5 months ago
ዳሽን ባንክ ለደንበኞቹ የኢፍጣር መርሃ ግብር አዘጋጀ
#ethiopia | ዳሽን ባንክ የረመዳን ወርን ምክንያት በማድረግ ለደንበኞቹ ያዘጋጀውን ልዩ የኢፍጣር መርሃ ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል አካሄደ።
መርሃ ግብሩ ባንኩ ያለውን ማህበራዊ ተሳትፎ ለማሳደግና ከደንበኞቹ ጋር ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
በዝግጅቱ ላይ የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው ዓለሙ ባደረጉት ንግግር፤ ለባንኩ ደንበኞችና ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አቶ አስፋው አክለውም ዳሽን ባንክ ከደንበኞች እሴትና የፋይናንስ ፍላጎት ጋር የሚጣጣሙ፣ የሸሪዓ መርሆዎችን ያከበሩ የባንክ አገልግሎቶችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
ማህበራዊ ኃላፊነትና ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት
ባንኩ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት (ሸሪካ) ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ባለው ቁርጠኝነት መሰረት ባለፈው ዓመት ካከናወናቸው ተግባራት መካከል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፦
ከደንበኞች በአደራ መልክ የሰበሰበውን ከ22 ሚሊዮን ብር በላይ ለ31 አገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ማከፋፈሉ፤
በሶማሌ ክልል ለሚገኙ ስራ ፈጣሪዎች ከወለድ ነፃ በሆነ መንገድ የ100 ሚሊዮን ብር ተዘዋዋሪ ብድር ማቅረቡ።
ዳሽን ባንክ በአሁኑ ወቅት ከ1.5 ሚሊዮን በላይ የኢንተረስት ፍሪ (ከወለድ ነፃ) አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች እንዳሉት የገለጸ ሲሆን፣ ይህም ባንኩ ያለውን ሁሉን አቀፍነትና የጋራ ተጠቃሚነት ባህል እንደሚያሳይ ተጠቁሟል።
ባንኩ በዘርፉ ባሳየው ጥንካሬ በ2023 በዱባይ በተካሄደው 9ኛው የኢስላሚክ ሪቴል ባንክ ሽልማት ላይ "በኢትዮጵያ ጠንካራው የኢስላሚክ የችርቻሮ ባንክ መስኮት" (The Strongest Islamic Retail Banking Window in Ethiopia) የሚል እውቅና ማግኘቱም ይታወሳል።
በተጨማሪም ዳሽን ባንክ ዓለም አቀፍ የእስልምና ፋይናንስ ተቋማትን የሂሳብ አያያዝ፣ የኦዲትና የሸሪዓ መስፈርቶችን የሚያወጣው AAOIFI (The Accounting and Auditing Organization for Islamic Financial Institutions) አባል የሆነ ብቸኛው የኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋም ነው።
#dashenbank #iftarprogram #islamicbanking #shariacompliant #ethiopianbanking #ramadankareem #financialinclusion

Comments