ውኃ የሚወቅጠው የግብጽ ዲፕሎማሲ እና የማይቀለበሰው የኢትዮጵያ ልማት
*********************
የግብፅ የውኃ ሀብት እና መስኖ ሚኒስቴር “በዓለም አቀፍ ሕግ መርሆዎች ላይ የተመሰረተ የውኃ መብቴን ለማስከበር ቁርጠኛ ነኝ” በሚል ያወጣው መግለጫ፣ የካይሮ ፖለቲከኞች ለዘመናት ሲያላምጡት የኖሩትና አሁንም መላቀቅ ያቃታቸው የተለመደ የሚዲያ ፍጆታ ነው።
ይህ መግለጫ መሬት ላይ ካለው ነባራዊ እውነት ጋር የማይገናኝ ነው፡፡ ዋናው ዓላማውም ኢትዮጵያ በውኃ ሀብቷ እያስመዘገበች ያለው የልማት ስኬት እና የጂኦ-ፖለቲካዊ ሚዛን ለውጥ የፈጠረባቸውን የሥነ-ልቦና መረበሽ ለመሸፈን የሚደረግ መፍጨርጨር ነው።
ካይሮ ዓለም አቀፍ ሕግን እንደ ሽፋን ብትጠቀምም፣ ትክክለኛው የውስጥ ሕመሟ የውኃ እጥረት ሳይሆን፣ የኢትዮጵያን ማንሰራራት እንደ ስጋት የመመልከትና የተፈጥሮ ሃብቷን ለመጠቀም የምታደርገውን ጥረት ለመግታት ያለመ ነው።
ግብፅ በረሃን እያለማች፣ ቶሽካን በመሳሰሉ ፕሮጀክቶች ከፍተኛ ውኃ የሚጠይቁ ሰብሎችን በበረሃ እያመረተች፣ በሌላ በኩል ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጸጋዋን ተጠቅማ ዜጎቿን ከድህነት ለማውጣት የምታደርገውን ጥረት እንደ ሥጋት መመልከቷ የፖለቲካ ግብዝነቷ ማሳያ ነው።
ታሪካዊ ዳራዎችን ወደ ኋላ መለስ ብለን ስንፈትሽ ግብፅ ኢትዮጵያን በውኃ ሀብቷ እንዳትጠቀም ስትጎነጉነው የኖረችው ሤራ ዘርፈ ብዙ ነው። በአንድ በኩል ኢትዮጵያ ፈፅሞ ዕውቅና ያልሰጠቻቸውን የ1929 እና የ1959 (እ.አ.አ) የቅኝ ግዛት ውሎችን እንደ ብቸኛ የሕግ ማዕቀፍ እያነሳች ለማስፈራራት ትሞክራለች።
በሌላ በኩል ደግሞ፣ ኢትዮጵያ የውኃ ሃብቷን ለማልማት ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ብድር እና እርዳታ እንዳይሰጧት ያልቆፈረችው የዲፕሎማሲ ጉድጓድ አልነበረም።
ከዚህም አልፎ ኢትዮጵያ ዕረፍት አግኝታ ወደ ልማቷ እንዳታተኩር የውስጥ ግጭቶችን በሎጂስቲክስ እና በፋይናንስ በመደገፍ እንዲሁም ፀረ-ሰላም ኃይሎችን በማሰባሰብ የዜሮ ድምር ፖለቲካ ስታራምድ ኖራለች።
ይሁን እንጂ ይህ የዘመናት ሤራ ከሽፎ፣ ኢትዮጵያ የውጭ የፋይናንስ በሮች መዘጋትን በገዛ ዜጎቿ አቅምና ላብ ተክታ ልማቷን እውን ስታደርግ ማየቷ ካይሮን ወደ ያልተገባ መደናገጥ ከትቷታል። የአሁኑ መሠረተ ቢስ መግለጫም የዚሁ ድንጋጤ ማስተጋቢያ ነው።
የኢትዮጵያ በዓባይ ውኃ ላይ ያላት አቋም ከመቼውም ጊዜ በላይ የጠራ፣ ዓለም አቀፍ የውኃ ሕግጋትን ያከበረ እና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሠረተ ነው።
ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ስትገነባም ሌሎች የተፋሰሱን ሀገራት በማግለል ሳይሆን፣ በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ላይ ተመስርታ ነው። ለዚህም ማሳያው ግድቡ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ጋር ያደረገችው ተከታታይ ውይይት እና ያሳየችው ግልፅነት ነው።
ከዚህም ባሻገር የናይል ተፋሰስ ሀገራት የትብብር ማዕቀፍ (CFA) በቅርቡ ወደ ትግበራ መግባቱ የጋራ ተጠቃሚነትን በተግባር ያረጋገጠ እና የግብፅን የብቻ የበላይነት ፍላጎት ሕገ-ወጥነት ያጋለጠ ትልቅ ፖለቲካዊ እና ሕጋዊ ድል ነው።
የግብፅ የአሁኑ ጥያቄ እና ጩኸት ጊዜ ያለፈበት እና አዲሱን የዓለም ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ ነው። ካይሮ ጉዳዩ ፈፅሞ የማይመለከታቸውን የሩቅ ኃይሎችና ተቋማት ደቦ በመሰብሰብ ኢትዮጵያ ላይ ጫና ለመፍጠር የምታደርገው ጥረት ዛሬ ላይ ውኃ አያነሳም።
የኢትዮጵያ ሕዝብም ሆነ መንግሥት በዲፕሎማሲ ጫና እጁ የማይጠመዘዝ መሆኑን በሕዳሴው ግድብ ስኬት በተግባር አሳይቷል።
በመሆኑም ለግብፅ የሚበጃት ብቸኛው አዋጭ አማራጭ ከንቱ ከሆነው የሚዲያ ፕሮፓጋንዳ እና የደቦ ዲፕሎማሲ ወጥታ፣ አዲሱን የትብብር ማዕቀፍ (CFA) በመቀበል ከኢትዮጵያ እና ከተቀሩት የተፋሰሱ ሀገራት ጋር በጋራ መሥራት ብቻ ነው።
በለሚ ታደሰ
#ebc #ethiopia #gerd #nilebasin #africansolutions #abay #diplomacy

13 days ago