5 months ago
የ‘U-GIRLS 2’ ፕሮጀክት የማጠቃለያ መርሐ ግብር ተከናወነ
#ethiopia | በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለስድስት ዓመታት ሲተገበር የቆየውና በሴት ተማሪዎች ሕይወት ላይ ጉልህ ለውጥ ያመጣው የ‘U-GIRLS 2’ ፕሮጀክት የማጠቃለያ መርሐ ግብር ተከናውኗል። ፕሮጀክቱ በኩሶ ኢንተርናሽናል ድጋፍ ሲከናወን የቆየ ሲሆን፣ በክልሉ የሚገኙ የሴት ተማሪዎችን የትምህርትና የማኅበራዊ ሕይወት ለመለወጥ የተሳካ ሥራዎችን አከናውኖ መጠናቀቁ ተገልጿል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የቀረቡ ዋና ዋና ስኬቶች እነሆ፦
የተደራሽነትና የድጋፍ ስፋት
* ተጠቃሚዎች፦ ፕሮጀክቱ በክልሉ በሚገኙ ሰባት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚማሩ 23,816 ሴት ተማሪዎችን ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል።
* የቁሳቁስ ድጋፍ፦ ለተማሪዎቹ የመማሪያ ቁሳቁሶች (ደብተር፣ ቦርሳ፣ ጫማ፣ ዩኒፎርም) ከመቅረባቸውም በላይ ለትምህርት ቤቶቹ የተማሪዎች መቀመጫ ወንበር (Desk) እና ኮምፒውተሮች ተከፋፍለዋል።
* መሰረተ ልማት፦ ሰባቱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተሟላ የሶላር ኃይል አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል።
የአቅም ግንባታና ስልጠናዎች
* ለትማሪዎች፦ ከአካዳሚክ ማጠናከሪያ ትምህርት በተጨማሪ በሥራ ፈጠራ፣ በገንዘብ አያያዝ፣ በሕይወት ክህሎትና በሥነ-ተዋልዶ ጤና ዙሪያ ተከታታይ ስልጠናዎች ተሰጥተዋል።
* ለማኅበረሰቡ፦ የተማሪ ወላጆች፣ መምህራንና የክልሉ የሥራ ኃላፊዎች በሥርዓተ-ጾታ እኩልነትና በተለያዩ የአቅም ግንባታ መስኮች ተሳታፊ ሆነዋል።
የፕሮጀክቱ አበርክቶ
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ እንደገለጸው፣ ፕሮጀክቱ ሴቶች በትምህርታቸው ጠንካራና መፍትሔ አምጪ እንዲሆኑ ከማስቻሉም በላይ የሴቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት በተጨባጭ ከፍ አድርጓል። የማኅበረሰቡ አባላትና ትምህርት ቤቶችም ፕሮጀክቱ ለችግራቸው ተደራሽ እንደነበር ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።
የመርሐ ግብሩ ማጠቃለያ ላይ ፕሮጀክቱ በይፋ መጠናቀቁ ቢበሰርም፣ ክልሉ መሰል የድጋፍ ፕሮግራሞች በቀጣይነት እንዲመቻቹ ያለውን ፍላጎት ገልጿል።
📸ከበደ መክብብ
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ቤኒሻንጉል_ጉሙዝ #የሴቶች_ትምህርት #ኩሶ_ኢንተርናሽናል #u_girls_2 #ኢትዮጵያ #ትምህርት #genderequality #cusointernational

Comments