Logo
Getu Temesgen
ከስምምነት የደረሱባቸው ጉዳዮች የትኞቹ ናቸው?
#ethiopia | አሜሪካ እና ኢራን ጦርነቱን ለማቆም ከስምምነት የደረሱባቸው የመግባቢያ ነጥቦች ይፋ ሆኑ።

አሜሪካ እና ኢራን ከሦስት ወራት በላይ የዘለቀውን ጦርነት ለማስቆም የሚያስችል ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታወቁ።

በመካከለኛው ምሥራቅ ብሎም በመላው ዓለም ከባድ ቀውስን አስከትሎ የቆየውን ጦርነት ለማስቆም ለወራት ሲደረግ የነበረው ድርድረ አርብ ዕለት ስዊትዘርላንድ ውስጥ በሚካሄድ የፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ይቋጫል ተብሏል።

አሜሪካ እና ኢራን ጦርነቱ እንዲቆም በደረሱት የመግባቢያ ስምምነት ላይ ሊባኖስን ጨምሮ በሁሉም ግንባሮች ጦርነቱ እንደሚቆም እና የሆርሙዝ ወሽመጥ እንደሚከፈት ተዘግቧል።

የኢራን ብሔራዊ መገናኛ ብዙኃን በቴህራን እና ዋሺንግተን መካከል ጦርነቱን ለማስቆም ስምምነት በተደረሰበት የመግባቢያ ሰነድ ውስጥ የተካተቱ ነጥቦችን ይፋ አድረገዋል።

የመገናኛ ብዙኃኑ ባቀረቧቸው ዝርዝሮች ውስጥ የተካተቱት ነጥቦች በሁለቱም ወገን ማረጋገጫ አልተሰጠባቸውም።

ሜህር የዜና ወኪል ከዘረዘራቸው ነጥቦች መካከል፦

* በሁሉም ግንባሮች ሊባኖስን ጨምሮ በቋሚነት ተኩስ ይቆማል

* አሜሪካ በኢራን ውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ አትገባም

* በ30 ቀናት ውስጥ የአሜሪካ የባሕር ዕገዳ ይነሳል

* የአሜሪካ ጦር ከኢራን ለቅቆ ይወጣል

* የሆርሙዝ ወሽመጥ “በኢራናውያን ቁጥጥር” በ30 ቀናት ውስጥ ዳግም ይከፈታል

* አሜሪካ እና አጋሮቿ 300 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ የመልሶ ግንባታ ዕቅድ ያቀርባሉ

* በኢራን የነዳጅ ዘይት እና ኢነርጂ ምርቶች ላይ የተጣለውን ማዕቀብ ማንሳት

* ኢራን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ላለማምረት ዳግም ታረጋግጣለች
አሜሪካ በቀጣናው ያላትን ጦር አትጨምርም እና አዲስ ማዕቀብም አትጥልም።

* ሜህር አክሎም የስምምነቱ መጨረሻ የኢራን እንዳይንቀሳቀሱ የታገዱ ግማሽ ሃብቷ እስኪለቀቅ፣ የኢራን ነዳጅ ዘይት ላይ የተጣለው ማዕቀብ እና የባሕር ላይ ዕገዳው እስኪነሳ ድረስ የመጨረሻው ድርድር አይጀመርም ሲል ዘግቧል።

እንዲሁም የመጨረሻው ስምምነት በተባበሩት መንግሥታት በፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ እንደሚጸድቅ ዘግቧል።
#አሜሪካ #ኢራን #ጦርነት #ስምምነት #bbc #ጌጡተመስገን #ሚዲያኮሚኒኬሽን #getutemsgen #mediacommunication

6 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.