15 days ago
በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ በሱዳን 1 ለ 0 ተሸነፈች
************
ኬኒያ፣ ታንዛኒያ እና ዩጋንዳ በጋራ ለሚያስተናግዱት የ2027 አፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በማጣሪያው የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደረገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሱዳን 1 ለ 0 ተሸንፏል።
በደቡብ ሱዳን ጁባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ በረከት ሳሙኤል የሰራውን ጥፋት ተከትሎ የተሰጠውን የፍፁም ቅጣት ምት ሙሐመድ ዒሳ 86ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሮ ሱዳን ሙሉ ሦስት ነጥብ ይዛ እንድትወጣ አስችሏል።
በተመሳሳይ ሰዓት ሞዛምቢክ ከ ሴኔጋል ያደረጉት የምድብ 10 ሌላኛው ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል።
ውጤቱን ተከትሎ ሱዳን ምድቡን በሦስት ነጥብ መምራት ጀምራለች።
ዋልያዎቹ 2ኛ የማጣሪያ ጨዋታቸውን በቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ከሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደርጋሉ።
#ethiopia #afcon #sudan #football #sports #ebc

የጨዋታ ቀን
መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታውን ዛሬ ከቀኑ 10፡00 ላይ ከሱዳን ብሔራዊ ቡድን ጋር በደቡብ ሱዳን ጁባ ናሽናል ስታዲየም ያደርጋል።
ከጨዋታው አስቀድሞ በጁባ ስታዲየም በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ እና አምበሉ ያሬድ ባየህ ዋሊያዎቹ ለድል ሙሉ በሙሉ መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል።
አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ እግር ኳስ የዛሬ እንጂ የትናንት ታሪክ አይደለም ያለፈውን ውጤት ወደ ጎን በመተው በ90 ደቂቃው ሙሉ ሦስት ነጥብ ለማስመዝገብ ተዘጋጅተናል።
ብሔራዊ ቡድናችን ላለፉት አምስት ዓመታት የሜዳውን ጨዋታዎች ከሀገር ውጭ ሲያደርግ በመቆየቱ ከሜዳ ውጭ መጫወት አዲስ አይሆንበትም።
ይልቁንም በጁባ የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን ደጋፊዎቻችን ለቡድኑ ትልቅ ተጨማሪ ጉልበት ይሆናሉ ያሉ ሲሆን አምበሉ ያሬድ ባየህ በበኩሉ ቡድናችን ለአንድ ወር ያህል ጠንካራ ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል።
በደቡብ ሱዳን የሚኖረው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ እና ወንድም የደቡብ ሱዳን ህዝብ የሚያደርጉልንን ድጋፍ ተስፋ በማድረግ የተሳካ ውጤት እንደምናስመዘግብ አንጠራጠርም ብሏል።
ዋሊያዎቹ ትላንት ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ በጁባ ብሔራዊ ስታዲየም የመጨረሻ ዝግጅታቸውን ያጠናቀቁ ሲሆን ሁሉም ተጫዋቾች በጥሩ የጤንነት እና የሥነ-ልቦና ዝግጅት ላይ ይገኛሉ።
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ከሱዳን ጋር የ 2027 አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታውን ያደርጋል።
የማጣሪያ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታው በጁባ ብሔራዊ ስታዲየም ከቀኑ 10:00 ሰዓት ላይ ይጀመራል።
ቡድኖቹ ምን አይነት ማልያ ይለብሳሉ ?
ዋልያዎቹ በጨዋታው አረንጓዴ ቲሸርት ፣ ቢጫ ቁምጣ እና ቀይ ካሶተኒ ለብሰው ወደ ሜዳ ይገባሉ።
የተጋጣሚ ሱዳን ብሔራዊ ቡድን በበኩሉ ሙሉ ነጭ ማልያ እንደሚለብስ ታውቋል።
ጨዋታውን ማን ይመራል ?
ላይቤሪያዊው ዳኛ ዋሽንግተን ን ዶሎ እንዲመሩ ተመርጠዋል።
ጨዋታውን በምን መከታተል ይቻላል ?
የሁለቱን ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ ቤን ስፖርት በቀጥታ ስርጭት ሊያስተላልፍ እንደሚችል ተዘግቧል።
ተጨማሪ ጨዋታውን መከታተያ አማራጮች ካሉ የጨዋታ ሰዓት ሲደርስ ወደ ቤተሰቦቻችን የምናደርስ ይሆናል።
@tikvahethsport kidusyoftahe

16 days ago
“ ሶስት ነጥቡን ለመውሰድ ተዘጋጅተናል ” አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ
የዋልያዎቹ ዋና አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ቡድኑ ለነገው የሱዳን ጨዋታ ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።
“ ለሱዳን ትልቅ ክብር አለን ” ያሉት ዮሐንስ ሳህሌ “ በደንብ የተደራጁ መሆናቸውን እናውቃለን ” ብለዋል።
ሱዳን በጨዋታው የሽግግር እግር ኳስ ልትጫወት እንደምትችል ገልፀው ለዚህም መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
አክለውም “ ቡድኑ ልምድ ያላቸውን ከወጣቶች አዋህዶ ተዘጋጅቷል “ ያሉ ሲሆን “ የተሰጣቸውን ስራ መስራት ይችላሉ ብለን እናምናለን "ብለዋል።
“ ያለፈ ታሪክ ያለፈ ነው ፣ ለዚህ ጨዋታ ተዘጋጅተናል ሶስት ነጥቡን ለመውሰድ ዝግጁ ነን። ” አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ
የኢትዮጵያ እና ሱዳን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ነገ ምሽት 10:00 ሰዓት ደቡብ ሱዳን ጁባ ስታዲየም ይካሄዳል።
@Tikvahethsport kidusyoftahe

18 days ago
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ ደቡብ ሱዳን አመራ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከሱዳን ብሔራዊ ቡድን ጋር ለሚያደርገው የመጨረሻ የምድብ ጨዋታ ወደ ደቡብ ሱዳን መዲና ጁባ የሚደረገውን ጉዞ ጀምሯል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት ለብሔራዊ ቡድኑ አባላት የማበረታቻ መልዕክት አስተላላፊው ሽኝት አድርገውላቸዋል።
ብሔራዊ ቡድኑ የመጀመሪያውን የማጣሪያ ጨዋታ የፊታችን አርብ ምሽት 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ከሱዳን ጋር የሚያደርግ ይሆናል።

Sponsored by
Surafel
19 days ago
የሰንደቅ ዓላማው ዘብ፤ የኢትዮጵያ የብረት አጥር፦ ከብቁ የሰው ኃይል እስከ ዘመናዊ ትጥቅ
************************
ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ከመቼውም ጊዜ በላይ ዘመናዊ፣ ብቁ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ የመከላከያ ኃይል እየገነባች ከዘመኑ እኩል ፍጥነት እየተጓዘች ትገኛለች።
ታድያ ይህ ጉዞ የሚጀምረው ትጥቅን እና ሎጅስቲክስን በራስ አቅም ከማምረት እና ከማደስ ነው።
መዳረሻው ደግሞ ዘመናዊ መሣሪያዎች በአግባቡ ታጥቆ የሀገርን ሉዓላዊነት የሚጠብቅ ለጠላት የበጋ መብረቅ ለሕዝብ ደጀን የሆነ የሰው ኃይል ማፍራት ነው።
ይህ መከላከያውን ብሎም ሌሎች የጸጥታ ተቋማትን የመገንባት ሂደት ኢትዮጵያን በአፍሪካ ደረጃ ተደማጭነት ያላት እና የሰላም ተምሳሌት የሚያደርጋት ነው።
የመከላከያ ኃይል ጥንካሬ የሚለካው በታጠቀው መሣሪያ ጥራት ብቻ ሳይሆን፣ ያንን መሣሪያ በራሱ አቅም የማምረት እና የመጠገን አቅሙ ላይ ነው። የኢትዮጵያ መከላከያ ኢንጂነሪንግ በዚህ ረገድ ትልቅ ለውጥ እያሳየ ይገኛል።
ቀደም ሲል ለብዙ ዐሥርተ ዓመታት የቆዩ፣ የተበላሹ እና የወደቁ ታንኮች፣ ተሽከርካሪዎች፣ መድፎች እና ሮኬቶች አሁን በአዲስ መልክ እየታደሱ ነው።
ይህ ሂደት "ሪቨርስ ኢንጂነሪንግን (Reverse Engineering) በመጠቀም የተከናወነ ሲሆን፣ አሮጌ መሣሪያዎችን ወደ ዘመናዊነት ከመቀየር ባለፈ፣ የተኩስ አቅማቸውን እና ፍጥነታቸውን በከፍተኛ ደረጃ እንዲጨምር አድርጎታል። ይህም ኢትዮጵያ መሣሪያዎችን ከመግዛት ወጥታ ወደ ማሻሻል እና ወደ ማምረት መሸጋገሯን ያሳያል።
በተለይም በሰማይ ላይ ያለውን የበላይነት ለማረጋገጥ "ስካይዊን ኤሮኖቲክስ ኢንዱስትሪ" መመሥረቱ ትልቅ ምዕራፍ ነው። ይህ ተቋም የሰው አልባ አውሮፕላኖችን ወይም ድሮኖችን በሀገር ውስጥ የማምረት አቅም ፈጥሯል። እነዚህ ድሮኖች ለስለላ፣ ለጥቃት እና ለደኅንነት ሥራዎች የሚውሉ ሲሆን፣ በከፍተኛ ከፍታ ላይ የመብረር ብቃት አላቸው።
እነዚህ ድሮኖች በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የታገዙ እና በሳተላይት ኮሙዩኒኬሽን የሚመሩ በመሆናቸው፣ ጠላት ሊያደርስ የሚችለውን የኤሌክትሮኒክስ መስተጓጎል (Jamming) የመቋቋም አቅም አላቸው።
ኢትዮጵያ ይህንን የቴክኖሎጂ አቅም መገንባቷ፣ በዘመናዊ ውጊያ ውስጥ ያላትን የበላይነት የሚያረጋግጥ ነው።
ዘመናዊ መሣሪያ ብቻውን ሀገርን አይከላከልም፤ ያንን መሣሪያ በአግባቡ የሚጠቀም እና በዲሲፕሊን የታነፀ የሰው ኃይል የግድ ይላል። የመከላከያ ኃይሉ የግንባታ ስትራቴጂ ዋናው አካል ፕሮፌሽናል ሠራዊት መገንባት ነው።
ፕሮፌሽናል ሠራዊት ማለት ከብሔር፣ ከፖለቲካ እና ከሃይማኖት ወገንተኝነት የጸዳ፣ አጀንዳው ኢትዮጵያን መጠበቅ ብቻ የሆነ ኃይል ነው። ይህ ኃይል በከፍተኛ ወታደራዊ ሳይንስ እና ጥበብ የሠለጠነ፣ የቴክኖሎጂ እውቀት ያለውና በአካል ብቃት የበለፀገ ነው።
በተለይ የ"ኤሊት ፎርስ" (Elite Force) ወይም የኮማንዶና አየር ወለድ ሠራዊት ግንባታ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል። እነዚህ ሠራዊቶች በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት በሰለጠኑ አሰልጣኞች አማካኝነት ጥብቅ ስልጠና ይወስዳሉ። የቀይ ቦኔት ባለቤት መሆን ከፍተኛ ክብርና ኃላፊነት ነው።
የኮማንዶ ሠራዊቱ በአየር፣ በባህርና በምድር በማንኛውም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ተሰማርቶ ተልዕኮ የመፈጸም ብቃት አለው። ታድያ በልምምድ ወቅት የሚያሳዩት ብቃት የአካል ብሎም የአዕምሮ ጥንካሬያቸውን እና ብስለታቸውን የሚመሰክር ነው።
እነዚህ ወታደሮች የቴክኖሎጂ ውጤት የሆኑትን ድሮኖች እና ዘመናዊ መሣሪያዎች ተጠቅመው ውጊያን የሚያስቀሩ፣ ውጊያ ቢመጣ ደግሞ በአጭር ጊዜ ውስጥ ድልን የሚያበስሩ ናቸው።
የመከላከያ ኃይሉ ጥንካሬ ዓላማው ውጊያ ሳይሆን ሰላም ነው። ጠንካራ መከላከያ መኖሩ ጠላት እንዳይደፍር ያደርጋል። ሠራዊቱ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ከማስከበር ባለፈ፣ ለቀጣናዊ ሰላም ትልቅ ሚና ይጫወታል።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ የሰላም ምንጭ እንጂ የጦርነት ምንጭ ሆና አታውቅም በአንጻሩ ከጁባ እስከ ባይደዋ ለጎረቤት ሀገራት ሰላም ዋጋ ከፍላለች። የሠራዊቱ መጠናከር ለጎረቤት ሀገራትም ጭምር ዋስትና ነው።
ሴት አየር ወለዶች፣ ኮማንዶዎች፣ የአየር ኃይል አብራሪዎች በብዛት መገኘታቸው ደግሞ የሠራዊቱን አካታችነትና ዘመናዊነት ያሳያል።
ሠራዊቱ ከቴክኖሎጂ ጋር ተስማምቶ፣ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና በዘመናዊ ዶክትሪን ተመርቶ የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማረጋገጥ የጀርባ አጥንት ሆኖ ያገለግላል።
ኢትዮጵያ ትፈርሳለች ለሚሉት እንኳን ልትፈርስ ከፍ ትላለች የተባለውም በምክንያት ነው፤ ምክንያቶቹ ደግሞ እንደነዚህ ያሉ የሀገር ፍቅር በልባቸው የሚነድ እና የጀግኖች አርበኞች ልጆች በቴክኖሎጂ ተክነው በአቅም ላይ ብቃት ደርበው ድንበር እንዳይደፈር ጥቅም እንዳይነካ ሰንደቋን ይዘው ስለተሰለፉ ነው።
የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል ግንባታ በስኬት እየተከናወነ ቀጥሏል፣ ፈተና አልበገረውም እንቅፋት አልስቆመውም። ሎጅስቲክስን እና ትጥቅን በሀገር ውስጥ የማምረት እና የማሻሻል አቅም ተገንብቷል። እየተገነባም ይቀጥላል።
ለዚህ ደግሞ ምስክሮቹ ሆሚቾ ተተኳሽ ማምረቻ "ስካይዊን ኤሮኖቲክስ ኢንዱስትሪ" ናቸው። ይህንን ቴክኖሎጂ በአግባቡ የሚጠቀም፣ በዲሲፕሊን የታነፀና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ያስቀደመ ብቁ የሰው ኃይልም እየተገነባ ነው።
ዛሬ የምናየው መከላከያ የትላንቱን አሮጌ መሣሪያ አድሶ ለዛሬው ጦርነት ዝግጁ ያደረገ፣ የነገውን ቴክኖሎጂ ደግሞ ዛሬውኑ እያመረተ ያለ ተቋም ነው። ይህ ተቋም ኢትዮጵያን ወደተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር የሚደረገውን ጉዞ በፅናት ይጠብቃል።
ኢትዮጵያ በልጆቿ ላብ እና ጥረት ብሎም በቴክኖሎጂ እና በእውቀት አስከብራ ታፍራ እና ተከብራ በነጻነት ታሪኳ አብባ ዛሬም ወደፊት እየገሰገሰች ትገኛለች።
በሰለሞን ከበደ
#ethiopia #ebc #nationalinterest #militarypower

22 days ago
ደቡብ ሱዳን በናይል ወንዝ ላይ የፉላ ግድብን ለመገንባት በዝግጅት ላይ መሆኗን ገለጸች
ደቡብ ሱዳን በናይል ወንዝ ላይ የሚገነባውን የፉላ የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድብ ፕሮጀክት ለማስጀመር ዝግጅት እያደረገች መሆኗን የሀገሪቱ የኃይል እና ግድቦች ሚኒስቴር አስታወቀ።
በጁባ በተካሄደው 7ኛው ዓለም አቀፍ የሎጂስቲክስ ኮንቬንሽን (GLC 2026) ይፋዊ የሚዲያ ማስጀመርያ ስነ-ስርዓት ላይ የተናገሩት የኃይል እና ግድቦች ሚኒስትር አጎክ ማኩር፣ ሀገራቸው የግድቡን ግንባታ ለማካሄድ ከግብፅ በኩል የሚመጣ ምንም ዓይነት ፍራቻ እንደሌላት ገልጸዋል።
ሚኒስትሩ አክለውም ደቡብ ሱዳን በአሁኑ ወቅት እየተጠቀመች ያለችው ከአጠቃላይ የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅሟ አንድ በመቶ ያህሉን ብቻ መሆኑን ጠቁመው፣ ይህም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን ያለ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት ማቆየቱን አስረድተዋል።
በዕቅድ ላይ ያለውና በኒሙሌ አካባቢ የሚገነባው የፉላ ግድብ 1,800 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ የደቡብ ሱዳንን የሀገር ውስጥ ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ማሟላት ከማስቻሉም በላይ ለጎረቤት ሀገራት የሚተርፍ ትርፍ ኃይል እንደሚያመነጭ ተገልጻል።
አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ለኢንዱስትሪ፣ ለኢንቨስትመንት፣ ለሎጂስቲክስ እና ለጠቅላላ የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ወሳኝ መሆኑን ያመለከቱት ሚኒስትሩ፣ ሀገሪቱ በነሐሴ ወር 2018 ዓ.ም (August 2026) በጁባ በሚገኘው ፒራሚድ ኮንቲኔንታል ሆቴል የምታስተናግደው የሎጂስቲክስ ኮንቬንሽን የዘርፉን ባለሙያዎች፣ ኢንቨስተሮችን እና ፖሊሲ አውጪዎችን እንደሚያገናኝ ተናግረዋል።
@TikvahethMagazine

1 month ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኢትዮጵያ ጸጥታ ኃይሎች በማዕከላዊ ሶማሊያ በሚገኘው የሀናንቡሬ ካምፕ ከአንድ ዓመት በላይ የፈጀ ወታደራዊ ስልጠናቸውን አጠናቀው ወደ ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የገቡ በመቶዎች የሚቆጠሩ የሶማሊያ ፌደራል መንግስት ወታደሮችን በቁጥጥር ስር አውለዋል። ይህ ክስተት ስለ ወታደሮቹ ምልመላ፣ የውጭ የገንዘብ ድጋፍ እና የወደፊት ስምሪት ዙሪያ አሳሳቢ ጥያቄዎችን አስነስቷል።
ሱናታይምስ ያነጋገራቸው የሶማሊያ የስለላ ምንጮች የታሰሩት ወታደሮች ቁጥር 316 መሆኑን ቢገልጹም፣ ሌሎች ሪፖርቶች ግን ቁጥሩ ከ180 እስከ 300 እና ከዚያም በላይ ሊደርስ እንደሚችል ያመላክታሉ። የሶማሊያ ብሔራዊ የጸጥታ አማካሪ አዌይስ ሀጂ ዩሱፍ ወታደሮቹ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መኖራቸውን አምነው፣ ስልጠናቸውን ሲያጠናቅቁ ቤተሰቦቻቸውን እንዲጠይቁ ፈቃድ እንደተሰጣቸውና የፌደራል መንግስቱም ስለ እንቅስቃሴያቸው ያውቅ እንደነበር ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ወታደሮቹ በኢትዮጵያ ጸጥታ ኃይሎች ተይዘው ለምርመራ ወደ ጅግጅጋ እና አካባቢዋ መወሰዳቸው ተዘግቧል።
የጉዳዩ አንዱ አሳሳቢ ገጽታ የጦር ኃይሉ ስብጥር ነው። በርካታዎቹ ወታደሮች በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ከሚገኙ የኦጋዴን ማህበረሰቦች የተመለመሉ ሲሆኑ፣ በኢትዮጵያ የሚኖሩ ግለሰቦች እንዴት የሶማሊያ ፌደራል ጦር አካል ሊሆኑ ቻሉ የሚለው ጥያቄ በሁለቱም መንግስታት በኩል እስካሁን ግልጽ ምላሽ አልተሰጠበትም። የሀናንቡሬው የጦር ስልጠና በሳዑዲ አረቢያ የገንዘብ ድጋፍ የተካሄደ ሲሆን፣ በነሐሴ ወር 3,000 የሚደርሱ ወታደሮች ስልጠናቸውን አጠናቀዋል። ግብጽ ከዚህ ጦር ጋር የተያያዘ የደህንነት እና የስለላ ፍላጎት እንዳላት ቢነገርም፣ የስልጠናው ዋና ፋይናንሰር መሆኗን የሚያሳይ መረጃ ግን አልተገኘም።
የሶማሊያ የስለላ ምንጮች እንደሚሉት፣ ከሰልጣኞቹ መካከል የተወሰኑት የፌደራል መንግስቱ ግጭት ውስጥ በሚገኝባት ጁባላንድ ሊሰማሩ ታቅዶ ነበር። በተጨማሪም የተወሰኑት ወታደሮች ወደፊት በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ለሚደረጉ ኦፕሬሽኖች ሊውሉ እንደሚችሉ ውይይት ተደርጎ ነበር የሚል ውንጀላ ቢኖርም፣ ይህንን የሚያረጋግጥ ነጻ ማስረጃ አልተገኘም። የሶማሊያ ብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት ኤጀንሲ ዳይሬክተር ማሀድ መሀመድ ሰላድ ከግብጽ የስለላ ባለስልጣናት ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳላቸው እና በአሁኑ ወቅትም በካይሮ እንደሚገኙ ምንጮች ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ ከግብጽ ጋር ያላት ስትራቴጂካዊ ውጥረት፣ እንዲሁም ሶማሊያ ከቀጠናው ሀገራት ጋር እያደረገችው ያለው የጸጥታ ግንኙነት ማስፋፋት የአዲስ አበባን ስጋት ጨምሮታል። ወታደሮቹ በዶሎ እና ቆራሄይ አካባቢዎች በኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች የተያዙ ቢሆንም፣ ኢትዮጵያ እስካሁን ግለሰቦቹ በምን ዓይነት የጸጥታ ጥሰት እንደተጠረጠሩ በይፋ የገለጸችው ነገር የለም። በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች ድንበር ሲሻገሩ መሳሪያ ታጥቀው ነበር ወይ፣ እንዲሁም ኢትዮጵያ አስቀድማ ታውቅ ነበር ወይ የሚሉት ጥያቄዎች እስካሁን ምላሽ ባለማግኘታቸው፣ ይህ ክስተት በሁለቱ ጎረቤት ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት በእጅጉ የሚፈትን ሆኖ ቀጥሏል።

ብሔራዊ ባንክ ሕገወጥ ያላቸውን 17 ድርጅቶች ይፋ አደረገ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ኅብረተሰቡ፣ የዳያስፖራ አባላትና ደንበኞች ፈቃድ የሌላቸውን የገንዘብ አስተላላፊ ወኪሎችና ሕገወጥ የሐዋላ መረቦችን ከመጠቀም እንዲቆጠቡ ጥብቅ ማሰሰቢያና ማስጠንቀቂያ አስተላለፈ።
ባንኩ ባወጣው መግለጫ እነዚህ ሕገወጥ ተግባራት በኢትዮጵያ ሕግ በጥብቅ የተከለከሉ መሆናቸውን ጠቁሞ በእነዚህ መንገዶች ገንዘብ መላክም ሆነ መቀበል ደንበኞችን ለከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ፣ ለክፍያ መዘግየት፣ ለባንክ ሒሳብ ዕገዳና ለሕግ ተጠያቂነት እንደሚያጋልጥ አስገንዝቧል።
ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባው የገንዘብ ዝውውር እያደገ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ ሕገወጥ መንገዶችን መጠቀም ላኪዎችንም ሆነ ተቀባይ ቤተሰቦችን ለአስተዳደራዊና ሕጋዊ እርምጃዎች ሊዳርግ ስለሚችል ዜጎች ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውን አማራጮች ብቻ እንዲጠቀሙ መክሯል።
በተጨማሪም ብሔራዊ ባንኩ ወደ ኢትዮጵያ የገንዘብ ማስተላለፍ አገልግሎት እንዲሰጡ ፈቃድ ያልተሰጣቸውንና ሕገወጥ ያላቸውን 17 ድርጅቶች ስም ይፋ አድርጓል።
በዚህም መሠረት አዱሊስ መኒ ትራንስፈር (Adulis Money Transfer)፣ አማል ኤክስፕረስ (Amal Express)፣ አማል ዩኤስኤ (Amal USA)፣ አማና ኤክስፕረስ (Amana Express)፣ አቫንቲ (Avanti)፣ አዋሽ ዳይሬክት (Awash Direct)፣ ባካል መኒ ትራንስፈር (Bakaal Money Transfer)፣ ጁባ ኤክስፕረስ (Jubba Express)፣ ራስሚ ፔይ (Rasmy Pay)፣ ረማድ ፔይ ወይም ረማዳ ፔይ ካህ (Ramad Pay / Ramada Pay (Kaah))፣ ሽጌይ መኒ ትራንስፈር (Shgey Money Transfer)፣ ታጅ ፋይናንሻል ሰርቪስ (Taaj Financial Service)፣ ታሳ ፔይ (Tasa Pay)፣ ተወከል መኒ ሰርቪሰስ (Tawakal Money Services)፣ ዩኤስዋየር (USwyre)፣ ወርልድ ዳይሬክት ሊንክ (World Direct Link) እና ዞላ (Zola) የተባሉት ድርጅቶች ሕጋዊ ፈቃድ የሌላቸው መሆኑ ተገልጿል።
ደንበኞች የገንዘባቸውን ደኅንነት ለመጠበቅና በአስተማማኝ ሁኔታ መድረሱን ለማረጋገጥ ሕጋዊ ፈቃድ የተሰጣቸውን ወኪሎች ብቻ እንዲጠቀሙ ያበረታታው ባንኩ፣ ማናቸውንም ዝውውር ከመፈጸማቸው በፊት የተመረጠው ድርጅት ሕጋዊነት በባንኩ ይፋዊ ድረ-ገጽ (https://nbe.gov.et/mta/) ገብተው ማረጋገጥ እንደሚችሉ አሳውቋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

(ዘ-ሐበሻ አጭር መረጃ) የተባበሩት መንግሥታት የደቡብ ሱዳን ልዑክ (UNMISS) በክብር ለተሰውት የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ጀግኖች የሐዘንና የክብር ስንብት ማድረጉን ባሰራጨው ፎቶ ላይ መግለጹን ዘ-ሐበሻ አይቷል። እንዲህ ይላል፦
"ግጭትና ሁከት በማይጠፋበት የደቡብ ሱዳኗ ጆንግሌይ ግዛት የተመደቡበትን ግዳጅ በመወጣት ላይ እያሉ፣ በተፈጸመባቸው ድንገተኛ ጥቃት ውድ ህይወታቸውን ላጡት ሁለት ኢትዮጵያውያን የሰላም አስከባሪዎች፣ የልዑኩ ባልደረቦች ዛሬ በጁባ ከተማ ተሰባስበው ጥልቅ ሀዘን በተሞላበት ስሜት የክብር ስንብት አድርገውላቸዋል።
"ወታደራዊ፣ የሲቪል እና የፖሊስ አባላትም እነዚህ ጀግኖች ለሰላም ሲሉ ላሳዩት ወደር የለሽ ጀግንነት፣ ጽኑ ቁርጠኝነት እና ለከፈሉት ታላቅ የህይወት መስዋዕትነት አክብሮታቸውን ገልጸዋል። ጀግኖቹ የመጨረሻውን የክብር ጉዟቸውን ወደ እናት ሀገራቸው ሲያደርጉ፣ ተቋሙ ከደቡብ ሱዳን ህዝብ ጋር በመሆን እነሱ ውድ ህይወታቸውን የገበሩለትን የሰላም ማስፈን ዓላማ ከዳር ለማድረስ የገባውን ቃል ኪዳን አድሷል።"
ፎቶ፦ ኔክታሪዮስ ማርኮጊያኒስ / ዩንሚስ

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በደቡብ ሱዳን የተገደሉት 2 የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች የሽኝትና የሀዘን መግለጫ ስነስርአት ተከናወነ፡፡ በዛሬው እለት በደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ የሀዘን መግለጫ ስነስርአትና የአስከሬን ሽኝት ፕሮግራም መከናወኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዘግቧል፡፡ እንደዘገባው ይህ ፕሮግራም የተካሄደው ከቀናት በፊት በጆንግሌይ ግዛት በተከፈተ ተኩስ ህይወታቸው ላለፈው የኢትዮጵያ ወታደሮች ነው፡፡ እነዚህ ወታደሮች የተመድ የደቡብ ሱዳን ተልእኮ አባላት መሆናቸውን ጠቅሶ በልኡኩ ተሸከርካሪ ላይ በተፈፀመ ጥቃት ህይወታቸው ማለፉን ‹‹ለሰላም የተከፈለ መስዋእትነት ነው›› ብሎታል፡፡
የልኡኩ ሀላፊና የተመድ ዋና ፀሀፊ ተወካይ አኒታ ኪኪ አጎቦ በስፍራው ተገኝተው ባሰሙት ንግግር የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሀይሎች ለደቡብ ሱዳን ህዝብ ላሳዩት ቁርጠኝነት ምስጋናቸውን አቅርበው እ.ኤ.አ ከ2014 አንስቶ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ በማያወላውል ሙያዊ ብቃትና ጀግንነት ሲሰሩ መቆየታቸውን ገልፀዋል፡፡ ጨምረውም ‹‹እነዚህ ህይወታቸው ያለፈ ሰላም አስከባሪዎች ወደዘላለም ቤታቸው የሄዱ ቢሆንም ውርሳቸውና ተፅእኗቸው ጥሩ መታሰቢያ ይሆናል፡፡ ሰላም ማስከበር ሙያ ብቻ ሳይሆን እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ማገዝም ጭምር ነው፡፡ ህይወታቸውን የከፈሉበትን አላማ እናከብራለን›› ብለዋል፡፡ በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ጉዳይ አስፈፃሚው አክሊሉ ታደሰ በበኩላቸው ‹‹እነዚህ በድፍረትና በቁርጠኝነት ሲቪሎችን ለመጠበቅ ተሰልፈው ለሌሎች ሲሉ ህይወታቸውን ያጡ ጀግኖች ናቸው፡፡ ዛሬ በአስከሬናቸው አበባ ስናስቀምጥ አገልግሎታቸውንና የተሰለፉለትን አላማ እያከበርን ነው፡፡ መስዋእትነታቸው ፈፅሞ አይረሳም›› ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሕገ ወጥ የሐዋላ እና ፈቃድ የሌላቸውን የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች ይፋ አደረገ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መግለጫ ህብረተሰቡ፣ የዳያስፖራ አባላት እና ደንበኞች ፈቃድ የሌላቸውን የገንዘብ አስተላላፊ ወኪሎች እና ሕገ ወጥ የሐዋላ መረቦችን ከመጠቀም እንዲቆጠቡ አሳስቧል።
እነዚህ ሕገ ወጥ ተግባራት በኢትዮጵያ ሕግ በጥብቅ የተከለከሉ መሆናቸውን በመግለጽ፣ በእነዚህ መንገዶች ገንዘብ መላክም ሆነ መቀበል ደንበኞችን ለከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ፣ ለክፍያ መዘግየት፣ ለባንክ ሒሳብ ዕገዳ፣ እንዲሁም ለሕግ ተጠያቂነት እንደሚያጋልጥ አስጠንቅቋል።
ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባው የገንዘብ ዝውውር እያደገ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ፣ ዜጎች ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውን የገንዘብ ማስተላለፊያ መንገዶችን ብቻ መጠቀም እንዳለባቸው አመልክቷል፡፡
ሕገ ወጥ መንገዶችን መጠቀም ላኪዎችንም ሆነ ተቀባይ ቤተሰቦችን አግባብነት ባላቸው ሕጎች መሠረት ለአስተዳደራዊ እና ሕጋዊ እርምጃዎች ሊያጋልጥ እንደሚችል ነው የገለጸው፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ወደ ኢትዮጵያ የገንዘብ ማስተላለፍ አገልግሎት እንዲሰጡ ፈቃድ ያልተሰጣቸውን 17 ሕገ ወጥ አስተላላፊ ድርጅቶችን ይፋ አድርጓል።
በዚህም አዱሊስ መኒ ትራንስፈር፣ አማል ኤክስፕረስ፣ አማል ዩኤስኤ፣ አማና ኤክስፕረስ፣ አቫንቲ፣ አዋሽ ዳይሬክት፣ ባካል መኒ ትራንስፈር፣ ጁባ ኤክስፕረስ፣ ራስሚ ፔይ፣ ረማድ ፔይ (ወይም ረማዳ ፔይ ካህ)፣ ሽጌይ መኒ ትራንስፈር፣ ታጅ ፋይናንሻል ሰርቪስ፣ ታሳ ፔይ፣ ተወከል መኒ ሰርቪሰስ፣ ዩኤስዋየር፣ ወርልድ ዳይሬክት ሊንክ እና ዞላ የተሰኙ ድርጅቶች ሕጋዊ ፈቃድ የሌላቸው መሆናቸው ገልጿል።
Seledadotio

2 months ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በደቡብ ሱዳን መዲና ጁባ በሚገኝ አንድ ጠባብ የወርቅ ገበያ ውስጥ፣ በኮንትሮባንድ ከሱዳን የሚገባው ወርቅ ህጋዊ ሽፋን ተሰጥቶት ወደ ዱባይ እንዴት እንደሚላክ ለግል ደህንነታቸው ሲሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ (F.A. በሚል ምህጻረ ቃል የተገለጹ) አንድ ነጋዴ አጋልጠዋል።
ነጋዴው ለሱዳን ትሪቢዩን እንደገለጹት፣ በየብስ ድንበር በኩል የሚደረገው የሱዳን ወርቅ ዝውውር አሁንም አልቆመም። ከዳርፉር እና ከደቡብ ኮርዶፋን ማዕድን ማውጫዎች የሚነሱ የጭነት መኪናዎች እና ሞተር ብስክሌቶች ቁጥጥር በማይደረግባቸው የድንበር መስመሮች በኩል ወርቁን ያለማቋረጥ ያጓጉዛሉ።
ወርቁ ወደ ጁባ የሚገባው ባልተጣራ እና ጥሬ በሆነ መልኩ መሆኑን ያስረዱት ነጋዴው፤ ደላሎች እና የሀገር ውስጥ ነጋዴዎች ማዕድኑን በሱዳን ማዕከላዊ ባንክ ከሚሰጠው መደበኛ የምንዛሬ ተመን እጅግ በተሻለ ዋጋ በአሜሪካ ዶላር በጥሬ ገንዘብ እንደሚገዙት አብራርተዋል።
ይህንን ወርቅ ህጋዊ ለማድረግ፣ ነጋዴዎቹ ማዕድኑን ዳግም በማቅለጥ እና በመቀላቀል አዲስ ቅርጽ ይሰጡታል። በመቀጠልም ወርቁ በደቡብ ሱዳን ኢኳቶሪያ ወይም ምዕራብ ባህር ኤል ጋዛል ግዛቶች እንደተመረተ የሚያስመስል የሀሰት ሰነድ ይዘጋጅለታል። ይህ የሀሰት ሰነድ ወርቁ ያለምንም ህጋዊ እንቅፋት በጁባ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል በአየር ጭነት ወደ አረብ ኤምሬትስ (ዱባይ) እና ዓለም አቀፍ ማጣሪያዎች እንዲላክ ያስችለዋል።
ይህ የምስክርነት ቃል በሱዳን የወርቅ አቅርቦት ሰንሰለት ላይ የታየውን መዋቅራዊ ለውጥ ፍንትው አድርጎ ያሳያል። የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ይህንን የተወሳሰበ ሂደት "የእሴት ሰንሰለት ዳግም ምህንድስና እና የመነሻ ሀገር ማጭበርበር" ሲሉ ይጠሩታል። በዚህም ህገ-ወጥ አውታረ መረቦች ጎረቤት ሀገራትን (በተለይም ደቡብ ሱዳንን) እንደ መሸጋገሪያ በመጠቀም ዓለም አቀፍ ማዕቀቦችን በማለፍ የማዕድኑን ህጋዊ ማንነት ይቀይራሉ።
በ2017 የጀበል አሜር የወርቅ ማዕድን ማውጫን በኃይል የተቆጣጠሩት የፈጣን ድጋፍ ሰጪ ኃይል (RSF) አዛዥ ሞሃመድ ሀምዳን ዳጋሎ (ሄሜቲ)፣ ከማዕድኑ የሚገኘውን ትርፍ ከRSF ጋር ግንኙነት ላላቸው 50 ገደማ ኩባንያዎች እንዲገባ ማድረጋቸው ይታወሳል። በ2019 ሄሜቲ የሱዳንን ኢኮኖሚ ለማረጋጋት በሚል ወደ 1 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ድጋፍ አቅርበው ነበር።
መረጃውን ያጋለጡት ነጋዴ አክለውም፣ ባለፈው መጋቢት ወር ብቻ ከጁባ ወደ አረብ ኤምሬትስ በተደረጉ ሁለት በረራዎች 115 ኪሎ ግራም የሚመዝን የሱዳን የኮንትሮባንድ ወርቅ መጓጓዙን ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ሱዳን ትሪቢዩን ይህንን የተወሰነ መረጃ በገለልተኛ ወገን ማረጋገጥ እንዳልቻለ በዘገባው አስፍሯል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኦገስት 1 ቀን 2026 ጀምሮ ከሰሃራ በታች ባሉ 25 የአፍሪካ ሀገራት በሚገኙ ዲፕሎማሲያዊ ሚሲዮኖች የሚሰጠውን መደበኛ የቪዛ ማስተናገጃ አገልግሎት ማቋረጡን አስታውቋል። የትራምፕ አስተዳደር ይህንን ውሳኔ በቅርብ ታሪክ ውስጥ ከተደረጉት የአሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ የቪዛ አገልግሎቶች ትልቁ የማሻሻያ መርሃ ግብር ሲል ገልጾታል።
በአዲሱ አሰራር መሰረት የቪዛ አመልካቾች ከዚህ በኋላ በአቅራቢያቸው በሚገኝ የአሜሪካ ኤምባሲ ወይም ቆንስላ ጽህፈት ቤት ቀጠሮ መያዝም ሆነ የቪዛ ሂደታቸውን ማጠናቀቅ አይችሉም። ከዚህ ይልቅ በአህጉሪቱ ወደተመደቡ 20 ቀጠናዊ ማስተናገጃ ማዕከላት እንዲያቀኑ ይደረጋል።
የቪዛ አገልግሎታቸው የተቋረጠባቸው 25ቱ ሚሲዮኖች አቡጃ (ናይጄሪያ)፣ አንታናናሪቮ (ማዳጋስካር)፣ አስመራ (ኤርትራ)፣ ባማኮ (ማሊ)፣ ባንጁል (ጋምቢያ)፣ ብራዛቪል (የኮንጎ ሪፐብሊክ)፣ ቡጁምቡራ (ብሩንዲ)፣ ኮናክሪ (ጊኒ)፣ ኮቶኑ (ቤኒን)፣ ደርባን (ደቡብ አፍሪካ)፣ ፍሪታውን (ሴራሊዮን)፣ ጋቦሮኔ (ቦትስዋና)፣ ሃራሬ (ዚምባብዌ)፣ ጁባ (ደቡብ ሱዳን)፣ ሊብረቪል (ጋቦን)፣ ሊሎንግዌ (ማላዊ)፣ ሉሳካ (ዛምቢያ)፣ ማፑቶ (ሞዛምቢክ)፣ ማሴሩ (ሌሴቶ)፣ ምባባኔ (ኤስዋቲኒ)፣ ንጃሜና (ቻድ)፣ ኒያሜይ (ኒጀር)፣ ኑዋክሾት (ሞሪታኒያ)፣ ዋጋዱጉ (ቡርኪና ፋሶ) እና ዊንድሆክ (ናሚቢያ) ናቸው። በደቡብ አፍሪካ ደርባን የሚገኘው የቪዛ ማዕከል ቢዘጋም፣ በኬፕታውን የሚሰጠው ተመሳሳይ አገልግሎት ግን ሳይቋረጥ እንደሚቀጥል ተገልጿል።
20ዎቹ አዳዲስ ቀጠናዊ ማስተናገጃ ማዕከላት በአቢጃን፣ አክራ፣ አዲስ አበባ፣ ኬፕታውን (ደቡብ አፍሪካ)፣ ዳካር፣ ዳሬሰላም፣ ጅቡቲ፣ ጆሃንስበርግ፣ ካምፓላ፣ ኪጋሊ፣ ኪንሻሳ፣ ሌጎስ፣ ሎሜ፣ ሉዋንዳ፣ ማላቦ፣ ሞንሮቪያ፣ ናይሮቢ፣ ፖርት ሉዊስ፣ ፕራያ እና ያውንዴ የሚገኙ ይሆናሉ። እያንዳንዱ ማዕከል በርካታ ጎረቤት ሀገራትን የሚያስተናግድ ሲሆን፣ ለምሳሌ ከማሊ የሚመጡ አመልካቾች በዳካር (ሴኔጋል)፣ እንዲሁም ከቤኒን እና ኒጀር የሚመጡት ደግሞ በሎሜ (ቶጎ) የቪዛ ሂደታቸውን እንዲያከናውኑ ይመራሉ።
ሚኒስቴሩ ውሳኔውን የትራምፕ አስተዳደር ብሔራዊ ደህንነትን ለማጠናከር፣ የማጣራት ሂደቶችን ወጥ ለማድረግ፣ የመንግስት ወጪን ለመቀነስ እና የአሰራር ቅልጥፍናን ለማሻሻል ከሚያደርገው ጥረት አንዱ አካል መሆኑን አብራርቷል። ተመሳሳይ የውህደት ስራዎች በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት እና በአውሮፓ ክፍሎች ቀደም ሲል መከናወናቸውን የገለጸው ሚኒስቴሩ፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ብሔራዊ ደህንነትን በማጠናከር እና የመንግስትን ብክነት በመቀነስ አሜሪካን እና አሜሪካውያንን እያስቀደሙ ነው ብሏል።
ይህ ማሻሻያ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት የቪዛ ማመልከቻዎችን የሚያስተናግዱ የአሜሪካ ሚሲዮኖችን ቁጥር ከ50 ገደማ ወደ 20 ዝቅ ያደርገዋል። ይህ በአመልካቾች ላይ ጉልህ የሆነ ተግባራዊ ተጽእኖ የሚያሳድር ሲሆን፣ የአገር ውስጥ የቪዛ አገልግሎት በተቋረጠባቸው ሀገራት የሚገኙ ዜጎች በአካል ለሚደረግ ቃለ ምልልስ እና የጣት አሻራ (ባዮሜትሪክ) ምዝገባ አለም አቀፍ ድንበሮችን አቋርጠው ለመጓዝ ስለሚገደዱ ለተጨማሪ የትራንስፖርት እና የማረፊያ ወጪዎች ይዳረጋሉ።

3 months ago
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ተቋማዊ ሪፎርም ተጠናክሮ ቀጥሏል
#ethiopia | የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ሁለንተናዊ ሀገራዊ ለውጡን መነሻ በማድረግ ለበርካታ ዓመታት ሲተገብረው የቆየውን ተቋማዊ ሪፎርም በተጠናከረ ሁኔታ እንደሚቀጥል አስታውቋል። በ2019 በጀት ዓመትም ሪፎርሙን የበለጠ ለማጠናከር የሚያስችሉ ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።
ኮርፖሬሽኑ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይትን በቢሾፍቱ ከተማ ለሁለት ቀናት ያካሄደ ሲሆን፣ በበጀት ዓመቱ የታቀዱ ሥራዎችን 97 በመቶ ማሳካቱ ተገልጿል። በገቢ ዕድገት፣ በቤት ልማት፣ በአፈጻጸም አቅም እና በቤት አስተዳደር የተመዘገቡ ውጤቶችም የተቋሙን የለውጥ ጉዞ እንዳጠናከሩ ተጠቁሟል።
በተጨማሪም የሕዝብና የመንግሥት ጥቅምን ለማስጠበቅ በተደረጉ የፍርድ ቤት ክርክሮች በርካታ ይዞታዎችን ማስመለስ መቻሉ ተገልጿል።
በውጭ ገበያ መስፋፋትን በተመለከተም፣ በደቡብ ሱዳን ጁባ ከተማ የቤት ልማት ፕሮጀክት ለማከናወን ከደቡብ ሱዳን ኢኳቶሪያል ስቴት ጋር የተደረሰውን ስምምነት ወደ ተግባር ለማስገባት ሥራዎች በመካሄድ ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።
በፕሮጀክቶች ዘርፍ የፒያሳ እና የጎልድ ሳይት ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ወደ አገልግሎት መግባታቸው የተጠቀሰ ሲሆን፣ ዘመናዊ 3ዲ የግንባታ ቴክኖሎጂን ለማስፋፋት የመጀመሪያ የሙከራ ቤቶች ግንባታም በሂደት ላይ መሆኑ ተገልጿል።
በተጨማሪም የቤቶች ቆጠራና የመረጃ ማሰባሰብ ሥራ በመጠናቀቁ ዘመናዊ የቤት አስተዳደር ሥርዓት መጠናከሩን እና ከደንበኞች ጋር በትብብር የተገነቡ የንግድ ቤቶች ወደ ኪራይ አገልግሎት በመግባታቸው ከፍተኛ ገቢ ማስገኘት መጀመራቸው ተጠቁሟል።
ኮርፖሬሽኑ በ50ኛ ዓመት ኢዮቤልዩ በዓሉ ወቅት የተቋሙን የግማሽ ምዕተ ዓመት ታሪክና ስኬቶች የሚያሳዩ መርሃ ግብሮችን ለአራት ተከታታይ ቀናት በድምቀት ማካሄዱ ተገልጿል። ይህም የተቋሙን ገጽታ በአዎንታዊ መልኩ ለመቀየር አስተዋጽኦ እንዳደረገ ተጠቅሷል።
በ2019 በጀት ዓመት የሚተገበሩ ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች ዘመናዊና ፈጣን የግንባታ ቴክኖሎጂዎችን በስፋት ሥራ ላይ ማዋል፣ የቤት አቅርቦትን ለማሳደግ ሰፋፊ የቤት ልማት ፕሮግራሞችን መተግበር፣ የገቢ ምንጮችንና የፋይናንስ አማራጮችን ማስፋፋት እንዲሁም የሰው ኃይልና የአሠራር አቅምን ማጠናከር መሆናቸው ተገልጿል።
ኮርፖሬሽኑም እነዚህን ስትራቴጂያዊ አቅጣጫዎች በመተግበር ለሀገራዊ የቤት ልማት ዕቅድ ስኬት በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አስታውቋል።

(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) የዓለም ዋንጫው ግለት ጣሪያ ነክቷል! ረቡዕ ዕለት በአትላንታ ስታዲየም (ቢትዮጵያ አቆጣጠር ምሽት) በሚካሄደው የዓለም ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ታላቅ ፍጥጫ፣ የአምናዋ ሻምፒዮኗ አርጀንቲና ከእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ጋር ስትፋጠጥ ታዋቂውን ጥቁር ሰማያዊ የሜዳ ውጪ ማልያዋን አጥልቃ ወደ ሜዳ እንደምትገባ ታውቋል። በበኩሏ እንግሊዝ ሙሉ ነጭ የሆነውን የሜዳዋን ማልያ ለብሳ ለዚህ ትልቅ ጦርነት ትቀርባለች።
አርጀንቲና በዘንድሮው ውድድር ይህንን ማልያ የተጠቀመችው በምድብ ድልድሉ ጆርዳንን 3 ለ 1 ባሸነፈችበት ጨዋታ ላይ ብቻ ነው። ይሁን እንጂ... ይህ የማልያ ምርጫ ከፊፋ የደንብ አሰራር ባሻገር ትልቅ የስነ-ልቦና እና የ"እምነት" ሚስጥር እንዳለው በአርጀንቲና ሚዲያዎች በስፋት እየተነገረ ይገኛል። ምክንያቱም ይህ ጠቆር ያለ ሰማያዊ ማልያ፣ አርጀንቲናውያን በእንግሊዝ ላይ ታሪካዊ ድል ለተቀዳጁባቸው የ1986ቱ እና የ1998ቱ የዓለም ዋንጫዎች ትልቅ ትዝታ ያለው በመሆኑ ነው!
በተለይም በ1986ቱ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና በታሪካዊቷ "የአምላክ እጅ" ጎል እንግሊዝን 2 ለ 1 ሲያሸንፉ፣ እንዲሁም በ1998ቱ የፈረንሳይ ዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ (Last-16) ጨዋታ በፔናሊቲ መለያ ምት የሶስቱን አናብስት ስብስብ ሲያሸንፉ ያጠለቁት ይሄንኑ ማልያ ነበር።
በተቃራኒው ግን በ2002ቱ በጃፓን በተካሄደው የዓለም ዋንጫ የምድብ ጨዋታ እንግሊዝ ቀይ ማልያ ለብሳ፣ አርጀንቲና ደግሞ ባህላዊውን ባለ መስመር ማልያዋን ለብሳ በተገናኙበት ጨዋታ እንግሊዝ 1 ለ 0 ማሸነፏ የማይዘነጋ ነው።
የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) አሰራር እያንዳንዱ ቡድን የሜዳውን የመጀመሪያ ምርጫ ማልያ እንዲለብስ ቅድሚያ የሚሰጥ ቢሆንም፣ የማልያ ቀለም መመሳሰል ካጋጠመ ግን የለቀቀ እና የደመቀ ቀለም እንዲኖር እርምጃ ይወስዳል። ይህም በተለይ colour blindness ችግር ላለባቸው ደጋፊዎች ጨዋታውን በቀላሉ እንዲከታተሉ ታስቦ የሚደረግ ጥንቃቄ ነው።
ወደዚህ ግዙፍ የግማሽ ፍጻሜ ጦርነት ለመድረስ ሁለቱም ቡድኖች ፈታኝ መንገድ አልፈዋል። እንግሊዝ ባለፈው ቅዳሜ ኖርዌይን በጭማሪ ሰዓት 2 ለ 1 ስታሸንፍ፤ አርጀንቲና ደግሞ እሁድ ዕለት 10 ተጫዋቾች ብቻ ቀርተውባት ከነበረችው ስዊዘርላንድ ጋር ባደረገችው እጅግ አጓጊ ጨዋታ በጭማሪ ሰዓት 3 ለ 1 አሸንፋ ማለፏ ይታወቃል። አሁን የዓለም እግር ኳስ አፍቃሪዎች ዓይን በአትላንታው የረቡዕ ምሽት ፍልሚያ ላይ አርፏል!

4 months ago
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በጁባ ዘመናዊ የመኖሪያና የንግድ ቤቶች ግንባታ ለመጀመር የመጨረሻ ዝግጅቱን አጠናቀቀ
የኢትዮጵያ ፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ ዘመናዊ የመኖሪያ እና የንግድ ተቋማት ግንባታን ለመጀመር የሚያስችሉትን ሁሉንም አስፈላጊ ቅድመ-ዝግጅቶች ማጠናቀቁንና ወደ ተግባር ለመግባት መዘጋጀቱን አስታወቀ።
ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት ወደ ትግበራ ምዕራፍ የተሸጋገረው ባለፈዉ ቅዳሜ ዕለት በጁባ ከተማ በተፈረመው የመጨረሻ የኦፕሬሽን ውል መሠረት ሲሆን፣ ስምምነቱ ቀደም ሲል በሁለቱ ወገኖች መካከል በአዲስ አበባ ተፈርሞ የነበረውን የመግባቢያ ሰነድ በቀጥታ ወደ ሥራ የሚያስገባ ነው።
ስምምነቱን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ረሻድ ከማል እና የደቡብ ሱዳን የመካከለኛው ኢኳቶሪያ ግዛት ገዥ ኢማኑኤል አዲል በጋራ ፈርመውታል። በዚህ ስትራቴጂካዊ አጋርነት መሠረት ኮርፖሬሽኑ በጁባ ከተማ በፍጥነት እያደገ የመጣውን የቤት ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችሉ ዘመናዊ የንግድ ማዕከላትን እና የመኖሪያ ሕንፃዎችን ግንባታ በበላይነት ይመራል ተብሏል።
Via capital

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በጁባ
#ethiopia | የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በደቡብ ሱዳን ጁባ ከተማ ለሚያካሂደው ዘመናዊ የመኖሪያና የንግድ ቤቶች ግንባታ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን የደቡብ ሱዳን መንግሥት አስታውቋል።
ኮርፖሬሽኑ ግንባታውን ለማከናወን የሚያስችለውን ስምምነት የፈረመ ሲሆን፣ የህንጻ ግንባታ ቦታዎች መረጣ እና ተያያዥ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች አፈጻጸም በግዛቱ የኮንስትራክሽን እና ቤቶች ኮርፖሬሽን በቀረበ የጥናት ሪፖርት አማካኝነት በዝርዝር ተገምግሟል።
ቀደም ሲል በአዲስ አበባ ከተማ የተደረሰውን የመግባቢያ ስምምነት ወደ ተግባር የሚቀይረው ይኸው አዲስ ውል በጁባ ከተማ ተፈርሟል።
ስምምነቱን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ረሻድ ከማል እና የደቡብ ሱዳን ሴንተራል ኢኳቶሪያል ግዛት አስተዳዳሪ ክቡር ኢማኑኤል አድል ተፈራርመውታል። በዚህም መሠረት ኮርፖሬሽኑ በጁባ ከተማ ዘመናዊ የንግድና የመኖሪያ ሕንጻዎችን የሚገነባ ይሆናል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ረሻድ ከማል ከደቡብ ሱዳን መንግሥት ልዩ መልዕክተኛ ክብርት አዱት ኪር ጋር ውጤታማ ውይይት አካሂደዋል።
በውይይቱ መድረክ ላይ በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ክቡር ደሊል ከድር እና በደቡብ ሱዳን በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች የተሰማሩት ታዋቂው ባለሀብት ዶክተር አይሸሽም ተካ ተገኝተዋል።
በመድረኩ ላይ ክብርት አዱት ኪር ኮርፖሬሽኑ በጁባ ከተማ ለሚያካሂደው የቤት ልማት ፕሮግራም የደቡብ ሱዳን ፌዴራል መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግ አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል።
ይህ የቤት ግንባታ መጀመር በሁለቱ እህትማማች አገራት መካከል ያለውን ጠንካራና ታሪካዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ያላቸውን ሙሉ እምነት በመግለጽ፣ የደቡብ ሱዳን መንግሥት ለስምምነቱ ተግባራዊነት ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።
ዋና ሥራ አስፈጻሚው ዶክተር ረሻድ ከማል በበኩላቸው፣ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በደቡብ ሱዳን የቤት ልማት ዘርፍ የተሰማራው የጋራ ተጠቃሚነትን፣ አብሮነትን እና ወንድማማችነትን መርህ አድርጎ መሆኑን ገልጸው፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን አጠናቆ ግንባታው በይፋ እንደሚጀመር አስታውቀዋል።
የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ረሻድ ከማል እና በርሳቸው የሚመራው የሥራ ልዑካን ቡድን ለአራት ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን ጉብኝት አጠናቆ ወደ አዲስ አበባ ተመልሷል።
#የፌዴራልቤቶችኮርፖሬሽን #ኢትዮጵያ #ደቡብሱዳን #ጁባ #ቤትልማት #ኮንስትራክሽን #ኢንቨስትመንት #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

ደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ ወሰን አቅራቢያ የሚገኘውን የግብፅ የጦር ሰፈር እንዲዘጋ አደረገች
#ethiopia | ደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ ድንበር ጋር በሚገናኘው የበላይኛው ናይል ክፍለ ሀገር ፓጋክ በተባለ ስፍራ ሲንቀሳቀስ የነበረውን የግብፅ ወታደራዊ ማዕከል እንዲዘጋ ወስነች።
ይህ የጦር ሰፈር ግብፅ ታላቁ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ ያላትን ጥቅምና ፍላጎት ለመጠበቅ ስትጠቀምበት የነበረ ስትራቴጂያዊ የክትትል ቦታ እንደነበር ተመልክቷል።
ይህ የጁባ ውሳኔ በቀጠናው የፖለቲካና የኃይል ሚዛን ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር የገለጹት የፖለቲካ ምሁራን፣ ደቡብ ሱዳን በሱዳን ጦርነት ምክንያት የተስተጓጎለባትን የነዳጅ ንግድ ለመተካት ከኢትዮጵያ ጋር የጀመረችውን የኢኮኖሚና የመሠረተ ልማት ትስስር ይበልጥ ለማሳደግ የያዘችውን አቋም የሚያሳይ ነው ብለዋል።
በፓጋክ ይንቀሳቀስ በነበረው በዚህ የግብፅ ወታደራዊ ጣቢያ ውስጥ የቴክኒክና የሎጂስቲክስ ባለሙያዎችን ጨምሮ ወደ 260 የሚጠጉ የግብፅ ዜጎች ይገኙበት እንደነበር ተገልጿል።
ባለፉት ሳምንታት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግንኙነት መሻከር አሳይቶ የነበረ ሲሆን፣ የደቡብ ሱዳን የአሁኑ እርምጃ በምስራቅ አፍሪካ የፖለቲካ አሰላለፍ ላይ ትልቅ መነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል።
#southsudan #egypt #gerd #grandethiopianrenaissancedam #pagak #eastafrica #politics #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

5 months ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) አቶ ጌታቸው ረዳ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በ35ኛው የነጻነት በዓል ላይ ያደረጉትን ንግግር አስመልክቶ ጠንካራ ትችት ሰንዝረዋል። አቶ ጌታቸው ይህን ትችት ያቀረቡት የአፍሪካ ጉዳዮች ተንታኝ የሆኑት ካሜሮን ሀድሰን በትዊተር)ገጻቸው ያነሱትን ጥያቄ መነሻ በማድረግ ነው። ካሜሮን ሀድሰን በመልእክታቸው፣ ማንኛውም ጤነኛ መሪ የብሔራዊ በዓል መልእክቱን አብዛኛውን ክፍል ስለ ሀገሩ እድገት እና መረጋጋት ከማውራት ይልቅ፣ ለዶናልድ ትራምፕ፣ ለማጋ (MAGA) እና በአሜሪካ ለሚመራው የዓለም አቀፍ ሥርዓት ለምን ይሰጣል? ሲሉ የፕሬዝዳንቱን ንግግር ይዘት ጠይቀው ነበር።
ይህንኑ የሀድሰንን ሀሳብ በማጋራት አቶ ጌታቸው ረዳ ባሰፈሩት ጽሁፍ፣ ይህ ጥያቄ ለብዙ ዓመታት ሲጠየቅ የኖረ መሆኑን ገልጸዋል። አክለውም፣ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በመፍረስ አደጋ አፋፍ ላይ ያለችን ሀገር ከሚመራ መሪ ይልቅ፣ ለዓለም ማንም ያልጠየቃቸውን ምክር እንደሚለግስ "ፈላስፋ ንጉሥ" ሆነው እንደሚናገሩ ክፉኛ ተችተዋል።
ከዚህም ባሻገር ከከረን፣ ከደቀመሃሪ ወይም ከዓዲ ዃላ ከተሞች ይልቅ በካምፓላ እና በጁባ የሚኖሩ ኤርትራውያን ቁጥር መብዛቱ፣ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ላለፉት 35 ዓመታት ሆን ብለው እና በደስታ ሲያዘጋጁት የነበረውን አጠቃላይ የተስፋ መቁረጥ ስሜት በሚገባ እንደሚያሳይ አብራርተዋል። በመጨረሻም፣ ፕሬዝዳንቱ ትናንትና ለ35ኛ ጊዜ በይስሙላ ሲያከብሩት የነበረውን የኤርትራን ነጻነት ራሱን የሚጠሉት እንደሚመስል አቶ ጌታቸው በመልእክታቸው አስፍረዋል።

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በደቡብ ሱዳን የቤት ግንባታ ለማከናወን ስምምነት ፈጸመ
***********************
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በደቡብ ሱዳን ጁባ ከተማ በቤት ግንባታ ዘርፍ ለመሰማራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።
ይህ ስምምነት በሁለቱ ሀገራት መሪዎች ደረጃ የተደረሰውን የጋራ ልማት ትብብር ተከትሎ የመጣ ሲሆን፣ በኮርፖሬሽኑ እና በደቡብ ሱዳን ማዕከላዊ ኢኳቶሪያል ግዛት መካከል በቤት ልማትና አስተዳደር ዘርፎች በጋራ ለመሥራት የሚያስችል መሠረት ጥሏል።
ስምምነቱን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል (ዶ/ር) እና በደቡብ ሱዳን ማዕከላዊ ኢኳቶሪያል ግዛት አስተዳዳሪ ሚስተር ኢማኑኤል አዲል ፈርመውታል።
በዚህ ውል መሠረት ኮርፖሬሽኑ ያለውን የረጅም ጊዜ ልምድና የቴክኒክ አቅም በመጠቀም በጁባ ከተማ ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶች፣ የንግድ ሕንፃዎችና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ግንባታን ያከናውናል።
ዋና ሥራ አስፈጻሚው ረሻድ ከማል (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ኮርፖሬሽኑ በምሥራቅ አፍሪካና በመላው አህጉሪቱ ገበያዎች ለመሰማራት ሲያደርግ የቆየው ዝግጅት አሁን ወደ ተግባር ምዕራፍ ተሸጋግሯል።
ስምምነቱ የሁለቱን ሀገራት የኢኮኖሚ ትስስር ከማጠናከር ባለፈ፣ ኮርፖሬሽኑ ያለውን ውጤታማ ተሞክሮ ለግዛቱ ባለሙያዎች የሚያጋራበትንና የአቅም ግንባታ ሥልጠና የሚሰጥበትን ዕድል ያመቻቻል።
የማዕከላዊ ኢኳቶሪያል ግዛት አስተዳዳሪ ሚስተር ኢማኑኤል አዲል በበኩላቸው፣ በኢትዮጵያ ያለው ፈጣን የከተሞች ለውጥና የቤት ልማት ተሞክሮ ለአፍሪካውያን ተምሳሌት መሆኑን ጠቅሰው፣ ይህንኑ ስኬት በጁባ ከተማ ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የስምምነቱን አፈጻጸም በቅርበት የሚከታተልና ዝርዝር የፕሮጀክት ሰነዶችን የሚያዘጋጅ የጋራ ቴክኒክ ኮሚቴ እንዲቋቋም የተወሰነ ሲሆን፣ ይህም የኢትዮጵያን የቤቶች ልማት ተሞክሮ ወደ ጎረቤት ሀገራት ለማስፋፋት ትልቅ መነቃቃትን ይፈጥራል ተብሏል።
Ethiopian Broadcasting Corporation #ethiopia #southsudan #juba #federalhousingcorporation #realestatedevelopment

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በደቡብ ሱዳን የቤት ግንባታ ለማከናወን ስምምነት ተፈራረመ
#ethiopia | የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በደቡብ ሱዳን ጁባ ከተማ በቤት ልማት ዘርፍ ለመሰማራት የሚያስችለውን ታሪካዊ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።
ይህ ስምምነት የተደረገው በኢትዮጵያ እና በደቡብ ሱዳን መሪዎች መካከል የተደረሰውን የጋራ ልማት ትብብር መነሻ በማድረግ ሲሆን በኮርፖሬሽኑ እና በደቡብ ሱዳን ማዕከላዊ ኢኳቶሪያል ግዛት መካከል የተፈጸመ ነው።
ስምምነቱን የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ረሻድ ከማል እና የማዕከላዊ ኢኳቶሪያ ግዛት አስተዳዳሪ ሚስተር ኢማኑኤል አዲል በጁባ ከተማ በጋራ ፈርመዋል።
ውሉ ኮርፖሬሽኑ ያለውን የቴክኒክ ብቃት እና የዳበረ ልምድ ተጠቅሞ በጁባ ዘመናዊ መኖሪያዎችን፣ የንግድ ማዕከላትንና የመንግሥት ቢሮዎችን እንዲገነባ ዕድል ይሰጣል።
ዶክተር ረሻድ ከማል እንደገለጹት ኮርፖሬሽኑ በምሥራቅ አፍሪካና በመላው አህጉሪቱ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቅረብ ባቀደው መሠረት ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ተሸጋግሯል።
የማዕከላዊ ኢኳቶሪያ ግዛት አስተዳዳሪ ሚስተር ኢማኑኤል አዲል በበኩላቸው የኢትዮጵያ የከተሞች ዕድገትና የቤት ልማት ተሞክሮ ለአፍሪካውያን አርአያ መሆኑን ጠቅሰው ይህን ተሞክሮ በጁባ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።
ይህ ትብብር የሁለቱን አገራት የኢኮኖሚ ትስስር ከማጠናከሩ ባሻገር በዘርፉ ለተሰማሩ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ሥልጠና ለመስጠት ያስችላል።
የስምምነቱን አፈጻጸም የሚከታተልና ዝርዝር የፕሮጀክት ሰነዶችን የሚያዘጋጅ የጋራ ቴክኒክ ኮሚቴ እንዲቋቋምም መግባባት ላይ ተደርሷል።
#ደቡብሱዳን #ቤትልማት #ኮንስትራክሽን #ኢኮኖሚ #አፍሪካ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

6 months ago
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስቸኳይ ማሳሰቢያ ሰጠ‼
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፣ 23 የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች ህጋዊ የሥራ ፈቃድ የሌላቸው ወይም በህገ-ወጥ ተግባር የተሰማሩ መሆኑን አሳውቋል።
ህብረተሰቡ ከእነዚህ ድርጅቶች ጋር ከማንኛውም የገንዘብ ዝውውር እንዲቆጠብ ባንኩ በጥብቅ አሳስቧል።
ዝርዝራቸው የተጠቀሱት ተቋማት፦
o አዱሊስ መኒ ትራንስፈር
o አማል ዩኤስኤ
o አማና ኤክስፕረስ
o አማል ኤክስፕረስ
o አቫንቲ
o አዋሽ ዳይሬክት
o ባካኣል መኒ ትራንስፈር
o ባናናፔይ
o ሆልደን ግሎባል
o ጁባ ኤክስፕረስ
o መኒቶስ
o ኦሊምፒክ ፋይናንሻል ግሩፕ (OFG)
o ኩዊክ ፔይ
o ራማድ ፔይ (ካአህ)
o ራስሚ ፔይ
o ሬድሲ (ዩኤስኤ)
o ሽጌይ
o ታአጅ መኒ ትራንስፈር
o ታሳ ፔይ
o ታዋካል መኒ ሰርቪስስ
o ዩኤስዋይር / ዴሮ
o ዋይዝ ትሬዲንግ መኒ ትራንስፈር
o ወርልድ ዳይሬክት ሊንክ ናቸው።
seledadotio

8 months ago
አድዋ የሚያስደንቀኝ ድልና ገድል ነው
ዓድዋ የዳዊትና ጎልያድ ተረክ ዳግም የተኖረበት የታሪክ እጥፋትም ነው፡፡ በመውረርና መዝረፍ፣ በቴክኖሎጂና ሴራ፣ በዓለማቀፍ ልማዶችና ዲፕሎማሲ የጠበደለችው ጣልያን በገዛ ሜዳዋ ላይ፣ ሀገራቸውን በሚወዱና በተለይም በጨበጣ ውጊያ እጅግ ከፍተኛ ልምድ ባላቸው የአቢሲኒያ ጀግኖች ጉድ ሆነች፡፡
ብዙ ጊዜ “በጦርነቱ ብንሸነፍስ ኖሮ?” ብዬ እጠይቅና የእነዚያ ጀግኖች ውለታ ልክ ያጣብኛል፡፡
እውነት ግን ብንሸነፍስ ኖሮ?
ሬሞን ጄናስ የተባለ ፃሐፊ “የአድዋ ድል የአፍሪካን ቀለም የወሠነ ድል ነው” ያለው በትክክል ድሉን ሳይገልፀው አይቀርም፡፡
አድዋ ላይ እነዚያ የአፍሪካ አንበሶች የነጭ ወራሪዎችን ማሸነፍ ቢሳናቸው ኖሮ እንደህንድና ሞዛምቢክ ሁሉ የመላው አፍሪካ ቅኝ ግዢ በ40 እና በ80 ዓመታት ተጠቃልሎ በነፃነት ባልተተካ ነበር፡፡ የማሸነፍ ተምሳሌት የሌለው የቅድመ አድዋ አፍሪካዊ በፍፁማዊ የበታችነት ተንበርክኮ ነበር፡፡
እነኮንጎና መሠል የምዕራብ አፍሪካ ሐገራትማ የነጠረ የዘር ጭፍጨፋን አስተናግደውም ኮሽታን ማሠማትም ተስኗቸው ነበር፡፡
የአድዋ ድል የጥቁሮችን የዓለም ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ተካፋይና ባለቤትነት ጮሆ መናገር ባይችል ኖሮ በካሪቢያን የሚገኘው የጥቁር ማሕበረሠብ ማርከስ ጋርቬይን መውለድ የሚያስችል ማሕፀን ባልነበረው ነበር፡፡
የማርከስ ጋርቬይም ሆነ ቀጥሎ የመጡት የፓን አፍሪካን ንቅናቄዎች ሁሉ የጉልበትና የተስፋ ምንጭ የአድዋ ድል ነበር፡፡
የአብዛኞቹን የአፍሪካ ሐገራት ሠንደቅ ዓላማዎችን ተመልከቱ …..
ምንጫቸው በቀጥታ የአድዋ ድል እናቷ ኢትዮጵያ ነች!
የነጻነትና ፍቅር መቀንቀኛ ሬጌም ሆነ የጥበብ ባለሟሎቿ የሐሳብ ምንጭ ኢትዮጵያችን የመሆኗ ብቸኛ ሚስጥር የአድዋው ድል ነው፡፡
ቦብ ማርሌይ፣ ቡጁባንታን፣ ካፕልተንና ፒተር ቶሽ፣ በርኒንግ ስፒርና ሲዝላ ካላንጄን የመሳሰሉት ከባባድ ሚዛን የሬጌ ሙዚቀኖች ሁሉ የታላቅነታቸው ምንጭ ኢትዮጵያ ትመስል ሁሉም አቀንቅነውላታል፡፡
በተለይ በተለይ ቦብ ማርሌይ exodus (ወደሐገር መመለስ) የተሠኘውን ሙዚቃውን መነሻው ያደረገው ኢትዮጵያን ነበር፡፡ ከዚህም ባሻገር የፊደላት አጣጣሉን በኢትጵያ ፊደሎች ዲዛይን አሠርቶም ነበር ለገበያ ያቀረበው፡፡
እንዲሁም እጅግ ዝነኛ ስራው የሆነውን “ዋር” የተሠኘ ሙዚቃ የሠራው ቀዳማዊ ሃይለስላሴ በተባበሩት መንግስታት ያደረጉትን ንግግር ወደ ግጥም በመቀየር ነበር ፡፡
በአድዋ ተራሮች ሽንፈትን ቀምሠን ቢሆን ኖሮ የማታ የማታ እንኳን ነፃነቱ ቢገኝ ገዥዎቻችን ጥለውልን በሚሄዱት የብሄር መርዝ እንደሶማሊያና ሱዳን፣ እንደሁቱና ቱትሲ፣ እንደኮጎ ጦርነቶች እርስበርስ በተፋጀን ነበር፡፡ (ገባ ብለው ወጣ ላሉት እንኳን ስንት የጨቋን ተጨቋኝ ተረኮችን ቀብረው እስካሁን ደም ይፈሳል)
በሌላ በኩል እንደምዕራብ አፍሪካውን የኢኮኒሚ ስሪታችንን “ጥሬ እቃን መላክ ብቻ” ላይ እንዲወሠን በማድረግ መከራ ያበሉን ነበር፡፡ ወታደራዊ ጣልቃገብነት፣ የመንግስት ግልበጣ ሴራዎች፣ የእጅ አዙር ጫናዎች ሁሉ ተረባርበው ባደቀቁን ነበር፡፡
የኔ የምንለውን ባሕል አራግፈው በ“ፍራንቻይዜሽን” ማዕበል በ”ኢስት አፍሪካን ኢታሊ” ቅኝት አፍርሠው በገነቡንም ነበር፡፡
“አበበ” መባል፣ “ትርሐስ” መሠኘት፣ “ኩርፋ” ተብሎ መጠራት የነፃነታችን ትሩፋት ነው
“ጥምቀትን” ማክበር፣ በ“አሸንዳ” መተጫጨት፣ “ጀፎረ” ላይ መምከር የአድዋ ድል ውለታ ነው በአማርኛ መዝፈን፣ በኦሮምኛ ማስታረቅ፣ በወላይትኛ መማር የአድዋ ድል ያስቀረልን ንዋያችን ነው ።
ዝዋይ ላይ አሳ እንድናሰግር፣ ድሬ ሺቲ እንድንገዛ፣ መቀሌ ቤት እንድንሠራ ….. የጀግኖች አባቶቻችንን ድል አስፈልጎት ያውቃል!
አሸናፊ መለሠ
ደራሲና የኮሙኒኬሽን ባለሙያ

9 months ago
ከአዲስ አበባ ቀጥሎ የልቤ ማረፊያ፣ የነፍሴ ወዳጅ የሆነችው ከተማ ሐዋሳ ነች። ሐዋሳን በቅርብ ዓመታት፣ በተለይም የሲዳማ ክልል ምስረታን ተከትሎ በቅርበት የማውቃት ቢሆንም፤ ገና ከመጀመሪያው ትውውቃችን ጀምሮ በአየሯና በህዝቧ እንግዳ ተቀባይነት ልቤን ገዝታዋለች።
ከተማዋ ያሏት የተፈጥሮ ሀብቶችና የልማት እድሎች የሚያስቀኑ ናቸው። አንድ ሰው ከአዲስ አበባ የዕለት ተዕለት ውጥረት ወጣ ብሎ ጥቂት ቀናትን በሰላም ለማሳለፍ ቢፈልግ፣ ከአዕምሮው ቀድመው የሚመጡት ቢሾፍቱ አልያም ሐዋሳ ናቸው። ጠዋት ሄዶ ከሰዓት መመለስ የሚያስችል የአውሮፕላን በረራ ያላት ከተማ ናት።
ቢሆንም ግን፣ በቅርብ ጊዜ ወዲህ የሐዋሳ ድምጽ እየራቀብኝ መጥቷል። ከተማዋ ጦርነት ውስጥ እንዳለች ስፍራ ሁሉ ጭጭ ብላለች። እንደ ሐዋሳ ያለች የቱሪዝም መዳረሻ ግን ድምጿ ሊጠፋ አይገባም። የከተማዋ ስም ከሰዎች አዕምሮና ከሚዲያ አጀንዳ እንዳይርቅ በየጊዜው ትኩረት የሚስቡ ሁነቶች ያስፈልጓታል።
ሐዋሳ እንደማንኛውም ከተማ ከሰኞ እስከ አርብ ተሠርቶባት፣ ቅዳሜ ተነግዶባት፣ እሁድ ደግሞ ልብስ ታጥቦባት የሚኖርባት ተራ ከተማ መሆን የለባትም። ይልቁንም፦
📌 ታላላቅ የሙዚቃ ኮንሰርቶችና የኪነ-ጥበብ ፌስቲቫሎች ሊዘጋጁባት ይገባል።
📌 አዳዲስና ዘመናዊ የመዝናኛ ግንባታዎች የጎብኚዎችን ቀልብ በሚስብ መልኩ ሊስፋፉ ይገባል።
📌 ዓለም አቀፍ ዝግጅቶች ወደ ከተማዋ እንዲመጡ በማድረግ የቱሪዝም እንቅስቃሴዋን ማነቃቃት ያስፈልጋል።
ሐዋሳ ዳግም ደምቃና ተንቀሳቅሳ እንድናያት፣ ከተለመደው የኑሮ ዘይቤ ወጣ ያሉ ከባባድ እንቅስቃሴዎች እና የፈጠራ ስራዎች ወደ ከተማዋ ሊመለሱ ይገባል።

10 months ago
ራስገዝ መንግሥት ተብላ እንድትጠራ
#ethiopia | የሶማሊያዋ ጁባላንድ ራስ ገዝ፣ ራሷን የቻለች መንግሥት ለመሆን የሽግግር ሂደት መጀመሯን አስታወቀች።
የጁባላንድ ግዛት ፓርላማ ትናንት ባደረገው የግዛቲቱ ሕገ መንግስት ማሻሻያ፣ ግዛቲቱ የሶማሊያ ፌደራል ግዛት መሆኗን የሚጠቅሱ አንቀጾችን በሙሉ ከሕገመንግስቱ ላይ አስወጥቷል።
ግዛቲቷ ከእንግዲህ "የጁባላንድ ፌደራል ግዛት" መባሏ ቀርቶ፣ የጁባላንድ መንግሥት ተብላ እንድትጠራ ፓርላማው ወስኗል።
ጁባላንድ ከፌደራሉ ሕገመንግስት ማሻሻያ እና ከምርጫ ጋር በተያያዘ ባለፈው ዓመት ከፌደራል መንግሥቱ ኃይሎች ጋር ደም አፋሳሽ ግጭት ውስጥ መግባቷ ይታወሳል ስትል ዋዜማ አስነብባለች።

11 months ago
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወረፍው ምክንያት ተቆጡ
📌እናቶች በሶማሊያ የብሔራዊ መታወቂያ ለመውሰድ በምሽት ውጪ ተቀምጠው የሚያሳይ ምስል ከተሰራጨ በኋላ የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር የብሔራዊ መታወቂያ ቢሯቸውን ወቅሰዋል።
#ethiopia | በሞቃዲሾ የብሔራዊ መታወቂያ እና ምዝገባ ባለስልጣን ቢሮ ውጪ ላይ በምሽት ሴቶች መሬት ላይ ተኝተው የሚያሳይ ምስል በማህበራዊ ሚዲያ ከተሰራጨ በኋላ መነጋገሪያ ሆኗል።
ሁኔታውን ተከትሎ የባለስልጣኑ ዳይሬክተር ሰዎች ተገቢ ባልሆነ ሰዓት በመጉላላታቸው ማዘናቸውን ገልፀው 20,000 ሰዎችን በቀን ለማስተናገድ የሚያስችል አቅም አዳዲስ የምዝገባ ማዕከላትን በመክፈት መገንባቱን ገልፀዋል።
ምስሉ በማህበራዊ ሚዲያዎች ከተሰራጨ በኋላ የሶማሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዛ አብዲ ዛሬ የብሔራዊ መታወቂያ ቢሮውን ሲጎበኙ ይህ ተግባር የሴቶችን ደህንነት ስጋት ውስጥ የሚጥል ነው በማለት ተቀባይነት እንደሌለው ገልፀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለስልጣኑ አገልግሎቱን ምቹና ተደራሽ ማደረግ አለበት ብለዋል።
ሶማሊያ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራምን ዘርግታ እየሰራች ሲሆን ተቋማት አገልግሎት ሲሰጡ መታወቂያውን እንዲጠይቁም ማድረግ ጀምራለች።
ምንም እንኳን ስርዓቱን ብትዘረጋም የማህበራዊ ሚዲያው ሁነት አዲስ ተመዝጋቢዎችን ማስተናገድ የሚያስችል አቅም ስለመገንባቷ ጥያቄ አጭሯል።
በተጨማሪ ፑንትላንድ እና ጁባላንድ ፕሮግራሙን አለመቀበላቸው ሌላኛው ፈተና ሆኗል ተብሏል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዛ አብዲ ከሰሞኑ በተለያዩ ተቋማት ድንገተኛ ጉብኝት እያደረጉ ሲሆን ከዚህ ቀደም በመንገደኞች ቅሬታ በቀረበበት የኤደን አዴ ኤርፖርትም ድንገተኛ ጉብኝት አድርገው እንደነበር ተዘግቧል።
ዘገባው የGEESKA ነው። #tm

12 months ago
ጥቅምት 14 ዘነበወርቅ ትደምቃለች
ትውልድና ዕድገቴ ዘነበወርቅ እንደመሆኑ መጠን ጥቅምት 14 እንደማንኛውም የአካባቢው ሰው ልዩ ስሜት ይሰጠኛል፡፡
ዘነበወርቅ ያለወትሮዋ በዚህ ቀን ታሸበርቃለች፡፡
ጎዳናዎቿ ነጠላና ነጭ ልብስ በለበሱ ክርስቲኖች ይሞላሉ፡፡ ከለሊት አንስቶ በሊቃውንት አባቶች የሚቀርበው ምስጋናና ዝማሬ መላ አካባቢውን ያደምቀዋል፡፡
የፈለገ ሰላም ሰንበት ትምህርት ቤት አገልጋዮች በተለየ ሁኔታ የተዘጋጁባቸው ዝማሬዎች ሲያቀርቡ አለማጀብ የሚቻል አይደለም፡፡ ተመሳሳይ ልብስ አሰርተው የሚያስተባብሩ የሰፈራችን ወጣቶች ለአላፊ አግዳሚው በፍቅር ፀበል ፃዲቅ ያቀርባሉ፡፡
በየቤቱ ድግስ አለ፤ እናቶች ወደቤታቸው ጋብዘው ብሉልኝ ጠጡልኝ ሲሉ ማነህ? ምንድን ነህ? ጥያቄ አይቀርብም፡፡
ምክንያቱም
ጥቅምት 14 የፃዲቁ አባታችን አቡነ አረጋዊና ቅዱስ ገብረክርስቶስ ዓመታዊ በዓል ነው፡፡
ይህንን በዓል ለመካፈል አንድ ጊዜ ወደ ዘነበወርቅ የመጣ ሰው ምናልባት ከተፃፈው በላይ ቢገጥመው እንጂ ቅጥፈት ሆኖ አያገኘውም፡፡
ኑ መንፈሳዊ በረከቱን እየተካፈላችሁ በዘነበወርቅ ሰፈር ሰዎች በፍቅር ስትጋበዙ ዋሉ!

1 year ago
ወደ እልቂት ሳናመራ ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ይድረሱልን ! / የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት /
የደቡብ ሱዳን ዋነኛው ተቃዋሚ ቡድን የሱዳን ህዝቦች ነፃ አውጪ ንቅናቄ-ኢን ኦፒዲኦ (SPLM-IO) በመሪው ሪክ ማቻር እና በሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣኖች ላይ የወንጀል ክስ በመመስረት መንግስትን በመወንጀል እርምጃዎቹ የሀገሪቱን ደካማ የሰላም ስምምነት ለማፍረስ እና የአንድ ፓርቲ አገዛዝን ለማጠናከር የተደረገ ሙከራ መሆኑን ማስጠንቀቁ ተሰማ ።
ቡድኑ ያስጠነቀቀው ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት በመንግስት ቁጥጥር ስር በሚገኘው የደቡብ ሱዳን ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኤስ.ኤስ.ቢ.ሲ) ላይ ባሰራጨው ፕሬዚዳንታዊ ትእዛዝ የሀገሪቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው የሚያገለግሉትን ማቻርን ጨምሮ የማቻር አጋር የሆነውን የፔትሮሊየም ሚኒስትር ፑት ካንግ ቾልንም ከስራ ማገዱን ካስታወቁ በኋላ ነው።
ከጥቂት ሰአታት በፊት የደቡብ ሱዳን የፍትህ ሚኒስትር ጆሴፍ ጌንግ በጁባ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ማቻር እና የቡድናቸው ሰባት ከፍተኛ አመራሮች በተለያዩ ወንጀሎች ማለትም ግድያ፣ የሀገር ክህደት፣ የሽብርተኝነት፣ የንብረት ውድመት እና በሰው ልጆች ላይ በተፈፀሙ ወንጀሎች ለፍርድ እንደሚቀርቡ ተናግረዋል።
የኤስፒኤልኤም-አይኦ የውጭ ግንኙነት ብሄራዊ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ Reath Muoch ክሱን መሠረተ ቢስ ሲሉ አውግዘዋል። ድርጊቱ ወደ አምባገነንነት እና የአንድ ጎሳ አገዛዝ በአለም አዲስ በሆነችው ሀገር ላይ እንደሚጠቁም አስጠንቅቋል።
"SPLM-IO ለደቡብ ሱዳን ህዝብ እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ እነዚህ ክሶች በSPLM-IG የተፈጠሩት የተሀድሶውን የሰላም ስምምነት ከዶ/ር ሪክ ማቻር እና ከኤስ.ፒ.ኤል.አይ.ኦ ጎን ለመሻር እና አጠቃላይ የአገዛዝ ቁጥጥር እና በሀገሪቱ ውስጥ የአንድ ጎሳ አስተዳደርን ለማጠናከር ሆን ተብሎ ሙከራ መሆኑን ያሳውቃል" ሲል ሙክ በመግለጫው ተናግሯል።
"ይህ ዉንጀላ በስምምነቱ ላይ ተደጋጋሚ ጥሰት የሚፈፅመዉ የSPLM-IO ባለስልጣናትን በማስወገድ ብቻቸውን ሀገሪቱን እንዳሻቸዉ ለመዘወር ነው" ሲሉም አክለዋል።
SPLM-IO ክሱ ማስረጃ እንደሌለው ተናግሮ ገዥውን የሱዳን ህዝቦች ነፃ አውጪ ንቅናቄ በመንግስት (SPLM-IG) በጉዳዩ ላይ የፖለቲካ ቁጥጥር ለማድረግ የፍትህ ስርዓቱን አሻሽሏል ሲል ከሰዋል።
ቡድኑ በቅርቡ የፍትህ ዋና ዳኛ እና ምክትላቸው ከስልጣን መባረር የፍትህ ነፃነትን ለማዳከም የወሰደው ስትራቴጂ አካል መሆኑን ጠቁሟል ።
SPLM-IO በስምምነቱ መሰረት በግጭቱ ወቅት የተፈጸሙ ወንጀሎችን የማጣራት ሥልጣን ያለው በአፍሪካ ህብረት የሚደገፈው የታቀደ ድብልቅ ፍርድ ቤት ብቻ መሆኑን ያረጋግጣል። ማንኛውም ሌላ ክስ ህገወጥ የፖለቲካ ጠንቋይ አደን ነው ብሏል።
"በ R-ARCSS ምዕራፍ V ስር የተደነገገው መሰረት በሰላም ጉዳዮች የተፈጸሙ ጥሰቶችን ለህግ ለማቅረብ በህጋዊ መንገድ የተሰጠው ብቸኛው ተቋም ለደቡብ ሱዳን ድብልቅ ፍርድ ቤት ነው ሌላ ማንኛውም ዘዴ የፖለቲካ ክስ ነው, ሕገ-ወጥ ነው እና ስምምነቱን ይጥሳል" ብለዋል ሙክ ።
የሰላም ስምምነቱን ለማራመድ የሚደረጉ ጥረቶች በየጊዜው የቆሙ ሲሆን እያንዳንዱ ቡድን ሌላውን አፈጻጸሙን እያናጋ ነው በማለት እየከሰሰ ነው።
እ.ኤ.አ. በ2013-2018 የእርስ በርስ ጦርነት ከኤስፒኤልኤ-አይኦ ጋር የተፋለመው የኑዌር ጎሳ ሚሊሻ በሰሜን ምስራቅ የላይኛው ናይል ናስር ካውንቲ ከደቡብ ሱዳን ህዝብ መከላከያ ሃይል (ኤስኤስፒዲኤፍ) ጋር ሲጋጭ ከመጋቢት ወር ጀምሮ ውጥረቱ መባባስ ጀምሯል ያለዉ ዘገባዉ።
መንግስት የአካባቢውን ሰላማዊ ዜጎች ትጥቅ ለማስፈታት ባደረገው ሙከራ የተቀሰቀሰው ግጭት በመቶዎች የሚቆጠሩ የመንግስት ወታደሮች ተገድለዋል፣ ቆስለዋል እና ተማርከዋል እና የብርጌድ አዛዡ ተገድሏል። ብሏል
የ2018 ስምምነትን ያደራጁት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ሌሎች የክልል መሪዎች በአስቸኳይ ጣልቃ እንዲገቡ ተቃዋሚዎች ጠይቀዋል። ስምምነቱን ለማፍረስ የሰላም ዋስትና ሰጪዎች እና ሰፊው አለም አቀፍ ማህበረሰብ ጁባ ተጠያቂ እንዲሆኑ አሳስቧል።
ተንታኞች እንደሚናገሩት በዚህ አመት ሊካሄድ የታቀደው ምርጫ እስከ 2026 እንዲራዘም መደረጉ የዘገየው የሀገሪቱን ሽግግር ሊያደናቅፍና ዳግም ግጭት ሊያስነሳ ይችላል።ብለዋል ሲል ያስነበበው ሱዳን ፖስት የዜና ወኪል ነዉ ።
የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ

Comments