5 months ago
350 ሺህ ዶላር :
ኸርት ቱ ኸርት ቺልድረንስ ኤይድ በዋሽንግተን ዲሲ አሰባሰበ
የኸርት ቱ ኸርት ቺልድረንስ ኤይድ ትላንት መጋቢት 12 ቀን 2018 ዓ.ም. በዋሽንግተን ዲሲ ማርዮት ሆቴል ባከናወነው የማጠቃለያ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር 350 ሺህ ዶላር በማግኘት በታላቅ ስኬት መጠናቀቁን የድርጅቱ መሥራችና የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ብርሃን ተድላ አስታውቀዋል።
እስካሁን 110 ሺህ ዶላር በቀጥታ በባንክ ገቢ የተደረገ ሲሆን፣ ቀሪው ቃል የተገባና በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚሰበሰብ ነው።
በተገኘው ገንዘብ በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ በወረፋ ላይ ለሚገኙ 120 ሕፃናት የልብ ቀዶ ጥገና ሕክምና ለመስጠት ዕቅድ ተይዟል።
ከጣሊያን ከመጡ ሦስት ድርጅቶች ጋር በመተባበር 50 ተጨማሪ ሕፃናትን ለማከም ዝግጅት እየተጠናቀቀ ነው። ይህም በቅርብ ወራት ውስጥ ሕክምና የሚያገኙ ሕፃናትን ቁጥር 170 ያደርሰዋል።
በቀጣይ አንድ ዓመት ውስጥ በአራት የሀገሪቱ አካባቢዎች በሚገኙ የመንግሥት ሆስፒታሎች የልብ ቀዶ ጥገና ማዕከላትን ለማቋቋም ታቅዶ እየተሠራ ይገኛል።
ለዝግጅቱ ስኬት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉት የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ወጣት አዶናይ ብርሃነ፣ ወይዘሮ ሐና ክብሩና ባለቤታቸው ሳሚ የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በዝግጅቱ ላይ የዋሽንግተን ዲሲ እጩ ከንቲባ ሚስተር ኬኒየን ማክደፊ፣ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል እና ሊቀ ማዕምራን ፕሮፌሰር ዘበነ ለማን ጨምሮ በርካታ እንግዶች ተገኝተዋል።
አቶ ብርሃን ተድላ ኢትዮጵያውያን የልብ ቀዶ ጥገና ባለሙያዎች አዲስ የሚቋቋመውን የባለሙያዎች ቡድን እንዲቀላቀሉና ወገኖቻቸውን እንዲረዱ ጥሪ አቅርበዋል።
#getu #ethiopiannews #hearttoheart #childrenshealth #fundraising #washingtondc #ethiopiandiaspora #heartsurgery #charity #የልብሕሙማን #ሰብአዊነት #ዋሽንግተንዲሲ #ኢትዮጵያ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

❤️ አዶናይ ለታላቅ ሰብዓዊ ተግባር ወደ አሜሪካ ተጓዘ
#ethiopia | የኸርት ቱ ኸርት ቺልድረንስ ኤይድ ፋውንዴሽን (Heart to Heart Children's Aid) የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ወጣት አዶናይ ብርሃነ፣ የልብ ሕሙማን ሕፃናትን ሕይወት ለመታደግ የሚያስችል ገቢ ለማሰባሰብ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ አቅንቷል።
የፋውንዴሽኑ መሥራችና የኢትዮ ኢስታንቡል ሆስፒታል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ብርሃን ተድላ እንደገለጹት፣ መርሃ-ግብሩ በሚከተለው መልኩ ይከናወናል፦
* የጅማሮ ቻሌንጅ፦
ነገ ቅዳሜ ማርች 14 (መጋቢት 5/2018 ዓ.ም) ከቀኑ 2:00 PM ጀምሮ የገቢ ማሰባሰቢያ ቻሌንጅ በይፋ ይጀምራል።
* የማጠቃለያ ፕሮግራም፦
ማርች 21 (መጋቢት 12/2018 ዓ.ም) በዋሽንግተን ዲሲ ማርዮት ሆቴል በሚከናወን ታላቅ ዝግጅት ይጠናቀቃል።
ጥሪ፦
በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ሕፃናቱ የሕክምና ዕድል እንዲያገኙ የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።
የኢትዮ ኢስታንቡል ሆስፒታል አስተዋጽኦ
ሆስፒታሉ እስካሁን ባለው ቆይታው የሚከተሉትን ተግባራት አከናውኗል፦
* ለ113 ሕፃናት ነፃ የልብ ቀዶ ጥገና አድርጓል።
* ለዚህም ከ120 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ አድርጓል።
* ይህ ሥራ በአንድ ተቋም ብቻ የማይገፋ በመሆኑ፣ በፋውንዴሽኑ በኩል የወገን ድጋፍ ማሰባሰብ አስፈላጊ ሆኗል።
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ ከ25 ሺህ በላይ የልብ ሕሙማን ሕፃናት የሕክምና ዕድል ለማግኘት በተስፋ በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ። የወጣት አዶናይ ጉዞና የፋውንዴሽኑ ጥረት የእነዚህን ሕፃናት ተስፋ ለማለምለም ያለመ ነው።
የሕፃናትን ልብ በጋራ እንታደግ!
#hearttoheart #የልብሕሙማን #አዶናይብርሃነ #ኢትዮኢስታንቡል #ሰብዓዊነት #ኢትዮጵያ #humanitarian #heartsurgery #ethiopia #getu #temesgen #getutemesgen #ጌጡ #ተመስገን #ጌጡተመስገን

Comments