Logo
Getu Temesgen
350 ሺህ ዶላር :
ኸርት ቱ ኸርት ቺልድረንስ ኤይድ በዋሽንግተን ዲሲ አሰባሰበ

​የኸርት ቱ ኸርት ቺልድረንስ ኤይድ ትላንት መጋቢት 12 ቀን 2018 ዓ.ም. በዋሽንግተን ዲሲ ማርዮት ሆቴል ባከናወነው የማጠቃለያ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር 350 ሺህ ዶላር በማግኘት በታላቅ ስኬት መጠናቀቁን የድርጅቱ መሥራችና የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ብርሃን ተድላ አስታውቀዋል።

​ እስካሁን 110 ሺህ ዶላር በቀጥታ በባንክ ገቢ የተደረገ ሲሆን፣ ቀሪው ቃል የተገባና በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚሰበሰብ ነው።

​ በተገኘው ገንዘብ በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ በወረፋ ላይ ለሚገኙ 120 ሕፃናት የልብ ቀዶ ጥገና ሕክምና ለመስጠት ዕቅድ ተይዟል።

​ ከጣሊያን ከመጡ ሦስት ድርጅቶች ጋር በመተባበር 50 ተጨማሪ ሕፃናትን ለማከም ዝግጅት እየተጠናቀቀ ነው። ይህም በቅርብ ወራት ውስጥ ሕክምና የሚያገኙ ሕፃናትን ቁጥር 170 ያደርሰዋል።

​በቀጣይ አንድ ዓመት ውስጥ በአራት የሀገሪቱ አካባቢዎች በሚገኙ የመንግሥት ሆስፒታሎች የልብ ቀዶ ጥገና ማዕከላትን ለማቋቋም ታቅዶ እየተሠራ ይገኛል።

​ለዝግጅቱ ስኬት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉት የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ወጣት አዶናይ ብርሃነ፣ ወይዘሮ ሐና ክብሩና ባለቤታቸው ሳሚ የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በዝግጅቱ ላይ የዋሽንግተን ዲሲ እጩ ከንቲባ ሚስተር ኬኒየን ማክደፊ፣ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል እና ሊቀ ማዕምራን ፕሮፌሰር ዘበነ ለማን ጨምሮ በርካታ እንግዶች ተገኝተዋል።

​አቶ ብርሃን ተድላ ኢትዮጵያውያን የልብ ቀዶ ጥገና ባለሙያዎች አዲስ የሚቋቋመውን የባለሙያዎች ቡድን እንዲቀላቀሉና ወገኖቻቸውን እንዲረዱ ጥሪ አቅርበዋል።

​#getu #ethiopiannews #hearttoheart #childrenshealth #fundraising #washingtondc #ethiopiandiaspora #heartsurgery #charity #የልብሕሙማን #ሰብአዊነት #ዋሽንግተንዲሲ #ኢትዮጵያ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.