8 days ago
"ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ሳትገዛም ድሃ ናት፤ በፈረንሳይ የተገዛችው ቬትናም ግን ዛሬ በልጽጋለች"
📌ቁጣን የቀሰቀሰው የ x ገጽ ልጥፍ
#ethiopia | የዓለማችን ቢሊየነር ኢሎን ማስክ እና ሴኔጋላዊቷ ስራ ፈጣሪ ማጋቴ ዋድ ሰሞኑን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ያራገቡት አወዛጋቢ ትርክት፣ በአፍሪካውያን እና በታሪክ ምሁራን ዘንድ ትልቅ ቁጣን ቀስቅሷል። ማጋቴ ዋድ "ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ሳትገዛም ድሃ ናት፤ በፈረንሳይ የተገዛችው ቬትናም ግን ዛሬ በልጽጋለች" በማለት የቅኝ ግዛትን አስከፊ ታሪክ ለማቃለል የሞከረች ሲሆን፣ ኢሎን ማስክም ለዚህ ታሪካዊ ስህተት አጋርነቱን አሳይቷል። ይሁን እንጂ ይህ መከራከሪያ ሆን ተብሎ የተመረጡ መረጃዎችን ብቻ በመጠቀም የተነዛ፣ ሚዛናዊነት የጎደለው እና የጥቁር ሕዝቦችን የነጻነት ተምሳሌት የሆነችውን ኢትዮጵያን ክብረ-ታሪክ ያጣጣለ ትልቅ የታሪክ ክህደት ነው።
የማጋቴ ዋድ ትልቁ የታሪክ ስህተት እና ማጭበርበር የሚጋለጠው፣ በእሷው አመክንዮ ውስጥ ያሉትን ግልጽ ተቃርኖዎች ስንመለከት ነው። ቬትናምን እንደ ብቸኛ የስኬት ማሳያ አድርጋ ስታቀርብ፣ ልክ እንደ ቬትናም በፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ስር የነበሩ ነገር ግን ዛሬም ድረስ ከኢትዮጵያ በታች በሆነ የድህነት አዘቅት ውስጥ የሚገኙትን በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ሆን ብላ ዘንግታዋለች።
ኒጀር፣ የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ቻድ፣ ማዳጋስካር እና ቡርኪና ፋሶን የመሳሰሉ ሀገራት ለዘመናት በፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ስር ቆይተዋል። ይሁን እንጂ ዛሬ ላይ በነፍስ ወከፍ ገቢያቸውም (GDP per capita) ሆነ በሰብዓዊ ልማት ጠቋሚያቸው (HDI) ከኢትዮጵያ በእጅጉ ያነሱ እና በዓለም መጨረሻ ላይ የሚገኙ ናቸው። ቅኝ ግዛት የብልጽግና እና የሰለጠነ መዋቅር ምንጭ ቢሆን ኖሮ፣ እነዚህ የፈረንሳይ ቅኝ ግዛቶች ዛሬ ለምን የዓለም አቀፍ የድህነት መለኪያ ሆኑ? አሁንም ድረስ ፈረንሳይ በዘረጋችው የኒዮ-ኮሎኒያሊዝም መዋቅር (በተለይም በCFA ፍራንክ የገንዘብ ሥርዓት) የራሳቸውን ሀብት ማስተዳደር አቅቷቸው በከፍተኛ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ውስጥ ይገኛሉ። ይህ ሐቅ "ቅኝ ግዛት የድህነት ምክንያት አይደለም" የሚለውን የማጋቴን መከራከሪያ ከመሠረቱ የሚያፈርስ ነው።
ቬትናም ዛሬ ላለችበት የኢኮኖሚ ከፍታ የበቃችው በፈረንሳይ ቅኝ ግዛት በረከት ሳይሆን፣ እንዲያውም የፈረንሳይን እና የአሜሪካን አውዳሚ ጦርነቶች በከፍተኛ መስዋዕትነት አሸንፋ ከወጣች በኋላ ነው። ሀገሪቱ ከጦርነቱ ፍርስራሽ ተነስታ ያደገችው በ1986 (እ.ኤ.አ.) ተግባራዊ ባደረገችው 'ዶይ ሞይ' (Doi Moi) የተሰኘው የውስጥ የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና የእስያ ቀጠና በፈጠረላት ምቹ የንግድ ትስስር እንጂ የቅኝ ገዥዎች ትሩፋት አይደለም። የቬትናምን የላብ እና የደም ውጤት ለቅኝ ገዥዎች ታሪክ ማሳመሪያ ማድረግ ፍጹም ስህተት ነው።
ማጋቴ ዋድ የኢትዮጵያን ነጻነት ከድህነት ጋር አያይዛ ለማቅረብ መሞከሯ፣ የሀገሪቱን ታላቅነት እና የገጠማትን ውስብስብ ፈተና ካለመረዳት የመነጨ ነው። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ምድር የነጭ የበላይነትን በአድዋ ተራሮች ላይ በመቅበር፣ ለመላው ጥቁር ሕዝብ የነጻነት እና የፓን-አፍሪካኒዝም ፋና ወጊ የሆነች ታላቅ ሀገር ናት። በቅኝ አለመገዛቷ የኩራቷ እንጂ የድህነቷ መንስኤ አይደለም።
የኢትዮጵያ ዘመናዊ የኢኮኖሚ ፈተናዎች የመነጩት ከነጻነቷ ሳይሆን፣ በዙሪያዋ ከነበሩት የቅኝ ገዥ ኃይሎች ሴራ እና ከውስጣዊ ፖለቲካዊ ውጣ ውረዶች ነው። መላው አፍሪካ በቅኝ ግዛት ሲከፋፈል፣ ነጻዋ ኢትዮጵያ በቅኝ ገዥዎች ተከባ የባህር በር እንድታጣ እና ከዓለም አቀፍ ንግድ እንድትገለል ተደርጋለች። በቅርቡ ታሪክም በቀዝቃዛው ጦርነት የጂኦፖለቲካዊ ሽኩቻ ሰለባ በመሆን፣ እንዲሁም ደርግ በተከተለው አውዳሚ የማርክሲስት የኢኮኖሚ ሥርዓት እና በተራዘሙ የእርስ በርስ ጦርነቶች ምክንያት ኢኮኖሚዋ ክፉኛ ተጎድቷል። እነዚህ ሁሉ ፈተናዎች ቢኖሩም፣ ኢትዮጵያ የራሷን ቋንቋ፣ ባህል፣ የቀን አቆጣጠር እና ሀገራዊ ኩራት ጠብቃ ያቆየች፤ ዛሬም በአፍሪካ ቀንድ ትልቅ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ተጽዕኖ ፈጣሪ መሆን የቻለች ሀገር ናት።
የአፍሪካን ወቅታዊ ችግሮች ለመፍታት ራስን መመርመር፣ ሙስናን መዋጋት እና የተሻለ አስተዳደር መገንባት አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው። ነገር ግን ይህንን ለማድረግ ሲባል የቅኝ ግዛትን አስከፊነት ማጠብ እና የኢትዮጵያን ደማቅ የነጻነት ታሪክ ማጠልሸት አይቻልም። ኢትዮጵያ ምንም እንኳን የኢኮኖሚ ፈተናዎች ቢኖሩባትም፣ የማንም ቅኝ ገዥ ሎሌ ሳትሆን የራሷን ዕድል በራሷ የወሰነች የአፍሪካ የቁርጥ ቀን ልጅ ናት። አህጉሪቱ ወደፊት መራመድ ያለባት የቅኝ ግዛትን ጠባሳ በማስተባበል ሳይሆን፣ እንደ ኢትዮጵያ ሁሉ የራስን ማንነት አጥብቆ በመያዝ እና ጠንካራ ኢኮኖሚን በነጻነት ላይ በመገንባት ሊሆን ይገባል።
#ዘሐበሻ
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

1 month ago
አዳዲስ መረጃ ከሕወሐት ዙሪያ
(ዘሐበሻ - ሐሙስ፣ ሚያዝያ 29) ከ22ኛ አርሚ የተውጣጣ የህወሓት ታጣቂ ቡድን በዛሬው ዕለት ወደ ሱዳን እየተጓዘ መሆኑን ከዘሐበሻ ምንጭ የተገኘው መረጃ አሳውቋል። የሰራዊቱ ቡድን 70ኛ አርሚ ወዳለበት ስፍራ ነው እየተጓዘ ያለው። በ ጄ/ል ሕንፃ ከሚመራቸው ይህ ለሜኬናይዝድ ታጣቂ ቡድን ወደ ሱዳን ሲጓዝ የአይን እማኞች ለዘሐበሻ ገልፀዋል።
በሌላ በኩል ከ60ኛ አርሚ ለልዩ ተልዕኮ ወደ ምዕራብ ግንባር የተላኩ ታጣቂ ሀይሎች ዛሬ ጠዋት ከዓቢይዓዲ ተነስተው ወደ ሽሬ ከተማ በመጓዝ ላይ እንደሆኑ እና ሽሬ ከተማ ሲደርሱ የምዕራብ ግንባር ተልዕኮ ተቀብለው ወደ ምዕራብ ትግራይ ጠረፋማ አካባቢ እንደሚገቡ የመረጃ ምንጮቻችን አመላክተዋል።
ዶ/ር ደብረፂዮን በአክሱም ከተማ አትራኖስ ፋንታሲ ሆቴል አስቸኳይ ሚስጥራዊ ስብሰባ በማካሄድ ላይ እንደሚገኙ የመረጃ ምብጩ የጠቆመ ሲሆን ያረፉበት ሆቴል ደግሞ ኮንሱላር ሆቴል መሆኑን ገልጿል።
ፌደራል መንግስት ለሕወሀት እንቅስቃሴ ምንም አይነት ምላሽ አልሰጠም።

7 months ago
"ሊፈርስ ከጫፍ ደርሷል"ምንጮች
የፌደራል መንግስቱ እና የትግራይ ክልል አመራሮች ከሁለት አመት ደም አፋሳሽ ጦርነት በኋላ የደረሱበት የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት፣ በተለያዩ አዳዲስ ውዝግቦች ምክንያት "ሊፈርስ ከጫፍ ደርሷል" ሲሉ የተለያዩ ሪፖርቶች አመልክተዋል።
ውጥረቱ በዋናነት የተከሰተው፣ በDDR (ትጥቅ መፍታት፣ ከሠራዊት ማሰናበት እና መልሶ ማቋቋም) ስምምነት መሠረት ለክልሉ ታጣቂዎች ከፌደራል መንግስቱ ይላክ የነበረው ድጎማ እና በጀት መቋረጡን ተከትሎ መሆኑን ዘገባዎቹ አመልክተዋል።
ይህ የDDR በጀት መቋረጥ በክልሉ ውስጥ አዲስ የፋይናንስ ቀውስ የፈጠረ ሲሆን፣ አብዛኞቹ የትግራይ ክልል የመንግስት ሰራተኞች የሁለት ወር ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው ከጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ተናግረዋል።
ለዚህም ምክንያት፣ አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የክልሉ ባለስልጣን እንደተናገሩት፣ የDDR በጀቱ በመቋረጡ የክልሉ አስተዳደር "ለሕዝቡ አገልግሎት (ለሲቪል ሰራተኞች) የተመደበውን መደበኛ በጀት፣ ለታጣቂዎቹ ኃይሎች ደመወዝ ክፍያ እያዋለው ነው" ብለዋል።
ምንም እንኳን ከፌደራል መንግስት የሚላከው መደበኛ በጀት ባይቋረጥም፣ በክልሉ አመራሮች በኩል በጀት የማዛወር ስራ እየተሰራ መሆኑ፣ የህዝብ አገልጋዮች ደመወዝ እንዲያጡ ማድረጉን ምንጮቹ ተናግረዋል። ከቀናት በፊትም የተለያዩ የመንግስት ሰራተኞች "ደሞዛችን ይከፈለን" የሚል ተቃውሞ በተለያዩ የትግራይ ከተሞች ማሰማታቸው ይታወሳል።
ከDDR በጀት መቋረጥ በተጨማሪ፣ ከዚህ ቀደም የትግራይ ኃይሎች የአፋር ክልልን ድንበር ጥሰው የገቡ ቢሆንም በኋላ ላይ ለቀው ቢወጡም፣ ድርጊቱ ራሱ በስምምነቱ ላይ የፈጠረው ስጋት ከፍተኛ እንደሆነ ተገልጿል።
በሌላ በኩል፣ የህዝቡን እንግልት አባብሷል የተባለ የነዳጅ እጥረት በክልሉ ተከስቷል። ምንም እንኳን ነዳጅ ወደ ክልሉ እየገባ መሆኑ ቢነገርም፣ "ነዳጁ የት እየደረሰ እንደሆነ አይታወቅም" ያሉት ነዋሪዎች፣ ህዝቡ በከፍተኛ የነዳጅ እጥረት እየተሰቃየ መሆኑን ገልጸዋል።
በክልሉ በተፈጠረው በዚህ አዲስ ውጥረት እና አስተዳደራዊ ችግር ዙሪያ፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ አካል የሆኑት ጄኔራል ታደሰ ወረደ ዝምታን መምረጣቸው የተለያዩ ጥያቄዎችን አስነስቷል።
ጄኔራሉ በጉዳዩ ላይ አስተያየት ከመስጠት መቆጠባቸው፣ "ምናልባት በህወሓት (TPLF) ሃይሎች ተጽዕኖ ስር ወድቀው ይሆን?" የሚል ግምት እንዲፈጠር ማድረጉን ዘሐበሻ ዘግቧል።
seledadotio

8 months ago
''ቲክቶክን አድኜዋለሁ ፣ ወጣቶች ውለታ አለባቸው''
#ethiopia | ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ታዋቂው የማህበራዊ መተግበሪያ ቲክቶክ በአሜሪካ ስራውን እንዲቀጥል የሚያስችል አዲስ አስፈጻሚ ትዕዛዝ መፈረማቸውን ተከትሎ፣ ሰኞ ጠዋት በቲክቶክ ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት የቪዲዮ መልዕክት፣ "ውለታ አለባችሁ" ሲሉ ለወጣት ተጠቃሚዎች ተናግረዋል።
"እናንተ የቲክቶክ ወጣቶች በሙሉ፣ ቲክቶክን ያዳንኩት እኔ ነኝ፣ ስለዚህ ትልቅ ውለታ አለባችሁ" ብለዋል ፕሬዝዳንቱ በቪዲዮው።
አክለውም፣ "አሁን እዚህ ኦቫል ቢሮ ውስጥ ሆኜ እያያችሁኝ ነው፤ ወደፊት ከእናንተ አንዱ በዚህ ወንበር ላይ ተቀምጦ ታላቅ ስራ እንደሚሰራ ተስፋ አደርጋለሁ" ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ይህ አዲስ ስምምነትና ትዕዛዝ የወጣው፣ በቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የስልጣን ዘመን በኮንግረስ በሁለቱም ፓርቲዎች ድጋፍ በጸደቀው ህግ መሰረት ነው።
ህጉ፣ የቲክቶክ እናት ኩባንያ የሆነው የቻይናው 'ባይትዳንስ' (ByteDance) በአሜሪካ ያለውን ንብረቱን እንዲሸጥ፣ ይህን ካላደረገ ደግሞ መተግበሪያው በመላ ሀገሪቱ እንደሚታገድ ይደነግግ ነበር። የትራምፕ አስተዳደር የወሰደው እርምጃ ይህንን ለዓመታት የዘለቀውን ውዝግብ ያጠናቀቀ ነው።
በአሜሪካ ውስጥ በአብዛኛው ወጣቶች የሆኑ ከ170 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች ያሉት ቲክቶክ፣ የማህበራዊ ግንኙነት፣ የመዝናኛ እና የመረጃ ልውውጥ ዋነኛ መድረክ ሆኖ አገልግሏል።
መተግበሪያው ከቻይና መንግስት ጋር ባለው ግንኙነት ምክንያት፣ የተጠቃሚዎችን መረጃ ደህንነትና የውጭ ተጽዕኖን በተመለከተ የብሔራዊ ደህንነት ስጋት በመፍጠሩ ለረጅም ጊዜ ሲያነጋግር ቆይቷል ያለው ዘሐበሻ ነው።

የቱኒዝያ ፕሬዝደንትን የተቸው ግለሰብ ሞት ተፈረደበት
📌የቱኒዝያ ፕሬዝደንትን ‹‹በማህበራዊ ሚዲያ ተችቷል›› የተባለው ግለሰብ ሞት ተፈርዶበታል
#ethiopia | በቱኒዝያ የሚገኘው ፍርድ ቤት የ51 አመቱ ተከሳሽ ላይ የሞት ፍርድ ማስተላለፉ ተዘገበ፡፡ ቲአርቲ አፍሪካ እንደዘገበው በዚህ ግለሰብ ላይ የቀረበበት ክስ በፕሬዝደንት ካኢስ ሰኢድ ላይ በፌስ ቡክ ትችት በመሰንዘሩ ነው፡፡
ስሙ ያልተጠቀው ይህ ተከሳሽ ሮብ እለት በቀረቡበት 3 ክሶች ማለትም መንግስትን ለመገልበጥ መሞከር፣ ፕሬዝደንቱን በመዝለፍና በኦንላይን ሀሰተኛ መረጃን በማሰራጨት ጥፋተኛ መባሉን ዘገባው አስታውቋል፡፡
ተከሳሹ ትላንት አርብ ለውሳኔ ተቀጥሮ ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን ዳኛው በቱኒዝያ የወንጀለኛ መቅጫ ህግና በ2022 በወጣው የሳይበር ወንጀል ህግ አንቀፅ 54 መሰረት አመፅና ብጥብጥን መቀስቀስ የሚለውን መተላለፉን ገልፀውለታል፡፡
ይህንን ተከትሎም በሞት እንዲቀጣ ውሳኔ ማሳለፋቸውን ዘገባው አስታውቋል፡፡ የተከሳሹ ጠበቃ እንደገለፁት ግለሰቡ ከታሰረ አንድ አመት የሆነው ሲሆን የ3 ልጆች አባትና እንብዛም የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም እውቀት የሌለው ነው፡፡
ጠበቃው ሲናገሩ ‹‹አብዛኛዎቹ የተከሰሰባቸው ፅሁፎች እሱ የፃፋቸው ሳይሆኑ ከሌሎች ገፆች ላይ ኮፒ አድርጎ የለጠፋቸው ናቸው›› ብለዋል፡፡
ግለሰቡ በማህበራዊ ሚዲያ ተፅእኖ ፈጣሪ አለመሆኑን ገልፀውም ከተከሰሰባቸው ልጥፎች መካከል አንዳንዶቹ አንድ እንኳ ላይክ ያላገኙ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡
በቱኒዚያ ከማህበራዊ ሚዲያ ጋር በተገናኘ የሞት ፍርድ ሲሰጥ ይህ የመጀመሪያው ነው፡፡ የቱኒዚያ ፍርድ ቤቶች ብዙውን ጊዜ ሞት ቢፈርዱም ውሳኔያቸው ተፈፃሚ የመሆን እድሉ ዝቅተኛ መሆኑ በተደጋጋሚ መታየቱን ዘገባው ጨምሮ አስረድቷል ያለው ዘሐበሻ ነው፡፡

9 months ago
"ኢትዮጵያ በመድሀኒት ቁጥጥር ደረጃ 3 ውስጥ በመካተቷ ደስ ብሎኛል" ሲሉ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም ገለፁ፡፡
#ethiopia | የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም በኤክስ ገፃቸው ላይ ኢትዮጵያ ደረጃ 3 ውስጥ በመካተቷ እንኳን ደስ አላችሁ የሚል መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
እዚህ ደረጃ ውስጥ በመግባቷም አሁን ከአፍሪካ ከግብፅ፣ ጋና፣ ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ታንዛኒያ፣ ዚምባቡዌ፣ ሴኔጋልና ሩዋንዳ ጋር መቀላቀሏን አስታውቀዋል፡፡ ይህም አፍሪካ የአገር ውስጥ ምርትን እንዲሁም ደህንነቱና ጥራቱ የተጠበቀ መድሀኒትን ወደማሻሻል እየተቃረበች መሆኑን እንደሚያሳይ ገልፀዋል፡፡
የአለም ጤና ድርጅት ባወጣው መግለጫ እንደደገለፀው ደግሞ ኢትዮጵያ ደረጃ 3 ውስጥ ልትገባ የቻለችው በምግብና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ቁርጠኝነት የተነሳ ነው፡፡ ባለስልጣኑ ከውጭ የሚገቡ መድሀኒቶችና ክትባቶች አለም አቀፍ ጥራትን፣ ብቃትንና ደህንነትን ያሟሉ እንዲሆኑ ከፍተኛ ስራ ማከናወኑንም አስረድቷል፡፡
የአለም ጤና ድርጅት በመግለጫው ይህንን የደረጃ ማሻሻያ የሰጠው 250 መስፈርቶችን በመገምገም እንደሆነ ጨምሮ አስረድቷል፡፡ በአለም ጤና ድርጅት ደረጃ 3 ማለት የተረጋጋ፣ የተቀናጀና በአግባቡ የሚሰራ የቁጥጥር ስርአት እንዳለ የሚገልፅ እውቅና ሲሆን ከዚህ ቀጣዩ ደረጃ 4 የመጨረሻውና ከፍተኛው ደረጃ ነው ሲል ዘሐበሻ ዘግቧል፡፡

የኡጋንዳ እጩ ፕሬዝደንት ከተመረጡ ኢትዮጵያዊያንንና ኤርትራዊያንን እንደሚያባርሩ ቃል ገቡ
#ethiopia | በኡጋንዳ የ2026 ፕሬዝደንታዊ ምርጫ እጩ ከሆኑት አንዱ የኮመን ማን ፓርቲ ሊቀመንበሩ ሙባረክ ሙንያግዋ ናቸው፡፡
እጩ ፕሬዝደንቱ ለምርጫ ቅስቀሳ ባደረጉት ንግግር ላይ ከተመረጡ በ100 ቀናት የሚያከናውኗቸውን ተግባራት ይፋ ማድረጋቸውን ዘ ካምፓላ ጆርናል ዘግቧል፡፡
በንግግራቸውም ‹‹በእኔ የፕሬዝደንትነት ዘመን የመጀመሪያዎቹ 100 ቀናት በኪስኒ ያሉ ሱማሊያዎችን፣ በካባላጋላ ያሉ ኤርትራዊያንንና ኢትዮጵያዊያንን እንዲሁም በማኪንዲ የሚገኙ ኮንጎያዊያንንና ደቡብ ሱዳናዊያንን ወደአገራቸው እንዲባረሩ አደርጋለሁ፡፡
ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች የኡጋንዳዊያንን ህይወት እያበላሹ ነው›› ማለታቸውን ጠቅሷል፡፡ ሙንያግዋ በመጪው ምርጫ ከፕሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴቪኒና ቢያንስ 5 ከሚሆኑ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ለፕሬዝደንትነት እንደሚፎካከሩም ዘገባው አውስቷል ሲል ዘሐበሻ ዘግቧል፡፡

ተዘርፌያለሁ
#ethiopia | የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ጀማል አህመድ፣ በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ፕሬዝዳንት በአቶ አብነት ገብረመስቀል ላይ በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ተዘርፌያለሁ ሲሉ ከባድ የሙስና ውንጀላ አቀረቡ።
ይህ አስደንጋጭ ክስ የመጣው፣ አቶ አብነት ገብረመስቀል ‘ክለቡን ለመጥለፍ ሴራ እየተካሄደ ነው’ ሲሉ መግለጫ ከሰጡ በኋላ ነው።
🔴 "የቦርድ አባል አልነበርኩም፤ የገነባሁትን አካዳሚ አፈረሱብኝ"
አቶ ጀማል ለዘ-ሐበሻ በሰጡት ምላሽ፣ የክለቡ የቦርድ አባል ተደርገው መቅረባቸው ስህተት መሆኑን ገልጸዋል። "የቅዱስ ጊዮርጊስ የቦርድ አባል ሆኜ አላውቅም፤ የቡድኑ እጅግ ታማኝ ደጋፊ ነበርኩ። ቡድኑን ለመርዳት የራሴን በአስር ሚሊዮን የሚቆጠሩ ገንዘብ አውጥቻለሁ" ብለዋል።
የውጭ ተጫዋቾችን እና አሰልጣኞችን ገንዘባቸውን አውጥተው በመክፈል ወደ ክለቡ እንዲመጡ ይደግፉ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ጀማል፣ አሁንም ቡድኑ የሚጠቀምባቸው ሁለቱ አውቶቡሶች በግል ገንዘባቸው የተገዙ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
ከክለቡ ጋር ግንኙነታቸው የተቋረጠበትን ምክንያት ሲያስረዱም ከባድ ውንጀላዎችን አቅርበዋል። “የሚድሮክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ከመሆናቸውና፣ አኔና አብነት ከመካሰሳችን ከሁለት ዓመት በፊት ነው ቅዱስ ጊዮርጊስን ለቀቄ የወጣሁት (ድጋፌን ያነሳሁት)” ብለዋል። ለዚህም ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶችን ጠቅሰዋል።
የመጀመሪያው የገንዘብ ምዝበራ እንደሆነ ገልጸዋል። “በ2010ን ጨምሮ ለዓመታት ለክለቡ ያሰባሰብኩት ገንዘብ በሙሉ በአብነት እና በዳዊት አማካኝነት ወደ ሌላ አካውንት ገብቶ ተዘርፏል። ለዓመታት በሚሊኒየም ይካሄድ የነበረው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶችም በተመሳሳይ በእነሱ መዘረፉን በማወቄ የተፈጠረ ቅሬታ ነው” ሲሉ ከሰዋል።
ሁለተኛው እና ዋነኛው ምክንያት ደግሞ በቢሾፍቱ የገነቡት ዘመናዊ የእግር ኳስ አካዳሚ መፍረስ እንደሆነ ተናግረዋል። "ይህ አካዳሚ የዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲኖረው፣ ከራሴ ገንዘብ በተጨማሪ፣ ሚድሮክ የሚመራቸው ድርጅቶችን ድጋፍ ጨምሮ፣ ሼህ መሐመድን አሳምኜ እና ከቢጂአይ ጋር ተነጋግሬ የጀመርኩት ነበር። ነገር ግን ውሳኔው፣ ከጀርባዬ ጀማል እንዳይሰማ ተብሎ በሶስት የወንጀል ተባባሪዎች ብቻ ተወስኖ ወደ ዋናው ቡድን ማሰልጠኛነት ተቀየረ፤ ዳዊት እና አብነት ይገኙበታል። በዚህ ቅሬታ ነው የወጣሁት።” ሲሉ ገልጸዋል።
🔴 "ወደ ክለቡ አልመለስም" - የአቶ ጀማል የመጨረሻ ውሳኔ
"አቶ ጀማል ክለቡ ይመለስ" የሚሉ ቅስቀሳዎች እንዳሉ ጠቅሰው፣ ወደ ክለቡ አመራር የመምጣት ምንም አይነት ፍላጎት እንደሌላቸው በግልጽ አስረድተዋል። "የአሁኑ አመራሮች እና አንዳንድ የደጋፊ ቡድኖች በተደጋጋሚ ስሜን በሀሰት ሲያጠፉ እና በማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ሲያካሂዱብኝ ቆይተዋል። አብነት ፍርድ ቤት ሲቀርብ ደጋፊዎችን አደራጅተው ሲያስፈራሩ ነበር። የአብነት ከእስር መፈታትም እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ድል አድርገው አክብረዋል። የሱን ክስ መቋረጥ ተከትሎ ወደ ክለቡ ላለመለስ ወስኛለሁ” በማለት ምሬታቸውን ገልጸዋል።
"የእኔ ተልዕኮ ላለፉት 5 ዓመታት ሙሉ በሙሉ ተለውጧል" ያሉት አቶ ጀማል፣ አሁን ትኩረታቸው ትልቅ ድርጅት እንደመምራታቸው “ሰው መር የሆነ፣ በህዝቡ እና በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ትልቅ አዎንታዊ ተጽዕኖ መፍጠር፣ ማህበራዊ ኃላፊነታቸው መወጣት” ላይ መሆኑን ገልጸው፣ እግር ኳስ ቅድሚያ የሚሰጡት ጉዳይ እንዳልሆነ አክለዋል።
የሊቨርፑል ቀንደኛ ደጋፊ መሆናቸውን የገለጹት አቶ ጀማል፣ ለታሪካዊው የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ታሪክ ልዩ ክብር እንዳላቸው ገልጸዋል። “ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጀመሪያው አርበኛ ክለብ ነው፣ በጣሊያን ወረራ ጊዜ ኢትዮጵያን ብሎ በእውነተኛ ኢትዮጵያውያን የተቋቋመ፣ ለብዙ ዓመታት እውነተኛ የኢትዮጵያ ወዳጆች የደገፉት፣ እኔም ብዙ ጊዜ የደገፍኩት፣ ብዙ ሰው ያስተዋወቀኝ ክለብ ነው። ለክለቡ ትልቅነት ሁሌም እመኛለሁ፣ ለክለቡ ያለኝ ፍቅር ዕድሜ ልኬን በልቤ ይኖራል፣ ግን ክለቡን ለመቀላቀል አልፈልህም” ሲሉ መልካሙን ሁሉ ተመኝተዋል።
ይህ የአቶ ጀማል ጠንካራ ምላሽ የመጣው፣ በአሜሪካ የሚገኙት አቶ አብነት ገብረመስቀል ክለቡን "ለመጥለፍ የሚደረግ የድብቅ ሴራ" አለ ሲሉ የክለቡን ጠቅላላ ጉባኤ ለመስከረም ወር መጨረሻ ከጠሩ በኋላ ነው።
የአቶ ጀማል አህመድ ክስ፣ በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ውስጥ ያለውን የአመራር እና የፋይናንስ ቀውስ ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገሩት ሲሆን፣ በመጪው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከፍተኛ ውጥረት እንደሚኖር አመላካች ነው። የክለቡ አባላት እና ደጋፊዎች በቀረቡት ከባድ ክሶች ላይ ተመስርተው የክለባቸውን የወደፊት እጣ ፈንታ መወሰን ይጠበቅባቸዋል ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።#ዘሐበሻ

Sponsored by
Surafel
Comments