያ #ሰላም #አንድነት #ንቁ_እንጠብቅ

Comments