28 days ago
በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አርሰናል፣ ፒኤስጂ እና ሊቨርፑል ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ
*********************
በ2026/27 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታዎች ዛሬም በሁለተኛው ቀን ሲቀጥሉ ወደ ኔፕልስ አቅንቶ በዲዬጎ አርማንዶ ማራዶና ስታዲየም ናፖሊን የገጠመው አርሰናል 1 ለ 0 አሸንፏል።
የአርሰናልን ብቸኛ ግብ ክርስቶስ ዞሊስ ያመቻቸለትን ኳስ ተጠቅሞ 75ኛው ደቂቃ ላይ ማርቲን ኦዲጋርድ ከመረብ አሳርፏል።
በሌሎች ጨዋታዎች የስሎቫኪያውን ስሎቫን ብራትስላቫን የገጠመው ፔኤስጂ 6 ለ 1 አሸንፏል። ፌራን ቶሬስ ሦስት ግቦች በማስቆጠር ሀትሪክ ሲሰራ፣ ኡስማን ዴምቤሌ ሁለት እንዲሁም ፋቢያን ሩዊዝ አንድ ግብ ከመረብ አሳርፈዋል። ሱለይማን ካማራ ለስሎቫኪያው ክለብ ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረ ተጫዋች ነው።
በአንፊልድ አትሌቲኮ ማድሪድን ያስተናገደው ሊቨርፑል ደግሞ 2 ለ 1 አሸንፏል። ዶሚኒክ ሶቦዝላይ እና አሌክሲስ ማካሊስተር ለሊቨርፑል ግቦቹን ሲያስቆጥሩ፣ ማርኮስ ሎሬንቴ የአትሌቲኮን ብቸኛ ግብ ከመረብ አሳርፏል።
የፖርቹጋሉ ስፖርቲንግ ሊዝበን የቱርኪዬውን ጋላታሳራይ 3 ለ 1 የረታበት ሌላኛው የዛሬ ምሽት የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ላይ የተመዘገበ ውጤት ነው።
#uefa #uefachampionsleague #arsenal #napoli #psg #liverpool #liverpoolfc #atleticomadrid #football #sports #ebc

8 months ago
ለሊቨርፑል ደጋፊዎች ትልቅ ነገር
#ethiopia | የርገን ክሎፕ ከሊቨርፑል ጋር የነበራቸው ቁርኝት ምን ያህል ጥልቅ እንደሆነ የሚያሳይ አዲስ ሚስጥር በወኪላቸው ማርክ ኮሲክ አማካኝነት ይፋ ሆኗል። እንደ ወኪሉ ገለጻ፣ ክሎፕ አንፊልድን ከለቀቁ በኋላ ማንችስተር ዩናይትድ እና ቼልሲ አሰልጣኙን ለመቅጠር ጥያቄ አቅርበውላቸው ነበር።
የክሎፕ "አይ" ለታሪካዊ ተቀናቃኞች
ምንም እንኳን ሁለቱ የለንደን እና የማንችስተር ግዙፍ ክለቦች የርገን ክሎፕን ወደ ስታምፎርድ ብሪጅ ወይም ኦልድ ትራፎርድ ለመውሰድ ቢሞክሩም፣ የጀርመናዊው አሰልጣኝ ምላሽ ግን የማያወላውል ነበር።
"የርገን በእንግሊዝ ውስጥ ከሊቨርፑል ውጪ ሌላ ክለብን በጭራሽ እንደማያሰለጥን ግልጽ አድርጓል" - ማርክ ኮሲክ (የክሎፕ ወኪል)
ታማኝነት ከገንዘብ በላይ
ይህ ውሳኔ ክሎፕ ለሊቨርፑል ደጋፊዎች ያላቸውን ልዩ ክብር እና የገቡትን ቃል ጠባቂነት የሚያሳይ ነው። ምንም እንኳን ከክለቡ ቢለዩም፣ ከሊቨርፑል ጋር ያላቸውን ታሪክ የሚያበላሽ ወይም ደጋፊዎቻቸውን የሚያስከፋ እርምጃ ለመውሰድ ፍቃደኛ አልሆኑም።
ይህ ዜና በተለይ በዩናይትድ እና በቼልሲ ደጋፊዎች ዘንድ "ምን አልባት ቢመጡስ?" የሚል ተስፋ ለነበራቸው ትልቅ መርዶ ሆኗል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #jurgenklopp #liverpoolfc #mufc #cfc #premierleague #footballnews #klopp #ethiosports #lfcfamily

9 months ago
🔴 "ቀይ ለበሶቹ ማሸነፍ አቅቷቸዋል፤ ለ5 ተከታታይ ጨዋታዎች ከድል ርቀዋል!"
#ethiopia | በ23ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከሜዳው ውጭ ወደ ቪታሊቲ ስታዲየም ያቀናው ሊቨርፑል፤ እጅግ አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ በቦርንማውዝ 3-2 ተሸንፏል።
የጨዋታው ድራማ:
ሊቨርፑል በቨርጂል ቫን ዳይክ እና በዶሚኒክ ሶቦዝላይ ግቦች አማካኝነት ነጥብ ተጋርቶ ለመውጣት ተቃርቦ የነበረ ቢሆንም፤ ቦርንማውዞች በኢቫኒልሰን እና አሌክስ ጂሚኔዝ ከመመራታቸው በተጨማሪ፤ በባከነ ሰዓት በአድሊ አማካኝነት የማሸነፊያዋን ግብ በማስቆጠር 3 ነጥቡን ጠቅልለው ወስደዋል።
የሊቨርፑል ቀውስ:
📉 በውድድር ዓመቱ ለ7ኛ ጊዜ ተሸንፈዋል።
📉 በሊጉ ብቻ ለ5 ተከታታይ ጊዜ ማሸነፍ ተስኗቸዋል።
የሊቨርፑል ችግር መከላከሉ ላይ ነው ወይስ አሰልጣኙ ጋር? ሀሳባችሁን ስጡን!
#liverpoolfc #bournemouth #premierleague #epl #lfc #football #ethiopia #sportsnews

Comments