#ethiopia | አጋዝ ገብረየሱስ ኃይለማሪያም ጉራጌ አቀፍ የምርምርና የድርሰር ስራዎች እንዲሁም ''የሚሊኒየሙ መሸኛና መቀበያ'' ፎቶግራፎችን ለብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) በስጦታ አበረከቱ።
የደራሲ ገብረየሱስ ኃይለማርያም ከ28 ዓመት በፊት (በፈረንጆቹ ሚሊኒየም የመጨረሻው ለሊት እና ንጋት) ወደ ወጨጫ ተራራ በመጓዝ ያነሷቸው የሚሊኒየሙ ጀንበር መሸኛና መቀበያ ፎቶግራፎችን ጨምሮ የጫሙት ሽካ፣ ተኬትነት አጂነት/አገኪ፣ ነሁቸርና The Gurage and their Culture የተሰኙ የድርሰት ሥራዎቻቸውን ለብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) አስረክበዋል።
ለጉራጌ በቋንቋ፣ በባህልና በማኅበረሰብ ልማት ዘርፎች ያበረከቷቸው የሕይወት ዘመን አገልግሎቶች "አጋዝ" የሚል ባህላዊ ስያሜ የተሰጣቸው አጋዝ ገብረኢየሱስ ኃይለማርያም በጉራግኛ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ 16 መጽሐፍትን ጽፈዋል።
ለጉራጌ ባህልና ቋንቋ ልማት ካበረከቱት አስተዋጽኦ ባሻገር የጉራጌ ባህል ማእከል እና የጉራጌ ሕዝብ ራስ አገዝ ልማት ድርጅትን (ጉህራልድ) በምስረታ ሂደት ላይ ላቅ ያለ ሚና ነበራቸው። በሌሎች ሀገራዊና ዓለምአቀፍ ተቋማትም አሻራቸውን አኑረዋል።
በዚሁ ወቅት የብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተ መፅሀፍት አገልግሎት ፅህፈት ቤት ኅላፊ አቶ አባተ ካሣው እንደተናገሩት ደራሲገብረየሱስ በኢትዮጵያ በብሔረሰቦች ቋንቋ ድርሰት መጽሐፍ ከጀመሩት ውስጥ ናቸው ያሉ ሲሆን ታሪካዊ ሰነዶችን ለወመዘከወር በማስረከባቸው የተሰማንን ልባዊ ደስታ እንገልፃለን ብለዋል።
ለደራሲ ገብረየሱስም ከወመዘክር የተዘጋጀ የእውቅናና ምስጋና የምስክር ወረቀት ሰርተፊኬት ሰጥተዋል።
በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ መሠረት አመርጋ በበኩላቸው እንዲህ አይነት ታሪካዊ ስራዎች በሰነድነት ታስበው የርክክብ ሥነ ሥርዓቱ መዘጋጀቱ ለሀገር ትልቅ ነገር ነው ብለዋል።
ደራሲ አጋዝ ገብረየሱስ ሀይለማርያም በበኩላቸው ስራዎቹን ሳከናውን እዚህ ይደርሳል ብዬ ባይሆንም የበርካታ ታሪክና ባለታሪኮች ሰነድ መገኛ የሆነው ወመዘክ ፎቶግራፎቼንና የድርሰት ስራዎቼን በአሻራነት መሰነድ በመቻሉ ደስታ ተሰምቶኛል ብለዋል።
ዝግጅቱ ተወዳጅ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ከሶዶ ለማ ሚድያ ጋር በመተባበር አዘጋጅተውታል።
ዓለም አቀፍ የጉራጌ ማህበር - International Gurage Association - IGA

4 months ago