Logo
Getu Temesgen
የተከዳው የጥበብ ዋርካ ሰብ ኸንከም በዛ አፈር ትትነብር ጥፉወ አትህን በገጋኸ ይሰብር ፣ ወሄነት ተሰብ ዋረም ያድር ወሄ ህን ዘር ተጡር ይነብር•••• ህይወቱን ሙሉ ሰጥቶ ሸርተት ሲል የተከዳው የጥበብ ዋርካ (ጀማል መሀመድ) #ethiopia | ጀማል መሀመድ ከውልደት እስከ እርጅና ህዝብና ሀገር በማገልገል ዘመኑን የጨረሰ ሰው ነው። ሰው ስለሆንን ሄደን ሄደን በዱኒያ ጉዳይ ልንዝል መቻላችን ሰውኛ ነው። እሱንም የገጠመው ይኸው ነው። ከአመታት በፊት ተዳፍኖ ከቀረበት ተስፋ የሚባል ልጅ ወደ ህዝብ አምጥቶት ለማንሰራራት ቢሞክርም በቋሚነት መቆም አልቻለም። ተደጋጋሚ የገንዘብ ስብራት ገጠመው። ያኔ ተስፋ ህዝብ አስተባብሮ የተከፈተው ሱቅም በኮሪደር ምክንያት ፈረሰ። ይባስ ብሎም ጤናው ታውኮ የነርቭና የዲስክ መንሸራተት ሰለባ ሆኖዋል። ጀማል መሀመድ ዛሬ እኛ በፅሁፍ በሌላ ቋንቋ(አነጋገር) የምናወራቸውን የጉራጌን ችግሮች አስቀድሞ ያየውን በምስክርነት የፈራውን በትንበያ አስቀምጧል። ጀማል ችግሮቻችንን ብቻ ሳይሆን መፍትሄያቸውንም ጭምር በሚገርም ኪነጥበባዊ ቋንቋ አመላክቷል። ዛሬ ጠፍንጎ የያዘን መንደርተኝን ጨምሮ። ስለደግነት፣ስለ ቤተሰብ፣ስለአንድነት፣ስለ አረፋና መስቀር፣ ስለአገር፣ ስለ ፍቅር፣ ስለ መሰዋእት... ወዘተ ጀማል ማህበራዊ ስሪቶቻችንን በሙሉ በማይሰለቸው ድምፁ በተራ በተራ እያነሳ አዝናንቶ አስተምሮናል። "እንዴ እማት ህሮ ሰበና፣ወፈንቻ አትመዝሮ በዘና: ቸሀ እኖሩ ጌታ ትንብነ፣እንጭመታ አተረ ሸመነ..." ከጀማል በዘመን አቧራ የማይሸፈኑ ወርቃማ ሀሳቦች ውስጥ ነው። ጀማል የጉራጌን ባህልና ኪነጥበብን እንዳይወርድና እንዳይነካ ከፍ አድርጎ ከሰቀለው በኋላ በክብሩና በዝናው ሳይታበይ ተከታዮችንም በቅንነት አፍርቷል። የጉራጌ ባህል፣ ማንነት፣ ስነልቦና፣ ማ/ሰባዊ ፍልስፍና ከማህበሰባችን አልፎ ለመላው ኢትዮጵያውያን አድርሷል። ያለ ምንም ልዩነት በአገር ደረጃ የሚወደድ የጥበብ ሰው! ዛሬ ታሞ፣ ስራ ፈትቶ እያለ የሱን ጉዳይ የሚመለከተው ተስፋ ነዳ ብቻ መሆኑ ያሳዝናል። በመሆኑም የሚከተሉትን የመፍትሄ ሀሳቦች ማስቀመጥ ወደድኩኝ። 1. በባለሃብት ተብዬዎች በኢንቨስትመንት ስምና በቀድሞ ዘርማ ነን ባይ ፈርሴቡላዎች እየተቸበቸበ ካለው የጉራጌ መሬት በየቦታው ሰው እያንጓጠጣቸው ላሉት ለጀማልና ሌሎች የጉራጌ ባህልና ወግ እያስተዋወቁ ላሉት የጉራጊኛ ድምፃዊያን የቤት መስሪያ ቦታ በከተማዎቹ ወልቂጤና ቡታጅራ ወይም ሌላ አቻ ቦታ ሊሰጣቸው ይገባል። ለዚህም አትነት የጉራጌ አርቲስቶች ማህበርና የዞኑ ባህልና ቱሪዝም ጫና ሊያደርጉ ይገባል። 2. በእኖር ወረዳ ዋና ከተማና በእኖር ኤነር መገር ወረዳ ዋና ከተሞች በሆኑት ጉንችሪየና ሚቄ ከተሞች ጀማል ለሰራቸው ስራዎች ባይመጥንም የቤት መስሪያ ቦታ በሁለቱም ከተሞች ሊሰጠው ይገባል። ለዚህም ከአካባቢው ተወላጆች ኮሚቴ በማዋቀር በፍጥነት ሊደረግለት ይገባል። 3. የትውልድ አካባቢው በሆነው እኖር ውስጥ በቁም እያለ በስሙ "ጀማል መሀመድ ጎዳና'' ሊሰየምለት ይገባል። ብናከብረው የምንከበረው እኛ በመሆናችን ይሄም ሊደረግለት ይገባል። በቁሙ እያየው ቢደሰት የሚገባው ነው። ለዚህም ከላይ አስቀድሜ ከወረዳው (አካባቢው) ተወላጅ ቢመሰረት ባልኩት ኮሚቴ ማስኬድ ይቻላል። 4. ለጉራጌ ባህል፣ልማትና ባህል የሚሰራው የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር እና የጉራጌ ዞን አስተዳደር ሁለቱ ለህክምና ሂደቱ ሀላፊነት ሊወስዱ ይገባል። 5. ጀማል በእርጅና ዘመኑ የገንዘብ ጉዳይ ሀሳብ እንዳይሆንበት እሱን የሚመጥን ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ልናደርግለት ይገባል። ለዚህም ወዳጆቹ፣ አትነት፣ የዞኑ መንግስት እና ጉልባማ ስራውን መስራት ይኖርባቸዋል። 6. የመሆኑ ነገር እርግጠኛ ባልሆንም በውትድርና ካገለገላት አገሩ አዲስ አበባ (ሻዋ) ላይ ቢያንስ ኮንዶሚኒየም እንዲያገኝ ጥረት ማድረግ ቢቻል። ይሄም መልካም ስምና ተፅእኖ ባላቸው ሰዎች ፕሮቶኮሉ ጠብቆ ከንቲባዋ ጋር ቢደርስ። በዚሁ አጋጣሚ በማናቸውም አስተባባሪ ኮሚቴዎች ውስጥ ገብቼ ለማገዝ ፈቃደኛ መሆኔን አስቀድሜ እገልፃለሁ። #unity #gurage

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.