11 hours ago
የኦሮሞ ሕዝብ ትግል በአንድ ቦታ የቆመ አይደለም ➡️ https://youtu.be/DVFhZjlaY... #abiyahmed #ethiopia #oromia #obn #ethiopianhistory #gadaasystem #pmabiy
12 hours ago
የኦሮሞ ጀግኖች መሥዕዋትነት ለኢትዮጵያ አንድነት ➡️ https://youtu.be/DVFhZjlaY... #abiyahmed #ethiopia #oromia #obn #ethiopianhistory #gadaasystem #pmabiy
2 months ago
የሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ሕያው ማሳያ፤ 71ኛው የቱለማ ገዳ የሥልጣን ርክክብ
************
የኦሮሞ ሕዝብ ለዘመናት ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና መንፈሳዊ ሕይወቱን የመራበት የገዳ ሥርዓት በዩኔስኮ የሰው ልጅ የማይዳሰስ የዓለም ቅርስ ሆኖ የተመዘገበ ሀገር በቀል የዴሞክራሲ ሥርዓት ነው።
ይህ ሥርዓት አምስቱ የገዳ ፓርቲዎች በየስምንት ዓመቱ እየተፈራረቁ የሚመሩበት የሰላማዊ እና የዴሞክራሲያዊ የሥልጣን ሽግግር (ባሊ) ዋነኛ መገለጫ ነው።
የቱለማ ገዳ ሥርዓት ታሪካዊ ዳራ ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት የጀመረ ነው። የቱለማ ገዳ መንፈሳዊ ልብ እና የሕግ መፍለቂያ ተደርጎ የሚወሰደው ኦዳ ናቤ የኦሮሞ ሕዝብ የአጽናፈ-ዓለም ዕይታ ከባህላዊ ሕግ ጋር የሚዋሃድበት ቅዱስ ስፍራ ነው።
በሸገር ከተማ ገላን ወረዳ የሚገኘው 'ደካ ኮራ' (Dhakaa Koraa) ደግሞ የቱለማ ገዳ ሕገ-መንግሥት እና ደንቦች የሚጸድቁበት እንዲሁም የሥልጣን ሽግግር ሥነ-ሥርዓት በጥብቅ ዲስፕሊን የሚከናወንበት ታሪካዊ የባህል ማዕከል ነው።
በአሁኑ ወቅት በዚሁ ታሪካዊ ስፍራ (በደካ ኮራ አርዳ ጂላ) የቱለማ ገዳ ሥርዓት 71ኛውን ዙር የሥልጣን ርክክብ በታላቅ ድምቀት ተካሂዷል።
በዚህ ዙር የሥልጣን ርክክብ የሜልባ ገዳ ክፍል አባ ገዳ የነበሩት እና ባለፉት ስምንት ዓመታት ሕዝቡን በታማኝነት ያገለገሉት አባ ገዳ ጎበና ሆላ፣ የሥልጣን እና የኃላፊነት ምልክት የሆነውን የገዳ አለንጋ፣ ቦኩ እና ባሊን የሙደና ገዳ ክፍል ተረካቢ ለሆኑት ለአዲሱ አባ ገዳ ጌቱ ተሊላ አስረክበዋል።
የቱለማ ሦስቱ ንዑሳን ጎሳዎች (ባቾ፣ ጂሌ እና ዳጪ) በጥልቅ ውይይት እና ስምምነት ካቀረቧቸው ዕጩዎች መካከል፣ ጥብቅ የሞራል እና የስብዕና ፈተናዎችን ያለፉ ዘጠኝ አባላት 'የሰግሊ' (Saglan Yaa'ii) ምክር ቤት የሥራ አስፈጻሚ በመሆን ተመርጠዋል።
የሥልጣን ርክክቡ በታላቅ ሰላም፣ መከባበር እና ባህላዊ ትውፊት መከናወኑ በረጅሙ የቱለማ ታሪክ ውስጥ የነበረውን የሽግግር ቀጣይነት በደማቅ ሁኔታ ያሳየ ነው።
እያንዳንዱ የገዳ የሥልጣን ዘመን ለ8 ዓመታት የሚቆይ ሲሆን የቱለማ ገዳ 71ኛውን የሥልጣን ርክክብ አካሂዷል።
ይህ ዑደት የቱለማ ገዳ ሥርዓት ቢያንስ ለ568 ዓመታት ያህል (ከ15ኛው ክፍለ-ዘመን አጋማሽ ጀምሮ) ሳይቋረጥ እና ታሪካዊ መዋቅሩ ሳይደፈርስ እዚህ መድረሱን ያረጋግጣል።
ይህ ሂደት የሥልጣን ገደብን ማክበርን፣ በሰላማዊ መንገድ ሥልጣንን ለቀጣዩ ትውልድ ማስረከብን እና ለሕግ የበላይነት መገዛትን በተግባር የሚያስተምር ሕያው ተሞክሮ ነው።
በገዳ ሥርዓት ውስጥ አንድ መሪ የሥልጣን ዘመኑ ሲያበቃ ያለምንም ማንገራገር፣ ሕግ ለማሻሻል ሳይሞክር ወይም ተቀናቃኞቹን ሳይጫን ሥልጣኑን ለተተኪው አስረክቦ ወደ አማካሪነት ደረጃ (ዩባ) ይሸጋገራል።
ይህም ለሀገራዊ አንድነት እና ለዴሞክራሲ ግንባታ እጅግ ወሳኝ የሆነ እሴት እና ለዘመናዊው ፖለቲካም ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ነው።
ከዚህም በተጨማሪ የገዳ ሥርዓት የዴሞክራሲ፣ የሕገ-መንግሥታዊነት እና የሰብዓዊ መብቶች ዋነኛ ምሰሶ ነው።
በአውሮፓ እና በምዕራቡ ዓለም ዘመናዊ የዴሞክራሲ ጽንሰ-ሐሳብ ከመጎልበቱ ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት፣ በአፍሪካ ምድር ላይ ፍጹም የሥልጣን ክፍፍል የነበረው ይህ ሥርዓት ይተገበር ነበር።
በውይይት ላይ የተመሠረተ የውሳኔ አሰጣጥ፣ የሴቶች መብት ጥበቃ እና የፖለቲካ ተሳትፎ በሲንቄ በኩል ይከበራል።
እንዲሁም አቅመ-ደካሞችን ለመደገፍ የሚሠራበት “ደራ-ባሱ” (Dharraa Baasuu) የተሰኘው ማኅበራዊ መዋቅር ሥርዓቱ ምን ያህል ፍትሐዊ እንደሆነ ያሳያል።
ይህንን ጥንታዊ፣ ባህላዊ ጥበብ እና ዘመናዊ የሕገ-መንግሥታዊነት መርሆዎችን በአግባቡ በማቀናጀት የአሁኑ ትውልድ የሀገራችንን የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ እና የሕግ የበላይነትን ይበልጥ ማጠናከር እንደሚችል የቱለማ ገዳ ታሪካዊ ጉዞ በግልጽ ይመሰክራል።
በለሚ ታደሰ
#gadaasystem #oromoculture #tulemagadaa #gadaamelbaa #gadaamudana #ethiopianbroadcastingcorporation

6 months ago
የገዳ ሥርዓት ተመራማሪ የነበሩት ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
#ethiopia | የገዳ ሥርዓትን ለዓለም በማስተዋወቅና ጥልቅ ፍልስፍናውን በመመርመር ረገድ ወደር የማይገኝላቸው ታዋቂው ምሁርና አንትሮፖሎጂስት ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተሰማ።
ፕሮፌሰር አስመሮም ሙሉ ዕድሜያቸውንና ዕውቀታቸውን የገዳ ሥርዓት እንዲጠበቅ፣ እንዲከበርና በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና እንዲያገኝ የደከሙ ታላቅ የቁርጥ ቀን ልጅ ነበሩ። በተለይም የኦሮሞ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ እሴቶችና የሰብአዊ መብት ጥበቃ መርሆዎች በጽሑፍ ተመዝግበው ለትውልድ እንዲሸጋገሩ ያበረከቱት አስተዋጽኦ በታሪክ ሲታወስ ይኖራል።
የፕሮፌሰሩ ዋና ዋና ሥራዎችና አስተዋጽኦዎች፡-
* የገዳ ሥርዓት ምርምር፡ የገዳን ሥርዓት ከመሠረቱ በመመርመር ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ በምሁራዊ መንገድ ያሳወቁ ቀዳሚ ምሁር ናቸው።
* የመጻሕፍት ደራሲ፡ በገዳ ሥርዓት ዙሪያ በርካታ መጻሕፍትንና የምርምር ሥራዎችን ለንባብ አብቅተዋል።
* የሰብአዊ መብት ተሟጋች፡ የሥርዓቱን ዲሞክራሲያዊነት በማጉላት ለሰብአዊ መብት መከበርና ለሕዝቦች ክብር በጽናት ታግለዋል።
የኦሮሚያ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ እንደገለጸው፣ የፕሮፌሰሩ ማለፍ በምሁራንና በሕዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ሐዘንን ፈጥሯል። ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ የአንድ ሕዝብን ብቻ ሳይሆን የአፍሪካን የጥንታዊ አስተዳደር ጥበብ ለዓለም ያሳዩ የዕውቀት ብርሃን ነበሩ።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #asmeromlegesse #gadaasystem #oromoculture #ethiopianscholar #legendaryanthropologist #rip

Sponsored by
Surafel
Comments