Logo
Getu Temesgen
"ኢትዮጵያ በመድሀኒት ቁጥጥር ደረጃ 3 ውስጥ በመካተቷ ደስ ብሎኛል" ሲሉ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም ገለፁ፡፡
#ethiopia | የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም በኤክስ ገፃቸው ላይ ኢትዮጵያ ደረጃ 3 ውስጥ በመካተቷ እንኳን ደስ አላችሁ የሚል መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

እዚህ ደረጃ ውስጥ በመግባቷም አሁን ከአፍሪካ ከግብፅ፣ ጋና፣ ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ታንዛኒያ፣ ዚምባቡዌ፣ ሴኔጋልና ሩዋንዳ ጋር መቀላቀሏን አስታውቀዋል፡፡ ይህም አፍሪካ የአገር ውስጥ ምርትን እንዲሁም ደህንነቱና ጥራቱ የተጠበቀ መድሀኒትን ወደማሻሻል እየተቃረበች መሆኑን እንደሚያሳይ ገልፀዋል፡፡

የአለም ጤና ድርጅት ባወጣው መግለጫ እንደደገለፀው ደግሞ ኢትዮጵያ ደረጃ 3 ውስጥ ልትገባ የቻለችው በምግብና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ቁርጠኝነት የተነሳ ነው፡፡ ባለስልጣኑ ከውጭ የሚገቡ መድሀኒቶችና ክትባቶች አለም አቀፍ ጥራትን፣ ብቃትንና ደህንነትን ያሟሉ እንዲሆኑ ከፍተኛ ስራ ማከናወኑንም አስረድቷል፡፡

የአለም ጤና ድርጅት በመግለጫው ይህንን የደረጃ ማሻሻያ የሰጠው 250 መስፈርቶችን በመገምገም እንደሆነ ጨምሮ አስረድቷል፡፡ በአለም ጤና ድርጅት ደረጃ 3 ማለት የተረጋጋ፣ የተቀናጀና በአግባቡ የሚሰራ የቁጥጥር ስርአት እንዳለ የሚገልፅ እውቅና ሲሆን ከዚህ ቀጣዩ ደረጃ 4 የመጨረሻውና ከፍተኛው ደረጃ ነው ሲል ዘሐበሻ ዘግቧል፡፡

9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.