በታሪካችን ለመጀመሪያ ጊዜ፣ የኢንዱስትሪ ዘርፍ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት ድርሻ ከግብርና እና ከአገልግሎት በልጧል - ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)
**************************
የብሔራዊ ባንክ ገዢ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ታከናውናለች በሚል መሪ ቃል በተደረገው መድረክ ላይ፣ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ በፋይናንስ፣ በወጪ ንግድ እና በኢንዱስትሪ ዘርፎች ያመጣውን አስደናቂ ሀገራዊ ለውጥ በዝርዝር አቅርበዋል።
የኢኮኖሚ ዕድገቱ ወደ ተከታታይ የሥራ ዕድል ፈጠራ መሸጋገሩን የገለፁት ዶ/ር ኢዮብ፣ ዘንድሮ ብቻ በተለያዩ ዘርፎች 4.9 ሚሊዮን አዳዲስ የሥራ ዕድሎች መፈጠራቸውን ጠቅሰዋል።
ከዚህም ጋር ተያይዞ የኢንዱስትሪው አቅም አጠቃቀም ከ49 በመቶ ወደ 66.3 በመቶ ማደጉን፣ ይህም በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢንዱስትሪው ዘርፍ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ድርሻ ከግብርና እና ከአገልግሎት ዘርፎች መብለጡን አብስረዋል።
የተደረገው የውጭ ምንዛሬ ተመን ማሻሻያም በወጪ ንግድ ዘርፍ የኢትዮጵያን ተወዳዳሪነት በከፍተኛ ደረጃ እንዳሳደገው ዶ/ር ኢዮብ አብራርተዋል።
በዚህም፣ የወጪ ንግድ በ2010 ዓ.ም ከነበረበት 2.83 ቢሊዮን ዶላር ባለፈው ዓመት ወደ 8.33 ቢሊዮን ዶላር ማደጉንና ዘንድሮ ደግሞ 11 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስታውቀዋል።
ይህ የወጪ ንግድ ዕድገት የዓለም አቀፍ ዋጋ መጨመር ውጤት ብቻ ሳይሆን፣ በፖሊሲ ለውጡ የመጣ መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ሽግግር መሆኑንም ገልጸዋል።
የፋይናንስ ዘርፉን በተመለከተም፣ የባንክ ኢንዱስትሪው አጠቃላይ ሀብት ባለፉት 8 ዓመታት ውስጥ በ680 በመቶ፣ ተቀማጭ ገንዘብ ደግሞ በ654 በመቶ ማደጉን ተናግረዋል።
ይህን ተከትሎም 93.8 በመቶ የሚሆነው ብድር ለግል ዘርፉ እየቀረበ መሆኑ ሌላው ትልቅ ስኬት ነው ብለዋል።
ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመንግሥት የልማት ድርጅቶች በሰጠው ብድር ምክንያት 845 ቢሊዮን ብር የማይመለስ ዕዳ ተሸክሞ ለቀውስ ተጋልጦ እንደነበር ያስታወሱት ዶ/ር ኢዮብ፣ መንግሥት በወሰደው እርምጃ ዕዳውን ወደ ሰነድ በማዞር እና ካፒታሉን በ3 እጥፍ በማሳደግ ባንኩን መታደግ መቻሉን አስረድተዋል።
በአሁኑ ሰዓት የባንክ ኢንዱስትሪው የተበላሸ ብድር ምጣኔ 3.07 በመቶ ብቻ ሲሆን፣ ይህም ብሔራዊ ባንክ ካስቀመጠው የ5 በመቶ ጣሪያ በታች መሆኑን አብራርተዋል።
የተደራረቡ ዓለም አቀፍ እና የሀገር ውስጥ ፈተናዎች ቢኖሩም፣ ኢኮኖሚው የመቋቋም አቅሙን የገነባ በመሆኑ ሀገራችን የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ለመሆን በተገቢው መንገድ ላይ መሆኗን አረጋግጣለች ሲሉ ዶ/ር ኢዮብ ገልጸዋል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #economicreform #industrialgrowth #exportgrowth #financesector #banking #ebc

4 months ago