2 months ago
በሕግ ስር ያሉ ተጠርጣሪ (ተከሳሾች) የዋስትና መብቶች
በኢትዮጵያ ሕግ ማእቀፍ
መግቢያ
#ethiopia | የዋስትና መብት አጠቃላይ ይዘት ተከሳሹ ፍርዱን በውጭ ሆኖ እንዲከታተል መፍቀድ እና የፍትህ ስራው ሳይደናቀፍ ተከሳሹ ችሎት መቅረቡን ማረጋገጥ ነው። ይህ መብት የአለምአቀፍ ሆነ ህገመንግስታዊ መርህ ሲሆን በወንጀል ሕግ ሥርዓት ውስጥም የግለሰብ ነጻነትን እና የህዝብ ደህንነትን ሚዛን ለመጠበቅ የሚያገለግሉ ዋና ዋና ዓላማዎችን፣ ሕጋዊ መሠረቶችን እና መመዘኛዎችን በማካተት የሚደነግግ ነው።
በዚህ ጽሁፍ የተከሰሻችን ወይም የተጠርጣሪዎችን መብቶችን ፣ ዋስትና የሚያስከለክሉ መብቶችን ፣ የይግባኝ መብቶችን እንዲሁም ዋስትና የተከለከሉ ሰወች እንዴት በፍርድ ቤት ሊስተናገዱ እንደሚገባ በማካተት ለህግ ግንዛቤ ለእናንተ ቀርቧል።
1. በኢትዮጵያ የሕግ ማዕቀፍ ውስጥ ያለ ዋስትና እስር (Pre-trial detention without bail) የሚፈጸመው
የዋስትና (Bail) መብት ዓለም አቀፋዊ መርሆች በዋናነት የተመሠረቱት በሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌዎች እና በዓለም አቀፍ የፍትሕ ሥርዓት ሥነ-ምግባር ላይ ነው። እነዚህ መርሆች አንድ ተጠርጣሪ ጥፋተኛነቱ በፍርድ ቤት ሳይረጋገጥ መታሰር የሌለበትን እና ነፃነቱን የማግኘት መብቱን የሚያስከብሩ ናቸው።
ዋና ዋናዎቹ ዓለም አቀፋዊ የዋስትና መርሆች የሚከተሉት ናቸው፦
1.1. የንጽሕና ግምት መርህ (Presumption of Innocence)ይህ የሁሉም መርሆች መሠረት ነው፤ ማንኛውም ሰው በሕግ ፊት ጥፋተኛነቱ እስካልተረጋገጠ ድረስ እንደ ንጹህ ሰው ይቆጠራል።በመሆኑም ተጠርጣሪን ያለ ፍርድ ማሰር ቅጣት መሆን ስለሌለበት፣ በመደበኛ ሁኔታ በዋስ የመፈታት መብት ሊኖረው ይገባል።
1.2. ነፃነት መርህ ነው፣ እስር ልዩ ሁኔታ ነው (Liberty as a Rule, Detention as an Exception)በዓለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ቃል ኪዳን (ICCPR አንቀጽ 9) መሠረት፣ የወንጀል ክስ የተመሠረተበት ሰው ፍርዱን በውጭ ሆኖ መከታተል አለበት።ቅድመ-ፍርድ እስር (Pre-trial detention) ጥቅም ላይ መዋል ያለበት ሌላ ምንም አማራጭ ከጠፋ ብቻ ነው።
1.3. የግለሰብ ሁኔታን ያገናዘበ መመዘኛ (Individualized Assessment)ዋስትና የመፍቀድ ወይም የመከልከል ውሳኔ በጅምላ ወይም በደፈናው መሆን የለበትም።ፍርድ ቤቶች የእያንዳንዱን ተጠርጣሪ የግል ታሪክ፣ የማምለጥ ስጋት፣ የደኅንነት ሁኔታ እና ከማኅበረሰቡ ጋር ያለውን ትስስር ለይተው ማየት አለባቸው።
1.4. የተመጣጣኝነት መርህ (Principle of Proportionality)
የዋስትና ሁኔታዎች እና የሚጠየቀው የገንዘብ መጠን ከተከሰሰበት ወንጀል ክብደት እና ከተጠርጣሪው የኢኮኖሚ አቅም ጋር የተመጣጠነ መሆን አለበት።ተጠርጣሪው ሊከፍለው የማይችለውን ከፍተኛ የገንዘብ መጠን መወሰን፣ በተዘዋዋሪ ዋስትናን የመከልከል ያህል ስለሚቆጠር በዓለም አቀፍ ሕግ የተከለከለ ነው።
1.5. የፍትሐዊነት እና የማድላት ነፃነት መርህ (Non-Discrimination)ዋስትና በሃብት፣ በዘር፣ በጾታ፣ በሃይማኖት ወይም በፖለቲካ አቋም ላይ ተመሥርቶ መገደብ የለበትም።ድሆች የዋስትና ገንዘብ መክፈል ባለመቻላቸው ብቻ እስር ቤት እንዲቆዩ መደረግ የለበትም፤ ለዚህም ነው ከገንዘብ ውጪ ያሉ የዋስትና አማራጮች (ለምሳሌ፦ በቃል መገደድ፣ የፓስፖርት እገዳ) እንዲተገበሩ የሚመከረው።
1.6. የፍርድ ቤት ቁጥጥር እና ይግባኝ መብት (Judicial Review and Right to Appeal)ዋስትናን የመከልከል ወይም የመፍቀድ ሥልጣን የገለልተኛ ፍርድ ቤት ብቻ መሆን አለበት (የፖሊስ ወይም የዓቃቤ ሕግ ውሳኔ ሊሆን አይችልም)።ተጠርጣሪው ዋስትና ከተከለከለ፣ ውሳኔውን ለከፍተኛ ፍርድ ቤት በይግባኝ የማስመርመር መብት ሊኖረው ይገባል።
2. በመርህ ደረጃ የዋስትና መብት ሕገ-መንግሥታዊ ጥበቃ የሚደረግለት ቢሆንም፣ በሕግ በተደነገጉ ልዩ ሁኔታዎችና ገደቦች ምክንያት ነው።የዚህ ሕጋዊ ማዕቀፍ ዋና ዋና ምሰሶዎች፣ መርሆዎች እና ልዩ ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው፦
2.1. መሠረታዊው ሕገ-መንግሥታዊ መርህበኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 19(6) መሠረት፣ ማንኛውም የተያዘ ሰው በዋስ የመፈታት መብት አለው። ይህም ማለት በሕጉ መሠረት ዋስትና መፈቀድ መርህ (Rule) ሲሆን፣ መከልከል ወይም ያለ ዋስትና መታሰር ደግሞ ልዩ ሁኔታ (Exception) ነው።
2.2 ዋስትና ሙሉ በሙሉ የሚከለከልባቸው ወንጀሎች (Non-Bailable Offences)
በ1954 ዓ.ም የወጣው የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 63 እና ሌሎች ልዩ ሕጎች መሠረት፣ አንድ ተጠርጣሪ በሚከተሉት ከባድ ወንጀሎች ሲጠረጠር ፍርድ ቤት ዋስትና የመከልከል ግዴታ አለበት፦የሞት ቅጣት ወይም ከ12 ዓመት በላይ ጽኑ እስራት የሚያስቀጡ ከባድ ወንጀሎች (ለምሳሌ፦ ግድያ፣ የሀገር ክህደት)።የሙስና ወንጀል፦ በተሻሻለው የፀረ-ሙስና ልዩ የሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ መሠረት፣ ወንጀሉ ከ10 ዓመት በላይ የሚያስቀጣ ከሆነ ወይም ተደራራቢ ወንጀሎች ተደምረው ከ10 ዓመት በላይ የሚያስቀጡ ከሆነ ዋስትና ይከለከላል።የሽብርተኝነት ወንጀል፦ በፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ ሥር የሚወድቁ አብዛኞቹ ከባድ ወንጀሎች ተጠርጣሪው ያለ ዋስትና በማረፊያ ቤት እንዲቆይ ያደርጋሉ።
2.3. ፍርድ ቤት በራሱ ሥልጣን ዋስትና የሚከለክልባቸው ምክንያቶችበወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 67 መሠረት፣ ወንጀሉ በዋስ የሚያስፈታ ቢሆንም እንኳ ፍርድ ቤቱ የሚከተሉት ስጋቶች ካሉት ዋስትና ሊከለክል ይችላል፦ተጠርጣሪው የዋስትና ግዴታውን አክብሮ አይቀርብም (ይጠፋል) ተብሎ ሲሰጋ ፣
በዋስ ቢለቀቅ ሌላ ወንጀል ሊፈጽም ይችላል የሚል ጠንካራ ጥርጣሬ ሲኖር ፣
የምስክሮችን ቃል በመቀየር ወይም ማስረጃዎችን በማጥፋት በምርመራ ሂደት ላይ እንቅፋት ይፈጥራል ተብሎ ሲታመን ነው።
2.4. የምርመራ ጊዜ ማራዘሚያ (Remand)
ፖሊስ የጀመረውን የወንጀል ምርመራ በተገቢው ሰዓት አጠናቆ ካልጨረሰ፣ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 19(4) መሠረት ፍርድ ቤቱን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ (ቀጠሮ) ሊጠይቅ ይችላል። ፍርድ ቤቱ የፍትሕ አሰጣጡን ሂደት ከግምት ውስጥ በማስገባት ተጠርጣሪው ያለ ዋስትና በማረፊያ ቤት ቆይቶ ምርመራው እንዲቀጥል እስከ 14 ቀናት (እና ከዚያ በላይ በተደራራቢ ቀጠሮዎች) ሊፈቅድ ይችላል።
3. የዋስትና ይግባኝ መብት
በኢትዮጵያ የሕግ ማዕቀፍ እና በዓለም አቀፍ መርሆች መሠረት፣ የዋስትና ይግባኝ መብት (Right to Appeal Bail Decisions) አንድ ተጠርጣሪ ወይም ዓቃቤ ሕግ የታችኛው ፍርድ ቤት በዋስትና ላይ የሰጠውን ውሳኔ ለበላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ እንዲመረመርለት የመጠየቅ ሕጋዊ መብት ነው።ይህ መብት በኢትዮጵያ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ እና በይግባኝ ሥርዓት ውስጥ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች ያጠቃልላል፦
3.1. የይግባኝ መብቱ ለማን ይሰጣል?
የዋስትና ይግባኝ መብት ለሁለቱም ወገኖች እኩል የተሰጠ መብት ነው፦
ለተጠርጣሪው/ተከሳሹ፦ የታችኛው ፍርድ ቤት ዋስትና ሙሉ በሙሉ ሲከለክለው ወይም ተከሳሹ ሊያሟላው የማይችለውን እጅግ ከፍተኛ የገንዘብ መጠን ወይም ከባድ ግዴታ ሲጥልበት ይግባኝ ማለት ይችላል።
ለዓቃቤ ሕግ (መንግሥት)፦ የታችኛው ፍርድ ቤት "ዋስትና ሊሰጠው የማይገባውን ከባድ ተጠርጣሪ በዋስ ለቋል" ወይም "የተወሰነው የዋስትና መጠን ከተፈጸመው ወንጀል አንጻር በጣም አነስተኛ ነው" ብሎ ካመነ ውሳኔውን በመቃወም ይግባኝ ማለት ይችላል።
3.2. በይግባኝ ጊዜ የዋስትና ውሳኔን የማገድ ሥልጣን (Stay of Execution)
የታችኛው ፍርድ ቤት ለተጠርጣሪው ዋስትና ሲፈቅድ፣ ዓቃቤ ሕግ ውሳኔውን በመቃወም ይግባኝ ለማለት ካሰበ የዋስትናው ውሳኔ ለጊዜው ታግዶ ተጠርጣሪው እሥር ቤት እንዲቆይ ፍርድ ቤቱን የመጠየቅ መብት አለው።ይሁን እንጂ ዓቃቤ ሕግ ይግባኙን በአጭር ቀናት ውስጥ (ብዙውን ጊዜ በ48 ሰዓት ወይም በሕጉ በተቀመጠው አጭር ጊዜ) ለበላይ ፍርድ ቤት ካላቀረበ፣ የእገዳ ትዕዛዙ ተነስቶ ተጠርጣሪው በዋስ ይፈታል።
3.3. የበላይ ፍርድ ቤት ሥልጣን (Powers of the Appellate Court)
የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ ሶስት ዓይነት ውሳኔዎችን ሊሰጥ ይችላል፦
ማጽናት (Affirm)፦ የታችኛው ፍርድ ቤት የሰጠው የዋስትና መከልከል ወይም መፍቀድ ውሳኔ ትክክል ነው ብሎ መወሰን።
መሻር (Reverse)፦ የታችኛው ፍርድ ቤት የከለከለውን ዋስትና መፍቀድ፣ ወይም የፈቀደውን ዋስትና ሰርዞ ተጠርጣሪው እንዲታሰር ማዘዝ ይሆናል።
ማሻሻል (Modify)፦ የተወሰነውን የዋስትና የገንዘብ መጠን መቀነስ/መጨመር ወይም የዋስትና ሁኔታዎችን (ለምሳሌ የማምለጫ ስጋትን ለመቀነስ የፓስፖርት እገዳ መጣል) መለወጥ።
3.4. መሠረታዊ ዓላማው
ፍርድ ቤቶች በዋስትና መብት ላይ ሊፈጽሙ የሚችሉትን የሕግ ስህተት ወይም የሥልጣን አጠቃቀም ጉድለት (Abuse of Discretion) ለማረም እና የአንድን ሰው ሰብዓዊና ሕገ-መንግሥታዊ የነፃነት መብት ያለ አግባብ እንዳይገደብ ዋስትና ለመስጠት ነው።
4. ዋስትና የተከለከሉ ሰወች ጉዳያቸው እንዴት ይታያል?
ዋስትና የተከለከሉ ተከሳሾች ጉዳያቸው በፍርድ ቤት በቶሎ እንዲታይ እና ውሳኔ እንዲያገኝ ማድረግ ፍትህን ለማረጋገጥ እና ሰብአዊ መብትን ለመጠበቅ በጣም አስፈላጊ ነው።ይህንን ሂደት ለማፍጠን የሚረዱ ዋና ዋና መንገዶችና መፍትሄዎች የሚከተሉት ናቸው።
4.1. የህግ እና የሥርዓት ማሻሻያዎችልዩ የችሎት ቀጠሮ፡ ዋስትና ለተከለከሉ ተከሳሾች ቀዳሚነት የሚሰጡ ተከታታይ የችሎት ቀናትን መመደብ።የጊዜ ገደብ ማስቀመጥ፡ ክስ ከቀረበበት ቀን ጀምሮ የመጨረሻ ውሳኔ የሚሰጥበትን ከፍተኛ የጊዜ ገደብ በህግ መወሰን።ቀላል የክስ ሂደቶች፡ ውስብስብ ያልሆኑ እና ግልጽ የሆኑ ክሶችን በአጭር ሥርዓት (Summary Procedure) ማየት።
4.2. የፍርድ ቤቶች አሰራርን ማዘመንየዲጂታል አሰራር (E-Court)፦ የክስ መዝገቦችን እና ማስረጃዎችን በኮምፒውተር በማደራጀት የቢሮክራሲ መዘግየትን መቀነስ።የቅድመ-ችሎት ስብሰባ (Pre-Trial Conference)፦ ከችሎት በፊት በዓቃቤ ህግ እና በተከሳሽ ጠበቃ መካከል የሚደረጉ ውይይቶችን በማበረታታት ክርክሮችን ማጥበብ።የዕለታዊ መዝገብ አስተዳደር፡ በአንድ ችሎት የሚታዩ መዝገቦችን ቁጥር በመመጠን ለእያንዳንዱ መዝገብ በቂ ጊዜ መስጠት።
4.3.. የባለድርሻ አካላት ቅንጅትየማስረጃ ዝግጁነት፡ ፖሊስና ዓቃቤ ህግ ሙሉ ማስረጃ ሳይኖራቸው ሰውን ከማሰር መቆጠብ እና ምርመራን በፍጥነት ማጠናቀቅ።የጠበቆች ተገኝነት፡ ለተከሳሾች በቂ የመንግስት መከላከል ጠበቃ (Public Defender) በወቅቱ መመደብ።የማረሚያ ቤቶች ትብብር፡ ተከሳሾችን ያለ ምንም መዘግየት በየቀጠሮው ፍርድ ቤት ማቅረብ።
4.4. አማራጭ የፍትህ መፍትሄዎችየጥፋተኝነት ድርድር (Plea Bargaining)፦ ተከሳሽ እና ዓቃቤ ህግ በህጉ መሠረት ተደራድረው ጉዳዩን በቶሎ እንዲያልቅ ማድረግ።የዋስትና ሁኔታዎችን እንደገና ማየት፡ ክርክሩ ከዘገየ የዋስትና እገዳውን በማንሳት በገንዘብ ወይም በሰው ዋስ እንዲፈቱ መፍቀድ፥
ዋና ዋና መሠረታዊ መብቶች ናቸው።
5. ማጠቃለያ
ዋስትና መሠረታዊ መብት ሲሆን ህጉ በተለየ ሁኔታ እንዲከለከል ያስቀመጠ እንደሆነ ዋስትና የሚከለከልበት ሁኔታ አለ። ይሁን እንጂ ዋስትና የተከለከለ ሰው ይግባኝ ህገመንግስታዊ መብት ነው። ዋስትና የተከለከሉ ሰወች ጉዳያቸው ከሌላው ይልቅ በቶሎ ኤንዲታይ ማድረግ ንጹህ ሆኖ የመገመት ህገመንግስታዊ መብትንና ፍትህ የማግኘት ህገመንግስታዊ መብትን ማስጠበቅ ነው።
ማጣቀሻዎች
1. የኢፊድሪ ሕገመንግስት
2. ዓለም አቀፍ ስምምነቶች
3. የኢፊዲሪ ወንጀል ሕግ
4. የኢፊድሪ ወንጀል ስነ ስርአት
በፋንታሁን ደለለው , Fantahun Delelew , Lawyer.
https://www.facebook.com/s...

7 months ago
#ethiopia | የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) በዚህ ወር ለሚደረገው የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ የደርሶ መልስ ጨዋታ ዝግጅታቸውን አጠናክረዋል። ዋና አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ሀገሪቱን ወክለው ሜዳ ላይ የሚፋለሙትን 23 ተጫዋቾች ዝርዝር በዛሬው ዕለት ይፋ አድርገዋል።
በስብስቡ ውስጥ ልምድ ያላቸውና በሊጉ ድንቅ ብቃት እያሳዩ ያሉ ተጫዋቾች የተካተቱ ሲሆን፣ ሙሉ ዝርዝሩም እንደሚከተለው ነው፡-
🧤 የግብ ዘብ (Goalkeepers)
መረባቸውን ለማስከበር ኃላፊነት የተሰጣቸው ግብ ጠባቂዎች፡-
* አቡበከር ኑራ
* ፍሬው ጌታሁን
* ሰይድ ሀብታሙ
🛡️ የኋላ መስመር (Defenders)
የተከላካይ ክፍሉን የሚመሩት ብርቱዎቹ ተጫዋቾች፡-
* ያሬድ ባየህ፣ ምኞት ደበበ፣ አስራት ቱንጆ፣ አለምብርሀን ይግዛው፣ ያሬድ ካሳዬ፣ አብዱሰላም የሱፍ፣ ራምኬል ጄምስ እና ግሩም ሀጎስ።
⚙️ የመሐል ሜዳ (Midfielders)
የጨዋታውን ፍሰት የሚቆጣጠሩት የሞተር ክፍሎቹ፡-
* ጋቶች ፓኖም፣ ሀብታሙ ተከስተ፣ ብሩክ እንዳለ፣ ብዙአየሁ ሰይፉ፣ ወገኔ ገዛኸኝ እና ቢኒያም አይተን።
🎯 የአጥቂ መስመር (Forwards)
ግብ ለማደን የተመረጡት ፊት አውራሪዎች፡-
* አቤል ያለው፣ ከነአን ማርክነ፣ ቸርነት ጉግሳ፣ መስፍን ታፈሰ፣ አቡበከር ሳኒ እና ከቤ ብዙነህ።
የአዘጋጁ አስተያየት፡ ይህ ስብስብ የተመጣጠነ እና በሁሉም መስመር ላይ አማራጮችን የያዘ ይመስላል። በተለይ በመሐል ሜዳ ላይ ያለው የልምድ እና የጉልበት ጥምረት ለቡድኑ ትልቅ አቅም እንደሚሆን ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ethiopia #walias #afcon #ethiopianfootball #ዮሐንስሳህሌ #ዋሊያዎቹ #ኢትዮጵያ
9 months ago
🔥 እንዳያመልጥዎ! | የኮከቦች ጨዋታ በአዲስ አበባ ስታዲየም
#ethiopia | ነገ፣ እሁድ የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች (በውጭ እና በሀገር ውስጥ ያሉ) የሚገናኙበት ልዩ ጨዋታ ይደረጋል።
ተሳታፊዎች እነማን ናቸው?
በውጪ የሚኖሩ የቀድሞ ኮከቦች 🆚 በሀገር ውስጥ ያሉ ኮከቦች
(እነ አሸናፊ ግርማ፣ ዮርዳኖስ ዓባይ እና ሽመልስ በቀለን ጨምሮ)
📅 ቀን፡ ነገ እሁድ
⏰ ሰዓት፡ ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ
📍 ቦታ፡ አዲስ አበባ ስታዲየም
ቤተሰብ ይሁኑ፣ ይዝናኑ!
🛡️ የማይደፈረው የመሀል ደጀን - አሸናፊ ግርማ ⚽️
በኢትዮጵያ እግር ኳስ በተለይም በቅዱስ ጊዮርጊስ እና በብሔራዊ ቡድን ታሪክ ውስጥ በጠንካራ ተከላካይነቱ እና በዲሲፕሊኑ የሚታወቀው አሸናፊ ግርማ!
በቀኝ ተከላካይነት ቦታ ላይ በሚያሳየው አስደናቂ ብቃት፣ ወደ ፊት ሄዶ ኳስ በማሻገር እና የቡድንን ሞራል በመጠበቅ ረገድ አሸናፊ ተወዳዳሪ አልነበረውም። "ፈረሰኞቹ" በስኬት በቆዩባቸው ዓመታት የአሸናፊ ግርማ ሚና እጅግ ከፍተኛ ነበር።
ለክለቡም ሆነ ለሀገሩ በታማኝነት ያገለገለ እውነተኛ የስፖርት ሰው! 🙌
⚽️ የጎል ማሽኑ - ዮርዳኖስ ዓባይ! 🥅
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ካፈራቸው፣ መረብን ማራድ የዘወትር ተግባራቸው ከሆነ ምርጥ አጥቂዎች አንዱ!
ዮርዳኖስ ዓባይ በመብራት ኃይል (ኤሌክትሪክ) እና በቅዱስ ጊዮርጊስ ባሳለፈው ጊዜ በግዙፍ ሰውነቱ፣ በአየር ላይ ኳስ አጠቃቀሙ እና በድንቅ የጨረስ አቅሙ ይታወሳል።
በተለይም ወደ የመን በማምራት በ አል ሳቅር ክለብ የሰራው ታሪክ እና የሰበራቸው የጎል ክብረወሰኖች ስሙን በውጭ ሀገር ጭምር ገናና አድርገውታል።
ከዓመታት በኋላ ይህንን "የጎል አዳኝ" ነገ እሁድ በአዲስ አበባ ስታዲየም በሚደረገው የናፍቆት ጨዋታ ላይ ልንመለከተው ነው።
⚽️ የሜዳው ታንክ - ፍቅሩ ተፈራ!
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ተክለ ሰውነቱ፣ ጉልበቱ እና አጨራረሱ ለየት ያለ ድንቅ አጥቂ!
ፍቅሩ ተፈራ (ሌሜሳ) ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች በውጭ ሀገር ፕሮፌሽናል ሊጎች ተፈላጊ እንዲሆኑ በር የከፈተ ፈር ቀዳጅ ነው። ከቅዱስ ጊዮርጊስ ተነስቶ በደቡብ አፍሪካው ታላቅ ክለብ ኦርላንዶ ፓይሬትስ እና ሱፐር ስፖርት ዩናይትድ ያሳየው ብቃት አይረሳም።
በተለይም በሕንድ ሱፐር ሊግ (ISL) ታሪክ የመጀመሪያውን ጎል ለአትሌቲኮ ደ ኮልካታ በማስቆጠር ስሙን በታሪክ መዝገብ ላይ አሰፍሯል። የተከላካዮችን ጥንካሬ የሚፈትነው ጉልበቱ እና አልፎ አልፎ የሚያስቆጥራቸው "አክሮባቲክ" ጎሎች የፍቅሩ መለያዎች ናቸው።
ለኢትዮጵያ እግር ኳስ በዓለም አቀፍ መድረክ ተጠሪ ለነበረው ለዚህ ጀግና ክብር ይገባዋል! 🙌
#fikrutefera #ethiopianlegend #orlandopirates #isl #historymaker #waliyas #shimelisbekele #ethiopianfootball #waliyas #legend #playmaker #sport #football #ethiopia #legendsgame #addisababa #ashenafigirma #saintgeorgefc #ethiopianfootball #legend #defender #waliyas #yordanosabay #goalmachine #ethiopianfootball #legend #waliyas #yemenleague

1 year ago
በአስገዳጅ ሁኔታዎች ከሥራ ኃላፊነት መልቀቄን አስመልከቶ የተሰጠ
ጋዜጣዊ መግለጫ !
እኔ ያሬድ ኃይለማርያም ከተመሰረተ አራት አመት ተኩል ያስቆጠረውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከልን (Ethiopian Human Rights Defenders Center) በዋና ዳይሬከተርነት ሳገለግል ቆይቼ ባጋጠሙኝ አስገዳጅ ሁኔታዎች ከአገስት 1 ቀን 2025 (ሐምሌ 25 2017) ጀምሮ ከሃላፊነቴ እና ከድርጅቱ ለመልቀቅ መገደዴን ለማሳወቅ እወዳለሁ፡፡
ይህ ድርጅት ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲቋቋምና በሌሎች አፍሪካ አገሮች ከሚገኙ አቻ ድርጅቶች ጎን ቆሞ ለሰብአዊ መብት ተሟጋቶች መብት መከበርና አቅማቸውንም ለማጎልበት በርካታ ሥራዎችን እንዲሰራ ምሪት በመስጠትና በአጭር ጊዜም ውስጥ ድርጅቱ በአገር ውስጥና ከአገር ውጭም እውቅና እና ተቀባይነት እንዲያገኝ ከፍተኛ ጥረት ሳደርግ ቆይቻለሁ፡፡
ድርጅቱ ከተመሰረተ አጭር እድሜ ያለው ቢሆንም ሲያከናውን የቆያቸው ሥራዎች እና አገሪቱ ውስጥ ለሚፈጽሙ የመብት ጥሰቶች፤ በተለይም በጋዜጠኞች፣ በሲቪል ማህበረሰብ አባላት እና በመብት ተሟጋቾ ላይ የሚፈጸሙ የመበት ጥሰቶችን በማጋለጥና መብታቸው እንዲከበርበአደባባይ በመሟገት ግንባር ቀደም ተቋም ሆኖ እንዲቀጥል ከድርጅቱ ጠንካራ ሠራተኞችና የቦርድ አባላት ጋርበመሆን ቁልፍ ሚና ስጫወት ቆይቻለሁ፡፡
ይሁንና ከአንድ አመት ወዲህ በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ በሚገኙ ሚዲያዎች ላይ እየቀረብኩ አገሪቱ ውስጥ ስላለው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች የምሰጠቸው መገልጫዎችና ማብራሪያዎች፣ በማህበረ ድህረ ገጾች ላይ ዜጎችን ስለ መብታቸው እንዲያውቁና በአገሪቱ ውስጥ ስላለው የሰብአዊ መብቶች አያያዝ በማስመልከት የማካፍላቸው ሃሳቦችና የምሰነዝራቸው የሰሉ ትችቶች በአገዛዝ ሥርአቱ ዘንድ በጥሩ ሁኔታ እየታ ባለመምጣታቸው የተነሳ በተለያዩ አቅጣጫዎች የተለያዩ አይነት ጫናዎችን ሳስተናግድ ቆይቻለሁ፡፡
የተለያዩ ዛቻዎች፣ ማስፈራሪያዎችና ትንኮሳዎችን በጸጥታ አካላት በኩል ሲፈጸሙ እንዲሁም በተንቀሳቃሽ ስልኮቼ ያልተለመዱ ጥሪዎችን ሳስተናግድ ያለውን ግልፅ ስጋት ችላ በማለት በሥራዬ ላይ አተኩሬ ቆይቻለሁ፡፡ ሆኖም በዚህ ሁኔታ ውስጥ በነጻነት ለመወጣትም ሆነ የተቀበልኩትን የሥራ ሃላፊነት በብቃት ለማከናወን የማልችልበት ደረጃ ላይ መድረሴን ስላረጋገጥኩ በተጓዳኝም በሥራ ጫና ብዛት ችላ ያልኳቸው የግል የጤና ጉዳዮችም ስለነበሩ እነዚህን ምክንያቶች በመጥቀስ ከወራቶች በፊት ለድርጅቱ ቦርድ የመልቀቂያ ጥያቄዬ አቅርቤ በምትኬ ሰው እንዲፈልጉ አሳውቄያለሁ፡፡
ቦርዱም ጥያቄዬን ተቀብሎ እስከ ዲሴምበር(ታህሳስ) ወር መጨረሻ 2025 ድረስ እንድቆይና አመራሩን የሚረከቡ ሠራተኞችን እያዘጋጀሁና እያሰለጠንኩ እንድቆይ ተስማምተን ነበር፡፡ ይሁንና ከላይ በገለጽኳቸው ምከንያቶች ከድርጅቱ ጋር የምቆይበት ጊዜ ከወራቶች ወደ ቀናት ለያጥር ችሏል፡፡ እኔም ሁኔታዎችን ከግምት በማስገባት ከዛሬ ሁለት ሳምንት በፊት ለድርጅቱ ሌላ የመልቀቂያ ደብዳቤ ለማስገባት ተገድጃለሁ፡፡
ይሁንና እኔ ለድርጅቱ ቦርድ የመልቀቂያ ደብዳቤ ባስገባሁ በሳምንቱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን መሥሪያ ቤት ሐምሌ 14፣ 2017 በአንድ ከፍተኛ ሃላፊው በኩል ለሥራ ባልደረቦቼ ስልክ በመደወል ወደ ቢሯቸው ከጠሩ በኋላ እኔን በተመለከተ የተለያዩ ጥያቄዎችን ካነሱ በኋላ በግልጽ የድርጅቱ ቦርድ በአስቸኳይተሰብስቦ እኔን ከምመራው ድርጅት ሃላፊነት ጋር ተያይዞ ያላቸውን አቋምና ውሳኔን በደብዳቤ ለባለሥልጣን መሥሪያቤቱ በጽሑፍ እንዲያሳውቅ የአንድ ሳምንት ጊዜ ሰጥቷል፡፡ ምንም እንኳን እኔ ቀደም ብዮ በራሴ ፍቃድ ሁኔታዎችን ከመረመርኩ በኋላ ከሥራ የመልቀቂያ ደብዳቤ ያስገባሁ ቢሆንም የባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ግን ፍጹም አግባብነት በሌለው መልኩ በድርጅቱ የውስጥ አሰራር ጣልቃ የገባ ተግባር ፈጽሟል፡፡
የዚህም ጋዜጣዊ መግለጫ ዋና አላማዎች፤
1ኛ/ ይህ መግለጫ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በማናቸውም ሚዲያ ልቀርብና ሃሳቤንም ላካፍል የምችለው እራሴን በመወከልና እንደ አንድ የሰብአዊ መብት ባለሙያ እንጂ እስከ አሁን ስመራ የቆየሁትንም ሆነ የትኛውንም ድርጅት ወክዬ እንዳልሆነ ለማሳወቅ ነው፡፡ በማህበራዊ ድህረ ገጾችም ከዚህ በኋላ የማካፍላቸው መረጃዎች እና የማስተላልፋቸው መልዕከቶች እኔን ብቻ የሚወከሉ እና እንደ አንድ በግል ለሰብአዊ መብቶች መከበር እንደሚቆረቆር ተሟጋች መሆኑን ለሁሉም የሚዲያ ባለሙያዎች፤ በተለይም በየጊዜው በመድረካቸው ሃሳቤን እንዳቀርብ ለሚያስተናግዱኝ መገናኛ ብዘሃን ለማሳወቅ ነው::
2ኛ/ ሁለተኛውና እጅግ ትልቅ ትኩረት እንዲሰጠው የምፈልገው ጉዳይ በተወሰነ ደረጃ መሻሻሎች ታይተወብት የነበረው የአገራችን የሲቪከ ምህዳር ዳግም እየተዘጋና ከፍተኛ አደጋዎችም ከፊቱ የተደቀኑ መሆኑን እና ሚዲያዎችም ለጉዳዩ በቂ ትኩረት ሰጥተው መንግስት በሲቪል ማህበራት ላይ እና በምህዳሩ ላይ እያሳደረ ያለውን ዘርፈ ብዙ ጫና ትኩረት ሰጥታቸው እውነታውን ለህዝብና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ማሳወቃችውን ተግታችሁ እንድትቀጥሉ ለማሳሰብ ነው፡፡ መንግስት የሲቪክ ምህዳሩን መልሶ በከፋ ጫና ውስጥ ለማቆየት እያረቀቀ ያለውን እጅግ አደገኛ የህግ ማሻሻያ ጨምሮ በሲቪል ማህበራት ላይ ውስጥ ለውስጥ እያደረሰ ላለው ጫና ከላይ የጠቀስኩት በእኔ እና በሌሎች አገር ጥለው እንዲሰደዱ በተደረጉት የኢሰመጉ የቀድሞ ዋና ዳይሬከተር አቶ ዳን ይርጋ ሌሎችም ተቋማት ጉዳይ በቂ ማሳያዎች ናቸው፡፡
3ኛ/ ላለፉት ስድስት ወራት ያህል በማህበራዊ ድህረ ገጾች በተለይም በፌስቡክና በቴሌግራም ዘወትር ቅዳሜ “መልዕከተ ቅዳሜ" በሚል ከአንድ አመት በላይ ያለምንም ማሰለስ ማህበረሰባችንን ስለ መብቱ እንዲያውቅና በአንዳንድ ወሳኝ በሆኑ የመብት ነክ ጉዳዮች ያለው ግንዛቤ እንዲሰፋ ውይይት አጫሪ የሆኑ አጫጭር መጣጥፎችን ከማካፈል ተቆጥቤ ቆይቻለሁ፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት ከላይ በጠቀስኳቸው ምክንያቶች ስመራው በቆየሁት ድርጅት ላይ ለደርሱ የሚችሉ ጫናዎችን ለመቀነስ በሚል ነበር፡፡ እኔ ወደ ማህበራዊ ሚዲያ በቋሚነት በመምጣት ሰፋፉና ጥልቅ ቁምነገሮች ላይ በማተኮር የግል ምልከታዬን ለማካፈል የወሰንኩት በአገሪቱ ውስጥ ያለው የሚዲያ ምህዳር እጅግ እየጠበበና በተለይም የሰላ ትችት በመሰንዘርየሚታወቁ የህትመት ጋዜጣዎችና መጽሄቶች በመንግስት በደረሰባቸው ከፍተኛ ጫና እና ወከባ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ በመቋረጣቸው ማህበረሰባችን ትምህርት ሊያገኝባቸው የሚችሉ መድረኮች ጠበዋል ከሚል መነሻ ነው:: በመሆኑም ከዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ በኋላ በቋሚነት በሙሉም የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ በሰብአዊ መብት እና ተያያዥ አገራዊ ጉዳዮች ላይ በቋሚነት ትንታኔዎችን እና የግል ምልከታዎቼን የማካፍል መሆኑን እየገለጽኩ የተለመደው መረጃዎችን የማጋራት ትብብራችሁ እንዳይለየኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡
በዚህ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ መረጃ ወይም ማብራሪያ ለምትፈልጉ የሚዲያ ባለሙያዎች በማናቸውም ጊዜ በቀጥታ ልታገኙን እንደምትችሉ እየገለጽኩ እስከ ዛሬ መድረኮቻችሁን ከፍት በማድረኛ ለሰብአዊ መብት ጉዳዮች ከፍተኛ ትኩረትና ቅድሚያ በመስጠት በቃለ ምልልስ፣ ጽሁፎቼን በማጋራት ወይም በማናቸውም መልኩ መድረክላመቻቻችሁልኝ ጋዜጠኞችና የሚዲያ ባለሙያዎች ሁሉ ምስጋናዮ የላቀ ነው፡፡
አሁንም ለተገፉ እና መብታቸው ለተጣሰባቸው ሰዎች ሁሉ ድምጽ የመሆን ቁርጠኝነቱ ከእኔ ጋር ስለሆነ በማናቸው ጊዜ በሰብአዊ መብቶች ጉዳይ ለምታደርጉት ጥረት እና ለምትፈልጉት መረጃና ማብራሪያ ሁሉ የበኩሌን ቀና ትብብርና ተሳትፎ ለማድረግ ዝግጁ መሆኔን በታላቅ ትህትና እገልጻለሁ፡፡
ያሬድ ሃይለማርያም
Yared Hailemariam
በሰብአዊ መብቶች አማካሪና ተመራማሪ

Sponsored by
Surafel
Comments