2 hours ago
በምርጫው ላይ የቀረቡ ቅሬታዎችን ለመመርመር ገለልተኛ የሕግ ባለሙያዎች ቡድን አደራጅቼ ማጣራት እያከናወንኩ ነው - ምርጫ ቦርድ
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቅሬታ ማቅረቢያው ጊዜ ነገ ቅዳሜ እንደሚያበቃ በማሳሰብ፣ ፖለቲካ ፓርቲዎች ሙሉ መረጃ የያዙ አቤቱታዎችን በአስቸኳይ እንዲያስገቡ በጥብቅ አሳሰበ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የተከናወነውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ተከትሎ፣ በሂደቱ ላይ ቅሬታና አቤቱታ ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች እስከ ነገ ቅዳሜ ግንቦት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የተሟላ ማስረጃ የያዘ አጠቃላይ አቤቱታቸውን እንዲያስገቡ በጥብቅ አሳሰበ።
ቦርዱ ዛሬ ባወጣው አስቸኳይ ማስታወቂያ እስካሁን የቀረቡ የተወሰኑ አቤቱታዎች የተቆራረጡና ሙሉ መረጃ የሌላቸው መሆኑ በገለልተኛ የሕግ ባለሙያዎች እየተከናወነ ባለው የምርመራ ሂደት ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩን አስታውቋል።
ምርጫ ቦርድ በድምፅ መስጫው ዕለት የፖለቲካ ፓርቲዎች አቤቱታ ዴስክ በማቋቋም እንዲሁም «የምርጫ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ጥቆማ ማድረጊያና ምላሽ መስጫ ሥርዓት» አማካኝነት በስልክ፣ በአጭር ጽሑፍና በደብዳቤ የቀረቡለትን ዕለታዊ ችግሮች ሲፈታ መቆየቱን ገልጿል።
በአሁኑ ወቅትም ከተለያዩ አካላት የቀረቡ ቅሬታዎችን ለመመርመር ገለልተኛ የሕግ ባለሙያዎች ቡድን አደራጅቶ ማጣራት እያከናወነ ይገኛል።
ይሁን እንጂ ቀደም ሲል ለፓርቲዎች ቅሬታ አቀራረብን በተመለከተ ግንዛቤ ተሰጥቶ የነበረ ቢሆንም፣ እስካሁን የቀረቡት አቤቱታዎች የተሟላ መረጃ ያላካተቱ መሆናቸውን ቦርዱ ጠቅሷል። ከተረቀቁት ቅሬታዎች መካከል አንዳንዶቹ በምርጫ ክልል ደረጃ መታየት ያለባቸው ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ በቦርዱ በቀጥታ በምርመራ የሚታዩ መሆናቸውን ለይቷል።
ለፓርቲዎች የቀረበ ጥብቅ ማሳሰቢያ እና መሟላት ያለባቸው መሥፈርቶች
የአቤቱታ ማቅረቢያው ጊዜ ነገ ቅዳሜ ግንቦት 29 ቀን 2018 ዓ.ም የሚያበቃ በመሆኑ፣ በድምፅ አሰጣጥ፣ በቆጠራና ውጤት አገላለጽ ላይ ቅሬታ ያላቸው ተወዳዳሪ ፓርቲዎች ያሏቸውን አቤቱታዎች በአንድ አጠቃልለው፣ የሚከተሉትን 16 መዋቅራዊ ፍሬ ነገሮች አሟልተው ማቅረብ እንዳለባቸው ቦርዱ በጥብቅ አሳስቧል፦
1. መሠረታዊ መረጃዎች እና የአቅራቢው ማንነት
* ቦርዱ ባፀደቀው ስም ብቻ የተጻፈ የምርጫ ክልል እና የምርጫ ጣቢያዎች ስም ዝርዝር (ከ20 በላይ ከሆኑ በተለየ ወረቀት መያያዝ አለበት)።
* አቤቱታው የቀረበበት የምክክር ቤት ዓይነት (ለክልል ምክር ቤት፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወይም ለሁለቱም)።
* የአቤት ባዩ ወኪል ሙሉ ስም፣ ኃላፊነት እና ስልክ ቁጥር እንዲሁም አቤቱታው ለመጀመሪያ ጊዜ የቀረበበት ቀን።
2. ከድምፅ አሰጣጥ፣ ቆጠራ እና ውጤት አገላለጽ ጋር የተያያዙ ጥሰቶች
በመራጮች ላይ የተደረጉ ግፊቶች፣ የሚስጥራዊነት መጓደል፣ መደለያዎች፣ ጣቢያው ሕገ-ወጥ በሆኑ ሰዎች መያዙ ወይም ታዛቢዎችና የዕጩ ወኪሎች እንዳይታዘቡ መከልከላቸው።
ውድቅ የሆኑ ወረቀቶች መቆጠር፣ የውጤት ማዳመር ሥርዓት መዛባት፣ የተሰበሩ/የተቀደዱ የባላቶ ሳጥኖች፣ ከተላከው በላይ የድምፅ ወረቀቶች መገኘት፣ ቆጠራው በቂ ብርሃን በሌለበት ወይም ከተፈቀደው ውጭ መከናወኑ።
የውጤት መግለጫ ቅጾች በአግባቡ አለመሞላት፣ ውጤት ማዘግየት እና የምርጫ ጣቢያ ኃላፊዎች የውጤት መተማመኛ ለወኪሎች ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆን።
3. የማስፈራራት ድርጊቶች እና ማረጋገጫዎች
* ሕገ-ወጥ እስራት፣ ዛቻና ማስፈራራት እንዲሁም የታጠቀ ኃይል ከመደበኛው መጠን በላይ በጣቢያው አካባቢ መሰማራቱ።
* በጥሰቱ የተሳተፉ ግለሰቦች ስም ዝርዝር ከነኃላፊነታቸው።
* የቀረቡ የሰነድ፣ የኦዲዮ፣ የፎቶግራፍ፣ የቪዲዮ ወይም የሰው ምስክሮች (ስም፣ አድራሻና ስልክ ቁጥር) ዝርዝር።
* ለታችኛው መዋቅር ቀርቦ የተሰጠ ውሳኔ ካለ መጥቀስ።
4. የሚጠየቀው የዳኝነት ዓይነት
ቅሬታ አቅራቢው ከቦርዱ የሚፈልገው ውሳኔ በግልጽ መቀመጥ እንዳለበት የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም ውጤት እንዳይገለጽ እንዲታገድ፣ ድጋሚ ቆጠራ እና ውጤት ማስተካከል፣ ውጤት መሠረዝ እና ድጋሚ ምርጫ መካሄድ፣ ወይም በጥሰት ፈጻሚዎች ላይ አስተዳደራዊ ዕርምጃ እንዲወሰድ የሚሉትን ያካትታል።
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በማጠቃለያው የሚቀርቡት አቤቱታዎች በሙሉ በእውነት የቀረቡ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ፊርማ፣ የተጻፈበት ቀን እና የፓርቲው ይፋዊ ማኅተም ሊያርፍባቸው እንደሚገባ በጥብቅ አሳስቧል።

በአርሲ በንጹሐን ላይ ለተፈጸመው ጥቃት መንግሥት ሸኔን ተጠያቂ አደረገ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዚህ ጥቃት ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች የተሰማቸውን ኀዘን የገለጹ ሲሆን የጸጥታ ኃይሎች በአካባቢው የተቀናጀ ርምጃ እየወሰዱ መሆኑን አስታውቀዋል።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ አፈጻጸም እና በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰቱ የጸጥታ ሥጋቶችን አስመልክቶ ሰፊ መግለጫ ሰጥቷል።
መንግሥት በምርጫው ወቅት ታጥቀው ከሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ሰፊ ተግዳሮት እንደገጠመውና ድርጊቶቹን ማክሸፉን አስታውቋል።
በመግለጫው መሠረት በምርጫው ላይ ለመሳተፍ ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የተመዘገቡ ሲሆን፣ ከ52,000 የምርጫ ጣቢያዎች መካከል አብዛኛዎቹ ያለምንም ዕንቅፋት አገልግሎት ሰጥተዋል። በምርጫው 42 የፖለቲካ ፓርቲዎችና በርካታ የግል ዕጩዎች ተሳትፈዋል።
የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የቀድሞዋ የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ስፔሲዮዛ ዋንዲራ የሚመሩት የአፍሪካ ኅብረት እና የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ቡድኖች ሂደቱ ሕጋዊና ተቋማዊ ማዕቀፍን የተከተለ መሆኑን በጊዜያዊ ሪፖርታቸው አመልክተዋል።
ይሁን እንጂ የተወሰኑ ዓለም አቀፍ ተንታኞች ምርጫውን «ውጤቱ አስቀድሞ የተወሰነ» ሲሉ የሰነዘሩትን ትችት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሙሉ በሙሉ እንደማይቀበለውና ከተጨባጩ እውነታ የራቀ መሆኑን ገልጿል።
መንግሥት በሰጠው መግለጫ ምርጫውን ለማስተጓጎልና በሀገሪቱ አለመረጋጋት ለመፍጠር በተለያዩ ክልሎች የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎች የተቀናጀ ጥረት አድርገዋል ሲል ከሷል።
መንግሥት «የኦነግ ሸኔ» (የኦሮሞ ነፃነት ጦር) ሲል በሚጠራው ታጣቂ ቡድን በአርሲ ዞን ንጹሐን ዜጎችና የሃይማኖት ተቋማት ላይ ጥቃት መፈጸሙንና በዜጎች ላይ ጉዳት መድረሱን ገልጿል።

በመግለጫው ላይ መንግሥት «የፋኖ ታጣቂ ቡድን» ሲል የገለፃቸውን የክልሉን ታጣቂዎች በባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ደብረ ብርሃንና ወልድያ ከተሞች የሽብር እንቅስቃሴ ለማድረግ አቅደው ነበር ሲል ወንጅሏል።
በተጨማሪም እነዚህ ኃይሎች በኦሮሚያ ከሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎችና ከውጭ አካላት ጋር የጋራ ቁርኝት (ፅምዶ) በመፍጠር በአዲስ አበባ የኅቡዕ ሴሎችን በማደራጀትና መንገዶችን በመዝጋት ምርጫውን ለማደናቀፍ ቢንቀሳቀሱም በጸጥታ ኃይሉ ጥረት ዕቅዳቸውን አክሽፊያለሁ ብሏል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በማጠቃለያው ማንኛውም የፖለቲካ ቅሬታ በሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱ፣ በብሔራዊ ምክክር ሂደቱና በዴሞክራሲያዊ ተቋማት አማካኝነት ብቻ መፍትሔ ማግኘት እንዳለበት ሲል በመግለጫው ገልፆል
በሌላ በኩል መንግሥት የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት በ2017 በጀት ዓመት 9.2 በመቶ መድረሱንና በ2018 ደግሞ 10.2 በመቶ ይደርሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጿል።
አጠቃላይ የወጪ ንግድ ገቢ 20 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሎ እንደሚገመትና የዋጋ ግሽበት ወደ አንድ አሐዝ እየተቃረበ መሆኑን አመልክቷል።
በተጨማሪም የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጨት ሥራ፣ የጎዴ ዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ፣ የሞጆ የሴራሚክ ማኑፋክቸሪንግ እና የቦረና ቀጠና የመስኖና የአውሮፕላን ማረፊያ መሠረተ ልማቶች በተያዘላቸው ዕቅድ መሠረት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስኬቶች መሆናቸውን በመግለጫው በስፋት ተብራርቷል።

3 hours ago
ጽንፈኝነት በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም!
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት
Federal Democratic Republic of Ethiopia
OFFICE OF THE PRIME MINISTER
ጋዜጣዊ መግለጫ
ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
#ethiopia | ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ማለዳ ላይ፤ የመጀመሪያው የወገግታ ጭላንጭል በከፍታማዎቹ የኢትዮጵያ ተራሮች ላይ ፈንጥቆ ጨለማውን ሳይቀድ በፊት ኢትዮጵያውያን ረጃጅም ሰልፍ ተሰልፈዋል። በጅማ፣ በድሬዳዋ፣ በሐዋሳ፣ በባሕር ዳር እንዲሁም ስማቸው በዓለም አቀፍ የዜና ጋዜጣዎች ላይ ፈጽሞ ሊወጣ በማይችሉ ከተሞችና መንደሮች ውስጥ ያሉ ወንዶችና ሴቶች፤ ወሳኝ ተግባር ለመፈጸም በሰልፍ ቆሙ። ድምፅ ሰጡ! ይህንን ታሪካዊ ኃላፊነት ለመወጣት ከሃምሳ አራት ሚልዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎች ተመዝግበው ነበር። ይህ ቁጥር ከአንዳንድ ሀገሮች አጠቃላይ ሕዝብ ቁጥር በላይ ነው። ይህ ምርጫ እውነተኛ ስለመሆኑ ጥያቄ ለሚያነሣ ለማንኛውም አካል ግልጽ እና የማያሻማ ምላሽ ሰጥቷል!
የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎት
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከ52,000 ምርጫ ጣቢያዎች መካከል ከ50,188 በላይ የሚሆኑት በሰዓቱ ተከፍተው ቀኑን ሙሉ መራጮችን ሲያስተናግዱ እንደነበር አረጋግጧል። ከ42 የፖለቲካ ፓርቲዎች የተወጣጡ ከ10,438 በላይ ዕጩዎች እና 80 የግል እጩዎች በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የክልል ምክር ቤት ወንበሮችን ለማሸነፍ ተወዳድረዋል። ይህ በማንኛውም ሊለካ በሚችል መሥፈርት በኢትዮጵያ ታሪክ ትልቁ እና በውሳኔ አሰጣጥም ሆነ በአስተዳደራዊ ረገድ እጅግ በረቀቀ ሁኔታ ተግባራዊ የተደረገ ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ የታየበት ኩነት ነበር።
የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ክቡር ኡሁሩ ኬንያታ የሚመሩትና ከ37 የአፍሪካ ሀገሮች የተወጣጡ 83 ታዛቢዎችን ያቀፈው የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን ምርጫውን “ዲሞክራሲያዊ አስተዳደርን በሰፊው በሚደግፍ ሕጋዊና ተቋማዊ ማዕቀፍ ውስጥ የተካሄደ” ሲል ገምግሞታል።
በቀድሞዋ የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዚዳንት ክቡር ዶክተር ስፔሲዮዛ ዋንዲራ ካዚብዌ የሚመራው የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ቡድን ባወጣው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት፤ በታዘቡባቸው ጣቢያዎች ሁሉ የምርጫ ሳጥኖች በትክክል የታሸጉ መሆናቸውን፣ የፓርቲ ወኪሎች በሂደቱ በሙሉ መገኘታቸውን እንዲሁም ምርጫው አስደናቂ ተቋማዊ፣ አስተዳደራዊና የቴክኖሎጂ ዕድገትን ያሳየ መሆናቸውን አረጋግጧል። የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ልዑክ ይህንን ምርጫ “የበርካታ አዳዲስ ምዕራፎች ምርጫ” ሲል ሰይሞታል።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በድምፅ መስጠት ሂደት ውስጥ ምንም ዓይነት የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳልተመለከተ አረጋግጧል። የሲቪክ ማኅበረሰብ ታዛቢዎች ጥምረት በምርጫ ቦርድ ዕውቅና ከተሰጧቸው 55 ድርጅቶች 65,299 ታዛቢዎችን በመላ ሀገሪቱ ያሠማራ ሲሆን፤ 99 በመቶ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ያለምንም ዕንቅፋት የመታዘብ ዕድል ማግኘቱን አረጋግጧል። እነዚህ ተዓማኒነት ያላቸው ሀገራዊ እና አኅጉራዊ ተቋማት ያደረጓቸው ግምገማዎችና የሰጧቸው እውነተኛ ፍርዶች ናቸው። እነዚህ ለአፍሪካ ጥላቻ ካላቸው ወይም የአፍሪካን ዴሞክራሲ በውጫዊ መሥፈርቶች ከሚለኩ ተቋማት የተደመጡ ድምፆች አይደሉም።
አንዳንድ ዓለም አቀፍ ተንታኞች ይህንን ምርጫ እንደ ንግሥና በዓል አድርገው ያቆሸሹት ሲሆን ውጤቱም አስቀድሞ የተወሰነ ድራማ እንደነበር አድርገው ሊያቀርቡት ሞክረዋል። እነዚህን መግለጫዎች ከአውነታው የራቁ፣ በጥናትና ትንተና ላይ ያልተመሠረቱ እንዲሁም ነፃና የታሰበበት ዲሞክራሲያዊ ምርጫቸውን በኩራት ላደረጉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ክብር የማይሰጡ በመሆናቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሙሉ በሙሉ የማይቀበላቸው መሆኑን ያረግጣል። አስቀድሞ የተወሰነ ውጤት ቢኖር ኖሮ፤ ከ37 የአፍሪካ ሀገሮች የተወጣጡ 83 ገለልተኛ ታዛቢዎችን፣ 65,299 የሀገር ውስጥ የሲቪል ማኅበረሰብ ታዛቢዎችን ወይም 1,100 ዕውቅና የተሰጣቸውን የዓለም አቀፍ ጋዜጠኞችን መጋበዝ ባላስፈለገ ነበር።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዚህ ሀገራዊ ምርጫ ለተሳተፉ የኢትዮጵያ ዜጎች፤ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና ላሠማራቸው ከ350,000 በላይ ኃላፊዎች፤ ሂደቱን ለመጠበቅ የጸጥታ ኃይሎች እንዲሁም ኢትዮጵያ ለዲሞክራሲ ግንባታ መጎልበት እና ለሂደቱ መሳካት ያላትን ቁርጠኝነት ላረጋገጡት የአፍሪካ እና ቀጠናዊ የታዛቢ ቡድኖች ምስጋናቸውን ያቀርባሉ።
ስለ ኢትዮጵያ ልማት
ኢትዮጵያውያን ግንቦት 24 2018 ዓ.ም ውሳኔያቸውን ሲያስቀምጡ፤ ሀገራቸውን በፍጹም የዲሞክራሲ ባህል ውስጥ ለማንበር ነው። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ባላት ጸጋ ልክ የሚያስፈልጋትን ሁለንተናዊ ልማት በፍጥነት እውን የማድረግ ባህል እንዲቀጥል ሕዝባችን ተናግሯል።
ባለፉት ዓመታት የታየው እውነት እንደሚያሳየን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግሥት የተስፋ ቃል መንግሥት አልነበረም፤ ይልቁንም በተጨባጭ የሚታዩ ውጤቶች የተመዘገቡበት ውጤት ተኮር መንግሥት ሲሆን፤ እነዚህም ውጤቶች በግልጽ የሚታዩ ናቸው።
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ2017 በጀት ዓመት የ9.2 በመቶ ዕድገት ያስመዘገበ ሲሆን፤ ይህም በዓለም ላይ ፈጣን ዕድገት ካስመዘገቡ ኢኮኖሚዎች አንዱ ያደርገዋል። ዕድገቱ መነቃቃትን መሠረት በማድረግ በ2018 በጀት ዓመት የኢኮኖሚ ዕድገቱ 10.2 በመቶ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። ዕድገቱ ግብርናን፣ ኢንዱስትሪንና የአገልግሎት ዘርፎችን በከፍተኛ ደረጃ ያካተተ ሰፊ መሠረት ያለው ቢሆንም፤ ከጊዜ ወደ ጊዜ ግን ኢንዱስትሪው ለዕድገቱ ዋነኛ አንቀሳቃሽ ኃይል ሆኖ እየመጣ ይገኛል። ይህም መንግሥት ለማኑፋክቸሪንግ፣ ለኢንዱስትሪ ልማት፣ ለዕሴት ጭማሪና ለውጭ ገበያ ተኮር ምርቶች የሰጠውን ቀጣይነት ያለው ትኩረት ያሳያል።
እነዚህ ውጤቶች እንዲሁ ግምቶች ብቻ ሳይሆኑ፤ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የ100 ቀናት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ሥርዓት አማካኝነት ክትትል የሚደረግባቸው የተጠያቂነትና የታቀደ አመራር ፍሬዎች ናቸው። አጠቃላይ የወጪ ንግድ ገቢ 20 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ይደርሳል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፤ ይህም ከ2016 ዓ.ም. ወዲህ የ100 በመቶ ገደማ ጭማሪ አሳይቷል።
የዋጋ ግሽበትም ወደ ታች ማሽቆልቆሉን በመቀጠል አሁን ላይ ወደ አንድ አሐዝ ደረጃ እየተቃረበ ይገኛል፤ ይህም በቅርብ ዓመታት ውስጥ በቤተሰቦችና በንግዶች ላይ ከባድ ጫና ፈጥሮ ከነበረው ባለ ሁለት አሐዝ የዋጋ ግሽበት አንጻር ትልቅ መሻሻል ነው። ይህ ስኬት የተመዘገበው ዓለም አቀፍ የኃይል አቅርቦትና ሌሎች ስትራቴጂካዊ ቁሳቁሶችን ገበያ ያናጋው የመካከለኛው ምስራቅ ወቅታዊ ጂኦፖለቲካዊ ውጥረት ጨምሮ፤ ውጫዊ ጫናዎች በነበሩበት ወቅት ነው።
የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ከተጀመረ ወዲህ መንግሥት ከውጭ ምንጮች ምንም ዓይነት አዲስ የንግድ ብድር ስምምነት ያላደረገ ሲሆን፤ ይህም የሀገሪቱን የብድር ዕዳ ጫና በከፍተኛ ሁኔታ አቅልሎታል። ከእነዚህ ቁጥሮች በስተጀርባ ኢትዮጵያውያን በዓይናቸው የሚያዩትና በእጃቸው የሚዳስሱት ተጨባጭ ለውጥ አለ። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለመኖሪያ ቤቶች፣ ለንግድ ተቋማትና ለጎረቤት ሀገራት የኤሌክትሪክ ኃይል እያመነጨ ይገኛል። ይህ ግድብ በራሳቸው በኢትዮጵያውያን የተደገፈ፣ በኢትዮጵያውያን መሐንዲሶች የተገነባ እና ቀጣይነት የነበረውን ውጫዊ
ጫናዎችን ተቋቁሞ የተጠናቀቀ ነው። ከሃይድሮ ፓወር ጎን ለጎን፤ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የሚገኘውን የአይሻ ሁለት የንፋስ ኃይል ማመንጫ እና በአርሲ ዞን የሚገኘውን የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች፤ በመሳሰሉ ሥራዎች ታዳሽ ኃይል አቅርቦቷን እያሰፋች ሲሆን፤ ይህም የቀጣናዊ ኢነርጂ ትብብርን እያሳደገ የብሔራዊ ኃይል አቅርቦት መረቡን የመቋቋም ዐቅም ያጠናክራል። በአፍሪካ አህጉር ታሪክ ውስጥ ትልቁ የመሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት አንዱ የሆነው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት የመሠረት ድንጋይ ተጥሎ ግንባታው ተጀምሯል። እነዚህ ምኞቶች አይደሉም፤ ተጨባጭ ሐቆች ናቸው።
ግብርና፣ አምራች ኢንዱስትሪና ቴክኖሎጂ
በግብርናው ዘርፍ፤ የመንግሥት የምግብ ሉዓላዊነት አጀንዳ ወቅታዊ ለውጦችን ሳይሆን መዋቅራዊ ውጤቶችን እያስገኘ ቀጥሏል። በሶማሌ ክልል የጎዴ ዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካን ለመገንባት ከአሊኮ ዳንጎቴ ግሩፕ ጋር የተፈረመው አጋርነት የዘመኑ ጉልህ የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንቶች አንዱ ማረጋገጫ ነው። ፋብሪካው በዓመት 3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ዩሪያ የማምረት አቅም እንዲኖረው ታቅዶ እየተገነባ ሲሆን፤ ይህም ኢትዮጵያን በዓለም ትላልቅ ማዳበሪያ አምራች ሀገራት ተርታ ያሰልፋታል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግንቦት 9 ቀን 2018 ዓ.ም. የፕሮጀክቱን የግንባታ ሂደት በጎበኙበት ወቅት እንደገለጹት፤ “ይህ ፕሮጀክት በግብርና ትራንስፎርሜሽን፣ በምግብ ዋስትና፣ በኢንዱስትሪ ዕድገትና በኢኮኖሚ ራስን መቻል ላይ የተደረገ ስትራቴጂካዊ ኢንቨስትመንት ነው” ብለዋል። አስተማማኝ ባልሆነና ውድ በሆነ የማዳበሪያ አቅርቦት ለረጅም ጊዜ ለተገደቡት ኢትዮጵያውያን አምራቾች የዚህ ፕሮጀክት ፋይዳ ፈጣንና ተጨባጭ ነው።
ከዚህ ምርጫ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም. በነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ ምርቃት ላይ ሲገኑ የታየው ተምሳሌትነት ለቦረና ሕዝብ ትልቅ ትርጉም ነበረው። ይህ ዞን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቅበት ስም የሀገርን አንገት ያስደፋ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ሲሆን፤ እርሱም ድርቅ ነው።
ለሦስት ተከታታይ ዓመታት የዝናብ መጥፋት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ከብቶችን የገደለ፣ ቤተሰቦች ለውኃ ፍለጋ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮችን እንዲጓዙ ያስገደደ፣ እንዲሁም በእነዚህ የግጦሽ መሬቶች ላይ ለዘመናት ራሳቸውን ችለው የኖሩ ማኅበረሰቦችን ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ እጅ እንዲዘረጉ አድርጎ ነበር። ዓለም የሚያውቃት ቦረና እርሷ ነበረች።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የግንቦት ወር ጉብኝት ግን የተለየ ታሪክ አሳይቷል።
አሁን ላይ ለአርብቶ አደር ማኅበረሰቦችና ለከብቶቻቸው ንጹሕ ውኃ እያቀረቡ ያሉትን የውኃና የመስኖ መሠረተ ልማቶችን የገመገሙ ሲሆን፤ ከጥቂት ዓመታት በፊት አቧራ ብቻ በነበረው መሬት ላይ የክላስተር እርሻዎችን ጎብኝተዋል፤ በያቤሎ የባህል ማዕከል መርቀዋል፤ እንዲሁም በአየር ንብረት ሁኔታዎች ምክንያት ቀድሞ ተገልሎ ለነበረው ቀጣና ዓመቱን ሙሉ ትስስር የሚፈጥር አውሮፕላን ማረፊያ መርቀው ከፍተዋል።
የአምራች ዘርፉም ተመሳሳይ የለውጥ ታሪክ አለው። በግንቦት 2018 ዓ.ም. በተካሄደው 4ኛው ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ላይ፤ መንግሥት ለአራት ዓመታት የተመዘገበውን ቀጣይነት ያለው የኢንዱስትሪ መስፋፋት ውጤቶች አቅርቧል። የአምራች ዘርፉ የግብአት አቅርቦት በዓመት 9 ሚሊዮን ቶን ወደ 15 ሚሊዮን ቶን አድጓል። የምርት አቅም አጠቃቀም ከ47 በመቶ ወደ 67 በመቶ ከፍ ማለቱን፣ የማኑፋክቸሪንግ ዕድገት ከ4.8 በመቶ ወደ 10.7 በመቶ ማደጉን፣ እንዲሁም ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚቀርበው ፋይናንስ ከ8.1 ቢሊዮን ብር ወደ 50 ቢሊዮን ብር ማደጉን ያሳያል።
እነዚህ ስኬቶች በሀገር ውስጥ ምርት ላይ በከፍተኛ ሁኔታ እየተንጸባረቁ ይገኛሉ። ኤክስፖው በተጠናቀቀ በሃያ ቀናት ውስጥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ብቻ ተጠናቆ ከ80 በመቶ በላይ ጥሬ ዕቃውን ከሀገር ውስጥ የሚያገኘውን ግዙፍ የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት «ግራንዲዩር የሴራሚክ ማኑፋክቸሪንግ» ፋብሪካን በሞጆ ከተማ መርቀዋል። ቀደም ሲል በገቢ የሴራሚክ ምርቶች ላይ ጥገኛ የነበረችው ኢትዮጵያ አሁን ላይ የሴራሚክ ምርቶችን ከውጭ ማስገባት ሙሉ በሙሉ ለማቆምና ለውጭ ገበያ የሚሆን ምርት ለማስፋፋት እየተዘጋጀች ትገኛለች።
በቴክኖሎጂው ዘርፍም፤ ዘመናዊ ልማት ከጊዜ ወደ ጊዜ በዳታ፣ በፈጠራና በዲጂታል ሥርዓቶች የሚወሰን መሆኑን በመገንዘብ፤ መንግሥት ኢትዮጵያን ሰው ሠራሽ አስተውሎት እና የኢንዱስትሪ 5.0 ማሕቀፎችን ቀድመው ከተገበሩ ሀገራት ተርታ እያሰለፋት ይገኛል።
የጽንፈኝነትን ፖለቲካ ውድቅ ማድረግ
በኦነግ ሸኔ ዐማጽያን በንጹሐን ዜጎች ላይ በተለይም በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ ዒላማ ተደርገው የተፈጸሙ ጥቃቶችን ተከተሎ፤ የቤተሰብ እና የወዳጆቻቸውን ሕይወት ላጡ፣ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው እና የቤት ንብረታቸው ለወደመባቸው በአርሲ ዞን ለሚገኙ ወገኖቻችን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ መንግሥት ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ኀዘን ይገልጻሉ።
እነዚህ ጥቃቶች የሀገሪቱን ብሔራዊ ዕድገት ለማደናቀፍ ከሚሹ አካላት፣ በአማራ ክልል ከሚንቀሳቀሱ የሀገር ውስጥ አማፂ ቡድኖች እና ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ ዕድገት ጥላቻ ካላቸው የውጭ ኃይሎች ጋር በጥምረት የተከናወኑ ሲሆኑ፤ ዓላማቸውም በኢትዮጵያ አለመረጋጋትንና የምርጫ መስተጓጎልን ለመፍጠር ሲደረግ የነበረ የጥፋት ውጥን ተከታይ ነው።
መንግሥት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ያለ አንዳች የፀጥታ ችግር ፍትሐዊና አሳታፊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከአንድ ዓመት በላይ የዘለቀ ልዩ ትኩረትና ዝግጅት በማድረግ በቁርጠኝነት ሲሠራ ቆይቷል። በሌላ በኩል የጥፋት ኃይሎች ከባዕዳን ጋር 'ፅምዶ' የሚል ቁርኝት በመፍጠር ዕኩይ ዓላማቸውን ለማሳካት ሰፊ የጥፋት ዝግጅት ሲያደርጉ ቆይተዋል፣ ሀገራዊ ምርጫው እንዳይከናወን ሰፊ ርብርብ አድርገዋል። በተጨባጭም በቅድመ ምርጫ እና በምርጫ ወቅት የዜጎችን የመምረጥ መብትና ነጻነት ለመጋፋትና ለማደናቀፍ አለን የሚሉትን የጥፋት እጅ ዘርግተዋል።
እነዚህ የጠላት ኃይሎች በመደጋገፍና በመናበብ ዐመፅና ሁከት ለማነሳሳት፣ ከተሞችን በሽብር ጥቃት ለማወክ፣ በመንገዶች የደፈጣ ጥቃት በመፈጸም እንቅስቃሴ ለመገደብ እና በተወሰኑ አካባቢዎች ዒላማ አድርገው ነጥሎ ለማጥቃት ተንቀሳቅሰዋል። እንደ ማሳያ የጦር መሣሪያ፣ ተተኳሾችንና ሌሎች ሎጀስቲክሶችን በድጋፍ በማቅረብ በደቡባዊ ትግራይ በሚገኙ አዋሳኝ የአማራ ክልል አንዳንድ ቦታዎች ላይ ትንኮሳ ፈጽመዋል፣ በአማራ ክልል ባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ደብረ ብርሃን እና ወልድያ ከተሞችን ጨምሮ በክልሉ ዋና ዋና ከተሞች እና ሲቪሎች ላይ ዒላማ በማድረግ ያካሄደው የሽብር እንቅስቃሴና ዝግጅት፣ በአዲስ አበባ ከተማ ባደራጃቸው የኅቡዕ ሴሎች አማካኝነት በተመረጡ አከባቢዎች ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ተንቀሳቅሰው የነበረ ቢሆንም ይሄን የጥፋት ሴራ እና ድርጊት እንዲከሽፍ ማድረግ ተችሏል።
በተመሳሳይ በኦሮሚያ ክልል የሸኔ ሽብር ቡድን ከጽንፈኛው ፋኖ ታጣቂ ቡድን ጋር በመናበብ በአንዳንድ አካባቢዎች መንገዶችን በመዝጋት እንቅስቃሴ ለማስቆምና ለማስተጓጎል ፍላጎት የተንቀሳቀሰ ቢሆንም በጸጥታ ኃይሉ በተወሰደበት የተጠናከረ እርምጃ ፍላጎቱን ማሳካት አልቻለም። ቡድኑ በፀጥታ ኃይሉ የተወሰደበትን ርምጃ መቋቋም ባለመቻሉ እና ፍላጎቱን ማሳካት ባለመቻሉ ስስ ዒላማዎች ላይ ያተኮረ ርምጃ በመውሰድ የሃይማኖት እና የብሔር ግጭት ለመቀስቀስ በማለም በአርሲ ዞን አሰኮ እና አካባቢው ጥቃት በመፈጸም ሁሉን አይነት የጥፋት ርብርብ ያደረገ ቢሆንም ሁኔታውን በመቆጣጠር ፀጥታ ኃይላችን በእነዚህ ኃይሎች ላይ የተቀናጀ ርምጃ እየወሰደ ይገኛል።
መንግሥት መሰል ሥጋቶችን በንቃት በመከታተል ላይ ሲሆን፣ በምርጫው ወቅትም በብዙ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተቀነባበሩ ተመሳሳይ ዕቅዶችን በስኬት ማክሸፍ ችሏል። በንጹሐን ዜጎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን፤ ፍርሃትና ክፍፍልን ከሚያጎሉ የሚዲያ ዘመቻዎች ጋር በማስተሣሠር የተቀነባበረው ይህ እኩይ ተግባር፤ በመንግሥት የደኅንነት መዋቅርና ኦፕሬሽኖች አማካኝነት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲስተጓጎል ተደርጓል። ብሔራዊ እና ሃይማኖታዊ ክፍፍልን ለመዝራት የኃይል ጥቃትን እና ውድመትን እንደ መሣሪያ የሚጠቀሙ አካላት በሁሉም ኢትዮጵያውያን ዘንድ በግልጽ ሊወገዙ ይገባል። መሰል ተግባሮች በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ዓይነት የወደፊት ዕድል እንደሌላቸው ለማሳየት የተቀናጀ ብሔራዊ ምላሽ በመስጠት ወሳኝ ርምጃዎችን ይቀጥላል።
በንጹሐን ዜጎች ላይ ጥቃት የሚፈጸሙ አካላት፣ ድርጊታቸውን ምክንያታዊ ለማስመሰል ምንም ዓይነት የፖለቲካ ንግግር ቢጠቀሙ፤ ወሳኝ ዓላማን እያሳኩ ሳይሆን ወንጀል እየፈጸሙ ነው። የፖለቲካ ቅሬታዎች በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት፣ በብሔራዊ ምክክር ሂደት እና በዴሞክራሲያዊ ተቋማት አማካኝነት መፍትሔ ሊያገኙ የሚችሉ እና ሊያገኙ የሚገባቸው ናቸው።
ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም::
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት

4 hours ago
በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፍራንስ 24 ምርጫውን አስመልክቶ በሰራው ዘገባ ላይ የአዲስ አበባን ልማት “አስከፊ” ብሎ በመፈረጅ ያሰራጨው ዘገባ የያዛቸው መረጃዎች “ከእውነት የራቁ ናቸው” አለ
#ethiopia | በፈረንሳይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ፍራንስ 24 ባለፈው ሰኞ የተካሄደውን 7ኛ ጠቅላላ ምርጫ በተመለከተ በሰራው ዘገባ “ምርጫውን የይስሙላ” እንዲሁም የአዲስ አበባን ልማት “አስከፊ” ሲል መግለጹ፣ ኢትዮጵያ ያለችበንት ሁኔታ እና እውነታ ያላገናዘበ ነው ሲል የተቃውሞ መግለጫ አውጥቷል።
ኤምባሲው ፍራንስ 24 የቴሌቪዥን ጣቢያ ከሳቢን ፕላኔል ከተባሉ “እንግዳ” ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ፤ የቀረቡትን ሀሳቦች፣ አሳሳችና ወገንተኝነት የተሞላባቸው ትችቶች ናቸው በማለት በጽኑ እንደሚቃወም አስታውቋል፡፡ ኤምባሲው ባወጣው መግለጫ የጣቢያው ዘገባ የሀገሪቱን ነባራዊ እውነታም ሆነ የመንግሥትን ሰፊ ጥረቶች የማያንጸባርቅ አሳሳች ትርክት ነው ሲል ፈርጆታል።
አክሎም ባለፉት ዓመታት ተመዝግበዋል ያላቸው የፖለቲካና የኢኮኖሚ ስኬቶችን ወደ ጎን በመተው አስተዳደሩን በ“እርስ በርስ ጦርነት” ብቻ ከፋፍሎ ለመግለጽ የተደረገው ሙከራ ማጋነንና ከተጨባጭ እውነታ የራቀ መሆኑን ጠቅሷል። ኢትዮጵያ በአስቸጋሪ ቀጣናዊ ሁኔታዎች ውስጥም ሆና በዋና ዋና ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት የተመሰከረለትን ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት አስመዝግባለች ሲል ምላሽ ሰጥቷል።
በተጨማሪም የአዲስ አበባ ከተማ ውበትና የመሠረተ ልማት ማዘመን ሥራዎችን “አስከፊ” ሲል የገለጸበትን አግባብ፣ ኤምባሲው ውድቅ እንደሚያደርገው በመግለጽ ይህ የልማት ፕሮጀክት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን ሕይወት እየቀየረ ያለና በዋና ከተማዋም ሆነ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች በከፍተኛ ደረጃ አድናቆት የተቸረው ስኬት ነው በማለት አወድሷል።
ኤምባሲው አክሎም በምርጫው ላይ ስለአሳታፊነትና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን አስመልክቶ የሰራውና የተቸበት መንገድ በስህተት የተሞሉ ናቸው ሲል በጽኑ ነቅፏል። የፈረንሳዩ የዜና አውታር በሰራው ዘገባ “በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች ግማሽ ያህሉ የምርጫ ክልሎች አልመረጡም” ማለቱን በተመለከተ ደግሞ ይህ መረጃ ሙሉ በሙሉ ሐሰት መሆኑን ኤምባሲው በአሐዛዊ መረጃዎች አስደግፎ ተከላክሏል።
ለአብነትም “በአማራ ክልል ከ138 የምርጫ ክልል በስምንቱ ብቻ አለመካሄዱን በመጥቀስ፣ ይህም ከክልሉ አጠቃላይ ቁጥር 6 በመቶ ብቻ መሆኑን” አመልክቷል።
እንዲሁም በቴክኖሎጂ እና አጠቃላይ ሂደቱ ዲሞክራሲን የተከተለ መሆኑን በመግለጽ መገናኛ ብዙኃኑ የሰራቸው እና ያሰራጫቸው መረጃዎች እውነታን ያላገናዘቡ ናቸው ሲል አጣጥሏል፡፡
ምርጫው በተለይም በዴሞክራሲ ምህዳር መስፋትና መገናኛ ብዙኃን ተሳትፎ ዙሪያ የይስሙላ እንደነበር በዘገባው መጠቀሱን ያወሳው መግለጫው፤ የተመራጮችን፣ የሲቪል ማህበራት፣ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች፣ ታዛቢዎችን፣ የሚዲያ ብዛት እና የሚዘግቡ ጋዜጠኞችን ቁጥር እንዲሁም በአጠቃላይ ምርጫው ላይ ያሉ ቁጥሮችን በመጥቀስ ውድቅ አድርጎታል።
ኤምባሲው አክሎም ሚዲያው የውጭ ወገኖችን ማለትም የአፍሪካ ሕብረት እና የኢጋድን ታዛቢዎችን ሚና ለማሳነስ “ትላልቅ ግድፈቶችን ሪፖርት አያደርጉም” ማለቱ የተቋማቱን ስራ ማሳነስ ነው ብሎታል ። የሁለቱንም ተቋማት ልዑካን የሚመሩትን ኃላፊዎች ማንነት በመግለጽ አንጋፋ ተቋማትና መሪዎችን ማጣጣል የአስተሳሰብ አድሏዊነት ማሳያ ነው በማለት ኮንኖታል።
በመጨረሻም የዚህ ምርጫ ውጤት የሀገሪቱን የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚወሰነው በራሱ በኢትዮጵያ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ እንጂ ከውጭ በሚሰጡ መግለጫዎችና አስተያየቶች አይደለም ሲል አስታውቋል።
#አዲስ_ማለዳ
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen

Sponsored by
Surafel
6 hours ago
“በአማራ ክልል 8 ምርጫ ክልሎች ምርጫ አልተካሄደም” የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዙሪያ የቅኝት ሪፖርት ይፋ አደረገ
#fastmereja I የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ ያደረገውን አጠቃላይ የንቅናቄና የቅኝት ስራ በተመለከተ ሰፋ ያለ መግለጫ የያዘ ይፋዊ የግምገማ ሪፖርት አውጥቷል። ፌዴሬሽኑ በምርጫው ሂደት የታዩ ጠንካራ ጎኖችን፣ የተመዘገቡ ስኬቶችን፣ ያጋጠሙ የጸጥታና የቴክኖሎጂ ተግዳሮቶችን እንዲሁም ለቀጣይ ምርጫዎች የሚረዱ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በዝርዝር አስታውቋል።
ፌዴሬሽኑ በምርጫው ወቅት ከ25,000 በላይ የምርጫ ጣቢያዎችን የሸፈነ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 14,160 ታዛቢዎችን (11,382 ቋሚ እና 2,241 ተንቀሳቃሽ) በማሰማራት ሰፊ የቅኝት ስራ ማከናወኑን አስታውቋል። በዚህም የምርጫው ሂደት በሴቶች ተሳትፎ፣ በጸጥታ ሁኔታ፣ በቴክኖሎጂ አጠቃቀምና በድህረ-ምርጫ ሒደት ምን እንደሚመስል ዝርዝር ግምገማ አቅርቧል።
በፌዴሬሽኑ ሪፖርት መሠረት በምርጫው ዝግጅትና አፈጻጸም ወቅት በርካታ አዎንታዊ ተሞክሮዎችና ጥንካሬዎች ተመዝግበዋል። የምርጫው ሂደት በአብዛኛዎቹ ክልሎች በሰላማዊ ሁኔታ መጠናቀቁ፣ የሕዝብ ተሳትፎ ከፍተኛ መሆኑ እና በድምፅ መስጫ ቀንም ሆነ በድህረ-ምርጫ የቆጠራ ሂደት ላይ የፓርቲ ወኪሎችና የሲቪል ማኅበረሰብ ታዛቢዎች በንቃት መሳተፋቸው በበጎ ጎኑ ተጠቅሷል። በተለይም የሴቶች ተሳትፎ በከፍተኛ ሁኔታ ማደጉ የተገለጸ ሲሆን፣ አጠቃላይ ከተመዘገቡት መራጮች ውስጥ 49.3 በመቶ ያህሉ ሴቶች መሆናቸውንና የሴት ዕጩዎች ቁጥርም ካለፉት ምርጫዎች አንጻር መሻሻል ማሳየቱ በጠንካራ ጎንነቱ ተቀምጧል። የጸጥታ አካላትም የምርጫውን ሰላማዊነት ለማረጋገጥና ግጭቶች እንዳይባባሱ በማድረግ ረገድ ውጤታማ ሚና መጫወታቸውን ፌዴሬሽኑ በምስጋና ገልጿል።
በሌላ በኩል በምርጫው ሂደት ውስጥ የታዩ መዋቅራዊና የአፈጻጸም ድክመቶች በሪፖርቱ ላይ በዝርዝር ተመልክተዋል። በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ረገድ የዲጂታል ምዝገባና የመረጃ ማስተላለፍ ስራዎች መጀመራቸው መልካም ቢሆንም፣ ቴክኖሎጂው ከመደበኛው አሰራር ጋር ሙሉ በሙሉ አለመቀናጀቱና ቅድመ-ሙከራ አለመደረጉ በተለይ በአዲስ አበባ ረጅም ሰልፎችንና የመራጮች መጉላላትን ፈጥሯል።
በተጨማሪም በአማራ ክልል በአንዳንድ አካባቢዎች የተኩስ ድምፅ መሰማቱና የምርጫ ቁሳቁስ እጥረት ማጋጠሙ፣ በትግራይ ክልል ሙሉ በሙሉ እንዲሁም በአማራ ክልል በ8 የምርጫ ክልሎች ምርጫ አለመካሄዱ፣ እና በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች በድምሩ በ7 ጣቢያዎች ምርጫ መቋረጡ ተገልጿል።
በአማራ፣ ሲዳማ፣ ሱማሌ፣ አዲስ አበባና አፋር ክልሎች ደግሞ አንዳንድ ጣቢያዎች በሰዓቱ አለመከፈታቸውና በጋምቤላ ክልል አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች መራጮችን ሕገ-ወጥ በሆነ መንገድ ለማስመዝገብ መሞከራቸው በደካማ ጎንነት ተጠቅሰዋል።
ፌዴሬሽኑ ያጋጠሙትን ችግሮች መሠረት በማድረግ ለተለያዩ ባለድርሻ አካላት የቀጣይ የውሳኔ ሃሳቦችንና ምክረ-ሀሳቦችን አቅርቧል። ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ረገድ ሰፊ ቅድመ-ሙከራ እንዲያደርግ፣ የቁሳቁስ አቅርቦትን አስቀድሞ እንዲያጠናክር፣ ለአስፈጻሚዎች በቂ ስልጠና እንዲሰጥና ለጋዜጠኞችና ታዛቢዎች ግልጽ መመሪያ እንዲያዘጋጅ ጠይቋል። ለመንግሥትና ለጸጥታ አካላት ደግሞ በአማራ፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉልና ኦሮሚያ ክልሎች ያሉ የጸጥታ ችግሮች በአስቸኳይ እንዲፈቱና ለሴቶችና አካል ጉዳተኞች ምቹ የምርጫ አካባቢ እንዲፈጠር አሳስቧል። የፖለቲካ ፓርቲዎችም በበኩላቸው በውስጥ ደንባቸው መሠረት ቢያንስ 30 በመቶ የሴት ዕጩዎችን እንዲያቀርቡ፣ የመራጮችን ነፃነት እንዲያከብሩና ሕገ-ወጥ ምዝገባዎችን እንዲከላከሉ ጥሪ አቅርቧል።

14 hours ago
ሰላም፣ ደህና አደራችሁ?
የስልጣን ምንጭ እና ባለቤት….
ኢትዮጵያ ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በተሳካ ሁኔታ አካሂዳለች። በዕለቱ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ በነፃነት ይወክለኛል የሚለውን በመምረጥ፤ የኃይል አማራጭን ለተከተሉት ጆሮ ባለመስጠት ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መጎለበት ያለውን ውግንና አሳይቷል፡፡
በቅድመ ምርጫ ወቅት መራጩ የተፎካካሪ አካላትን ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ እና እሳቤዎች በሚገባ ሲከታተል ቆይቷል፡፡ ሲያሰላስል ቆይቶም በምርጫው ዕለት ይወክለኛል የሚለውን በምስጢር በካርዱ ወስኗል፡፡ አሁን የምርጫውን ውጤት በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡ ይህ ዴሞክራሲያዊ እሳቤ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ ብዙ የትግል ታሪኮችን አሳልፏል፡፡ ረዥም የሰላምና የልማት መንገድ የሚያስኬደውን አቅሙንም በዚሁ ውስብስብ ሂደት ሲያጣ ኖሯል፡፡ የዘንድሮው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ ከኃይል ይልቅ ሰላምን፣ ከጠብመንጃ ይልቅ የምርጫ ካርድን እንደሚመርጥ በግልጽ አስመስክሯል፡፡ ይህ ለምርጫ ያለው ቦታ እያደገ መምጣቱን ያሳየ ነው፡፡ ለዚያም ነው ብርድ፣ ዝናብ፣ ፀሐይ፣ ህመም፣ ኀዘን፣ ሙቀት፣ እርጅና እና ማስፈራሪያ ሳይገድበው ወጥቶ ድምጹን ይወክለኛል ለሚለውና ለሚሻው የሰጠው፡፡
እኔ አውቅልሀለሁ ለሚሉት፣ አይዞን እኔ ለራሴ አውቃለሁ ብሏል፡፡ ይህ የህልውና ጉዳይ ነው፡፡ የዴሞክራሲ ጥማት፡፡ የጥይት አረር በቃኝ ያለበት ውሳኔ፡፡
ሂደቱን ለማደናቀፍ ግዝትና ግዞት ቢኖርም በዕለቱ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ በቀጥታ በመወሰን በየትኛውም ቦታ ይወክለኛል ላሉት ተመራጭ ድምጻቸውን ሰጥተዋል፡፡ በዚህ ሂደት የስልጣን ምንጭ እና ባለቤትነታቸውንም አረጋግጠዋል፡፡
ይህንንም ያደረጉት ዴሞክራሲ ህዝብ - በህዝብ - ለህዝብ የሚመራበት ስርዓት ስለሆነ ነው፡፡ በዚህም ስለራሳቸው ጉዳይ ከባዳ ባእድ በማምጣት ሳይሆን፣ ራሳቸው በራሳቸው ጉዳይ የወሰኑበት ነው፡፡ ዝም ብሎ ለታዘበ ሰው ኢትዮጵያውያን ምርጫ፣ ዜጎች በሀገሪቱ ፖለቲካዊ እና አስተዳደራዊ ውሳኔዎች ላይ በቀጥታ የሚሳተፉበት ዋና መድረክ እንደሆነ እንደገባቸው ይረዳል፡፡ የስልጣን ምንጭ እና ባለቤት እንደሆነም እንዲሁ፡፡ ለዚህም ነው ከአዋካቢዎች ይልቅ በእርጋታ በካርዳቸው የሚወክላቸውን ለመምረጥ የወሰኑት፡፡
ምርጫ ለኢትዮጵያውያን የይስሙላና የቅንጦት አይደለም፡፡ የህልውና ጉዳይ ነው፡፡ የስልጣን ውክልናቸውን የሚያስተላልፉበት መንገድ፡፡ ይህም ነባሩን የኃይል ልማድ ገርስሶ፣ ዴሞክራሲያዊ እሳቤው ሚዛን መድፋቱን ያሳያል፡፡ በምርጫ ድምፅ ተጠቅሞ ውክልናና ስልጣን የሚሰጥበት እና የሚነሳበት መሆኑ ፍንትው ብሎ ታይቶታል፡፡
በምርጫ ወቅት የታየውን የህዝብ መሻት የገባው ተመራጭ እንደ መራጩ ጨዋ ሆኖ ቃሉን ይጠብቃል፡፡ ህዝቡም ትወክለኛለህ ብሎ በድምጹ ስልጣን የሰጠውን አካል፣ ምን ሰራህልኝ ብሎም ይጠይቃል፡፡ ምርጫ ተጠያቂነትን ያረጋግጣል ማለት ነው፡፡ ህዝቡ በስልጣን ላይ ያሉ መሪዎችን ስራ የሚገመግምበት እና ካላገለገሉት በጠብ መንጃ ሳይሆን ምርጫ ሲካሄድ ጠብቆ በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ በካርዱ ይቀጣቸዋል፡፡
የተመራጭ ኃላፊነት ላልመረጠውም ነው፡፡ በዕለቱ እድሜው የደረሰ ዜጋ ያለ ምንም ልዩነት የመምረጥ እና የመመረጥ መብቱን ተጠቅሞ መርጧል፡፡ ያልመረጠውና ድምጹን ለተሸናፊ የሰጠም፣ ዜጋ ስለሆነ እኩል መስተናገድን ይሻል፤ መብቱም ነው፡፡ ቀጣይም ምርጫ አለና፡፡
የዘንድሮው ምርጫ ሂደቱ ትክክለኛ እንደነበር በርካቶች መስክረውለታል፡፡ የምርጫ አስፈጻሚው አካልም ገለልተኛ እና ግልጽ አሰራር ያለው ስለመሆኑ የአፍሪካ ሕብረት፣ የኢጋድና የሀገር ውስጥ የምርጫ ታዛቢዎች መስክረውለታል፡፡ታዛቢዎቹ ምርጫ ቦርድ ገለልተኛነቱን በቅድመ ምርጫና በምርጫ ዕለት ሥራዎች አስመስክሯል ብለዋል፡፡ ቦርዱ ይህንኑ በማጠናከር አሁንም የድህረ ምርጫ ስራዎችን እየሠራ ይገኛል፡፡
ህዝቡ ዴሞክራሲያዊ መንገድ መሻቱን ካርድ በማውጣት፣ በነቂስ ወጥቶ በመምረጥ አሳይቷል፡፡ ይህ የስልጡንነት መገለጫ ነው፡፡ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲካሄድ በድምፁ ስለወሰነ፡፡ በዚሁ መሠረት የሚመረጠው አካል ከባድ የቤት ሥራ ይጠብቀዋል፡፡ የልማት፣ የሕግ የበላይነት፣ ሰላምና ደህንነትን የማስፈን፣ አገልግሎት አሰጣጥን ማዘመን፣ ዴሞክራሲያዊ እና ሰብዓዊ መብቶችን ማክበርና ማስከበር፣ ሉዓላዊነት፣ ብሔራዊ ክብር፣ ሀገራዊ አንድነት፣ ብቻ ብዙ ብዙ፡፡
እናማ መራጩ የድርሻውን ከተወጣ፣ ተመራጩ የሚሰጠውን ህጋዊ ውክልና መወጣቱ የግድ ነው፡፡ ውክልናው በየአምስት ዓመቱ የሚታደስ ኮንትራት በመሆኑ፣ ተመራጭ በቅድመ ምርጫ ወቅት በየሚዲያው ቃል የገባውን ሁሉ ህዝቡ ቆጥሮ ይዟል፡፡ አሸናፊነቱ በምርጫ ቦርድ ይፋ ሲደረግና መንግሥት ሲመሠርትም ገና የሚገባው መሀላ አለ፤ ህዝቡ ይህንንም ይከትባል፡፡ቃል የሚገባውም ድምጽ ለሰጠው ብቻ ሳይሆን ላልመረጠውም ነው፡፡ በቀጣይ ልቡን ለመግዛት፡፡ ተመራጩ ቃሉን ከጠበቀ ህዝቡ የስልጣን ምንጭና ባለቤት ስለሆነ የአምስት ዓመት ኮንትራቱን ያድስለታል፡፡ ቃላባይ ከሆነ ግን የካበተ ባህል፣ ታሪክ፣ ፍልስፍናና ጥብቅ ማህበራዊ እሴት ያለው ሰላምና ዴሞክራሲ መወዳዱ ህዝብ በሰላማዊ መንገድ ይወስናል፡፡ ስለዚህ ወደ ስልጣን የሚያደርሰውም የሚመልሰውም መንገድ ቃልን መጠበቅና ምርጫ ብቻ ነው ማለት ነው፡፡
መችም በዘንድሮው ምርጫ ካርድ ወስዶ ምንም ሳያሰናክለው በነቂስ ወጥቶ የመረጠውን ህዝብ ያየና የሰማ ሌላ መንገድ አያስብም፡፡ ወጥቶ ጢሻ ያለውም ቢመለስ፤ ያሰበም ካለ የህዝቡን ስነልቦና የበላይነት ቢረዳ ይበጀዋል፡፡ ምክንያቱም ሥልጣን ለመያዝ ህዝብን ማሳመንና በካርድ መመረጥ ብቻ በቂ ስለሆነ፡፡ የስልጣን ምንጭ እና ባለቤት፣ ሰጪም ነሺም ህዝብ ነውና፡፡
ኑ ሀገር እንሥራ!

23 hours ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ‹‹የሱማሌ ህዝብ ጥምረት›› ምርጫውን እንደሚቃወም አስታወቀ፡፡ ራሱን ‹‹የሱማሌ ህዝብ ጥምረት›› ብሎ የሚጠራውና በኦጋዴን ብሄራዊ ነፃነት ግንባር(ኦብነግ)፣ በኮንግረስ ፎር ሱማሊያ ኮዝ(ሲኤስሲ)ና በሱማሊያ ክልል ዲሞክራሲያዊ ጥምረት(ኤስአርዲኤ) አማካኝነት መመስረቱን የሚናገረው ጥምረት ዛሬ ባወጣው መግለጫ በምርጫው ላይ ጠንካራ ተቃውሞ አቅርቧል፡፡
በኦብነግ ማህበራዊ ሚዲያ አማካኝነት ይፋ ባደረገው በዚህ መግለጫው ‹‹ግንቦት 24 ቀን በኢትዮጵያ ውስጥ የተካሄደው ብሄራዊ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሀዊና ሁሉን አቀፍ ወይንም ተአማኒ አይደለም›› ብሏል፡፡ ጨምሮም የምርጫው ሂደት የዲሞክራሲን ዝቅተኛ መስፈርቶች እንኳ እንዳላሟላ ገልፆ ‹‹በምርጫው ሂደት ፖለቲካዊ ጭቆና፣ በተቃዋሚዎች እንቅስቃሴ ላይ ገደብ፣ ማስፈራራት፣ እኩል ያልሆነ ፖለቲካዊ ውድድርና የመንግስትን ሀብት አለአግባብ መጠቀም ሰፍኖበት ነበር›› በማለት አስረድቷል፡፡
አስከትሎም ከአንዳንድ አለም አቀፍ ተቋማት ብሄራዊ ምርጫ ቦርድን የሚያወድሱ መግለጫዎች መውጣታቸው እንዳሳሰበው የገለፀው መግለጫው፣ ‹‹እንዲህ አይነት ግምገማዎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህዝቦች የገጠማቸውን እውነታ አያንፀባርቅም›› ብሏል፡፡

1 day ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የተካሄደውን 7ኛውን አጠቃላይ ምርጫ የታዘቡት የአፍሪካ ኅብረት እና የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) የምርጫ ታዛቢ ልዑካን ቡድኖች የመጀመሪያ ደረጃ ግኝቶቻቸውን በአዲስ አበባ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ አድርገዋል። ሁለቱም ተቋማት በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምና ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር እንዲሁም እምነትን ለማጎልበት አካቶ አጠቃላይ እና ቀጣይነት ያለው የፖለቲካ ውይይት መደረግ እንዳለበት ጥሪ አቅርበዋል።
በቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሚመራው የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን ባወጣው መግለጫ፣ በፖለቲካ ኃይሎች መካከል ልዩነቶችን ለመፍታት እና ዲሞክራሲያዊ አስተዳደርን ለማጠናከር ውይይት ወሳኝ መሆኑን ገልጿል። ይህ ውይይት በሀገሪቱ ሕገ-መንግሥታዊ ማዕቀፍ ውስጥ ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እና የዜጎችን ተሳትፎ ለማሳደግ መርዳት እንዳለበት ቡድኑ ጠቁሟል። በተጨማሪም የፖለቲካ ብዙሃነትን ማሳደግ እና ዜጎች መብቶቻቸውን በነፃነት የሚለማመዱበት ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንደሚያስፈልግ አሳስቧል።
በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ በትግራይ እና ምርጫ ባልተካሄደባቸው ሌሎች አካባቢዎች ላይ ቡድኑ ለምን ምክረ-ሐሳብ አላካተተም ተብሎ ለቀረበለት ጥያቄ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጸጥታ ሁኔታው ሲሻሻል ምርጫውን ለማካሄድ ዝግጁ መሆኑን እንዳረጋገጠላቸው ኬንያታ ምላሽ ሰጥተዋል። ታዛቢ ቡድኑ ይህንን ያልተጠናቀቀ የምርጫ ሂደት በቀጣይ እንደሚከታተልም ገልጿል።
በሌላ በኩል በምርጫው ወቅት የአንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ፈቃድ መታገድን እና የሚዲያ ነፃነትን በተመለከተ ለቀረበው ጥያቄ ታዛቢ ቡድኑ ቀጥተኛ ምላሽ ከመስጠት የተቆጠበ ሲሆን፣ ዝርዝር ምልከታው በመጨረሻው ሪፖርት ላይ እንደሚወጣ አስታውቋል። ገዥው የብልጽግና ፓርቲ በምርጫ ሊሸነፍ የሚችልበት እውነተኛ ዕድል ስለመኖሩ እና ስለ ምርጫው ተወዳዳሪነት ለቀረበው ጥያቄ ኬንያታ ሲመልሱ፣ ምርጫው ተወዳዳሪ እንደነበር በመግለጽ ተሟግተዋል። በዲሞክራሲያዊ ምርጫ ውስጥ መሳተፍ የውጤቱን አለመታወቅ እና የሽንፈትን ዕድል መቀበልን አብሮ የሚያካትት መሆኑን አብራርተዋል። የአፍሪካ ኅብረት ለዚህ ምርጫ ከተለያዩ 37 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ 73 የአጭር ጊዜ ታዛቢዎችን አሰማርቶ የነበረ ሲሆን፣ በቀጣዮቹ ወራት የተሟላ የመጨረሻ ሪፖርት እንደሚያወጣ አስታውቋል።
በቀድሞዋ የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ዋንዲራ ስፔሲዮሳ ካዚብዌ የሚመራው የኢጋድ ታዛቢ ቡድን በበኩሉ፣ ምርጫው በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ እና ምርጫ ዕድገት ላይ ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን ገልጿል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባስተዋወቃቸው ተቋማዊ እና ቴክኖሎጂያዊ ማሻሻያዎች ምክንያት ውድድሩን የበርካታ አዳዲስ ነገሮች ማሳያ ምርጫ ሲል ጠርቶታል። የኢጋድ ልዑክ 26 ታዛቢዎችን በሰባት ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች አሰማርቶ የነበረ መሆኑም ታውቋል።
በዘንድሮው የኢትዮጵያ 7ኛ አጠቃላይ ምርጫ ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች የተመዘገቡ ሲሆን፣ ውድድሩ ከ547 የምርጫ ክልሎች ውስጥ በ501ዱ እና በአገር አቀፍ ደረጃ ባሉ 52 ሺህ ገደማ የምርጫ ጣቢያዎች ተካሂዷል።
ይሁን እንጂ በምርጫው ዕለት በጸጥታ ስጋት ምክንያት 143 የምርጫ ጣቢያዎች ሳይከፈቱ ቀርተዋል። በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች፣ በተለይም እንደ ቢሎኖፓ፣ መቆሳቺ፣ ቀርሳ እና ኩታበር ባሉ አካባቢዎች ድምጽ አሰጣጥ ከተጀመረ በኋላ በጸጥታ እክሎች ምክንያት መቋረጡን ቦርዱ አስታውቋል። በትግራይ ክልል እንዲሁም በአማራና በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች በጸጥታና በሎጅስቲክስ ምክንያት ድምጽ አልተሰጠም። ይህ ከመደረጉ በፊት ተቃዋሚዎችና ታዛቢዎች በእነዚህ አካባቢዎች ያለው ግጭት የመራጮችን ተሳትፎ ሊጎዳ እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸው ነበር። ምንም እንኳን እነዚህ መስተጓጎሎች ቢያጋጥሙም፣ በአብዛኛዎቹ የሀገሪቱ አካባቢዎች ድምጽ አሰጣጡ በሰላማዊ መንገድ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ የዚህ ምርጫ የመጨረሻ ውጤት በመጪው ሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ጠንካራ መሠረት መጣሉን የኦሮሚያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አስታወቀ
*************************
የኦሮሚያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሂደት አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል፡፡
በክልሉ የሚወዳደሩ 22 የፖለቲካ ፓርቲዎችን ያቀፈው ምክር ቤቱ መግለጫውን ያወጣው፣ የፓርቲዎቹ መሪዎችና ተወካዮች በተገኙበት የምርጫውን አጠቃላይ ሂደት ገምግሞ ካጠናቀቀ በኋላ ነው፡፡
ምክር ቤቱ በመግለጫው ምርጫው የሕዝብ ከፍተኛ ተሳትፎ የታየበትና የአስፈጻሚ አካላት ፍትሐዊነት የተረጋገጠበት መሆኑን አስታውቋል፡፡
የጋራ ምክር ቤቱ አባላት በምርጫው ሂደት የታየው የሕዝቡ የነቃ ተሳትፎ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የማስፈጸም አቅም፣ ኢትዮጵያ ለጀመረችው የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ትልቅ ተስፋ የሰጠ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ምክር ቤቱ በመግለጫው በተለይ ለምርጫው ሰላማዊነት የፀጥታ አካላት የተጫወቱትን ሚና ያደነቀ ሲሆን፣ ምርጫ ቦርድም ሂደቱን ከማስፈጸም ባለፈ የሚነሱ ቅሬታዎችን ከስር ከስር በመፍታት በኩል የነበረውን ጥረት አጉልቷል፡፡
ከሁሉም በላይ ደግሞ ኅብረተሰቡ ምርጫውን ለማደናቀፍ የተሰማሩ ኃይሎችን በማምከን፣ ሥልጣን ማግኘት የሚቻለው በምርጫ ካርድ ብቻ መሆኑን በተግባር ያሳየበት ሂደት እንደነበር በአፅንኦት ገልጿል፡፡
ምርጫው ሰላማዊ፣ ነጻ እና ፍትሐዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ባለድርሻ አካላት ያደረጉትን ከፍተኛ ርብርብ ያደነቀው ምክር ቤቱ፣ ሂደቱ የኢትዮጵያን ሕዝብ ስልጡንነት እና መብቱን ለመጠቀም ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን ያመላከተ መሆኑን አስታውቋል፡፡
በዘሃራ መሀመድ #የምርጫውጤት #ኢትዮጵያ #oromiajointcouncil #ethiopianelection #democracy #ethiopia

2 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ዛሬ ጌታቸው ረዳ እና የአማራ ማህበር በሰሜን አሜሪካ ተወካዩ ሮቤል በቲአርቲ ቴሌቭዥን የተናገሯቸውን ማቅረባችን ይታወሳል። ለጌታቸው ረዳ በዛው ቲሌቭዥን የሰጠውን ምላሽ ተከትሎ ከቀረቡት መካከል የማህበረሰብ አንቂዋ መአዛ ግደይ ገብረመድህን አንዷ ናት። ስለምርጫው ከተናገረችው መካከል፦
"የአሁኑ ሥርዓት አካል የሆነ ሰው የምርጫውን አፈጻጸም ትክክለኛነት ለማስረዳት መሞከሩ የሚጠበቅና የማያስገርም ነው። ነገር ግን፣ በትግራይ ምርጫ ሳይካሄድ የቀረበትን ምክንያት በአንድ የተወሰነ የፖለቲካ ፓርቲ ላይ ብቻ ማሳበብ ሚዛናዊነት የጎደለው ነው። ትክክለኛው ምክንያት የፕሪቶሪያው ስምምነት ቢፈረምም፣ አሁንም ድረስ በትግራይ ውስጥ ሰላምና መረጋጋት ባለመስፈኑ ነው።
"በመሆኑም፣ በኢትዮጵያ መንግሥትም ሆነ በሌሎች የፖለቲካ ኃይሎች ተግባር እንዲሁም ኃላፊነትን በአግባቡ ካለመወጣት የተነሳ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችሉ መሠረታዊ ቅድመ-ሁኔታዎች አልተሟሉም። ስለዚህ የኢትዮጵያን መንግሥት ሚና ሙሉ በሙሉ ነጻ አድርጎ፣ ጥፋቱን በህወሓት ላይ ብቻ መጫን ተገቢነት የለውም።"

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ዛሬ ጌታቸው ረዳ በቲአርቲ ቴሌቭዥን የተናገራቸውን ማቅረባችን ይታወሳል። ለጌታቸው ረዳ በዛው ቲሌቭዥን የሰጠውን ምላሽ ተከትሎ ከቀረቡት መካከል የአማራ ማህበር በሰሜን አሜሪካ አባሉ ሮቤል ዓለሙ አንዱ ነው። እርሱ የሰጠው አስተያየት እንደሚከተለው ቀርቧል።
"ሰኞ ዕለት [የምርጫው ቀን] የታየው ነገር የዲሞክራሲ አስመሳይነት ነበር፤ ምክንያቱም በኢትዮጵያ ያለው የአሁኑ እውነታ ከዚያ የራቀ ነው። ይህን ለመረዳት የዐቢይ አሕመድን አስተዳደር የሰብዓዊ መብት አያያዝ ታሪክ መመልከት ብቻ በቂ ነው፣ ይህም በዓለም ላይ ካሉ በጣም አስከፊዎች መካከል ይመደባል። እንደ ምሳሌ ብንወስድ... ባለፉት አምስት ዓመታት የታጠቁ ግጭቶች ሲካሄዱበት በነበረው፣ እና ባለፉት ሦስት ዓመታት ደግሞ በዐቢይ 'የኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ' አስተዳደር ሥር ባሉ የመንግሥት ኃይሎች በኩል የአማራ ክልል የዕለት ተዕለት የጭካኔ ድርጊቶች እያስተናገደ ይገኛል። ባለፈው ወር የለምኪን ኢንስቲትዩት የዐቢይ ጦርነት በአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ነው በማለት የዘር ማጥፋት ማስጠንቀቂያ አውጥቷል፤ እናም ድርጅታችን በመንግሥት ኃይሎች የጤና ጣቢያዎችን፣ ትምህርት ቤቶችን፣ ቤቶችን፣ የአምልኮ ቦታዎችን እና ሌሎች የሲቪል ተቋማትን ዒላማ ያደረጉ፣ እና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለሞት የዳረጉ ከ370 በላይ የአየር ድብደባዎችን መዝግቧል። የቅርብ ጊዜ የቢቢሲ ሪፖርት ከአነስተኛ የጤና ማዕከላት በተወሰደ ናሙና፣ በአማራ ክልል በሺዎች የሚቆጠሩ የአስገድዶ መድፈር ጉዳዮችን ያሳየ ሲሆን፣ አብዛኛዎቹ በመንግሥት ኃይሎች የተፈጸሙ መሆናቸው ተመላክቷል። ባለፈው ሳምንትም፣ የጤና እና የግጭት ጥበቃ ጥምረት በጤና አጠባበቅ ላይ እየጨመረ ያለውን ጥቃት የሚያሳይ ሪፖርት አውጥቷል።
"ዩኒሴፍ ከ9 ሚሊዮን በላይ ልጆች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን ሪፖርት አድርጓል፣ ከነዚህ ውስጥ ግማሹ ከአማራ ክልል ናቸው። እናም በአጎራባች ኦሮሚያ ክልል፣ በብሔረሰብ አማራዎች እና በኦርቶዶክስ ክርስቲያን ማኅበረሰቦች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ቀጥሏል። ምርጫው ዕለትም በምስራቅ አርሲ አካባቢ የነቃ ጭፍጨፋ ሲካሄድ፣ የአካባቢው ታጣቂዎች ተሳታፊ ሆነዋል። በወለጋ አካባቢ ደግሞ በፌዴራል እና በኦሮሚያ ክልል ኃይሎች በኩል ቀጣይነት ያለው ጥቃት እና የከበባ ሁኔታ ይታያል። ስለዚህ በጣም አሳሳቢ የሆነ የሰብዓዊ መብት ቀውስ አለ፣ የፖለቲካ ብዝሃነት የለም፣ የሐሳብ ነጻነት የለም፣ የተዘጋ የሲቪክ ምህዳር አለ፣ ነጻ ፕሬስ የለም፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በአማራ ማንነታቸው፣ በፖለቲካዊ እምነታቸው ታስረዋል፣ ወይም በአንዳንድ ሁኔታዎች ያለምንም ምክንያት ታስረዋል። ከእነዚህም መካከል የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፣ የፓርላማ አባላት፣ ነጻ ጋዜጠኞች፣ የሲቪል ማኅበረሰብ መሪዎች ይገኛሉ፤ እነዚህ ሰዎች በጣም ከባድ በደል ይደርስባቸዋል።"

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የቲአርቲ ጋዜጠኛዋ ዛሬ ጌታቸው ረዳን ስትጠይቅ "በመጀመሪያ ማንም ሰው በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባለ የተከፋፈለ ሀገር ውስጥ፣ አንድ ፖለቲከኛ ከ80 እስከ 90 በመቶ ሀገራዊ ድምጽ አገኘ ሲባል ሲሰማ፣ የዚህ ምርጫ ፍትሃዊነት ላይ ምክንያታዊ ጥርጣሬዎች መፈጠራቸው አይቀርም። ስለዚህ አሁን ይህ ምርጫ ፍትሃዊ ነበር ማለት ይችላሉ?" አለች።
ጌታቸው ረዳ ሲመልሱ... "እንግዲህ ለአንደኛው ነገር ማን እንዳሸነፈ እና በስንት በመቶ እንዳሸነፈ የተሰጠ ምንም ዓይነት መግለጫ እስካሁን አልሰማሁም። ይህ እንዳለ ሆኖ፣ ባለፉት 20 ምናምን ዓመታት በዚህች ሀገር ፖለቲካ ውስጥ እንደመቆየቴ፣ እኔ አባል የነበርኩበት ገዥ ፓርቲ 90 ምናምን በመቶ ድምጽ ያሸነፈበት ጊዜ ነበር። ለዚህ ማብራሪያዎች አሉት። የነገሩ እይታ እና ሁሉም ነገር ትክክል ላይመስል ይችላል፣ እናም ሰዎች 90 በመቶ ድምጽ በማግኘታቸው የተለየ ኩራት አይሰማኝም። ነገር ግን አንደኛው ጉዳይ፣ በሀገሪቱ ያለው የምርጫ ሥርዓት 'አብላጫ ድምጽ ያገኘ የሚያሸንፍበት' በመሆኑ፣ ብዙ ዕጩዎች በሚኖሩበት ጊዜ በቀላሉ ከፍተኛ ድምጽ ያገኘው ወንበሩን ያሸንፋል ማለት ነው። ይህ ደግሞ በመጨረሻ ሲታይ በርካታ የሕዝብ ድምጽ ያገኙት እንኳን አንድም ወንበር ሳያገኙ ሊቀሩ ይችላሉ ማለት ነው። ፍትሃዊ ላይሆን ይችላል፣ ያ አሠራር ፍትሃዊ ላይሆን ይችላል፣ ነገር ግን ሕገ-መንግሥቱ የሚለው ያንን ነው፣ በሌሎች የዓለም ክፍሎችም የምዕራባውያን ዴሞክራሲዎችን ጨምሮ የሚከሰተው ይሄው ነው።
"ሌላኛው ማብራሪያ ደግሞ፣ ከምርጫው በፊት ለ5 ወይም ለ9 ወራት ብቻ ቅስቀሳ የሚጀምሩ "ወቅት ጠባቂ" የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው ፓርቲዎች ሲኖሩ፣ አብዛኛውን ጊዜ በሥልጣን ላይ ያለው አካል በእነዚህ ወቅት ጠባቂ ፖለቲከኞች ላይ ብልጫ ይኖረዋል።"

ከምርጫ በኋላ ምን ይከናወናል?
****************
1. የድምፅ ቆጠራ እና ማረጋገጥ
ከምርጫ ጣቢያዎች ጀምሮ የተሰጡ ድምፆችን በጥንቃቄ መቁጠር እና ማረጋገጥ።
2. ውጤትን ይፋ ማድረግ
ከምርጫ ጣቢያ ጀምሮ በየደረጃው ውጤት መግለጽ፣ በመጨረሻም በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል የተረጋገጠውን አጠቃላይ ውጤት ለሕዝብ ይፋ ማድረግ።
3. የታዛቢዎች መግለጫ
የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ የምርጫ ታዛቢዎች የሒደቱን አጠቃላይ ሁኔታ አስመልክቶ ሪፖርት (መግለጫ) ማቅረብ።
4. ቅሬታዎችን በሕግ መፍታት
ተፎካካሪ ፓርቲዎችና የግል ዕጩዎች የሚያነሷቸውን አቤቶታዎች በሕገ-መንግሥታዊ መንገድ እና በሕግ አግባብ መፍትሔ መስጠት።
5. የአፈጻጸም ግምገማ
የምርጫ አስፈጻሚ አካላት በምርጫው የነበራቸውን አጠቃላይ ሒደት፣ ጥንካሬና ክፍተት መገምገም።
6. መንግሥት መመሥረት
የሕዝብን ውሳኔ (ድምፅ) መሠረት በማድረግ ሥልጣን ማስተላለፍ እና ወደ ተግባራዊ የመንግሥት ምሥረታ መቀየር።
Ethiopian Broadcasting Corporation #ምርጫ #ኢትዮጵያ

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሀገር መፃኢ እድል እና ለዲሞክራሲ ግንባታ ያለው ፋይዳ የጎላ እንደሆነ መራጮች ገለጹ
*********************
ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ሰላማዊ በሆነ መልኩ የተሄደ ሲሆን የዜጎችን የፖለቲካ ንቃትና የዲሞክራሲ ፍላጎት በግልጽ ያሳየ ክስተት ነበር።
በምርጫው ሂደት ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ ዜጎች እንደገለጹት መምረጥ ማለት ተራ ተግባር ሳይሆን የሀገርን መፃኢ እድል የመወሰንና የዲሞክራሲ መሰረትን የማጠናከር ወሳኝ ሂደት ነው ብለዋል።
ዜጎች ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በነቂስ የወጡት ያለምንም አስገዳጅነትና በራሳቸው ተነሳሽነት መሆኑን ገልፀው ለዚህም ዋነኛው ምክንያት ይሆነኛል የሚሉትን እና ለሀገር እድገት ይሰራል የሚሉትን አካል በነፃነት ለመሰየም መምጣታቸውን ገልጸዋል።
ምርጫው ለሀገር ገንባታ ትልቅ መድረክ ነው የምርጫ ሂደት ኢትዮጵያ ወደተሻለ የዲሞክራሲ ምህዳር ለማሸጋገርና ለቀጣዩ ትውልድ የምትመች ሀገርን ለመገንባት የምታደርገውን ጉዞ የሚያፋጥን ነው ብለዋል።
ምርጫ ዜጎች በመረጡት መሪ የመተዳደር መብታቸውን በማስጠበቅ ለሀገራዊ አንድነትና ለዘላቂ ሰላም መሰረት ሆኖ ያገለግላል።
በቢታኒያ ሲሳይ
Ethiopian Broadcasting Corporation #ebc #ethiopia #election #democracy

"በሚሊተሪ ካምፓች እና በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ምርጫ ሰኔ 2 ይካሄዳል" - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በሚሊተሪ ካምፓች እና በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች በተመዘገቡባቸው ልዩ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ የመራጮች ምዝገባ ሰኔ 1 ቀን እንደሚያካሂድ የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን በዛሬው ዕለት በሪፖርቱ ጠቅሶት ነበር።
ይህንን አስመልክቶ ማብራሪያ እንዲሰጡበት ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ በሚሊተሪ ካምፓች እና በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች በተመዘገቡባቸው ልዩ የምርጫ ጣቢያዎች ምርጫው በተለየ ቀን እንደሚካሄድ አረጋግጠዋል።
ሆኖም ህብረቱ "June-8 / ሰኔ 1" ቀን እንደሚካሄድ ሪፖርቱ ቢጠቅስም፥ ወ/ሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ ግን ምርጫው በእነዚህ ልዩ ጣቢያዎች የሚካሄደው #ሰኔ_2 መሆኑን ነው የገለጹት።
ይህ የተፈጠረበትን ምክንያትም ቦርዱ ያለበትን የተጨናነቀ ጊዜ ታሳቢ በማድረግ ውጤቶቹም "በፍጥነት ተጠቃለው መቅረብ የሚችሉ ውጤቶች በመሆናቸው " ነው ሲሉ ቦርዱ ከሌሎች ውጤቶች ጋር አብሮ የሚያቀርባቸው መሆኑን ገልጸዋል።
ከዚህ ቀደም በሀገር ውስጥ ተፈናቃይ ካምፖች 28,632 እንዲሁም በሚሊተሪ ካምፖች 126,498 ሺ መራጮች መመዝገባቸው መገለጹ ይታወሳል።
በተጨማሪም ህብረቱ የተጠናቀቀ ውጤት የሚገለጽበትን ቀን በተመለከተ ህብረቱ ሰኔ 4 መሆኑን በሪፖርቱ ጠቅሷል።
የቦርዱ ሰብሳቢ በበኩላቸው ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ቦርዱ ከገጠመው የድምጽ በይፋ የማሳወቅ ሥራ እስከ 20 ቀን የመግፋት መብት እንዳለውም ጠቁመዋል።
Seledadotio

#ethiopia | የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በሚሊተሪ ካምፓች እና በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች በተመዘገቡባቸው ልዩ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ የመራጮች ምዝገባ ሰኔ 1 ቀን እንደሚያካሂድ የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን በዛሬው ዕለት በሪፖርቱ ጠቅሶት ነበር።

#getutemesgen #getu

የኢትዮጵያን ዴሞክራሲ ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገረው ምርጫ …
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያን የዴሞክራሲና የሀገረ መንግሥት ግንባታ ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገረ ነው አሉ የህግና ፌደራሊዝም ባለሙያ በላይ ወዲሻ።
ባለሙያው ከፋና ፖድካስት ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ዜጎች ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 6 ሰዓት በሰላማዊ መንገድ ድምፅ መስጠታቸውን አስታውሰዋል።
ይህም በሀገሪቱ የፖለቲካ ንቃትና የዴሞክራሲ ባህል መዳበሩን የሚያሳይ ነው ብለዋል።
የዘንድሮው የፖለቲካ ፓርቲዎች ቅስቀሳ፣ የምርጫ ቦርድ ዝግጅትና በዕለቱ የምርጫ ሂደት የታየው መነቃቃት የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋት ረገድ አዎንታዊ ሚና እንደነበረው ጠቅሰዋል።
የመገናኛ ብዙሃን እና የሲቪክ ማህበራት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ገልጸው፤ ጠቅላላ ውጤቱ ይፋ እስኪሆን መጠበቅ የሁሉም ፖለቲካ ፓርቲዎች እና የዜጎች ቀጥተኛ ኃላፊነት ነው ብለዋል።
ፓርቲዎች ውጤቱ ይፋ ሳይሆን ከመገመት ተቆጥበው ሂደቱን በትዕግስት መጠበቅ እስኪገለጽ መጠበቅ ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።
በውጤቱ ፓርቲ ሳይሆን ኢትዮጵያ ናት የምታሸንፈው ያሉት ባለሙያው፤ ፓርቲዎች ውጤቱን በፀጋ ተቀብለው በሀገር ልማት እና ግንባታ ላይ በንቃት መሳተፍ ይገባቸዋል ሲሉ ገልጸዋል።
የምርጫው በሰላም መጠናቀቅ ለሀገር ግንባታ ዋስትና መሆኑን ጠቅሰው፤ በህዝብ ድምፅ የበላይነት ያገኘው ፓርቲ ለሕዝብ የገባውን ቃል በታማኝነት የመፈጸም ኃላፊነት እንዳለበትም ጠቁመዋል።
ምርጫው የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ፣ ተዓማኒነትን ለመገንባት እና የኢትዮጵያን የሀገር ግንባታ ጉዞ ለማፅናት ትልቅ ስኬት መሆኑንም አንስተዋል።
በቅድስት ዘውዱ
የህግና ፌደራሊዝም ባለሞያ በላይ ወዲሻ
ከፋና ፖድካስት ጋር ያደረገውን ቆይታ ለመከታተል ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ https://youtu.be/jUX8tmYTs...

የምርጫው ሰላማዊነት የመተባበር ውጤት ነው - የክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊነት የመተባበር ውጤት ነው አለ።
የጋራ ምክር ቤቱ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሂደት በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል።
የምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ አብዱሰላም ሸንገል እንደገለጹት፤ የዘንድሮው ምርጫ ከዝግጅት ጀምሮ የተሻለ ሂደት አለው።
ምርጫው ያለምንም ችግር በሰላም መጠናቀቁ የሚያስደስት መሆኑን ገልጸው፤ በድምጽ መስጫ ዕለት ህብረተሰቡ ከማለዳ ጀምሮ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ድምጹን በመስጠት ያሳየው ጽናት የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል።
በክልሉ ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ለተወጡ ዜጎች፣ ለጸጥታ፣ ለፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ለሲቪክ ማኅበራት እና ለምርጫ አስፈጻሚዎች ምስጋና አቅርበው፤ የምርጫው ሰላማዊነት የመተባበር ውጤት መሆኑን ገልጸዋል።
የጋራ ምክር ቤቱ በሂደቱ ትኩረት ሰጥቶ የድርሻውን መወጣቱንም አንስተዋል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑክ በኢትዮጵያ ጁን 1 ቀን 2026 በተካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ያደረገውን ምልከታ መነሻ በማድረግ የመጀመሪያ ደረጃ መግለጫውን ጁን 3 ቀን 2026 በአዲስ አበባ ከተማ ይፋ አድርጓል።
ልዑኩ በቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የተመራ ሲሆን፣ በቀድሞው የናይጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄፍሪ ኦንያማ ደግሞ በምክትል ኃላፊነት ተደግፏል። ቡድኑ 61 በመቶ ሴቶችን ያካተተ 73 የአጭር ጊዜ ታዛቢዎችን የያዘ ሲሆን፣ ከ35 የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡት እነዚህ ታዛቢዎች አዲስ አበባ፣ ኦሮሚያ፣ ድሬዳዋ፣ ሲዳማ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ፣ ሐረሪ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ሶማሌን ጨምሮ በስምንት የኢትዮጵያ ክልሎች ስምሪት አድርገዋል። በአጠቃላይ 27 የታዛቢ ቡድኖች በ38 የምርጫ ክልሎች በሚገኙ 495 የምርጫ ጣቢያዎች ተዘዋውረው የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱን በቅርበት ታዝበዋል።
ከምርጫው በፊት የነበሩ ሁኔታዎችን በተመለከተ መግለጫው እንዳብራራው፣ ለምርጫው 54 በመቶ ወንዶች እና 46 በመቶ ሴቶችን ያካተተ 50.5 ሚሊዮን መራጮች የተመዘገቡ ሲሆን፣ ይህ አሃዝ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስቀምጦት ከነበረው የ40 ሚሊዮን መራጮች ግብ ብልጫ አሳይቷል። በምርጫው 47 የፖለቲካ ፓርቲዎች እና 73 በግል የገቡ ዕጩዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 10,934 ዕጩዎች የተወዳደሩ ቢሆንም፣ በጸጥታ ችግር ምክንያት በትግራይ ክልል እንዲሁም በአንዳንድ የኦሮሚያ እና የአማራ ክልል አካባቢዎች ምርጫው ሳይካሄድ ቀርቷል።
የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱን በተመለከተ ታዛቢ ልዑኩ እንዳረጋገጠው፣ 70 በመቶ የሚሆኑት የምርጫ ጣቢያዎች ልክ በጠዋቱ 06:00 በሰዓቱ ተከፍተዋል። በ99 በመቶ የምርጫ ጣቢያዎች የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ሰላማዊ በሆነ መንገድ የተካሄደ ሲሆን፣ በ97 በመቶ ጣቢያዎች ደግሞ የጸጥታ አካላት በስፍራው ተገኝተው ሙያዊ ሥነ-ምግባር በተላበሰ መልኩ ደህንነትን አስጠብቀዋል። ሆኖም ከምሽቱ 18:00 የድምጽ መስጫ ሰዓት መጠናቀቅ በኋላ 88 በመቶ በሚሆኑ ጣቢያዎች መራጮች አሁንም ተሰልፈው ስለነበር፣ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የድምጽ መስጫ ሰዓቱን እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ በ6 ሰዓታት እንዲራዘም አድርጓል።
የተፈናቃዮች እና የጸጥታ አካላት አባላት ልዩ የድምጽ አሰጣጥ ጁን 8 ቀን 2026 የሚካሄድ መሆኑን የጠቆመው መግለጫው፣ የመጨረሻው ይፋዊ የምርጫ ውጤት ጁን 11 ቀን 2026 ይገለጻል ተብሎ እንደሚጠበቅ አመላክቷል። በመጨረሻም የአፍሪካ ኅብረት ታዛቢ ልዑክ የኢትዮጵያ መንግሥት፣ የፖለቲካ ተዋንያን እና ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር እና ዴሞክራሲን ለማጎልበት ሁሉን አቀፍ እና ዘላቂ የፖለቲካ ውይይት እንዲያደርጉ በማበረታታት የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱን አጠቃልሏል።

በ130 ምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች መዝገብ ላይ ያልተገኙ እና ካርድ ያልያዙ መራጮች እንዲመርጡ መደረጋቸውን ኅብረት ለምርጫ ገለጸ
የኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ (CECOE / ኅብረት ለምርጫ) ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የተከናወነውን 7ኛውን ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ አስመልክቶ ዛሬ ረቡዕ ባወጣው የመጀመሪያ ደረጃ የትዝብት ሪፖርቱ፣ በ130 ምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች መዝገብ ላይ ያልተገኙ እና ካርድ ያልያዙ፣ በእያንዳንዱ ጣቢያ ከአንድ እስከ 10 የሚሆኑ መራጮች እንዲመርጡ መደረጋቸውን ገለጸ።
እንዲሁም በስምንት የድምጽ መስጫ ጣቢያዎች ደግሞ ከ10 በላይ ሰዎች ስማቸው በመራጮች መዝገብ ላይ ሳይገኝ እና የመራጭነት ካርድ ሳይዙ እንዲመርጡ መፈቀዱንም ኅብረቱ በምርጫ ትዝብት ጊዜያዊ ሪፖርቱ ላይ አስታውቋል።
ኅብረቱ ከታዘባቸው 2,506 የምርጫ ጣቢያዎች መካከል በ2,458 ጣቢያዎች ስማቸው በመራጮች መዝገብ ላይ ሰፍሮ ድምጽ መስጠት የተከለከለ ሰው እንዳልነበር መታዘቡን ጠቅሷል፤ ይሁንና በ46 የድምጽ መስጫ ጣቢያዎች ከ1 እስከ 10 ግለሰቦች ስማቸው በመራጮች መዝገብ ላይ ሰፍሮ ድምጽ መስጠት መከልከላቸው ተገልጿል።
በሁለት ድምጽ መስጫ ጣቢያዎች ደግሞ ከ10 በላይ ሰዎች ስማቸው በመራጮች መዝገብ ላይ ሰፍሮ ድምጽ መስጠት መከልከላቸውን የኅብረቱ ሰብሳቢ ተናግረዋል።
Via ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

የኢጋድና የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ትዝብት ሪፖርታቸውን ዛሬ ረፋድ በቀጥታ ስርጭት ለዓለም ይፋ አድርገዋል። የኢጋድና አፍሪካ ኅብረትን ታዛቢነት እውቅና እሰጣለሁ ያለው የአውሮፓ ኅብረትም አዲስ መግለጫ ይዞ ብቅ ብሏል። #ethiopia #generalelection #igad #au
" target="_blank" class="inline-link">https://new-en.yenevibe.co...
" target="_blank" class="inline-link">https://new-en.yenevibe.co...
2 days ago
በኢትዮጵያ የአውሮጳ ኅብረት ልዑክ እና በአዲስ አበባ የሚገኙ የኅብረቱ አባል አገራት ኤምባሲዎች ስለ ሰባተኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ያወጡት መግለጫ
በኢትዮጵያ የአውሮጳ ኅብረት ልዑክ እና በአዲስ አበባ የሚገኙ የኅብረቱ አባል አገራት ኤምባሲዎች ግንቦት 24 ቀን 2018 ምርጫ ያልተካሔደባቸው የምርጫ ክልሎች ድምጽ የመስጠት “ዕድል ይሰጣቸዋል” የሚል ተስፋ እንዳላቸው አስታወቁ።
በኢትዮጵያ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ምርጫ መካሄዱን በበጎ እንደሚቀበሉ የኅብረቱ ተልዕኮ መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ካደረጉ 25 ኤምባሲዎች ጋር በጋራ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
ምርጫው በተካሔደ በሁለተኛው ቀን ዛሬ ረቡዕ መግለጫውን ከኅብረቱ ጋር ካወጡ የአውሮፓ ኅብረት አባል አገራት ኤምባሲዎች መካከል የጀርመን እና የፈረንሳይ የዲፕሎማሲ ተልዕኮዎች ይገኙበታል። የአውሮፓ ኅብረት አባል አገር ያልሆኑት ካናዳ፣ ኖርዌይ እና ስዊትዘርላንድም ምርጫን በተመለከተ በመግለጫው አቋማቸውን ካንጸባረቁ መካከል ናቸው።
በመግለጫው “የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የምርጫ ሠራተኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ዕጩዎች እና የሲቪል ማኅበራት ተዋናዮች ያበረከቱትን አስተዋጽዖ እናደንቃለን” ብለዋል።
የአፍሪካ ኅብረት እና የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) እንደ ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ያላቸውን ጠቃሚ ሚና እንገነዘባለን ያለው የጋራ መግለጫው ዘገባዎቻቸውን በጉጉት እንደሚጠብቅም አስታውቋል።
ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ምርጫ ማካሄድ ያልቻሉ የምርጫ ክልሎች በሙሉ ይህን ለማድረግ እድሉ እንደሚሰጣቸው ተስፋ እናደርጋለን ሲል በኢትዮጵያ የኅብረቱ ልዑካንና የኅብረቱ አባል ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮዎች የጋራ መግለጫ አስታውቋል።
DW Amharic

የምርጫ ቦርድ ይፋዊ መግለጫ እስከሚሰጥ ድረስ ማንኛውም አካል ራሱን አሸናፊ አድርጎ ከመግለጽ ይቆጠብ":-ኢሰመጉ‼️
ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ባወጣው የምርጫ መታዘብ ቅድመ መግለጫ ላይ ያነሳቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦
ጥብቅ ማሳሰቢያ፦የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ (NEBE) ይፋዊ መግለጫ እስከሚሰጥ ድረስ ማንኛውም ግለሰብ፣ የፖለቲካ ድርጅት ወይም የማኅበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ጊዜያዊ ውጤት በማጋራት ማኅበረሰቡን ከማደናገር እንዲቆጠቡ አሳስቧል።
የምልከታ ስፋት፦ኢሰመጉ ባሰማራቸው 433 ታዛቢዎች አማካኝነት ከ800 በላይ የምርጫ ጣቢያዎችን ተከታትሏል።
⚠️ የተስተዋሉ ዋና ዋና ተግዳሮቶች፦
* የአዲሱ ዲጂታል የመራጮች ምዝገባ ሥልት መጀመሩ የሚበረታታ ቢሆንም፣ የአስፈጻሚዎች ሥልጠና ማነስ ለመራጮች መጨናነቅና ለሰዓት መራዘም ምክንያት ሆኗል።
* በበርካታ አካባቢዎች የትራንስፖርት መቋረጥ፣ በአዲስ አበባ የሰልፍ አስተባባሪዎች ማነስ እና በመራጮች ላይ የደረሰ የእንግልት ሰዓት።
* በሐዋሳና አካባቢው በሚገኙ ውስን ጣቢያዎች የምርጫ አስፈጻሚዎች በሚስጥራዊ ድምፅ መስጫ ቦታ በመግባት የሥነ-ልቦና ጫና ማድረጋቸው እና ያልተመረጡ ወረቀቶችን ወደ ሳጥን ማስገባት የመሳሰሉ የነፃነት መብትን የገደቡ ክስተቶች መታየታቸው።
✅ በበጎ ጎን የተነሱ ነጥቦች፦
* የመራጮች ከፍተኛ ተነሳሽነት፣ በቂ የቁሳቁስ አቅርቦት እና በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች የጎላ የጸጥታ መደፍረስ ሳይኖር ሂደቱ መጠናቀቁ።
"ኢሰመጉ ምርጫ ቦርድ በአንጻራዊነት ስኬታማና ሰላማዊ ምርጫ ማከናወኑን በመግለጽ ዕውቅና የሰጠ ሲሆን፣ በቀጣይ ግን የተስተዋሉ ችግሮችን በዝርዝር ለይቶ እንዲያርም ጥሪ አቅርቧል።"

የአውሮፓ ኅብረት እና አጋር ሀገራት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሂደት አደነቁ
**************
የአውሮፓ ኅብረት አባል ሀገራት፣ ካናዳ፣ ኖርዌይ እና ስዊዘርላንድ በጋራ ባወጡት መግለጫ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አድንቀዋል።
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ለፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ለእጩዎች እና ለሲቪል ማኅበራት ለምርጫው ስኬት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እንዲሁም ለአፍሪካ ኅብረት እና ለኢጋድ የምርጫ ታዛቢነት ሚና እውቅና ሰጥተዋል።
#ebc #ethiopia #democracy #peace #democraticrights

የአውሮፓ ኅብረትና አጋር ሀገራት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሒደት አደነቁ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአውሮፓ ኅብረት እና አጋር ሀገራት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አድንቋል፡፡
ምርጫውን አስመልክቶ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ የኅብረቱ አባል ሀገራትና በኢትዮጵያ የካናዳ፣ የኖርዌይ እና ስዊዘርላንድ ኤምባሲዎች የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡
ሀገራቱ በመግለጫቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ እጩዎችና የሲቪል ተቋማት ጠቅላላ ምርጫው በስኬት እንዲካሄድ ያደረጉትን አስተዋጽኦ አድንቀዋል፡፡
የአፍሪካ ኅብረት እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) በምርጫው ላይ ለነበራቸው የታዛቢነት ሚና እውቅና እንደሚሰጡም ሀገራቱ አረጋግጠዋል፡፡
#ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያመርጣለች #በምርጫብቻ #ፋናዲጂታል #election #fanadigital #ethiopia #ethiopiavoted #democracy #fanatelevision

3 days ago
የተገለጠው እውነታ
በ ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ
በምሥራቃዊው ኢትዮጵያ ይልቁንም በሐረር፣ አርሲና ባሌ አካባቢዎች ላይ ትኩረት አድርጎና አቅዶ ክርስቲያኖችን የሚገድል፣ የሚያፈናቅል እና የሚያሳድድ የአክራሪ ክንፍ መኖሩ ተደጋግሞ ሲነገር ኖሯል። ይህ አካል ደርግ ወድቆ ኢህአዴግ ከተተካበት ጊዜ ጀምሮ ማንኛዋንም የለውጥ፣ የምርጫ እና የመሳሰሉትን የጫና ወቅቶች ጠብቆ አደጋ ያላደረሰበት ጊዜ የለም።
ከተቻለ የመንግሥት መዋቅርን በመጠቀምና በየዘመኑ ያለውን የፖለቲካ ትኩሳት እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም እና ለሚገድላቸው አካላት ከወቅቱ ፖለቲካ አንጻር የሚስማማ ታርጋ በመስጠት የሚቻለውን ያህል ይገድላል፣ ያፈናቅላል፣ ያሳድዳል።
ይህ የተገለጠ እውነት ነው። ተደጋግሞም ተነግሯል፣ ተገልጿል። ሆኖም እንደዚህ ዘመን እንደ ልቡ ክርስቲያኖችን የሚያጸዳበት ስለመኖሩ ግን አላውቅም። በእኔ እምነት ኢህአዴግ ከመጣበት ጀምሮ የተፈጸሙት ተደምረው በዚህ ዓመት ብቻ የፈጸመውን የመግደልና የማሳደድ ተግባር የሚያክሉ አይመስለኝም። ይህ ሁሉ ሲሆን አንድም መንግሥታዊ ተቋም ሐዘኔታ ሲያሳዩ፣ አንድም አካል ተጠያቂ ሲደረግ ዓይተንም ሰምተንም አናውቅም።
ይህም የተገለጠ እውነት ነው።
ምንም ቢሆን፣ ማንም ቢሆኑ ይህ ሁሉ መከራ የሚደርስባቸው ሰዎች ደግሞም ዜጎች ነበሩ። በደቡብ አፍሪካ ላለው ከሀገራችን ውጡ የሚል ዐመጽ ዜጎቹን ለመከላከል መንግሥት በኢንባሲው በኩል እየሠራ እንደሆነ የሚገልጽ ዜና ከሰማንና ለዚህኛው መንግሥት በዝምታ የሚያልፍ ከሆነ ድርጊቱን የሚፈጽመው እርሱም ጭምር ነው የሚለውን ወቀሳ እውነት ነው ብሎ በአዎንታ እንደተቀበለው ለመረዳት ግዴታችን ጭምር ይሆናል። ይህ በእውነት ከልብ ያሳዝናል።
አንድ የተረጋገጠና የትገለጠ እውነት ደግሞ አለ። የሰው ደም በከንቱ ፈስሶ አይቀርም። እግዚአብሔር የሚባል ተበቃይ አምላክ አለና። ለንስሐ ጊዜ ቢሰጥም "በቀል የእኔ ነው" ያለውና "ከኦሪትና ከነቢያት አንዲት ቃል ከምታልፍ ሰማይና ምድር ቢያልፍ ይቀላል" ያለው አምላክ ቃሉ የታመነ ነውና አይቀርም። እርሱ ሁላችንንም ይቅር ይበለን፣ የመከራውንም ወቅት አሳልፎ ለሰላምና ለፍቅር ያብቃን።

በካርዳችን ያጸናናትን ሀገር በአንድነታችን እንገንባት
*****************
( የዕለቱ መልዕክት)
የአንድ ሀገር ህልውና እና ጥንካሬ መሰረቱ የህዝቡ አንድነት፤ ትብብርና ቁርጠኝነት ነው። ሰኞ ዕለት መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ያሳየው ታሪካዊ ተሳትፎ የዚሁ እውነት ህያው ማረጋገጫ ነው።
የራሳቸውን ፍላጎት በራሳቸው ለመወሰን፣ የወደፊት የ5 ዓመት እጣ ፈንታቸውን በራሳቸዉ እጅ ለመጻፍ ከ54 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን በነቂስ ወጥተው ድምጻቸውን ሰጥተዋል።
ይህ ቁጥር ዝም ብሎ ስታቲስቲክስ ሳይሆን የህዝባችንን ፍጹም መነሳሳትና ለሀገረ መንግስት ግንባታ ያለውን ጽኑ አቋም ፍንትው አድርጎ ያሳየ ታላቅ ኩራት ነው።
ከወዲያ ማዶ ሆኖ ማውራት ለነጋሪው ቀላል ነው፤ እንደሚባለው ሀገርን ማቅናትና ዲሞክራሲን መገንባት በወሬ ሳይሆን በተግባርና በጽናት የሚገኝ መሆኑን መራጩ ህዝብ በግልጽ አስመስክሯል።
ማለዳው ገና ሳይቀድ፣ ንጋቱ ሳይተካ ጀምሮ በየምርጫ ጣቢያው የተሰለፈው ህዝብ ያሳየው ትዕግስት የሚደነቅ ነው። የጠዋቱ ቅዝቃዜና ብርድ፣ የቀትሩ አስገዳጅ ጸሀይም ሆነ ከባዱ ዝናብ ሳይበግረው፤ ረጃጅም ሰልፎችንና የአካል ድካምን ተቋቁሞ ከሌሊት እስከ ሌሊት የቆመው ለራሱ ጥቅም ብቻ አልነበረም።
ይልቁንም፣ "የቆረጠ አይመለስም" እንደሚባለው የነገዋን ኢትዮጵያ ለማጽናት፣ ጠንካራና የማይናወጥ ሀገረ መንግስት ለመገንባት ባለው ጽኑ ህልም እንጂ።
ይህ ጽናት ህዝቡ የሀገር ጉዳይ ከምንም ነገር እንደሚቀድም ብሄራዊ ጥቅም እና ሉዓላዊነት የሚከበሩት ደግሞ በዜጎች ንቁ ተሳትፎ መሆኑን ያሳየበት የታሪክ አሻራ ነው።
ህዝቡ ፍላጎቱን በምርጫ ካርዱ መግለጹ የዲሞክራሲ ባህላችን ከቃል ባለፈ ወደ ተግባር እየተሸጋገረ ለመምጣቱ ትልቅ ማሳያ ነው። "ስልጣን የህዝብ ነው" የሚለው መርህ መሬት የረገጠው፣ ዜጎች ያለ ምንም ስጋትና በከፍተኛ ተነሳሽነት መብታቸውን ሲጠቀሙ ነው።
በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የታየው ታሪካዊ ክስተት ኢትዮጵያ መምረጧን ብቻ ሳይሆን በልጆቿ ጽናት መጽናቷንና ወደፊት መራመዷን ጭምር ያበሰረ ነው።
አሁን የምርጫው ውጤት እስኪገለጽ ድረስ ባለው ወቅት፣ ሁላችንም ልባችንን ሰብስበን፣ የተጀመረውን የሰላምና የዲሞክራሲ ጉዞ ማገዝ ይኖርብናል። ምክንያቱም "በአንድ እጅ አያጨበጭቡም" እና ሀገርን የመስራት፣ ተቋማትን የማጠንከርና ሰላምን የማስፈን ኃላፊነት የሁላችንም የጋራ የቤት ስራ ነው።
የህዝብ ስልጣን ባለቤትነት የሚረጋገጠው በዚህ መልኩ በካርድ በሚሰጥ ድምጽ እና በሚታይ ቁርጠኝነት ነው። ትናንት የፈሰሰው ድካምና መስዋዕትነት፣ ዛሬ ለምናየው የነጻነት አየር መሰረት ሆኗል። ህዝባችን ያሳየው ታላቅ የሀገር ፍቅር የነገዋን የበለጸገች ኢትዮጵያ ለመገንባት መተኪያ የሌለው የሞራል ስንቅ ነው።
አሁን ኑ፣ እጅ ለእጅ ተያይዘን፣ በምርጫ ካርዳችን ያጸናናትን ሀገር በስራችንና በአንድነታችን እንገንባት።
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጽናትና ፍቅር ለዘላለም ትኑር!
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል

ሰላም! እንደምን አደራችሁ?
ለቀጣይ አምስት ዓመታት የሚመራቸውን መንግሥት ለመምረጥ ኢትዮጵያውያን ግንቦት 24 ቀን ከማለዳ ጀምሮ እስከ ሌሊት ድምፃቸውን ሰጥተዋል።
ዜጎች በየአካባቢው በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ድምፅ የሰጡበት ይህ ሂደት÷ ኢትዮጵያውያን ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታና ለሀገረ መንግሥት ምስረታ ያላቸውን ፅኑ ቁርጠኝነት በተግባር ያሳዩበት ሆኖ አልፏል።
በሚሊየን የሚቆጠሩ መራጮች በነቂስ ወጥተው ዝናብና ጸሐይን እንዲሁም ከተለያዩ አካላት የሚነዙ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻዎችንና ዛቻዎችን ሳያዳምጡ በረጃጅም ሰልፎች ተሰልፈው ውሳኔያቸውን አስተላልፈዋል።
በሕመም አልጋ ላይ የነበሩ ከሕመማቸው ጋር እየታገሉ፣ ሐዘን የገጠማቸውም ከሐዘናቸው ተነስተው በመውጣት ለነጋቸው የሚበጀውን ድምፅ የሰጡበት ዕለት ነው ግንቦት 24።
በዚህ ታሪካዊ ሂደት ላይ ለመሳተፍ በሚያስችል ዕድሜ ላይ የሚገኙ ከ54 ሚሊየን በላይ ዜጎች ተመዝግበው ከ10 ሺህ በላይ የፖለቲካ ፓርቲ ዕጩዎችና 80 የግል ዕጩዎች በተወዳደሩበት ምርጫ ድምጻቸውን በመስጠት ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል።
የምርጫውን ግልጽነት፣ አሳታፊነትና ተዓማኒነት ከፍ ለማድረግ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉ ሲሆን÷ ከእነዚህም መካከል ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ወሳኝ ሚና ያላቸውና ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፈቃድ ያገኙ 68 የመገናኛ ብዙኃን ተሰማርተዋል፤ ከእነዚህ ውስጥ 12ቱ የውጭ መገናኛ ብዙኃን ናቸው።
በተጨማሪም ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የድምፅ አሰጣጥና የውጤት ቆጠራ ሂደቱን በቅርበት ለመከታተል ከ250 ሺህ በላይ ተወካዮቻቸውን በየምርጫ ጣቢያዎቹ መድበዋል።
በሌላ በኩል የኬንያ ቀድሞ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሚመራውና 59 አባላትን የያዘው የአፍሪካ ሕብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን እንዲሁም 26 አባላትን ያሰማራው የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በመሰማራት ሂደቱን በንቃት ታዝበዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ በሰጡት መግለጫ÷ የምርጫው ድምፅ የመስጠት ሂደት በስኬት መጠናቀቁንና በየምርጫ ጣቢያዎቹ የምርጫ ውጤቶችን ለሕዝብ የመለጠፍ ሥራዎች በይፋ መከናወናቸውን አረጋግጠዋል።
ይህም ኢትዮጵያ የራሷን ዕድል ለመወሰን መካሪና ገሳጭ እንደማያስፈልጋት በድጋሚ ያሳየበት ነው።
በድምፅ መስጫው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከመራጩ ሕዝብ በላይ የተመራጮች ጉዳይና ኃላፊነት ይበልጥ እንደሚያሳስባቸው መግለጻቸው ይታወሳል።
በመሆኑም ሕዝብ ያሳየውን ፅኑ እምነትና የዴሞክራሲ ፍላጎት ሳይሸረሽር፣ በታማኝነትና በንጹሕ ልብ ማገልገል የነገው መንግሥት ቀዳሚ የቤት ሥራ እንደሚሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አጽንዖት ሰጥተዋል።
የሕዝቡን ሕይወት የሚነካና የሀገሪቱን የነገ ዕጣ ፈንታ የሚወስን እውነተኛ ለውጥ ማምጣት የሚቻለውም ተመራጮች የተጣለባቸውን ታሪካዊ ኃላፊነት በትክክል ተረድተው ሲሰናዱ ብቻ በመሆኑ የኢትዮጵያ ቀጣይ አምስት ዓመታት ጉዞ በዚሁ የተመራጮች የዝግጁነት ሚዛን ላይ የሚያርፍ ይሆናል።
ኢትዮጵያ መርጣለች፤ ኢትዮጵያ አሸንፋለች!!

የሕዝብ ጽናት፦ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የስኬት ምስጢር
*****************
በኢትዮጵያ የዴሞክራሲያዊ ተቋማት ግንባታና ተዓማኒነትን ለማረጋገጥ የተከናወነው ተግባር ተጨባጭ ፍሬ እያፈራ መሆኑን የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሂደት በተግባር አሳይቷል።
በምርጫው ዕለት የኢትዮጵያ ሕዝብ ድምፁ እንዳይባክን እና ሉዓላዊ መብቱን ለመጠቀም ያሳየው ጽናት፣ ብስለት እና ቁርጠኝነት ሀገሩን ለማጽናት የከፈለው ታላቅ የዜግነት መስዋዕትነት ሆኖ ተመዝግቧል።
በምርጫው ዕለት ሕዝባችን ቁር ሳይበግረው ጎሕ ከመቅደዱ፣ የምርጫ ጣቢያዎችም ከመከፈታቸው በፊት በየምድብ ስፍራው በመድረስና ረጃጅም ሰልፎችን በመታገስ ጽናቱን አሳይቷል።
እናቶች፣ አባቶች፣ ወጣቶችና አካል ጉዳተኞችን ጨምሮ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች የመራጭነት ካርዳቸውን በመያዝ በየምርጫ ጣቢያዎቻቸው በማለዳ ደርሰዋል።
ዜጎች ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ለመጠቀምና የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣት ያደረጉት ኃላፊነት የተሞላበት እንቅስቃሴና ያሳዩት ጽናት እጅግ የሚያስደንቅ ነበር።
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ስምሪት የተሰጣቸው አስመራጮች፣ ታዛቢዎችና የጸጥታ አካላትም አስቀድመው በየምድብ ጣቢያዋቻቸው በመገኘት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ተወጥተዋል።
የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ምሽት 12 ሰዓት ላይ መጠናቀቅ የነበረበት ቢሆንም፣ በነበረው ከፍተኛ የመራጮች ቁጥርና የሂደት መጓተት ችግር ምክንያት በምርጫ ቦርድ ውሳኔ ሂደቱ እስከ እኩለ ሌሊትና ከዚያም በላይ እንዲራዘም ተደርጓል።
ይህን ተከትሎም ምርጫው በስኬት የተጠናቀቀ ሲሆን፣ ይህም ሀገራችን ማንኛውንም ታላቅ ሁነት በብቃት ማካሄድ እንደምትችል ዳግም ያረጋገጠችበት ሆኗል።
ይህም ሕዝባችን ምርጫ ተራ ሁነት ሳይሆን፣ የሀገርን እጣ ፈንታ መወሰኛ ታላቅ ዕድል መሆኑን በተግባር ያሳየበት ነው።
በአጠቃላይ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሕዝባችን ያሳየው የፖለቲካ ብስለትና ጽናት፣ የሰላም እና የሀገር ወዳድነቱ መገለጫ ነው።
አዎ፣ ምርጫው ሕዝባችን ለነገዋ ኢትዮጵያ ጠንካራ የዴሞክራሲ መሠረት ለመጣል ያለውን የላቀ ፍላጎት በግልጽ ያሳየበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው።
በመሐመድ ፊጣሞ
#ኢትዮጵያ_መርጣለች #ኢትዮጵያ_አሸንፋለች

Comments