Logo
FIDEL POST NEWS
እስራኤል 8,000 ኢትዮጵያውያን ጥገኝነት ጠያቂዎችን ልታባርር ነው

​እንደ Middle East Eye ዘገባ፣ የእስራኤል መንግሥት በመጪው ሚያዝያ ወር በሀገሪቱ የሚገኙ 8,000 ኢትዮጵያውያን ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ አቅዷል።

የሕዝብና ኢሚግሬሽን ባለሥልጣን ከሚያዝያ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ስደተኞቹን በቁጥጥር ስር ማዋልና ማባረር እንደሚጀምር ታውቋል።

​የእርዳታ ድርጅቶች እንደሚገልጹት፣ ሊባረሩ ካሉት መካከል 1,000 ያህሉ ከትግራይ ክልል የመጡ ናቸው።

የእስራኤል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መንግሥት "አይሁዳዊ አይደሉም" ያላቸውን እነዚህን ስደተኞች እንዲያባርር ፈቅዷል።

​በአሁኑ ወቅት እስራኤል ውስጥ 72,000 ገደማ ጥገኝነት ጠያቂዎች የሚገኙ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 57% የሚሆኑት በድህነት ውስጥ እንደሚኖሩ የ Assaf ድርጅት መረጃ ያመለክታል።

መንግሥት ስደተኞቹን "ህገ-ወጥ ሰርጎ ገቦች" በሚል መፈረጁም ተገልጿል።

​ምንጭ፦ Middle East Eye

https://www.middleeasteye....
3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.