''ቲክቶክን አድኜዋለሁ ፣ ወጣቶች ውለታ አለባቸው''
#ethiopia | ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ታዋቂው የማህበራዊ መተግበሪያ ቲክቶክ በአሜሪካ ስራውን እንዲቀጥል የሚያስችል አዲስ አስፈጻሚ ትዕዛዝ መፈረማቸውን ተከትሎ፣ ሰኞ ጠዋት በቲክቶክ ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት የቪዲዮ መልዕክት፣ "ውለታ አለባችሁ" ሲሉ ለወጣት ተጠቃሚዎች ተናግረዋል።
"እናንተ የቲክቶክ ወጣቶች በሙሉ፣ ቲክቶክን ያዳንኩት እኔ ነኝ፣ ስለዚህ ትልቅ ውለታ አለባችሁ" ብለዋል ፕሬዝዳንቱ በቪዲዮው።
አክለውም፣ "አሁን እዚህ ኦቫል ቢሮ ውስጥ ሆኜ እያያችሁኝ ነው፤ ወደፊት ከእናንተ አንዱ በዚህ ወንበር ላይ ተቀምጦ ታላቅ ስራ እንደሚሰራ ተስፋ አደርጋለሁ" ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ይህ አዲስ ስምምነትና ትዕዛዝ የወጣው፣ በቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የስልጣን ዘመን በኮንግረስ በሁለቱም ፓርቲዎች ድጋፍ በጸደቀው ህግ መሰረት ነው።
ህጉ፣ የቲክቶክ እናት ኩባንያ የሆነው የቻይናው 'ባይትዳንስ' (ByteDance) በአሜሪካ ያለውን ንብረቱን እንዲሸጥ፣ ይህን ካላደረገ ደግሞ መተግበሪያው በመላ ሀገሪቱ እንደሚታገድ ይደነግግ ነበር። የትራምፕ አስተዳደር የወሰደው እርምጃ ይህንን ለዓመታት የዘለቀውን ውዝግብ ያጠናቀቀ ነው።
በአሜሪካ ውስጥ በአብዛኛው ወጣቶች የሆኑ ከ170 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች ያሉት ቲክቶክ፣ የማህበራዊ ግንኙነት፣ የመዝናኛ እና የመረጃ ልውውጥ ዋነኛ መድረክ ሆኖ አገልግሏል።
መተግበሪያው ከቻይና መንግስት ጋር ባለው ግንኙነት ምክንያት፣ የተጠቃሚዎችን መረጃ ደህንነትና የውጭ ተጽዕኖን በተመለከተ የብሔራዊ ደህንነት ስጋት በመፍጠሩ ለረጅም ጊዜ ሲያነጋግር ቆይቷል ያለው ዘሐበሻ ነው።

8 months ago