ተዘርፌያለሁ
#ethiopia | የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ጀማል አህመድ፣ በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ፕሬዝዳንት በአቶ አብነት ገብረመስቀል ላይ በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ተዘርፌያለሁ ሲሉ ከባድ የሙስና ውንጀላ አቀረቡ።
ይህ አስደንጋጭ ክስ የመጣው፣ አቶ አብነት ገብረመስቀል ‘ክለቡን ለመጥለፍ ሴራ እየተካሄደ ነው’ ሲሉ መግለጫ ከሰጡ በኋላ ነው።
🔴 "የቦርድ አባል አልነበርኩም፤ የገነባሁትን አካዳሚ አፈረሱብኝ"
አቶ ጀማል ለዘ-ሐበሻ በሰጡት ምላሽ፣ የክለቡ የቦርድ አባል ተደርገው መቅረባቸው ስህተት መሆኑን ገልጸዋል። "የቅዱስ ጊዮርጊስ የቦርድ አባል ሆኜ አላውቅም፤ የቡድኑ እጅግ ታማኝ ደጋፊ ነበርኩ። ቡድኑን ለመርዳት የራሴን በአስር ሚሊዮን የሚቆጠሩ ገንዘብ አውጥቻለሁ" ብለዋል።
የውጭ ተጫዋቾችን እና አሰልጣኞችን ገንዘባቸውን አውጥተው በመክፈል ወደ ክለቡ እንዲመጡ ይደግፉ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ጀማል፣ አሁንም ቡድኑ የሚጠቀምባቸው ሁለቱ አውቶቡሶች በግል ገንዘባቸው የተገዙ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
ከክለቡ ጋር ግንኙነታቸው የተቋረጠበትን ምክንያት ሲያስረዱም ከባድ ውንጀላዎችን አቅርበዋል። “የሚድሮክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ከመሆናቸውና፣ አኔና አብነት ከመካሰሳችን ከሁለት ዓመት በፊት ነው ቅዱስ ጊዮርጊስን ለቀቄ የወጣሁት (ድጋፌን ያነሳሁት)” ብለዋል። ለዚህም ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶችን ጠቅሰዋል።
የመጀመሪያው የገንዘብ ምዝበራ እንደሆነ ገልጸዋል። “በ2010ን ጨምሮ ለዓመታት ለክለቡ ያሰባሰብኩት ገንዘብ በሙሉ በአብነት እና በዳዊት አማካኝነት ወደ ሌላ አካውንት ገብቶ ተዘርፏል። ለዓመታት በሚሊኒየም ይካሄድ የነበረው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶችም በተመሳሳይ በእነሱ መዘረፉን በማወቄ የተፈጠረ ቅሬታ ነው” ሲሉ ከሰዋል።
ሁለተኛው እና ዋነኛው ምክንያት ደግሞ በቢሾፍቱ የገነቡት ዘመናዊ የእግር ኳስ አካዳሚ መፍረስ እንደሆነ ተናግረዋል። "ይህ አካዳሚ የዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲኖረው፣ ከራሴ ገንዘብ በተጨማሪ፣ ሚድሮክ የሚመራቸው ድርጅቶችን ድጋፍ ጨምሮ፣ ሼህ መሐመድን አሳምኜ እና ከቢጂአይ ጋር ተነጋግሬ የጀመርኩት ነበር። ነገር ግን ውሳኔው፣ ከጀርባዬ ጀማል እንዳይሰማ ተብሎ በሶስት የወንጀል ተባባሪዎች ብቻ ተወስኖ ወደ ዋናው ቡድን ማሰልጠኛነት ተቀየረ፤ ዳዊት እና አብነት ይገኙበታል። በዚህ ቅሬታ ነው የወጣሁት።” ሲሉ ገልጸዋል።
🔴 "ወደ ክለቡ አልመለስም" - የአቶ ጀማል የመጨረሻ ውሳኔ
"አቶ ጀማል ክለቡ ይመለስ" የሚሉ ቅስቀሳዎች እንዳሉ ጠቅሰው፣ ወደ ክለቡ አመራር የመምጣት ምንም አይነት ፍላጎት እንደሌላቸው በግልጽ አስረድተዋል። "የአሁኑ አመራሮች እና አንዳንድ የደጋፊ ቡድኖች በተደጋጋሚ ስሜን በሀሰት ሲያጠፉ እና በማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ሲያካሂዱብኝ ቆይተዋል። አብነት ፍርድ ቤት ሲቀርብ ደጋፊዎችን አደራጅተው ሲያስፈራሩ ነበር። የአብነት ከእስር መፈታትም እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ድል አድርገው አክብረዋል። የሱን ክስ መቋረጥ ተከትሎ ወደ ክለቡ ላለመለስ ወስኛለሁ” በማለት ምሬታቸውን ገልጸዋል።
"የእኔ ተልዕኮ ላለፉት 5 ዓመታት ሙሉ በሙሉ ተለውጧል" ያሉት አቶ ጀማል፣ አሁን ትኩረታቸው ትልቅ ድርጅት እንደመምራታቸው “ሰው መር የሆነ፣ በህዝቡ እና በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ትልቅ አዎንታዊ ተጽዕኖ መፍጠር፣ ማህበራዊ ኃላፊነታቸው መወጣት” ላይ መሆኑን ገልጸው፣ እግር ኳስ ቅድሚያ የሚሰጡት ጉዳይ እንዳልሆነ አክለዋል።
የሊቨርፑል ቀንደኛ ደጋፊ መሆናቸውን የገለጹት አቶ ጀማል፣ ለታሪካዊው የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ታሪክ ልዩ ክብር እንዳላቸው ገልጸዋል። “ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጀመሪያው አርበኛ ክለብ ነው፣ በጣሊያን ወረራ ጊዜ ኢትዮጵያን ብሎ በእውነተኛ ኢትዮጵያውያን የተቋቋመ፣ ለብዙ ዓመታት እውነተኛ የኢትዮጵያ ወዳጆች የደገፉት፣ እኔም ብዙ ጊዜ የደገፍኩት፣ ብዙ ሰው ያስተዋወቀኝ ክለብ ነው። ለክለቡ ትልቅነት ሁሌም እመኛለሁ፣ ለክለቡ ያለኝ ፍቅር ዕድሜ ልኬን በልቤ ይኖራል፣ ግን ክለቡን ለመቀላቀል አልፈልህም” ሲሉ መልካሙን ሁሉ ተመኝተዋል።
ይህ የአቶ ጀማል ጠንካራ ምላሽ የመጣው፣ በአሜሪካ የሚገኙት አቶ አብነት ገብረመስቀል ክለቡን "ለመጥለፍ የሚደረግ የድብቅ ሴራ" አለ ሲሉ የክለቡን ጠቅላላ ጉባኤ ለመስከረም ወር መጨረሻ ከጠሩ በኋላ ነው።
የአቶ ጀማል አህመድ ክስ፣ በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ውስጥ ያለውን የአመራር እና የፋይናንስ ቀውስ ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገሩት ሲሆን፣ በመጪው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከፍተኛ ውጥረት እንደሚኖር አመላካች ነው። የክለቡ አባላት እና ደጋፊዎች በቀረቡት ከባድ ክሶች ላይ ተመስርተው የክለባቸውን የወደፊት እጣ ፈንታ መወሰን ይጠበቅባቸዋል ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።#ዘሐበሻ

9 months ago