አዲስ አበባ ፡ የኤምኤምኤ እና የቦክስ ስፖርት ውድድር ሊካሄድ ነው
#ethiopia | በአዲስ አበባ ከተማ ከዚህ ቀደም ከተደረጉት የንክኪ ስፖርት ሁነቶች ሁሉ እጅግ ግዙፍ የሆነው የኢትዮ ፋይት ናይት የውድድር መድረክ ይፋ ሆኗል::
ዝግጅቱ የአዲስ አበባ ኪክ ቦክስ ፌዴሬሽን፣ የአዲስ አበባ ቦክስ ፌዴሬሽን እና የአዲስ አበባ ወጣቶች ስፖርት ቢሮ በጋራ በመተባበር ያዘጋጁት ሲሆን ነሀሴ 23 ቀን 2018 ዓ.ም (Aug 29/2026) በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቤንሽን ሴንተር በደመቀ ሁኔታ ይካሄዳል::
በዚህ ልዩ ስፖርታዊ ፌስቲቫል ላይ በድብልቅ ማርሻል አርት (MMA) ዘርፍ ዓለም አቀፍ እውቅና ያላቸው የውጭ ሀገር ተወዳዳሪዎች የሚሳተፉ ሲሆን ሀገራችንን ወክለው ደግሞ ቢኒያም ሽብሬ፣ ክብሮም ንጉሴ እና አገረሰላም አርባን ጨምሮ በርካታ ስፖርተኞች ወደ መድረኩ ይወርዳሉ::
በጠቅላላው ከ6 እስከ 8 የሚደርሱ ብርቱ ፍልሚያዎች የሚስተናገዱ ሲሆን ተወዳዳሪዎቹ የተመረጡት በውድድር ታሪካቸው፣ በዓለም አቀፍ ልምዳቸው፣ በአካል ብቃት ጥንካሬያቸው እና ማራኪ ትዕይንት ማሳየት በሚችሉበት ብቃታቸው ላይ ተመስርቶ ነው::
አትሌቶቹ በፌዴሬሽኑ ህግ መሰረት አስፈላጊውን የህክምና ምርመራ፣ የክብደት ልኬትና የፈቃድ አሰጣጥ ሂደቶችን ያጠናቀቁ ሲሆን ዝርዝር የክብደት መጠናቸውና ዜግነታቸው በቅርቡ ይፋ ይደረጋል::
ይህንን ታሪካዊ ፍልሚያ ለመታደም ከ8,000 እስከ 10,000 የሚደርሱ የስፖርት አፍቃሪዎች በአዳራሹ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል::
አዘጋጆቹ የአፍሪካንና የሀገራችንን ስፖርታዊ አቅም ለዓለም የሚያስተዋውቅ፣ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና ፍጹም ሙያዊ ብቃት የተላበሰ ዝግጅት ለማቅረብ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል::
የውድድሩ ዋነኛ ዓላማ የንክኪ ስፖርቶችን ከማሳደግ ባለፈ ለሀገር ውስጥ አትሌቶች ሙያዊ መድረክ መፍጠር፣ ወጣቶችን ማነሳሳት፣ ስፖርታዊ ቱሪዝምን በአዲስ አበባና በኢትዮጵያ ማስፋፋት እንዲሁም ሀገራችንን የዓለም አቀፍ ውድድሮች ማዕከል ማድረግ ነው::
ዝግጅቱ የሚስተናገድበት አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቤንሽን ሴንተር (AICC) ዘመናዊ የዲጂታል ምስልና የድምፅ መገልገያ መሳሪያዎች የተሟሉለት በመሆኑ ለታዳሚው ምቹ መዝናኛን ለመፍጠር ተመራጭ አድርጎታል::
ገራሚ ኢቨንትስ የዝግጅቱን አጠቃላይ የፕሮዳክሽን ስራ በማስተናገድ ከባለቤቶቹ ጋር በጋራ የሚሰራ ሲሆን ለአትሌቶች ስልጠና፣ ለደህንነት፣ ለቦታ ዝግጅትና ለሎጂስቲክስ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ፈሷል::
ይህንን ውድድር በኢትዮጵያና በአፍሪካ ደረጃ ተከታታይነት ባለው መልኩ ለማዘጋጀት የታቀደ በመሆኑ፣ የዝግጅቱን ጥራት ይበልጥ ለማሳደግ ሀገር በቀልና ዓለም አቀፍ ተቋማት በስፖንሰርሺፕ፣ በሚዲያ ሽፋን፣ በዲጂታል ግብይትና በቪአይፒ ተሳትፎ ላይ አብረው እንዲሰሩ ጥሪ ቀርቧል::
የመግቢያ ትኬት ዋጋንና የስርጭት ሽፋንን በተመለከተ ከሚዲያ አጋሮች ጋር ውይይት እየተደረገ ሲሆን የቴሌቪዥንና የዲጂታል ቀጥታ ስርጭት መረጃዎች በቅርቡ ይፋ የሚደረጉ ይሆናል::
#mma #boxing #ethiofightnight #sportstourism #aicc #ethiopianathletes #geramievents #sports #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

4 months ago