2 days ago
#mekelleuniversity
መቐለ ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም ለተመደቡ አዲሰ ገቢ የቅድመ-ምረቃ እና የሪሚዲያል ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ጊዜን ወደፊት እንደሚያሳውቅ ገልጿል።
በሌላ በኩል የሁሉም የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች የ2019 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ረቡዕ ጥቅምት 04/2019 ዓ.ም የሚጀመር መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
@tikvahuniversity #moe ትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ ለነበሩ ነባር ተማሪዎች ካደረገው ጊዜያዊ ምደባ ጋር በተያያዘ ለቀረቡ ቅሬታዎች የማጣራት ሥራ አጠናቆ ምላሽ ሰጥቷል። በጊዜያዊነት የተመደባችሁበትን ዩኒቨርሲቲ ለመመልከት 👇 https://student.ethernet.e... የምደባ መረጃችሁ በቀጥታ ለየዩኒቨርሲቲዎቹ የሚላክ ሲሆን፣ ተቋማቱ በሚያወጡት…

3 months ago
የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በተለያዩ ዙሮች በስኬት እየተካሄደ ነው፡-የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
**************
የ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በተለያዩ ዙሮች በስኬት እየተካሄደ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ።
አገልግሎቱ እንዳመለከተው፣ ፈተናው በአብዛኛው በበይነ መረብ (ኦንላይን) እየተሰጠ ሲሆን፣ ተፈታኞች በስድስት ዙሮች ተከፋፍለው በተሳካ ሁኔታ ፈተናቸውን እየወሰዱ ይገኛሉ።
ሆኖም የተወሰኑ የመሠረተ ልማት ተደራሽነትና የኮምፒውተር እጥረት ባለባቸው አካባቢዎች ፈተናውን በአራት ዙሮች በወረቀት ለመስጠት አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉ ተገልጿል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በበይነ መረብ ለመፈተን ለተመዘገቡ 14 ሺህ 755 ተፈታኞች በስድስቱ ዙር ከሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ፈተናው እየተሰጠ ይገኛል።
በሌላ በኩል በወረቀት ለመፈተን ለተመዘገቡ 15 ሺህ 325 የክልሉ ተፈታኞች ፈተናው ከሐምሌ 22 እስከ 24 ቀን 2018 ዓ.ም በመቐለ እና በአክሱም ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ ተመላክቷል።
እነዚህ በወረቀት የሚፈተኑ ተማሪዎች ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ወደ መቐለ እና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች በመግባት፣ ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም የሚሰጠውን ገለጻ (ኦሬንቴሽን) በመከታተል ፈተናቸውን መውሰድ እንደሚችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ጨምሮ ገልጿል።
#ethiopianbroadcastingcorporation #grade12exam #nationalexam #mekelleuniversity #axumuniversity

መቐለ ዩኒቨርሲቲ ከ2,900 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ
#ethiopia | የመቐለ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2,931 ተማሪዎችን በዛሬው እለት አስመርቋል።
የትምህርት ገበታቸውን በስኬት አጠናቀው ለምረቃ ከበቁት የዘንድሮ ተመራቂዎች መካከል 849ኙ ሴቶች መሆናቸው
በምረቃው መርሐግብር ላይ ተገልጿል።
ዩኒቨርሲቲውን በዘንድሮ አመት 1,864 ተማሪዎችን በመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም 45 ዓለም አቀፍ ተማሪዎችን ጨምሮ 939 ተማሪዎችን በሁለተኛ ዲግሪ አስመርቋል።
ከተመራቂዎቹ ውስጥ 45 ተማሪዎች በሦስተኛ ዲግሪ (ፒኤችዲ) ሲሆኑ 83 የሚሆኑት ደግሞ በስፔሻሊቲ አጠናቀዋል።
በመርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፋና ሓጎስ (ዶ/ር) ባደረጉት ንግግር የትምህርት ጥራትን ይበልጥ ለማረጋገጥ እና የተመራቂዎችን የፈጠራ ክህሎት ለማሳደግ የሚያስችል ሰፊ የሥርዓተ ትምህርት ክለሳ መደረጉን ጠቁመው፣ ተመራቂዎቹ በተሰማሩበት የሥራ መስክ ኅብረተሰቡን በቅንነትና በትጋት እንዲያገለግሉ አሳስበዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#mekelleuniversity #graduation#ethiopianuniversities#highereducation

Comments