Logo
Getu Temesgen
ወልቂጤ : የምስጋና እና የክብር ፕሮግራም
#ethiopia | ለአንጋፋው ለጉራጊኛ ድምፃዊ ደምሴ ተካ የምስጋና እና የክብር ፕሮግራም በወልቂጤ ከተማ ተካሄደ

አርቲስት ደምሴ ተካ በግጥም እና ዜማ ድርሰቶቹ እንዲሁም በጉራጊኛ 10 አልበሞች እና በርካታ ነጠላ ሙዚቃዎችን የሰራ ሲሆን በኢትዮጵያ ብሔረሰዊ ቴአትር የረጅም ጊዜ የባህል ድምጻዊ በመሆን እየሰራ ይገኛል።

‎የምስጋና ፕሮግራሙ በአትነት የጉራጌ አርቲስቶች ማህበር፣ በጉራጌ ዞንና በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር በጋራ በጆካ ኢንተርናሽናል ሆቴል ተዘጋጅቷል።

‎በመርሀ ግብሩ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር ፣የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሀላፊ ወ/ሮ መሠረት አመርጋ ፣የወልቂጤ ከተማ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ታደለ በቀለ ፣አትነት የጉራጌ አርቲስቶች ማህበር አባላት ፣የዞንና ከተማ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ፣የከተማ ነዋሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመርሀ -ግብር ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ዓለም አቀፍ የጉራጌ ማህበር
- International Gurage Association - IGA



11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.