5 months ago
የትራምፕ ገሃነም
#ethiopia | የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሃማስ በአስቸኳይ ትጥቅ ካልፈታ "ገሃነም ይጠብቀዋል" ሲሉ ዝተዋል። ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያሉት ሰኞ ዕለት በፍሎሪዳ ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር ባደረጉት ስብሰባ ወቅት ነው።
ትራምፕ ያቀረቡት ባለ 20 ነጥብ የሰላም ዕቅድ ሃማስ ትጥቅ እንዲፈታ የሚጠይቅ ሲሆን፣ ዕቅዱን "በጣም በፍጥነት" ወደ ሁለተኛው ምዕራፍ ለማሸጋገር ተስፋ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
እስራኤል በጋዛ ወታደራዊ እርምጃዋን ብትቀጥልም፣ የዩናይትድ ስቴትስን ዕቅድ መቶ በመቶ እየተገበረች መሆኑን ፕሬዝዳንቱ አረጋግጠዋል።
ኢራን የኒውክሌር ፕሮግራሟን ወይም የባለስቲክ ሚሳኤል ግንባታዋን በድጋሚ ከጀመረች፣ አሜሪካ ከፍተኛ ወታደራዊ ጥቃት እንደምትሰነዝር አስጠንቅቀዋል።
የኢራን ከፍተኛ የፖለቲካ አማካሪ አሊ ሻምኻኒ በበኩላቸው፣ በማንኛውም የጠብ አጫሪነት ተግባር ላይ ሀገራቸው "ፈጣን እና የከፋ ምላሽ" እንደምትሰጥ በኤክስ (X) ገጻቸው መልሰዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ዓለም_አቀፍ_ፖለቲካ #የመካከለኛው_ምስራቅ_ውጥረት #trump #netanyahu #israel #hamas #iran #gazapeaceplan #usa #middleeast #geopolitics