8 days ago
ዋልያው ተሸነፈ፤ ውቢቷ ባህርዳርና ታማኙ የእግር ኳስ ቤተሰብ ግን ዛሬም አሸንፈዋል!
#ethiopia | ዋልያው ተሸንፏል። ውቢቷ ባህርዳርና ታማኙ የእግር ኳስ ቤተሰብ ግን ዛሬም አሸንፈዋል።
የታራንጋው አንበሳ በጨዋታው እንደተጠበቀው ጥርሱን አላሳየም። ኳሱን በትዕግሥት ከግራ ወደ ቀኝ እያንቀሳቀሰ፣ ውዱን ሦስት ነጥብ በዕቅድና በተደራጀ አጨዋወት ነጥቆ ወጥቷል።
እኛ ግን ያነበብነውን የትናንት መጽሐፍ ዛሬም እየደገምን ነው።
ከጎል ፊት እየደረሱ መሽኮርመም፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ አጥቂዎች የተለመደ ችግር ሆኖ ቀጥሏል። ዋልያው በጨዋታው በላቀ ተነሳሽነትና ፍላጎት ተንቀሳቅሶ፣ በተደራጀ እንቅስቃሴም የጎል ዕድሎችን ለመፍጠር ሞክሯል።
ጥሩ ለመጫወት መሞከር ግን ሞራል እንጂ ድል አይሆንም። በጨዋታው የታዩ መልካም ጥረቶች ሁሉ የሚፈለገውን ውጤት ካላመጡ፣ ጥያቄው አንድ ነው፦ ለምን?
በመጨረሻው የማጥቃት ሦስተኛ ክፍል — Final Third — እየደረሱ ዕድሎችን ማባከን፣ እንደ ትናንቱ ዛሬም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ሕያው ውርስ ሆኖ ቀጥሏል።
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጎል ማስቆጠር እንደ መስቀል ወፍ በዓመት አንዴ የሚታይ ነገር ሆኗል፤ ያውም ቀንቶ ከተሳካ።
ብሔራዊ ቡድኑም ሆነ ክለቦቻችን በዓለም አቀፍ መድረክ ተጋጣሚያቸው ላይ ጎል ማስቆጠር ለምን እንዲህ ከባድ ሆነ? ይህ ጥያቄ ከውጤት በላይ የሚመለከተው የሥልጠና፣ የተጫዋች ልማትና የአጥቂዎች የመጨረሻ ውጤታማነት ጉዳይ ነው።
ከጎል ፊት የሚፈለገው የማስቆጠር ሂደት ግን ግልጽ የሆነ የሥልጠና እቅድና የተደጋጋሚ ልምምድ ይፈልጋል። የFinal Third እንቅስቃሴ፣ የመጨረሻ ፓስ፣ የኳስ ቁጥጥር፣ የጎል ላይ የመወሰን ችሎታና የመጨረሻ ምት ውጤታማነት በተከታታይ ሊሰሩባቸው የሚገቡ መስኮች ናቸው።
ከዚህ ይልቅ በእግር ኳሱ ዙሪያ በመጠላለፍ፣ በመወቃቀስና በመቧደን የሚጠፋው ጉልበት ለልማትና ለሥልጠና ቢውል ይሻላል። በተለይም በብሔራዊ ቡድን ኃላፊነት የሚኖራቸው ሰዎች ከውጤት በተጨማሪ የረጅም ጊዜ የእግር ኳስ ልማት ላይ ሊያተኩሩ ይገባል።
ሽንፈት ሲመጣ ትችት ይኖራል። ይህም የስፖርት ቤተሰቡ ተፈጥሯዊ ምላሽ ነው። የሚጠበቀው ግን ትችትን ከጠላትነት ይልቅ ለማሻሻያ እድል ማድረግ ነው።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ወጥነት ባለው መልኩ መሸነፍን እንጂ ማሸነፍን እንደማያውቅ የሚያሳየው ይህ የውጤት ችግር ነው። ታማኙ የስፖርት ቤተሰብም መሸነፍን ተለማምዶ ድልን ለእናት ሀገሩ ይናፍቃል፤ ነገር ግን ብሔራዊ ቡድኑን መደገፍ አያቆምም።
ዛሬም ከውቢቷ ባህርዳር ማራኪ የስታዲየም ድባብ ጋር፣ እንደ ሁልጊዜው በተሸነፈው የእግር ኳሳችን ስሌት ውስጥ አሸንፎ የታየው ታማኙ የስፖርት ቤተሰብ ነው።
የባህርዳር አለም አቀፍ ስታዲየምም በደረጃው ተጠናቆ፣ ለብዙ የለውጥ የቤት ሥራዎች የሚጠብቀው የኢትዮጵያ ስፖርት እንደ ትንሳኤ ብቅ ያለ የትውልዱ አዲስ የኩራት ምንጭ ሆኖ ታይቷል።
ሳይሰራ ብዙ የሚጠበቀው ውጤት ሲጠፋ እጅግ የሚበሳጨው እግር ኳሳችን ግን፣ በእልፍ የቤት ሥራዎች መካከል ያልዘራውን ለማጨድ እየተመኘ ዛሬም ቀጥሏል።
ዋልያው ዛሬ ተሸንፏል፤ የባህርዳር የእግር ኳስ ቤተሰብ ግን በድጋፉ፣ በፍቅሩና በታማኝነቱ እንደገና አሸንፏል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ግን ከዚህ በላይ መጠበቅ የለበትም፤ መሥራት አለበት።
Via ኤፍሬም የማነ
#ethiopianfootball #waliyas #bahirdar #ethiopiansport #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

9 months ago
🔥 እንዳያመልጥዎ! | የኮከቦች ጨዋታ በአዲስ አበባ ስታዲየም
#ethiopia | ነገ፣ እሁድ የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች (በውጭ እና በሀገር ውስጥ ያሉ) የሚገናኙበት ልዩ ጨዋታ ይደረጋል።
ተሳታፊዎች እነማን ናቸው?
በውጪ የሚኖሩ የቀድሞ ኮከቦች 🆚 በሀገር ውስጥ ያሉ ኮከቦች
(እነ አሸናፊ ግርማ፣ ዮርዳኖስ ዓባይ እና ሽመልስ በቀለን ጨምሮ)
📅 ቀን፡ ነገ እሁድ
⏰ ሰዓት፡ ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ
📍 ቦታ፡ አዲስ አበባ ስታዲየም
ቤተሰብ ይሁኑ፣ ይዝናኑ!
🛡️ የማይደፈረው የመሀል ደጀን - አሸናፊ ግርማ ⚽️
በኢትዮጵያ እግር ኳስ በተለይም በቅዱስ ጊዮርጊስ እና በብሔራዊ ቡድን ታሪክ ውስጥ በጠንካራ ተከላካይነቱ እና በዲሲፕሊኑ የሚታወቀው አሸናፊ ግርማ!
በቀኝ ተከላካይነት ቦታ ላይ በሚያሳየው አስደናቂ ብቃት፣ ወደ ፊት ሄዶ ኳስ በማሻገር እና የቡድንን ሞራል በመጠበቅ ረገድ አሸናፊ ተወዳዳሪ አልነበረውም። "ፈረሰኞቹ" በስኬት በቆዩባቸው ዓመታት የአሸናፊ ግርማ ሚና እጅግ ከፍተኛ ነበር።
ለክለቡም ሆነ ለሀገሩ በታማኝነት ያገለገለ እውነተኛ የስፖርት ሰው! 🙌
⚽️ የጎል ማሽኑ - ዮርዳኖስ ዓባይ! 🥅
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ካፈራቸው፣ መረብን ማራድ የዘወትር ተግባራቸው ከሆነ ምርጥ አጥቂዎች አንዱ!
ዮርዳኖስ ዓባይ በመብራት ኃይል (ኤሌክትሪክ) እና በቅዱስ ጊዮርጊስ ባሳለፈው ጊዜ በግዙፍ ሰውነቱ፣ በአየር ላይ ኳስ አጠቃቀሙ እና በድንቅ የጨረስ አቅሙ ይታወሳል።
በተለይም ወደ የመን በማምራት በ አል ሳቅር ክለብ የሰራው ታሪክ እና የሰበራቸው የጎል ክብረወሰኖች ስሙን በውጭ ሀገር ጭምር ገናና አድርገውታል።
ከዓመታት በኋላ ይህንን "የጎል አዳኝ" ነገ እሁድ በአዲስ አበባ ስታዲየም በሚደረገው የናፍቆት ጨዋታ ላይ ልንመለከተው ነው።
⚽️ የሜዳው ታንክ - ፍቅሩ ተፈራ!
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ተክለ ሰውነቱ፣ ጉልበቱ እና አጨራረሱ ለየት ያለ ድንቅ አጥቂ!
ፍቅሩ ተፈራ (ሌሜሳ) ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች በውጭ ሀገር ፕሮፌሽናል ሊጎች ተፈላጊ እንዲሆኑ በር የከፈተ ፈር ቀዳጅ ነው። ከቅዱስ ጊዮርጊስ ተነስቶ በደቡብ አፍሪካው ታላቅ ክለብ ኦርላንዶ ፓይሬትስ እና ሱፐር ስፖርት ዩናይትድ ያሳየው ብቃት አይረሳም።
በተለይም በሕንድ ሱፐር ሊግ (ISL) ታሪክ የመጀመሪያውን ጎል ለአትሌቲኮ ደ ኮልካታ በማስቆጠር ስሙን በታሪክ መዝገብ ላይ አሰፍሯል። የተከላካዮችን ጥንካሬ የሚፈትነው ጉልበቱ እና አልፎ አልፎ የሚያስቆጥራቸው "አክሮባቲክ" ጎሎች የፍቅሩ መለያዎች ናቸው።
ለኢትዮጵያ እግር ኳስ በዓለም አቀፍ መድረክ ተጠሪ ለነበረው ለዚህ ጀግና ክብር ይገባዋል! 🙌
#fikrutefera #ethiopianlegend #orlandopirates #isl #historymaker #waliyas #shimelisbekele #ethiopianfootball #waliyas #legend #playmaker #sport #football #ethiopia #legendsgame #addisababa #ashenafigirma #saintgeorgefc #ethiopianfootball #legend #defender #waliyas #yordanosabay #goalmachine #ethiopianfootball #legend #waliyas #yemenleague

Comments