የኡጋንዳ እጩ ፕሬዝደንት ከተመረጡ ኢትዮጵያዊያንንና ኤርትራዊያንን እንደሚያባርሩ ቃል ገቡ
#ethiopia | በኡጋንዳ የ2026 ፕሬዝደንታዊ ምርጫ እጩ ከሆኑት አንዱ የኮመን ማን ፓርቲ ሊቀመንበሩ ሙባረክ ሙንያግዋ ናቸው፡፡
እጩ ፕሬዝደንቱ ለምርጫ ቅስቀሳ ባደረጉት ንግግር ላይ ከተመረጡ በ100 ቀናት የሚያከናውኗቸውን ተግባራት ይፋ ማድረጋቸውን ዘ ካምፓላ ጆርናል ዘግቧል፡፡
በንግግራቸውም ‹‹በእኔ የፕሬዝደንትነት ዘመን የመጀመሪያዎቹ 100 ቀናት በኪስኒ ያሉ ሱማሊያዎችን፣ በካባላጋላ ያሉ ኤርትራዊያንንና ኢትዮጵያዊያንን እንዲሁም በማኪንዲ የሚገኙ ኮንጎያዊያንንና ደቡብ ሱዳናዊያንን ወደአገራቸው እንዲባረሩ አደርጋለሁ፡፡
ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች የኡጋንዳዊያንን ህይወት እያበላሹ ነው›› ማለታቸውን ጠቅሷል፡፡ ሙንያግዋ በመጪው ምርጫ ከፕሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴቪኒና ቢያንስ 5 ከሚሆኑ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ለፕሬዝደንትነት እንደሚፎካከሩም ዘገባው አውስቷል ሲል ዘሐበሻ ዘግቧል፡፡

9 months ago