16 days ago
የሰንደቅ ዓላማው ዘብ፤ የኢትዮጵያ የብረት አጥር፦ ከብቁ የሰው ኃይል እስከ ዘመናዊ ትጥቅ
************************
ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ከመቼውም ጊዜ በላይ ዘመናዊ፣ ብቁ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ የመከላከያ ኃይል እየገነባች ከዘመኑ እኩል ፍጥነት እየተጓዘች ትገኛለች።
ታድያ ይህ ጉዞ የሚጀምረው ትጥቅን እና ሎጅስቲክስን በራስ አቅም ከማምረት እና ከማደስ ነው።
መዳረሻው ደግሞ ዘመናዊ መሣሪያዎች በአግባቡ ታጥቆ የሀገርን ሉዓላዊነት የሚጠብቅ ለጠላት የበጋ መብረቅ ለሕዝብ ደጀን የሆነ የሰው ኃይል ማፍራት ነው።
ይህ መከላከያውን ብሎም ሌሎች የጸጥታ ተቋማትን የመገንባት ሂደት ኢትዮጵያን በአፍሪካ ደረጃ ተደማጭነት ያላት እና የሰላም ተምሳሌት የሚያደርጋት ነው።
የመከላከያ ኃይል ጥንካሬ የሚለካው በታጠቀው መሣሪያ ጥራት ብቻ ሳይሆን፣ ያንን መሣሪያ በራሱ አቅም የማምረት እና የመጠገን አቅሙ ላይ ነው። የኢትዮጵያ መከላከያ ኢንጂነሪንግ በዚህ ረገድ ትልቅ ለውጥ እያሳየ ይገኛል።
ቀደም ሲል ለብዙ ዐሥርተ ዓመታት የቆዩ፣ የተበላሹ እና የወደቁ ታንኮች፣ ተሽከርካሪዎች፣ መድፎች እና ሮኬቶች አሁን በአዲስ መልክ እየታደሱ ነው።
ይህ ሂደት "ሪቨርስ ኢንጂነሪንግን (Reverse Engineering) በመጠቀም የተከናወነ ሲሆን፣ አሮጌ መሣሪያዎችን ወደ ዘመናዊነት ከመቀየር ባለፈ፣ የተኩስ አቅማቸውን እና ፍጥነታቸውን በከፍተኛ ደረጃ እንዲጨምር አድርጎታል። ይህም ኢትዮጵያ መሣሪያዎችን ከመግዛት ወጥታ ወደ ማሻሻል እና ወደ ማምረት መሸጋገሯን ያሳያል።
በተለይም በሰማይ ላይ ያለውን የበላይነት ለማረጋገጥ "ስካይዊን ኤሮኖቲክስ ኢንዱስትሪ" መመሥረቱ ትልቅ ምዕራፍ ነው። ይህ ተቋም የሰው አልባ አውሮፕላኖችን ወይም ድሮኖችን በሀገር ውስጥ የማምረት አቅም ፈጥሯል። እነዚህ ድሮኖች ለስለላ፣ ለጥቃት እና ለደኅንነት ሥራዎች የሚውሉ ሲሆን፣ በከፍተኛ ከፍታ ላይ የመብረር ብቃት አላቸው።
እነዚህ ድሮኖች በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የታገዙ እና በሳተላይት ኮሙዩኒኬሽን የሚመሩ በመሆናቸው፣ ጠላት ሊያደርስ የሚችለውን የኤሌክትሮኒክስ መስተጓጎል (Jamming) የመቋቋም አቅም አላቸው።
ኢትዮጵያ ይህንን የቴክኖሎጂ አቅም መገንባቷ፣ በዘመናዊ ውጊያ ውስጥ ያላትን የበላይነት የሚያረጋግጥ ነው።
ዘመናዊ መሣሪያ ብቻውን ሀገርን አይከላከልም፤ ያንን መሣሪያ በአግባቡ የሚጠቀም እና በዲሲፕሊን የታነፀ የሰው ኃይል የግድ ይላል። የመከላከያ ኃይሉ የግንባታ ስትራቴጂ ዋናው አካል ፕሮፌሽናል ሠራዊት መገንባት ነው።
ፕሮፌሽናል ሠራዊት ማለት ከብሔር፣ ከፖለቲካ እና ከሃይማኖት ወገንተኝነት የጸዳ፣ አጀንዳው ኢትዮጵያን መጠበቅ ብቻ የሆነ ኃይል ነው። ይህ ኃይል በከፍተኛ ወታደራዊ ሳይንስ እና ጥበብ የሠለጠነ፣ የቴክኖሎጂ እውቀት ያለውና በአካል ብቃት የበለፀገ ነው።
በተለይ የ"ኤሊት ፎርስ" (Elite Force) ወይም የኮማንዶና አየር ወለድ ሠራዊት ግንባታ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል። እነዚህ ሠራዊቶች በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት በሰለጠኑ አሰልጣኞች አማካኝነት ጥብቅ ስልጠና ይወስዳሉ። የቀይ ቦኔት ባለቤት መሆን ከፍተኛ ክብርና ኃላፊነት ነው።
የኮማንዶ ሠራዊቱ በአየር፣ በባህርና በምድር በማንኛውም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ተሰማርቶ ተልዕኮ የመፈጸም ብቃት አለው። ታድያ በልምምድ ወቅት የሚያሳዩት ብቃት የአካል ብሎም የአዕምሮ ጥንካሬያቸውን እና ብስለታቸውን የሚመሰክር ነው።
እነዚህ ወታደሮች የቴክኖሎጂ ውጤት የሆኑትን ድሮኖች እና ዘመናዊ መሣሪያዎች ተጠቅመው ውጊያን የሚያስቀሩ፣ ውጊያ ቢመጣ ደግሞ በአጭር ጊዜ ውስጥ ድልን የሚያበስሩ ናቸው።
የመከላከያ ኃይሉ ጥንካሬ ዓላማው ውጊያ ሳይሆን ሰላም ነው። ጠንካራ መከላከያ መኖሩ ጠላት እንዳይደፍር ያደርጋል። ሠራዊቱ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ከማስከበር ባለፈ፣ ለቀጣናዊ ሰላም ትልቅ ሚና ይጫወታል።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ የሰላም ምንጭ እንጂ የጦርነት ምንጭ ሆና አታውቅም በአንጻሩ ከጁባ እስከ ባይደዋ ለጎረቤት ሀገራት ሰላም ዋጋ ከፍላለች። የሠራዊቱ መጠናከር ለጎረቤት ሀገራትም ጭምር ዋስትና ነው።
ሴት አየር ወለዶች፣ ኮማንዶዎች፣ የአየር ኃይል አብራሪዎች በብዛት መገኘታቸው ደግሞ የሠራዊቱን አካታችነትና ዘመናዊነት ያሳያል።
ሠራዊቱ ከቴክኖሎጂ ጋር ተስማምቶ፣ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና በዘመናዊ ዶክትሪን ተመርቶ የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማረጋገጥ የጀርባ አጥንት ሆኖ ያገለግላል።
ኢትዮጵያ ትፈርሳለች ለሚሉት እንኳን ልትፈርስ ከፍ ትላለች የተባለውም በምክንያት ነው፤ ምክንያቶቹ ደግሞ እንደነዚህ ያሉ የሀገር ፍቅር በልባቸው የሚነድ እና የጀግኖች አርበኞች ልጆች በቴክኖሎጂ ተክነው በአቅም ላይ ብቃት ደርበው ድንበር እንዳይደፈር ጥቅም እንዳይነካ ሰንደቋን ይዘው ስለተሰለፉ ነው።
የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል ግንባታ በስኬት እየተከናወነ ቀጥሏል፣ ፈተና አልበገረውም እንቅፋት አልስቆመውም። ሎጅስቲክስን እና ትጥቅን በሀገር ውስጥ የማምረት እና የማሻሻል አቅም ተገንብቷል። እየተገነባም ይቀጥላል።
ለዚህ ደግሞ ምስክሮቹ ሆሚቾ ተተኳሽ ማምረቻ "ስካይዊን ኤሮኖቲክስ ኢንዱስትሪ" ናቸው። ይህንን ቴክኖሎጂ በአግባቡ የሚጠቀም፣ በዲሲፕሊን የታነፀና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ያስቀደመ ብቁ የሰው ኃይልም እየተገነባ ነው።
ዛሬ የምናየው መከላከያ የትላንቱን አሮጌ መሣሪያ አድሶ ለዛሬው ጦርነት ዝግጁ ያደረገ፣ የነገውን ቴክኖሎጂ ደግሞ ዛሬውኑ እያመረተ ያለ ተቋም ነው። ይህ ተቋም ኢትዮጵያን ወደተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር የሚደረገውን ጉዞ በፅናት ይጠብቃል።
ኢትዮጵያ በልጆቿ ላብ እና ጥረት ብሎም በቴክኖሎጂ እና በእውቀት አስከብራ ታፍራ እና ተከብራ በነጻነት ታሪኳ አብባ ዛሬም ወደፊት እየገሰገሰች ትገኛለች።
በሰለሞን ከበደ
#ethiopia #ebc #nationalinterest #militarypower

2 months ago
በተቋማዊ ሪፎርሙ ሕዝባዊነቱን ያጠናከረው ሠራዊት
**************
የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሠራዊት የሀገር ሉዓላዊነት፣ የሕዝብ ደኅንነት እና የጽናት ታላቅ ምሰሶ ነው።
ባለፉት ስምንት ዓመታት በሠራዊቱ ውስጥ የተተገበሩት ጥልቀት ያላቸው የሪፎርም እና የተቋማዊ መዋቅር ማሻሻያዎች ሠራዊቱን ወደ አዲስ የልህቀት ደረጃ ያሸጋገሩ ናቸው።
ይህ የሪፎርም ሂደት የሠራዊቱን ሕዝባዊነት የበለጠ ያጠናከረ፣ ሙያዊ ገለልተኝነቱን ያረጋገጠ እና መዋቅራዊ አደረጃጀቱን በዘመናዊ ወታደራዊ ሳይንስ መርሆዎች ላይ ያቆመ ነበር።
ተቋሙን ከፖለቲካዊ ወገንተኝነት በማፅዳት እና አደረጃጀቱን በማዘመን የአየር ኃይል፣ የባሕር ኃይል እንዲሁም የሳይበር ደኅንነት ክፍሎች ዘመኑ የሚጠይቀውን አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የዝግጁነት ደረጃ እንዲላበሱ አስችሏቸዋል።
በተቋማዊ ሪፎርሙ ከተመዘገቡት ዋና ዋና ውጤቶች መካከል በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በሰው ኃይል ግንባታ ላይ የታየው የላቀ ዕድገት ይጠቀሳል።
ሠራዊታችን ዘመናዊ የክትትል ቴክኖሎጂዎችን፣ የሰው አልባ አየር (ድሮን) ሥርዓቶችን እና የተራቀቁ የመረጃ መረቦችን በመታጠቅ ተቋማዊ ቁመናውን አዳብሯል።
በየደረጃው ባሉ ወታደራዊ አካዳሚዎች የተሰጡት የላቁ የስልጠና መርሐ-ግብሮች የሠራዊቱን ሥነ-ልቦናዊና ቴክኒካዊ አቅም በማሳደግ፣ አደጋዎችን በሳይንሳዊ ስልት፣ አነስተኛ የሰው እና የቁሳቁስ ጉዳት በሚያስከትል መልኩ የመከላከልና የማክሸፍ ብቃቱን አጎልብተውለታል።
በሀገራችን ያጋጠሙ ውስብስብ የውስጥ ደኀንነት ፈተናዎችን በማረጋጋት ሂደት ሠራዊቱ ያሳየው አስተዋይነት እና ሕዝባዊ ወገንተኝነት ጎልቶ የወጣበት ነው።
የሕዝብን ሰላም እና ደኅንነት ለማስጠበቅ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች የትዕግሥት እና የሰላም መንገዶችን በማስቀደም፣ የሲቪሎችን ሕይወት ከጉዳት በመጠበቅ እና የሀገር ሀብት የሆኑ መሠረተ-ልማቶችን በጥንቃቄ በመጠበቅ ረገድ ውጤታማ ሥራ ሠርቷል።
ይህም ሠራዊቱ የኃይል አጠቃቀምን የመጨረሻ አማራጭ በማድረግ የሰላም እና የሕግ ሥርዓት ዋስትና መሆኑን ያስመሰከረበት ነው።
ከሀገር ውስጥ ተልዕኮ ባሻገር፣ ሠራዊታችን በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ለሚከናወኑ የሰላም ማስከበር ሥራዎች የጸና አለኝታ ሆኖ ዘልቋል።
በአፍሪካ ኅብረት እና በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተልዕኮዎች የሚያሳየው የላቀ ሙያዊ ሥነ-ምግባር፣ ለሕዝብ ያለው ቅርበት እና የተላበሰው ሕዝባዊነት የሀገራችንን በጎ ገፅታ በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ አድርጎታል።
ባለፉት የሪፎርም ዓመታት የተገነቡት ዘመናዊ አቅሞች እና ተቋማዊ ነፃነት፣ ሠራዊታችን ወደፊትም የሀገርን ሉዓላዊነት እና የሕዝብን አደራ በላቀ ብቃት ለመወጣት የሚያስችለውን አስተማማኝ መሠረት ጥለዋል።
በሀብተሚካኤል ክፍሉ
#ethiopiandefenseforce #endf #ethiopianarmy #heroesofethiopia #militarypower #ethiopiandiplomacy

6 months ago
የኢራን ያልተደፈሩት "የሚሳኤል ከተሞች''
#ethiopia | በመካከለኛው ምስራቅ እየናረ የመጣውን ወታደራዊ ውጥረት ተከትሎ፣ የኢራን ስትራቴጂካዊ የጥቃት አቅምና ከመሬት በታች የተገነቡት "የሚሳኤል ከተሞች" የዓለም አቀፍ ተንታኞችን ትኩረት ስበዋል። ኢራን በተራራማ ስንጥቆችና በከፍተኛ ጥልቀት ውስጥ የገነባቻቸው እነዚህ ምስጢራዊ ማከማቻዎች ከማንኛውም የአየር ጥቃት የተጠበቁ መሆናቸው ስጋቱን እጥፍ አድርጎታል።
እነዚህ ከመሬት በታች ያሉ ምሽጎች በሺዎች የሚቆጠሩ ባሊስቲክ ሚሳኤሎችን የያዙ ሲሆን፣ በማንኛውም ቅፅበት ወደ ተፈለገው ኢላማ ለመተኮስ ዝግጁ መሆናቸው ይነገራል። በተለይም እስከ 2,000 ኪሎ ሜትር ርቀት ድረስ መምታት የሚችሉት እንደ 'ሻሀብ-3' ያሉ ሚሳኤሎች፣ እስራኤልንና በቀጣናው ያሉ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮችን በቀጥታ ኢላማ ውስጥ ያስገባሉ።
የኢራንን ወታደራዊ ጡንቻ ይበልጥ አስፈሪ የሚያደርገው በቅርቡ ይፋ የሆነው 'ፋታህ' የተሰኘው የሃይፐርሶኒክ ሚሳኤል ነው። ከድምፅ ፍጥነት በላቀ ሁኔታ የሚጓዝ በመሆኑ፣ በአሁኑ ሰዓት ያሉ ዘመናዊ የአየር መከላከያ ሥርዓቶች ሊያቆሙት እንደማይችሉ ይገመታል።
* ሚሳኤሎቹን ከረቂቅ ሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮኖች) ጋር በማቀናጀት ማጥቃት።
* የተቃራኒ ወገንን የመከላከል አቅም የማጨናነቅ ከፍተኛ ብቃት።
* በገዛ አቅም የሚመረቱ የጦር መሣሪያዎች መበራከት።
ወታደራዊ ተንታኞች እንደሚሉት፣ ኢራን እስካሁን በነበሩ ግጭቶች የተጠቀመችው ከጠቅላላ ክምችቷ እጅግ ጥቂቱን ብቻ ነው። ይህም "የኢራን እውነተኛ አቅም ገና አልተነካም" የሚለውን መላምት ሚዛን እንዲደፋ አድርጎታል። ምዕራባውያን ማዕቀቦችን ቢያጠነክሩም፣ አገሪቱ በራሷ ቴክኖሎጂ የምታከናውነው የጦር መሣሪያ ግንባታ የቀጣናውን የኃይል ሚዛን እየቀየረው ይገኛል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #iran #middleeasttension #missilecity #militarypower #globalnews #breakingnews #persiangulf #defensetechnologytrainingacademy

Comments