5 months ago
እናት ባንክ የሴት አመራሮችን አቅም ለማሳደግ ያለመ የፓናል ውይይት አካሄደ
#ethiopia | እናት ባንክ "High Level Women Leadership" በሚል መሪ ቃል ባዘጋጀው ስልታዊ የምክክር መድረክ፣ በፋይናንስ ዘርፉ ውስጥ የሴቶችን ተሳትፎ እና የአመራር ብቃት ለማሳደግ ያለውን ቁርጠኝነት ገልጿል።
በውይይቱ ላይ የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተው በዘርፉ ስላለው ተግዳሮት እና ተስፋ ሰጪ ሁኔታዎች ሰፊ ምክክር አድርገዋል።
የሴቶች ተሳትፎ 🔎
የእናት ባንክ የቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ አስቴር ሰለሞን በመክፈቻ ንግግራቸው እንዳሳሰቡት፣ ባንኩ ባለፉት 13 ዓመታት የሴት ሠራተኞችን አቅም በማጎልበት እና ወደ አመራርነት በማምጣት የደንበኞች አገልግሎቱን ማሻሻል ችሏል። በአሁኑ ወቅት የባንኩን እድገት ለማፋጠን በሚደረገው ጥረት ውስጥ ሴት ሠራተኞች ከፍተኛውን ድርሻ እየተወጡ እንደሚገኙም ጠቁመዋል።
ባንኩ በአሁኑ ወቅት በአሃዝ ሲገለጽ፡-
* አጠቃላይ ሠራተኞች፦ ከ2,000 በላይ ሲሆኑ ከእነዚህም ውስጥ 952ቱ ሴቶች ናቸው።
* የቦርድ አመራር፦ ከ11 የቦርድ አባላት መካከል 7ቱ ሴቶች ናቸው።
* ከፍተኛ የሥራ ካውንስል፦ 44 በመቶ የሚሆኑት አባላት ሴቶች ናቸው።
ተግዳሮቶች እና የኢኮኖሚ ፋይዳው
የባንኩ ዋና የፋይናንስ ኦፊሰር (CFO) ወ/ሮ ትዕግስት አባተ እንደገለጹት፣ በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ በከፍተኛ አመራርነት ደረጃ ያለው የሴቶች ቁጥር አሁንም አነስተኛ ነው። ለዚህም እንደ እንቅፋት የሚጠቀሱት፦
* በራስ የመተማመን ሁኔታ።
* የቤት ውስጥ ኃላፊነትን ከቢሮ ሥራ ጋር አስተካክሎ የመምራት (Work-life balance) ተግዳሮት ናቸው።
ይሁን እንጂ ሴቶች በአመራርነት ደረጃ መሳተፋቸው የሀገሪቱን ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) ከ3 እስከ 4 በመቶ ሊያሳድገው እንደሚችል ተጠቁሟል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክም በፋይናንስ ዘርፉ የሴቶች የአመራር ድርሻ ወደ 25 በመቶ እንዲያድግ ግብ አስቀምጧል ብለዋል።
በመረሃግብሩ ላይ ወ/ሮ አስቴር ሰለሞን፣ ተዋበች ቢሻው (ዶ/ር)፣ ናስሪን መሐመድ እና ገመቹ ዋቅቶላ (ዶ/ር) ያላቸውን የካበተ ልምድ ለታዳሚዎች አጋርተዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #enatbank #womeninleadership #ethiopianbanking #empoweringwomen #financialsector #addisababa #ethiopia

Comments