የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በተለያዩ ዙሮች በስኬት እየተካሄደ ነው፡-የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
**************
የ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በተለያዩ ዙሮች በስኬት እየተካሄደ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ።
አገልግሎቱ እንዳመለከተው፣ ፈተናው በአብዛኛው በበይነ መረብ (ኦንላይን) እየተሰጠ ሲሆን፣ ተፈታኞች በስድስት ዙሮች ተከፋፍለው በተሳካ ሁኔታ ፈተናቸውን እየወሰዱ ይገኛሉ።
ሆኖም የተወሰኑ የመሠረተ ልማት ተደራሽነትና የኮምፒውተር እጥረት ባለባቸው አካባቢዎች ፈተናውን በአራት ዙሮች በወረቀት ለመስጠት አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉ ተገልጿል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በበይነ መረብ ለመፈተን ለተመዘገቡ 14 ሺህ 755 ተፈታኞች በስድስቱ ዙር ከሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ፈተናው እየተሰጠ ይገኛል።
በሌላ በኩል በወረቀት ለመፈተን ለተመዘገቡ 15 ሺህ 325 የክልሉ ተፈታኞች ፈተናው ከሐምሌ 22 እስከ 24 ቀን 2018 ዓ.ም በመቐለ እና በአክሱም ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ ተመላክቷል።
እነዚህ በወረቀት የሚፈተኑ ተማሪዎች ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ወደ መቐለ እና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች በመግባት፣ ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም የሚሰጠውን ገለጻ (ኦሬንቴሽን) በመከታተል ፈተናቸውን መውሰድ እንደሚችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ጨምሮ ገልጿል።
#ethiopianbroadcastingcorporation #grade12exam #nationalexam #mekelleuniversity #axumuniversity

1 month ago