Logo
EBC
በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና እየተሰጠ ነው
******************

የትግራይ ክልል ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና በአዲስ አበባ፣ በመቐለ እና በአክሱም ዩኒቨርሲቲዎች ማዕከላት በወረቀት እና በበይነ-መረብ መውሰድ ጀምረዋል።

በትምህርት ሚኒስቴር እና በፌዴራል መንግሥት የተደረገውን አጠቃላይ ርብርብ ተከትሎ አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ሥራ ተጠናቅቆ ተማሪዎች ወደ ፈተና አዳራሾች ገብተዋል።

ተማሪዎቹ ያለምንም እንግልትና ሥጋት ሂደቱን እንዲከታተሉ የጸጥታና የትምህርት ባለሙያዎች የተቀናጀ ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ።

በዘንድሮው መርሐ ግብርም 30 ሺህ ገደማ የክልሉ ተማሪዎች በፈተናው በመሳተፍ ላይ እንደሆኑ ተገልጿል።

ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፤ የፈተናው መጀመር በክልሉ የሚገኙ ወጣቶች የወደፊት ዕጣ ፈንታ እንዲቃና እና የቋረጡትን ትምህርት በዘላቂነት እንዲቀጥሉ የሚያስችል ትልቅ ማኅበራዊና ሥነ-ልቦናዊ ፋይዳ ያለው ነው።
#ethiopia #ebc #tigraystudents #nationalexam #educationforall

11 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.