Logo
FBC
የምርጫው ሰላማዊነት የመተባበር ውጤት ነው - የክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊነት የመተባበር ውጤት ነው አለ።

የጋራ ምክር ቤቱ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሂደት በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል።

‎የምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ አብዱሰላም ሸንገል እንደገለጹት፤ የዘንድሮው ምርጫ ከዝግጅት ጀምሮ የተሻለ ሂደት አለው።

‎ምርጫው ያለምንም ችግር በሰላም መጠናቀቁ የሚያስደስት መሆኑን ገልጸው፤ በድምጽ መስጫ ዕለት ህብረተሰቡ ከማለዳ ጀምሮ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ድምጹን በመስጠት ያሳየው ጽናት የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል።

‎በክልሉ ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ለተወጡ ዜጎች፣ ለጸጥታ፣ ለፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ለሲቪክ ማኅበራት እና ለምርጫ አስፈጻሚዎች ምስጋና አቅርበው፤ የምርጫው ሰላማዊነት የመተባበር ውጤት መሆኑን ገልጸዋል።

‎የጋራ ምክር ቤቱ በሂደቱ ትኩረት ሰጥቶ የድርሻውን መወጣቱንም አንስተዋል።

15 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.