5 hours ago
በትግራይ የተከናወነው ፍፁም ህገወጥና እውቅና የሌለው ድርጊት ነው፦ ጄኔራል ሳሞራ የኑስ
የቀድሞው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሳሞራ የኑስ በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ የፖለቲካና የፀጥታ ሁኔታ በተመለከተ ቃለ መጠይቅ አድርገዋል፡፡
ጄኔራሉ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) የትግርኛ ክፍል ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ በክልሉ በህወሓትና “በአቶ መለስ ዜናዊ ስም ተገን” በማድረግ የሚከናወኑ እንቅስቃሴዎች ሊቆሙ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
በትግራይ ክልል የተቋቋመውን ጊዜያዊ አስተዳደር አፍርሶ “የራስ አስተዳደር አዋቀርኩ” የሚለውን አካሄድ የተቃወሙት ጄኔራል ሳሞራ፣ ድርጊቱ ፍጹም ሕገ-ወጥና እውቅና የሌለው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ይህ ቡድን በአክሱም ከተማ ተሰብስቦ ያደረገውን ውሳኔ “ሕጋዊነት የጎደለው መንግሥት ምስረታ” ሲሉ የገለጹት ጄኔራሉ፣ መጀመሪያ በአቶ ጌታቸው ረዳ በመቀጠልም በሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ የሚመሩትን ጊዜያዊ አስተዳደሮች ሥራቸውን እንዳይሠሩና ሕዝቡን ወደ ምርጫ እንዳይወስዱ እንቅፋት ሲፈጠርባቸው መቆየቱንና በመጨረሻም ማኅተምና የአሠራር መሣሪያዎችን በመቀማት የማባረር ተግባር መፈጸሙን ተናግረዋል፡፡
የክልሉ ፖለቲከኞች ዋና ዓላማ ሥልጣን ብቻ መሆኑንና ይህንን ሥልጣን የሚፈልጉት ከተጠያቂነት ለማምለጥ እንደሆነ የገለጹት ጄኔራሉ፣ የፌዴራል መንግሥት ጉዳዩን በትዕግሥትና በሰላማዊ መንገድ እየያዘበት ያለውን አካሄድ አድንቀዋል፡፡
የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በተፈረመበት ወቅት የትግራይ ሕዝብ ከፍተኛ ደስታውን የገለጸ ቢሆንም፣ በክልሉ ያሉት ፖለቲከኞች ግን ወደ ሥልጣን ሽሚያ ማምራታቸውን ጄኔራሉ ጠቁመዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት በክልሉ እየተካሄደ ስላለው “የወጣቶች አፈሳ” ሲያብራሩም፣ ድርጊቱ ከሻዕቢያን የድሮ የትግል ስትራቴጂ የተቀዳ መሆኑንና ሻዕቢያ ኢትዮጵያን የማተራመስ ስትራቴጂውን እንዳልቀየረ ገልጸዋል፡፡
ከፌዴራል መንግሥት በጀት እየወሰዱ መንግሥትን “ጠላት” ብሎ መፈረጅ ስህተት መሆኑን የጠቀሱት ጄኔራል ሳሞራ፣ የክልሉ አመራሮች “ከምርጫ በኋላ መንግሥት ይወጋናል” የሚል ፕሮፓጋንዳ ለወጣቶች አፈሳ እየተጠቀሙበት እንደሚገኝና በአንጻሩ መንግሥት ጉዳዩን በጦርነት ለመፍታት ፍላጎት እንደሌለው ገልጸዋል፡፡
ጄኔራል ሳሞራ ለትግራይ ሕዝብና ለወላጆች ባቀረቡት ጥሪም የወላጆች ስጋት የሆነውን የወጣቶች አፈሳ ለመግታት ወላጆች ተደራጅተው ሊቃወሙትና “ልጆቻችንን አንሰጥም” ብለው ሊታገሉ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ምርጫ በተካሄደበት በዚህ ወቅት የትግራይ ሕዝብ እንዳይመርጥ መከልከል እንደሌለበትና በመረጠው መሪ የመተዳደር መብቱ ሊከበርለት እንደሚገባ በመግለጽ የሕዝቡ ዋና ዋስትና እራሱ ሕዝቡ ብቻ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
EBC

"የአርሲው ጥቃት በሸኔ ታጣቂዎች የተፈጸመ ነው"፦ አቶ ሀይሉ አዱኛ
"የአርሲው ጥቃት ምርጫውን ለማደናቀፍ በሸኔ ታጣቂዎች የተፈጸመ ነው" የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ሀይሉ አዱኛ።
በጥቃቱ ከዚህም በላይ ጉዳት እንዳይደርስ ህዝቡና የኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ሀይል መስዋዕትነት ከፍሏል ብለዋል። አሸባሪው ሸኔ ይህንን ጥቃት ያደረሰው ከታሪካዊ ጠላቶች ተልዕኮ ተቀብሎ የሀይማኖት ግጭት ለማስነሳት የነበረ ቢሆንም በህዝቡ አስተዋይነት ከሽፏል ብለዋል።
መከላከያ ሰራዊት፣የፌዴራል ፖሊስ የኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ሀይል የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ እና አካባቢውን ለማረጋጋት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
Seledadotio

7 hours ago
ህወሃት ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በአስቸኳይ ጣልቃ እንዲገባ ጠየቀ
#fastmereja I የሕዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ (ህወሃት) ከፍተኛ አመራር የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት የፌደራል መንግስቱ በይፋ ማፍረሱንና ክልሉን በከበባ ውስጥ ማድረጉን በመጥቀስ፣ አዲስ ሊቀሰቀስ የሚችለውን አስከፊ ጦርነት ለመግታት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በአስቸኳይ ጣልቃ እንዲገባ ጥሪ አቀረበ።
በትግራይ ክልል ያለውን የፖለቲካ የሥልጣን ክፍተት ለመሙላትና ተቋማዊ ቀጣይነትን ለማረጋገጥ ከ1 ሚሊዮን በላይ የክልሉ ነዋሪዎች የተሳተፉበት ሰፊ ውይይት መደረጉን የገለጸው የህወሃት መግለጫ፣ በዚህም መሠረት በ2012 ዓ.ም የተመረጠው የትግራይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወደ ሉዓላዊ ሥልጣኑ እንዲመለስ መወሰኑን ይፋ አድርጓል። ምክር ቤቱ ወደ ሥራው ሲመለስ አካታች የሆነ የሕግ አስፈጻሚና የዳኝነት መዋቅር እንደሚያዋቅር የተገለጸ ሲሆን፣ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች በካቢኔው ውስጥ የ33 በመቶ (አንድ ሶስተኛ) የሥልጣን ድርሻ እንዲኖራቸው ጥሪ መቅረቡም ገልጿል።
በትግራይ ክልል ያለው ሰብአዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ አሁንም እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑን የጠቀሰው ይኸው አለም አቀፍ ጥሪ፣ የፌደራል መንግስቱ በነዳጅ እና በንግድ ዕቃዎች ላይ የጣለው እገዳ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴውን ሙሉ በሙሉ ማሽመድመዱንና ከፍተኛ የዋጋ ንረትን ማስከተሉን ያብራራል። ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በትግራይ ድንበሮች ዙሪያ መጠነ-ሰፊ ወታደራዊ ዝግጅትና ከበባ እያደረገ እንደሚገኝ በመግለጽ፣ ይህ ድርጊት በሕዝቡ ላይ ከፍተኛ የስነ-ልቦና እና የማኅበራዊ ጫና እየፈጠረ መሆኑን ይከሳል።
በተመሳሳይ በምዕራብ ትግራይ የሚገኙ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዳይመለሱ በፌደራል መንግስቱና በአጋሮቹ በኩል እንቅፋት እየተፈጠረባቸው መሆኑንና ዓለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶችም ድጋፋቸውን እያቋረጡ መምጣታቸውን ሰነዱ ያስረዳል።
የቀጣናው የፖለቲካ አቅጣጫ ወደ ግትርነት፣ ወታደራዊ ኃይል አማራጭነትና አንድ ወገንተኝነት እያዘገመ በመሆኑ አዲስ ጦርነት የመቀስቀስ ስጋቱ ከአሁን በኋላ ግምታዊ ሳይሆን በተጨባጭ ከደጃፍ ላይ የደረሰ መሆኑን ሰነዱ ያስጠነቅቃል። ይህ ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኢትዮጵያ ድንበር ብቻ ሳይወሰን መላውን የአፍሪካ ቀንድ (Horn of Africa) ቀጣና ክፉኛ ሊያናጋ እንደሚችል በማመልከት፣ የጋራ ሰላምን ለማውረድ አሁንም ቢሆን የትግራይ መስተዳድር እና ህወሃት ለውይይት ዝግጁ መሆናቸውን በመግለጽ፣ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሁለቱንም ወገኖች ወደ ድርድር ጠረጴዛ ለማምጣት ዲፕሎማሲያዊ ተጽዕኖውን እንዲጠቀም ጥሪ አቅርቧል።

8 hours ago
በሚቀጥሉት ቀናት የክረምት ዝናብ ስርጭት
በሚቀጥሉት ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ የሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ የኢትዮጵያ የሚቲዮሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
የኢትዮጵያ የሚቲዮሮሎጂ ኢንስቲትዮት ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው በሚቀጥሉት ቀናት ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይጠበቃል።
እርጥበታማው የአየር ሁኔታ ከቀን ወደ ቀን በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብና በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው ያመላክታል።
የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ የሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች እና የደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎችን የሚሸፍን ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙም አስታውቋል።
በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ከ30 ሚሊ ሜትር በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖርም አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች እንደሚያሳዩ ገልጿል።
በሌላ በኩል በተለይም የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት በአፋር ክልል፣ በሰሜንና ደቡብ ምዕራብ የአገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከ32 እስከ 40 ዲግሪ ሴሊሺየስ በላይ ይሆናል።

9 hours ago
የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ አዋጅ ስልጣን ተፈጻሚነት እና አፈጻጸም
በኢትዮጵያ ህግ ማእቀፍ
ፋንታሁን ደለለው የህግ ባለሙያ
መግቢያ #ethiopia | የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓለማ የሃገራችን ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦችን የእኩልነት መብታቸው ተጠብቆ ወግ፣ ባህልና ሃይማኖታቸው ተከብሮላቸው በፍላጎታቸው በአንድነት የሚኖሩ በኢፊድሪ ህገ መንግስት እውቅና የተሰጠው ሲሆን በሰንደቅ አላማ አዋጅ ቁጥር 654/2001 እና በማሻሻያው አዋጅ ቁጥር 863/2006 ዝርዝር ህጎች ተቀምጠዋል። በዚህ ጽሁፍ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ አዋጅ ምንነት ፥ አላማ ፥ ተፈጻሚነት እንዲሁም የብሔራዊ የሀዘን ቀን ሲታወጅ ያለውን አፈጻጸም በተመለከተ ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ በዚህ ጹሁፍ አስቀምጠናል።
1. የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ አዋጅ ህጋዊ መሠረት ከኢፊድሪ ህገ መንግስት አንጻር
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 3 ስር ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በሚል ርዕስ ተደንግጎ እናገኘዋለን፡፡ በዚሁ አንቀፅ ስር የሃገሪቷ ሰንደቅ አላማ ከላይ አረንጓዴ ፣ ከመሃል ቢጫ፣ ከታች ቀይ ሆኖ በመሐሉ ብሔራዊ አርማ እንደሚኖረው ደንግጓል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በሰንደቅ አላማው ላይ የሚቀመጠው ብሔራዊ አርማ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ሕዝቦች እና ሃይማኖቶች በእኩልነትና በአንድነት ለመኖር ያላቸውን ተስፋ የሚያንፀባርቅ መሆኑን የተደነገገ ሲሆን የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ህገመንግስታዊ ጥበቃ ያለው መሆኑን ያሳያል።
2. የሰንደቅ አላማ አዋጅ ቁጥር 654/2001 ይዘት
ይህ በአሁኑ ጊዜ በስራ ላይ ያለው አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በ2001 ዓ/ም የወጣ እና ከዚህ አዋጅ በፊት የነበሩ የሰንደቅ ዓላማ ህጎችን የተካ ነው፡፡ ይህ አዋጅ 6 ክፍሎች እና 28 አንቀጾችን ያካተተ ዝርዝር ህግ ነው፡፡
3. የሰንደቅ ዓላማ ሕግ ተፈፃሚነት ወሰን
በአዋጁ አንቀፅ 3 ላይ እንደተመለከተው የሰንደቅ አላማ ሕጉ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የግዛት ወሰን ዉስጥ የክልል መንግስታትና የከተማ መስተዳድሮችን ጨምሮ እና በዉጭ ሀገር በሚገኙ ኢትዮጵያውያን፣ የኢትዮጵያ ኤንባሲዎችና ቆንስላዎች፣ የኢትዮጵያ ንግድ መርከቦችና ጀልባዎች እና አውሮፕላኖች ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
በህገ መንግስቱ አንቀፅ 2 ላይ የኢትዮጵያ የግዛት ወሰን የፌደራሉን አባሎችን ወሰን የሚያጠቃልል ሆኖ በአለም አቀፍ ስምምነቶች መሠረት የተወሰነ መሆኑን ይገልፃል፡፡ በመሆኑም የሰንደቅ ዓላማ ሕጉ በሃገሪቷ ሁሉም አካባቢ እና ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ላይ ተፈፃሚነት ይኖረዋል፡፡
4. የብሔራዊ ሀዘን ቀን ትርጉም
የብሔራዊ ሀዘን ቀን የመንግሥት ኃላፊዎች በሞቱ ጊዜ
ከሚደረገው ግልጽ ድንጋጌ በቀር በአዋጁ አንቀጽ /2/ መሠረት ብሔራዊ የሀዘን ቀን የኢፊድሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያዋጅል ከማለት ውጪ የብሔራዊ ሀዘን ቀን ለማለት ምን ምን ሲያሟላ እንደሆነ በግልጽ አልተቀመጠም። ለምሳሌ ያክል በአሸባሪው የISS ንፁሃን ኢትዩጵያን በግፍ ግድያ የፈጸመባቸዉ ጊዜ ብሔራዊ ሀዘን ታውጇል።
5. የብሔራዊ ሀዘን ለማወጅ ስልጣን ያለው አካል እና የሚያበቁ ሁኔታዎች
የብሔራዊ ሀዘን ቀን አስመልክቶ በአዋጅ ቁጥር 654/2001 አንቀጽ 22 መሠረት የተደነገገ ሲሆን በንኡስ አንቀጽ አንድ ላይ እንደተደነገገው በኃላፊነት ላይ ያሉ ወይም ከኃላፊነታቸው የተነሱ ቢሆንም እንኳን የኢፊድሪ ፕሬዝዳንት ፣ ጠቅላይ ሚኒስተር ፣የምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር ከዚህ አለም በሞት በተለዩ ጊዜ የብሔራዊ ሀዘን ቀን በመሆኑ የሰንደቅ አላማ ዝቅ ስለሚል ምክር ቤቱ የብሔራዊ ሀዘን ቀን እንደሚያውጅ ተደንግጓል። ከዚህ ውጭ ባሉ ሁኔታዎች የኢፊድሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የብሔራዊ ሀዘን ቀን እንደሚወስን በንኡስ አንቀጽ ሁለት ላይ ተደንግጓል። በብሔራዊ ሀዘን ጊዜ ስለሚኖረው የሰንደቅ ዓላማ ስነስርዓት
በአንድ ሉዓላዊት ሀገር ውስጥ በተለያዩ ጊዜ ብሔራዊ የሀዘን ጊዜ /ቀን/ ሊታወጅ ይችላል፡፡
በሀገራችንም በተለያዩ ጊዜ በተለያዩ ምክንያቶች የብሔራዊ ሀዘን ቀን ታውጇል፡፡ ለምሳሌ ያክል በአሸባሪው የISS ንፁሃን ኢትዩጵያን በግፍ ግድያ የፈጸመባቸዉ ጊዜ፣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒሰቴር መለስ ዜናዊ ከዚህ አለም በሞት በተለዩ ጊዜ ሊጠቀስ ይችላል፡፡ ሌላው በቅርብ በደቡብ ክልል በጋሞ ዞን በመሬት መደርመስ ፣ መንሸራተት ህይወታቸው ላለፈ ለተጎዱ በዚህ በ2018 ዓ.ም ታውጇል።
በሃገራችን የብሔራዊ ሃዘን ቀን ሚወሰነው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ብሔራዊ የሀዘን ጊዜ ሲታወጅ የሪፐብሊኩ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ይደረጋል፡፡ ነገር ግን በማንኛውም ህዝናዊና ሀይማኖታዊ በዓላት በሚውልበት ጊዜ ሰንደቅ ዓላማው ዝቅ ብሎ እንደማይውለበለብ በአዋጅ ቀአንቀፅ 22/3/ ላይ ተደንግጓል ፡፡ ይሁን እንጂ ይህ አዋጅ ምክር ቤቱ በስራ ላይ ባልሆነ ጊዜ እንዴት እንደሚታወጅ ያልተቀመጠ በመሆኑ የአዋጅ ቁጥር 654/2001 ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 863/2006 አንቀጽ 2/2/ መሠረት
አፈ ጉባኤው የብሔራዊ ሀዘን ቀን ሊያውጅ እንደሚችል ተደንግጓል።
6. ማጠቃለያ እና የጸሀፊው አስተያየት
የሰንደቅ አላማ አዋጅ አላማው የሀገርን ክብር ፣አንድነት፣ እኩልነት አብሮ ተቻችሎ መኖርን የሚያመላክት ሲሆን በሰንደቅ አላማ ህጉ ባስቀመጠው መሠረት ከፍ ብሎ የሚውለበለብ ሲሆን የብሔራዊ ሀዘን ቀን በኢፊድሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
ሲታወጅ በደንቡ መሠረት ዝቅ የሚል ይሆናል። ይሁን እንጂ የብሔራዊ ሀዘን ቀን የሚባሉት በአዋጁ አንቀጽ 22/1/ ላይ ከተደነገጉት ከሀገር መሪዎች ውጪ በምክር ቤቱ ለሚወሰነው
የብሔራዊ ሀዘን ቀን ለማለት ምን ሁኔታዎች ሲሟሉ እንደሆነ በህጉ በግልጽ ያልተቀመጠ በመሆኑ በመመሪያ ለወጥነት አፈጻጸም በግልጽ ቢቀመጥ የተሻለ የሚሆን ነው።
ማጣቀሻዎች/References/
1. የኢፊድሪ ህገመንግስት አዋጅ ቁጥር 1987
2. የሰንደቅ ዓላማ አዋጅ ቁጥር 654/2001
3. የሰንደቅ ዓላማ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 863/ 2006
ፋንታሁን ደለለው የህግ ባለሙያ 0929101037

11 hours ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ዛሬ ጌታቸው ረዳ በቲአርቲ ቴሌቭዥን የተናገራቸውን ማቅረባችን ይታወሳል። ለጌታቸው ረዳ በዛው ቲሌቭዥን የሰጠውን ምላሽ ተከትሎ ከቀረቡት መካከል የአማራ ማህበር በሰሜን አሜሪካ አባሉ ሮቤል ዓለሙ አንዱ ነው። እርሱ የሰጠው አስተያየት እንደሚከተለው ቀርቧል።
"ሰኞ ዕለት [የምርጫው ቀን] የታየው ነገር የዲሞክራሲ አስመሳይነት ነበር፤ ምክንያቱም በኢትዮጵያ ያለው የአሁኑ እውነታ ከዚያ የራቀ ነው። ይህን ለመረዳት የዐቢይ አሕመድን አስተዳደር የሰብዓዊ መብት አያያዝ ታሪክ መመልከት ብቻ በቂ ነው፣ ይህም በዓለም ላይ ካሉ በጣም አስከፊዎች መካከል ይመደባል። እንደ ምሳሌ ብንወስድ... ባለፉት አምስት ዓመታት የታጠቁ ግጭቶች ሲካሄዱበት በነበረው፣ እና ባለፉት ሦስት ዓመታት ደግሞ በዐቢይ 'የኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ' አስተዳደር ሥር ባሉ የመንግሥት ኃይሎች በኩል የአማራ ክልል የዕለት ተዕለት የጭካኔ ድርጊቶች እያስተናገደ ይገኛል። ባለፈው ወር የለምኪን ኢንስቲትዩት የዐቢይ ጦርነት በአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ነው በማለት የዘር ማጥፋት ማስጠንቀቂያ አውጥቷል፤ እናም ድርጅታችን በመንግሥት ኃይሎች የጤና ጣቢያዎችን፣ ትምህርት ቤቶችን፣ ቤቶችን፣ የአምልኮ ቦታዎችን እና ሌሎች የሲቪል ተቋማትን ዒላማ ያደረጉ፣ እና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለሞት የዳረጉ ከ370 በላይ የአየር ድብደባዎችን መዝግቧል። የቅርብ ጊዜ የቢቢሲ ሪፖርት ከአነስተኛ የጤና ማዕከላት በተወሰደ ናሙና፣ በአማራ ክልል በሺዎች የሚቆጠሩ የአስገድዶ መድፈር ጉዳዮችን ያሳየ ሲሆን፣ አብዛኛዎቹ በመንግሥት ኃይሎች የተፈጸሙ መሆናቸው ተመላክቷል። ባለፈው ሳምንትም፣ የጤና እና የግጭት ጥበቃ ጥምረት በጤና አጠባበቅ ላይ እየጨመረ ያለውን ጥቃት የሚያሳይ ሪፖርት አውጥቷል።
"ዩኒሴፍ ከ9 ሚሊዮን በላይ ልጆች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን ሪፖርት አድርጓል፣ ከነዚህ ውስጥ ግማሹ ከአማራ ክልል ናቸው። እናም በአጎራባች ኦሮሚያ ክልል፣ በብሔረሰብ አማራዎች እና በኦርቶዶክስ ክርስቲያን ማኅበረሰቦች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ቀጥሏል። ምርጫው ዕለትም በምስራቅ አርሲ አካባቢ የነቃ ጭፍጨፋ ሲካሄድ፣ የአካባቢው ታጣቂዎች ተሳታፊ ሆነዋል። በወለጋ አካባቢ ደግሞ በፌዴራል እና በኦሮሚያ ክልል ኃይሎች በኩል ቀጣይነት ያለው ጥቃት እና የከበባ ሁኔታ ይታያል። ስለዚህ በጣም አሳሳቢ የሆነ የሰብዓዊ መብት ቀውስ አለ፣ የፖለቲካ ብዝሃነት የለም፣ የሐሳብ ነጻነት የለም፣ የተዘጋ የሲቪክ ምህዳር አለ፣ ነጻ ፕሬስ የለም፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በአማራ ማንነታቸው፣ በፖለቲካዊ እምነታቸው ታስረዋል፣ ወይም በአንዳንድ ሁኔታዎች ያለምንም ምክንያት ታስረዋል። ከእነዚህም መካከል የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፣ የፓርላማ አባላት፣ ነጻ ጋዜጠኞች፣ የሲቪል ማኅበረሰብ መሪዎች ይገኛሉ፤ እነዚህ ሰዎች በጣም ከባድ በደል ይደርስባቸዋል።"

21 hours ago
የምርጫው ሰላማዊነት የመተባበር ውጤት ነው - የክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊነት የመተባበር ውጤት ነው አለ።
የጋራ ምክር ቤቱ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሂደት በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል።
የምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ አብዱሰላም ሸንገል እንደገለጹት፤ የዘንድሮው ምርጫ ከዝግጅት ጀምሮ የተሻለ ሂደት አለው።
ምርጫው ያለምንም ችግር በሰላም መጠናቀቁ የሚያስደስት መሆኑን ገልጸው፤ በድምጽ መስጫ ዕለት ህብረተሰቡ ከማለዳ ጀምሮ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ድምጹን በመስጠት ያሳየው ጽናት የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል።
በክልሉ ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ለተወጡ ዜጎች፣ ለጸጥታ፣ ለፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ለሲቪክ ማኅበራት እና ለምርጫ አስፈጻሚዎች ምስጋና አቅርበው፤ የምርጫው ሰላማዊነት የመተባበር ውጤት መሆኑን ገልጸዋል።
የጋራ ምክር ቤቱ በሂደቱ ትኩረት ሰጥቶ የድርሻውን መወጣቱንም አንስተዋል።

Sponsored by
Surafel
22 hours ago
የንፁሀን እልቂት በቃ ሊባል ይገባል!!
በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን በአሰኮ ወረዳ፣ በሺርካ ወረዳ እና ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ ታጣቂዎች ንፁሀን የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮችን በመግደል በርካቶችን ከቤት ንብረታቸው ማፈናቀላቸውን በመስማቴ እጅግ አዝኛለው::
ይህን ሰይጣናዊ የጥፋት ተግባርም በፅኑ አወግዛለሁ::
በአርሲ በተደጋጋሚ ንፁሀኖችን ኢላማ ያደረገ ጥቃት እየተበራከተ በየጊዜው ለቅሶ እና ዋይታ ብቻ እየተሰማ ያለ መፍትሄ መቀጠሉ እጅግ ያሳምማል::
ንፁሃን ዜጎች እያለቁ ያለው ከውጪ በመጣ ወራሪ ጠላት ሳይሆን ወንድም ወንድሙ ላይ እየሰነዘረው ባለው አሳዛኝ ከጭካኔ ጥቃት ነው::
በሀገሩ ምድር በድህነት ህይወቱን እየመራ ለሚገኝ ንፁህ ህዝብ ከግራ እና በቀኝ ጠብመንጃ በታጠቁ ሃይሎች በማያውቁት አጀንዳ ለሞት፣ ለእልቂት፣ ለስደት መዳረጉ ልብ ሰባሪ ነው::
ይህ የንፁሀን እልቂት በቃ ሊባል ይገባል!!
ሁሉም ኢትዮጵያዊ የዚህ መሰሉን እልቂት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስቆም እጅ ለእጅ ተያይዞ ሊቆም ይገባል::
በአርሲ በተደጋጋሚ እየተፈፀመ በሚገኘው ጥቃት ህይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን ቤተሰቦች መፅናናትን እመኛለው::
ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችንም ቶሎ ያገግሙ ዘንድ አላህ እንዲረዳቸው እንዲሁም የተፈናቀሉትም ወደቄያቸው ደህንነታቸው ተጠብቆ ባስቸኳይ ይመለሱ ዘንድ ልባዊ ምኞቴ ነው::
አላህ ሀገራችንን እና ወገኖቻችንን ይጠብቅልን::
ሰላም መግባባቱንና መተዛዘኑን በመላው ሀገራችን ሀያሉ ጌታችን አላህ(ሱ.ወ) ያስፍንልን
ኡስታዝ አቡበከር

23 hours ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑክ በኢትዮጵያ ጁን 1 ቀን 2026 በተካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ያደረገውን ምልከታ መነሻ በማድረግ የመጀመሪያ ደረጃ መግለጫውን ጁን 3 ቀን 2026 በአዲስ አበባ ከተማ ይፋ አድርጓል።
ልዑኩ በቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የተመራ ሲሆን፣ በቀድሞው የናይጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄፍሪ ኦንያማ ደግሞ በምክትል ኃላፊነት ተደግፏል። ቡድኑ 61 በመቶ ሴቶችን ያካተተ 73 የአጭር ጊዜ ታዛቢዎችን የያዘ ሲሆን፣ ከ35 የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡት እነዚህ ታዛቢዎች አዲስ አበባ፣ ኦሮሚያ፣ ድሬዳዋ፣ ሲዳማ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ፣ ሐረሪ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ሶማሌን ጨምሮ በስምንት የኢትዮጵያ ክልሎች ስምሪት አድርገዋል። በአጠቃላይ 27 የታዛቢ ቡድኖች በ38 የምርጫ ክልሎች በሚገኙ 495 የምርጫ ጣቢያዎች ተዘዋውረው የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱን በቅርበት ታዝበዋል።
ከምርጫው በፊት የነበሩ ሁኔታዎችን በተመለከተ መግለጫው እንዳብራራው፣ ለምርጫው 54 በመቶ ወንዶች እና 46 በመቶ ሴቶችን ያካተተ 50.5 ሚሊዮን መራጮች የተመዘገቡ ሲሆን፣ ይህ አሃዝ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስቀምጦት ከነበረው የ40 ሚሊዮን መራጮች ግብ ብልጫ አሳይቷል። በምርጫው 47 የፖለቲካ ፓርቲዎች እና 73 በግል የገቡ ዕጩዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 10,934 ዕጩዎች የተወዳደሩ ቢሆንም፣ በጸጥታ ችግር ምክንያት በትግራይ ክልል እንዲሁም በአንዳንድ የኦሮሚያ እና የአማራ ክልል አካባቢዎች ምርጫው ሳይካሄድ ቀርቷል።
የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱን በተመለከተ ታዛቢ ልዑኩ እንዳረጋገጠው፣ 70 በመቶ የሚሆኑት የምርጫ ጣቢያዎች ልክ በጠዋቱ 06:00 በሰዓቱ ተከፍተዋል። በ99 በመቶ የምርጫ ጣቢያዎች የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ሰላማዊ በሆነ መንገድ የተካሄደ ሲሆን፣ በ97 በመቶ ጣቢያዎች ደግሞ የጸጥታ አካላት በስፍራው ተገኝተው ሙያዊ ሥነ-ምግባር በተላበሰ መልኩ ደህንነትን አስጠብቀዋል። ሆኖም ከምሽቱ 18:00 የድምጽ መስጫ ሰዓት መጠናቀቅ በኋላ 88 በመቶ በሚሆኑ ጣቢያዎች መራጮች አሁንም ተሰልፈው ስለነበር፣ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የድምጽ መስጫ ሰዓቱን እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ በ6 ሰዓታት እንዲራዘም አድርጓል።
የተፈናቃዮች እና የጸጥታ አካላት አባላት ልዩ የድምጽ አሰጣጥ ጁን 8 ቀን 2026 የሚካሄድ መሆኑን የጠቆመው መግለጫው፣ የመጨረሻው ይፋዊ የምርጫ ውጤት ጁን 11 ቀን 2026 ይገለጻል ተብሎ እንደሚጠበቅ አመላክቷል። በመጨረሻም የአፍሪካ ኅብረት ታዛቢ ልዑክ የኢትዮጵያ መንግሥት፣ የፖለቲካ ተዋንያን እና ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር እና ዴሞክራሲን ለማጎልበት ሁሉን አቀፍ እና ዘላቂ የፖለቲካ ውይይት እንዲያደርጉ በማበረታታት የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱን አጠቃልሏል።

24 hours ago
የንፁሀን እልቂት በቃ ሊባል ይገባል!!
በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን በአሰኮ ወረዳ፣ በሺርካ ወረዳ እና ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ ታጣቂዎች ንፁሀን የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮችን በመግደል በርካቶችን ከቤት ንብረታቸው ማፈናቀላቸውን በመስማቴ እጅግ አዝኛለው:: ይህን ሰይጣናዊ የጥፋት ተግባርም በፅኑ አወግዛለሁ
በአርሲ በተደጋጋሚ ንፁሀኖችን ኢላማ ያደረገ ጥቃት እየተበራከተ በየጊዜው ለቅሶ እና ዋይታ ብቻ እየተሰማ ያለ መፍትሄ መቀጠሉ እጅግ ያሳምማል::
ንፁሃን ዜጎች እያለቁ ያለው ከውጪ በመጣ ወራሪ ጠላት ሳይሆን ወንድም ወንድሙ ላይ እየሰነዘረው ባለው አሳዛኝ ከጭካኔ ጥቃት ነው::
በሀገሩ ምድር በድህነት ህይወቱን እየመራ ለሚገኝ ንፁህ ህዝብ ከግራ እና በቀኝ ጠብመንጃ በታጠቁ ሃይሎች በማያውቁት አጀንዳ ለሞት፣ ለእልቂት፣ ለስደት መዳረጉ ልብ ሰባሪ ነው::
ይህ የንፁሀን እልቂት በቃ ሊባል ይገባል!!
ሁሉም ኢትዮጵያዊ የዚህ መሰሉን እልቂት ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስቆም እጅ ለእጅ ተያይዞ ሊቆም ይገባል::
በአርሲ በተደጋጋሚ እየተፈፀመ በሚገኘው ጥቃት ህይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን ቤተሰቦች መፅናናትን እመኛለው::
ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችንም ቶሎ ያገግሙ ዘንድ አላህ እንዲረዳቸው እንዲሁም የተፈናቀሉትም ወደቄያቸው ደህንነታቸው ተጠብቆ ባስቸኳይ ይመለሱ ዘንድ ልባዊ ምኞቴ ነው
አላህ ሀገራችንን እና ወገኖቻችንን ይጠብቅልን::
ሰላም መግባባቱን እና መተዛዘኑን በመላው ሀገራችን ሀያሉ ጌታችን አላህ(ሱ.ወ) ያስፍንልን
ኡስታዝ አቡበከር አህመድ

በሚቀጥሉት ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገራችን አካባቢዎች ከቀላል እስከ ከባድ ዝናብ ያገኛሉ
*****************
በሚቀጥሉት ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገራችን አካባቢዎች ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚጠበቅ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
ኢንስቲትዩቱ እንዳስታወቀው እርጥበታማው የአየር ሁኔታ ከቀን ወደ ቀን እየተጠናከረ በመምጣት በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛው እና በደቡብ ምሥራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የተሻለ የዝናብ ስርጭት ይኖራቸዋል።
በተለይም በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በመካከለኛው የሀገራችን ክፍሎች ከ30 ሚሊ ሜትር በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖር አኃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ።
በሌላ በኩል የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት በአፋር ክልል፣ በሰሜን እና በደቡብ ምዕራብ ዝቅተኛ ቦታዎች ላይ ከ32 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሆኖ እንደሚቀጥል ተገልጿል።
በመደበኛ ሁኔታ ወቅታዊው የክረምት ዝናብ ቀደም ብሎ በምዕራብና በደቡብ ምዕራብ አጋማሽ የሀገራችን ክፍሎች ላይ የሚጀምር ሲሆን፣ በሂደት እየተጠናከረ የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ ሌሎች አካባቢዎችም እንደሚስፋፋ ተጠቁሟል።
በዚህም መሠረት በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛው እና በምሥራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ዝናቡ በመጠንም ሆነ በስርጭት የተሻለ እንደሚሆን ይጠበቃል።
ይህ የሚኖረው እርጥበት ለግብርና ሥራ የማሳ ዝግጅት ለማድረግ፣ የመኸር ሰብሎችን ለመዝራት እንዲሁም ለበልግ ሰብል ተጠቃሚ አካባቢዎች መልካም አጋጣሚን እንደሚፈጥር ኢንስቲትዩቱ ጠቁሟል።
በሚቀጥሉት አሥር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገራችን ተፋሰሶች ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው የገጸ ምድር የውኃ ፍሰት እንደሚኖርም ታውቋል።
በዚህም መሠረት በመካከለኛው እና ታችኛው አባይ፣ በላዩኛው እና መካከለኛው ባሮ አኮቦ፣ በላዩኛው ስምጥ ሸለቆ፣ በኦሞ ጊቤ፣ በአዋሽ እንዲሁም በገናሌ ዳዋ ተፋሰሶች ከመካከለኛ እስከ ከባድ የገጸ ምድር የውኃ ፍሰት እንደሚጠበቅ ተጠቅሷል።
በተመሳሳይ በላይኛው አባይ፣ በኦጋዴን፣ በመካከለኛው አዋሽ፣ በስምጥ ሸለቆ እና በኦሞ ጊቤ ተፋሰሶች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው የገጸ ምድር የውኃ ፍሰት እንደሚኖራቸውም ኢንስቲትዩቱ ለኢዜአ ገልጿል።
#ethiopiaweather #rainny #sunny

1 day ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኩዌት መከላከያ ሚኒስቴር ከማለዳ ጀምሮ ከኢራን ተነስተው ወደ አገሪቱ የአየር ክልል የገቡ 13 ባሊስቲክ ሚሳኤሎችን እና 17 ድሮኖችን በተሳካ ሁኔታ ማክሸፉን በይፋ አስታውቋል። ሚኒስቴሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ባሰፈረው አስቸኳይ መረጃ መሠረት፣ እነዚህ የአየር ላይ መጥለፎች የተከናወኑት "በተለያዩ የመኖሪያ አካባቢዎች" ላይ በመሆኑ፣ በጥቃቱ ማክሸፍ ሒደት የተከሰከሱ የብረትና የተተኳሽ ፍርስራሾች በሰዎች መኖሪያ መንደሮች ላይ ወድቀዋል።
ይህ ክስተት በመካከለኛው ምስራቅ በፍጥነት እየተባባሰ የመጣውን ከባድ የጸጥታ ቀውስ እና በንጹሃን ዜጎች ሰላማዊ ሕይወት ላይ የተጋረጠውን ከፍተኛ አደጋ በተግባር የሚያሳይ እጅግ አሳሳቢ ክስተት ሆኗል። ሚኒስቴሩ በፈነዱትና በወደቁት ፍርስራሾች ሳቢያ ተጨማሪ አደጋ እንዳይከሰት በማስጠንቀቅ፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ጉዳት ወደደረሰባቸው እና ፍርስራሽ ወደወደቀባቸው የጥቃት ቀጠናዎች በፍጹም እንዳይቀርቡ በጥብቅ አሳስቧል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ታዋቂዋ ኢትዮጵያዊት አርቲስት መሰረት መብራቴ፣ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ አርሲ ዞን በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ላይ እየደረሰ ያለውን ተደጋጋሚ ጥቃት፣ መፈናቀል እና ግድያ በተመለከተ መንግሥትን እና የፍትሕ አካላትን ክፉኛ የሚወቅስ ጠንካራ መልእክት አስተላለፈች። አርቲስቷ በማኅበራዊ ትስስር ገጿ ባጋራችው እና በማህበራዊ ትሥሥር ላይ በግልጽ በሚታየው ጽሁፍ፣ የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ ያልቻለውን ሥርዓት እና የሕግ ማስከበር ክፍተቱን በጽኑ ተችታለች።
በመልእክቷም "የኦርቶዶክሳውያን ሞትና መከራ እስከመቼ?!" በማለት መሠረታዊ የፍትሕ ጥያቄ ያነሳች ሲሆን፣ ምስራቅ አርሲን "የደም ምድር" ስትል ገልጻዋለች። ድርጊቱ ማቆሚያ የሌለው እልቂት እና ሰሚ የሌለው ጩኸት መሆኑን የጠቀሰችው አርቲስቷ የንጹሃን ደም ፍትሕ እየጠየቀ መሆኑን በአጽንኦት አስገንዝባለች። በተለይም በመልእክቷ ላይ "ከምድራዊ ዳኛ ፍትህ ባናገኝ፣ የሰማዩ አምላክ ይፈርዳችኋል!!!" በማለት ያሰፈረችው ሐሳብ የሕግ የበላይነት መጓደልን እና ምድራዊ የፍትሕ ተቋማት የዜጎችን ደህንነት በማስጠበቅ ረገድ ያሳዩትን ደካማ አፈጻጸም በቀጥታ የሚሞግት ወሳኝ መልእክት ነው።
በቅርብ ዓመታት በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በምስራቅ አርሲ እና አካባቢው ማንነትን እና ሃይማኖትን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች መበራከታቸውን የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፣ የሃይማኖት ተቋማት እና እንደ ኢዜማ፣ እናት ፓርቲ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተደጋጋሚ ሲገልጹ ቆይተዋል። በእነዚህ ክስተቶች የተነሳ በርካታ ዜጎች ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን፣ አያሌዎች ደግሞ ከቀያቸው ተፈናቅለው ለከፍተኛ እንግልት ተዳርገዋል።
በዚህ አውድ ውስጥ የሀገሪቱ ታዋቂ ግለሰቦች እና የኪነ-ጥበብ ሰዎች ከዝምታ ወጥተው ድምፃቸውን ማሰማት መጀመራቸው ትልቅ ትርጉም አለው። እንደ መሰረት መብራቴ ያሉ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰዎች እንዲህ ያሉ የአደባባይ ጩኸቶችን ማሰማታቸው፣ ችግሩ ብሔራዊ ትኩረት እንዲያገኝ ከማድረጉም ባለፈ የፍትሕ ተቋማት እና የጸጥታ ኃይሎች በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት በአፋጣኝ አምነው ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ ከፍተኛ ማኅበራዊ ጫና ይፈጥራል።
አርቲስት መሰረት መብራቴ "ወገኖቼ ነፍሳችሁን በቅዱሳን እቅፍ ይቀበለው" በማለት በግፉ ሕይወታቸውን ላጡ ንጹሃን ዜጎች ያላትን ጥልቅ ሀዘን በመግለጽ መልእክቷን አጠቃላለች።

የንጹኃን ደም እየፈሰሰ "መረጃ የለንም" የሚሉ አስተዳዳሪዎች — የመንግሥት መዋቅር የሞራል ክስረት!
በአርሲ ሀገረ ስብከት ሦስት ወረዳዎች ውስጥ የንጹኃን ኦርቶዶክሳውያን ደም በገዛ ቀያቸው እንደ ጎርፍ በፈሰሰበት፣ የ101 ዓመት ታሪካዊ ቤተ ክርስቲያን በደመኛ እሳት በጋየበት እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ሜዳ ላይ በተጣሉበት በዚህ አስከፊ ሰዓት፤ የመንግሥት መዋቅር ያሳየው ፍጹም ደንታ ቢስነት እና ቸልተኝነት የኃላፊነት ብቻ ሳይሆን የሞራል ክስረት መድረሱን በግልጽ ያሳያል።
የሟቾች ስም ዝርዝር፣ ዕድሜያቸው እና የተገደሉበት ወረዳ ሳይቀር ተለይቶ በይፋ እየተነገረ ባለበት ሁኔታ፣ የአካባቢው መሪዎች እና የክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት "መረጃ የለንም" እና "እናጣራለን" የሚሉ ሰበቦችን ማቅረባቸው በቁስል ላይ እንጨት የመስደድ ያህል አሳፋሪ ድርጊት ነው።
ቢቢሲ ስለደረሰው አረመኔያዊ ጥቃት መረጃ ለመጠየቅ ወደ ኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ እና የክልሉ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አራርሳ መርዳሳ በተደጋጋሚ ቢደውልም ስልካቸውን ዘግተው መቀመጣቸው፣ የመንግሥት ባለሥልጣናት ዜጎች ሲታረዱ ከተጠያቂነት እና ከሕዝብ ጥያቄ ለመሸሽ የትጥቅ ያህል የሚጠቀሙበት የተለመደ አድርባይነት ማረጋገጫ ነው።
ከሁሉም በላይ ግን፣ ጥቃቱ ከተፈጸመባቸው ግንባር ቀደም ቀጠናዎች አንዱ በሆነው በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ የገዛ ነዋሪዎቹ እነ አቶ ንጉሱ ማንደፍሮ እና አቶ በቀለ ኃ/ሚካኤል ተለይተው ሲታረዱ፣ የወረዳው አስተዳዳሪ ሐሰን መሐመድ "መረጃ የለንም" ማለታቸው ፍጹም የሚያስጠይቅና የሚያስቆጣ ነው።
እዚህ ላይ በግልጽ ሊጠየቁ የሚገቡ ጠንከር ያሉ ጥያቄዎች አሉ፦
አንድ የወረዳ አስተዳዳሪ የገዛ ወረዳው ነዋሪዎች ተለይተው ሲታረዱና አብያተ ክርስቲያናት ሲጋዩ መረጃ ከሌለው፣ የዚህ አስተዳዳሪና የመዋቅሩ ጥቅሙ ምንድን ነው? ወንበሩ ላይ የተቀመጠው ሕዝብን ለመጠበቅ ነው ወይስ ሬሳ ለመቁጠር?
የአርሲ ዞን ኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሶሪ ወጊ "እስከአሁን የደረሰን መረጃ የለም" ሲሉ፣ ይህ የዞን መዋቅር ከሕዝቡ ሰቆቃ እና ከገዳዮች እኩል ርቀት ላይ መሆኑን እያመኑ አይደለምን?
የንጹኃን ደም እየጮኸ፣ እናቶች ጽላት አቅፈው በየበርሃው እየተሰደዱ ባሉበት አንገብጋቢ ወቅት፣ መረጃን ለመሸሸግ መሞከር ገዳዮችን በተዘዋዋሪ ከማበረታታት አይተናነስም። ዜጎችን ከጥቃት መከላከል ያልቻለ መዋቅር፣ ቢያንስ የደረሰውን ጥፋት አምኖ በአስቸኳይ ፍትሕ ከመስጠት ይልቅ "አላወቅንም" በሚል ድንቁርና ራሱን ነፃ ለማውጣት መሞከሩ በታሪክም በሕግም የሚያስጠይቅ ከባድ የቅሌት ማህተም ነው።

(ከተዋሕዶ ወርልድ) የአርሲ ተራሮች ለዘመናት የሰላም፣ የግብርና እና የአብሮነት ምልክት ሆነው ኖረዋል። የጠዋቱ ጸሐይ ሲወጣ የከብቶች ጩኸት፣ የእረኞች ዜማ እና የቤተ ክርስቲያን የደወል ድምፅ ተቀናጅተው መንፈስን የሚያድስ ተስፋን ይሰጡ ነበር። ዛሬ ግን... ዛሬ ከእነዚህ ተራሮች ጀርባ የሚወጣው ጭስ የዕጣን አይደለም፤ የቃጠሎ ነው። ዛሬ የሚሰማው ድምፅ የዝማሬ ሳይሆን የእንባ እና የዋይታ ነው። ከግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በአርሲ ሀገረ ስብከት በአሰኮ፣ በሺርካ እና በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳዎች ላይ ያንዣበበው የሞት ጥላ፣ ንጹሐንን በግፍ ቀጥፏል፤ ታሪካዊ መቅደሶችንም ወደ አመድነት ቀይሯል።
ይህ የተዋህዶ ወርልድ ትንታኔ የቁጥሮች ድምር አይደለም፤ የ13 የከበሩ የሰው ልጆች ሕይወት መነጠቅ፣ የ101 ዓመት ታሪክ መቃጠል፣ እና የ280 ዜጎች በባዶ እጅ መሰደድ ታሪክ እንጂ። ይህ፣ ሃይማኖት እና ማንነትን መሠረት አድርጎ የሚፈጸም አክራሪነት የሰውን ልጅ ምን ያህል ወደ አውሬነት እንደሚቀይረው የሚያሳይ የዘመናችን ህያው ማሳያ ነው።
የጠላታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያንን እናስበው። ለ101 ዓመታት ሙሉ፣ አባቶች እና እናቶች በደጃፉ ተንበርክከው ፈጣሪያቸውን ተማጽነዋል። በዚያ መቅደስ ውስጥ ስንቱ ተጠምቋል? ስንቱ ተክሊል አስሯል? ስንቱስ በጸሎት ተጽናንቷል? ከአንድ ምዕተ ዓመት በላይ የቆመው ይህ የጸጋ ቤት፣ የበርካታ ትውልዶች የእምነት ማህደር ነበር። ነገር ግን፣ ጥላቻ ታሪክን አያውቅም፤ ክፋት ቅድስናን አይረዳም። በአንድ ጀንበር፣ ያ ሁሉ ታሪክ፣ ያ ሁሉ የእንጨት ጠረንና የዕጣን መዓዛ፣ በጭካኔ እሳት ተበላ።
በሌላ በኩል ደግሞ የካራ ኩፍተና መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ዕጣ ፈንታ ሌላ ልብ ሰባሪ ትዕይንት ነበር። ታጣቂዎች መቅደሱን ሲዘርፉ፣ አማኞች የራሳቸውን ሕይወት እና ንብረት ለማዳን አልተጣደፉም። ይልቁንም፣ መኖሪያ ቤታቸው እያዩት በእሳት ሲጋይ፣ የዕድሜ ልክ ጥሪታቸው፣ ከብቶቻቸውና ማሳቸው ሲዘረፍ፣ እነርሱ ግን ከሁሉ የሚያስበልጡትን የቤተ ክርስቲያኑን ጽላት (ታቦት) በደረታቸው አቅፈው በጨለማ ወደማያውቁት ስደት መጓዝን መረጡ።
ይህ ትዕይንት ወደ ኋላ መለስ ብለን የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪክ እንድናስታውስ ያደርገናል። እስራኤላውያን ታቦተ ጽዮንን ተሸክመው በበረሃ እንደተጓዙት ሁሉ፣ የአርሲ ምእመናንም አምላካቸውን በደረታቸው አቅፈው መከራውን ተቀበሉ።
ሞት በቁጥር ሲገለጽ ስሜት አይሰጥም፤ ነገር ግን እያንዳንዱ ቁጥር ከጀርባው ቤተሰብ፣ ተስፋ እና ህልም አለው። በአጠቃላይ 13 ንጹሐን ኦርቶዶክሳውያን በግፍ ተገድለዋል።
የ80 ዓመቱን አቶ አማረ በላይነህን እንመልከት። እኚህ አረጋዊ በህይወት ዘመናቸው ስንት መንግስታትን አይተዋል? ስንት የሀገር መከራን አሳልፈዋል? በስተእርጅናቸው ዘመን ክፋት አላርፍ ብሎ አስጨናቂ ሞትን አመጣባቸው። የ70 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ የሆኑት አቶ ደምረው አበራ፣ አቶ ሐይሉ ንጉሴ እና አቶ ሰሙ አባይነህም እንዲሁ የዚህ ጭካኔ ሰለባ ሆነዋል። እነዚህ አባቶች ለሀገር ምርቃት እንጂ መርገም ያልነበሩ፣ በእምነታቸው ጸንተው የኖሩ የሰላም ሰዎች ነበሩ።
እንደነ እሸቴ ዳመና (42 ዓመት) እና አበባየሁ ዳኜ (42 ዓመት) ያሉ የጎልማሳነት ዘመናቸው ላይ የነበሩ አባወራዎች ሲገደሉ፣ ከጀርባቸው ስንት ቤተሰብ በትነው እንደሄዱ ማሰብ ያሳምማል። ገና ለሀገር እና ለወገን ይደርሳሉ የተባሉ ወጣቶችም የዚህ ጽዋ ቀማሾች ሆነዋል። ተሬ ደሴ (የ25 ዓመት ወጣት)፣ ገነነ ጥላሁን እና ሙርቴሳ ጥላሁን በሺርካ ወረዳ ሕልማቸው ተጨናግፎ፣ ደማቸው በመሬት ላይ ፈሷል።
አቶ ንጉሱ ማንደፍሮ፣ አቶ በቀለ ኃ/ሚካኤል፣ ከፈለኝ ልክየለው... እነዚህ ስሞች ዝም ብለው በወረቀት ላይ የሰፈሩ አይደሉም። እነዚህ አባቶች ያሏቸው፣ እናቶች ያሳደጓቸው፣ ልጆች የሚጠብቋቸው ነፍሶች ነበሩ። በሃይማኖታቸው ምክንያት ብቻ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ።
ይህ ዓይነቱ እምነትን መሠረት ያደረገ መከራ፣ በዓለማችን ታሪክ አዲስ አይደለም። የሰው ልጅ በፈጣሪው በማመኑ ብቻ የተከፈለው ዋጋ ብዙ ነው።
ወደ ሩቅ ጎረቤት ሀገር ግብጽ ስንሄድ የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ለዘመናት በእምነታቸው ምክንያት ከፍተኛ ዋጋ ሲከፍሉ ኖረዋል። በተለይም እ.ኤ.አ. በ2015 በሊቢያ የባህር ዳርቻ አይ ኤስ በተባለው አሸባሪ ቡድን የታረዱት 21 የግብጽ ኮፕቲክ ክርስቲያኖችን ዓለም መቼም አይረሳም። ቢላዋ በአንገታቸው ላይ ሲያርፍ እንኳን የፈጣሪያቸውን ስም እየጠሩ በድፍረት ሰማዕትነትን ተቀብለዋል። የአርሲዎቹም ሰማዕታት ከዚሁ የጽናት መንገድ የወጡ አይደሉም። ኢትዮጵያውያንም በተመሳሳይ በሊቢያ እንዲሁ።
ወደ ምዕራብ አፍሪካ ስናቀና ደግሞ ናይጄሪያ እናገኛለን። በቦኮሃራም እና በአክራሪ የፉላኒ ታጣቂዎች አማካኝነት በሰሜን እና በመካከለኛው የሀገሪቱ ክፍል በሺዎች የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች አብያተ ክርስቲያናቶቻቸው ተቃጥለውባቸው፣ መንደራቸው ወድሞ በግፍ ተጨፍጭፈዋል።
የአርሜንያ የዘር ማጥፋት ታሪክም ሌላው ትልቅ ትምህርት ነው። በ1915 በኦቶማን ኢምፓየር ዘመን፣ ከአንድ ሚሊዮን በላይ አርመናውያን በክርስትና እምነታቸው እና በማንነታቸው ምክንያት ብቻ በግፍ ተጨፍጭፈዋል፣ በበረሃም ተሰደው አልቀዋል። ነገር ግን ዛሬ አርሜንያውያን ከየትኛውም ጊዜ በላይ አብበው፣ እምነታቸውንም አጽንተው ይገኛሉ። ጥይት እና እሳት ስጋን ሊገድል ይችላል፣ እምነትን እና መንፈስን ግን መቼም ሊያጠፋ አይችልም።
ታዋቂው የጥንት ቤተ ክርስቲያን ጸሐፊ ቴርቱሊያን እንዳለው፡-
"የሰማዕታት ደም የቤተ ክርስቲያን ዘር ነው።"
በአርሲ ተራሮች ላይ የፈሰሰው የነ አቶ አማረ፣ የነ ወጣት ተሬ ደሴ ደም በከንቱ አይቀርም። የቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደሚያስተምረን፣ መከራ በበዛ ቁጥር፣ መቅደሶች በነደዱ ቁጥር፣ የእምነት ስር ይበልጥ ይጠልቃል እንጂ አይደርቅም።
በእንደዚህ ዓይነት ጥልቅ ሀዘን እና የሰብአዊነት ውድቀት ውስጥ ስናልፍ፣ የሰው ልጅ ታሪክ ካፈራቸው ታላላቅ መሪዎች እና ፈላስፎች የምንማረው ብዙ ነገር አለ። ጭካኔን በጭካኔ መመለስ የትም አያደርስም።
የሰብአዊ መብት ታጋዩ ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር (የተናገረው ኃያል ቃል በዚህ ጊዜ ትዝ ይለናል፡-
"ጨለማ ጨለማን ሊያባርር አይችልም፤ ይህንን ማድረግ የሚችለው ብርሃን ብቻ ነው። ጥላቻ ጥላቻን ሊያጠፋ አይችልም፤ ይህንን ማድረግ የሚችለው ፍቅር ብቻ ነው።"
በአርሲ የተፈጸመው ድርጊት የጨለማ እና የጥላቻ ፍሬ ነው። ነገር ግን የተፈናቀሉት ምዕመናን ጽላቱን አቅፈው መውጣታቸው፣ ብርሃንን እና ፍቅርን ምርጫቸው እንዳደረጉ ያሳያል።
የሰላም ኖቤል ሽልማት አሸናፊው እና የሆሎኮስት (የአይሁዳውያን ጭፍጨፋ) ተራፊው ኤሊ ዊሰል ስለ ግፍ ዝምታ ሲናገር፡-
"ዝምታ ሁልጊዜም የሚጠቅመው አጥቂውን እንጂ ተጠቂውን አይደለም። ገለልተኝነት የሚረዳው ጨቋኙን እንጂ ተጨቋኙን አይደለም።" ብሎ ነበር።
ስለሆነም የነዚህን ንጹሐን መገደል፣ የ101 ዓመት ታሪካዊ ቅርስ መቃጠል፣ እና የ280 ሰዎች መፈናቀል እንደ ቀላል ዜና አልፈነው ልንሄድ አይገባም። ህመማቸውን ልንጋራ፣ ድምጻቸው ልንሆን ይገባል።
ታላቁ የነጻነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ ደግሞ ስለ መጽናት እንዲህ ይላሉ፡-
"ትልቁ የህይወት ክብር ያለው ፈጽሞ ባለመውደቅ ውስጥ ሳይሆን፣ በወደቅን ቁጥር ተመልሶ በመነሳት ውስጥ ነው።"
ኦርቶዶክሳውያኑ ዛሬ ቤታቸው ፈርሶ፣ ዘመዶቻቸው ተገድለውባቸው ሜዳ ላይ ወድቀው ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን እምነታቸው እስካለ ድረስ፣ ነገ ከአመዱ ላይ ተመልሰው ይነሳሉ።
በአሰኮ ወረዳ ብቻ ከ280 በላይ የሚሆኑ ዜጎች ተፈናቅለዋል። መፈናቀል ማለት መጓዝ ብቻ አይደለም። መፈናቀል ማለት ትዝታን፣ ልፋትን፣ የልጅነት የቦረቁበትን አፈር፣ እና የዘመዶችን መቃብር ትቶ መሄድ ማለት ነው። እነዚህ ሰዎች አሁን ያሉት ሜዳ ላይ ነው። የለበሱት ልብስ ብቻ ነው ያላቸው። የሌሊቱ ብርድ ሲቆራርጣቸው፣ የጠዋቱ ጸሐይ ሲያቃጥላቸው፣ የልጆቻቸው ርሃብ አንጀታቸውን ሲበላው... ያላቸው ብቸኛ መጽናኛ በደረታቸው ያቀፉት እምነታቸው ብቻ ነው።
"ስለ አንተ ሁልጊዜም ተገድለናል እንደሚታረዱም በጎች ሆነናል" (መዝሙር 43:22)። የአርሲና ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሀዘን መግለጫቸውን የጀመሩት በዚህ የዳዊት መዝሙር ነበር። ይህ ቃል የዛሬን ብቻ ሳይሆን የዘመናትን የክርስቲያኖችን ህይወት የሚገልጽ ነው።
በእርግጥም እንደ በግ ለመታረድ የተሰለፉት እነዚህ ወገኖች ጥፋታቸው ምንድን ነው? ከማንም ጋር ያልተጣሉ፣ የፖለቲካ አጀንዳ የሌላቸው፣ ኑሯቸውን ለማሸነፍ መሬት የሚጭሩ ምስኪን ገበሬዎች ነበሩ። ነገር ግን በአክራሪነት የታወረው አእምሮ ይህንን ሊረዳ አይችልም።
እሳት ሁሉንም ነገር ያወድማል፤ መጽሐፍትን ያቃጥላል፣ ግድግዳን ያፈርሳል፣ ስጋን ያጠፋል። ነገር ግን እሳት እምነትን ሊያቃጥል አይችልም። የ101 ዓመቱ የጠላታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ዛሬ በአካላዊ ገጽታው ባይኖርም፣ ያ መቅደስ የሰራው መንፈሳዊ ህንጻ ግን አሁንም በምዕመናኑ ልብ ውስጥ ጸንቶ ይገኛል።
የ13ቱ ሰማዕታት ነፍስ በሰላም ታርፋለች፤ ደማቸው ግን ለትውልድ የሚተላለፍ የጽናት ትምህርት ሆኖ ይኖራል። የተሰደዱት ወገኖቻችን ዛሬ ሜዳ ላይ ቢሆኑም፣ የታሪክ ጌታ የሆነው አምላክ ነገን አዲስ አድርጎ ይሰራላቸዋል። የጥላቻ ኃይሎች በክፋታቸው መቅደሱን አፍርሰውታል፤ ሆኖም እውነተኛዋ ቤተ ክርስቲያን የድንጋይ እና የእንጨት ክምር ሳትሆን፣ ያቺ በስደት መሃልም ጽላቷን አቅፋ የምትጓዘዋ የሰው ልጅ ልብ ናት።
እስከዚያው ግን እንደ አቡነ ኤልሳዕ ጸሎት፤ ፈጣሪ የሞቱትን ነፍስ በመንግሥተ ሰማያት ያሳርፍ፣ የተፈናቀሉትን፣ የተራቡትን እና የተራቆቱትን ደግሞ በምህረት እጁ ይጎብኝ፣ ያጽናናም። ከጭስ እና ከአመድ በስተጀርባ፣ ብርሃን አለና።

2 days ago
ቢቢሲ በአርሲ በደረሰው ጥቃት ላይ መረጃ ለመጠየቅ ለኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ እና የክልሉ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አራርሳ መርዳሳ በተደጋጋሚ ቢደውልም ስልካቸው ባለመነሳቱ ምላሽ ማግኘት አልቻለም።
ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ የአርሲ ዞን ኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑትን አቶ ሶሪ ወጊን ስለተፈጸመው ጥቃት ማክሰኞ አመሻሽ ላይ ላቀረበላቸው ጥያቄ "እስከአሁን የደረሰን መረጃ የለም፤ እናጣራለን" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ጥቃቱ ከተፈጸመባቸው አካበቢዎች አንዱ የሆነው የሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ አስተዳዳሪ ሐሰን መሐመድም ሰዎች ስለሞቱበት እና ንብረት ስለወደመበት ክስተት "መረጃ የለንም" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በድል መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገለጸ
#ethiopia | ከፍተኛ የዕጩ ተወዳዳሪዎች ቁጥር የተመዘገበበት ሰባተኛው አገራዊ ምርጫ በስኬታማ ሁኔታ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።
የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ እንደገለጹት በአሁኑ ወቅት በየምርጫ ጣቢያዎቹ የተሰጡ ድምጾችን የማደመርና ውጤቱን ይፋ የማድረግ ተግባር በመከናወን ላይ ይገኛል።
በየምርጫ ጣቢያው የተሰበሰበው ድምፅ በይፋ ከተለጠፈ በኋላ ውጤቱ ተጠቃሎ ወደ የምርጫ ክልሉ ይላካል። በምርጫ ክልል ደረጃም የድምፅ ማጠቃለል ሥራው ከተከናወነ በኋላ ውጤቱን በይፋ ለማወጅና ለማረጋገጥ ወደ ዋናው መሥሪያ ቤት የማረጋገጫ ማዕከል እንዲመጣ ይደረጋል።
ውጤቶቹ ወደ ማረጋገጫ ማዕከሉ በሚደርሱበት ወቅት የእያንዳንዱ ምርጫ ክልል መረጃ በተናጠል ተለይቶ የሚታይ ሲሆን ተወዳዳሪዎች ያገኙት የድምፅ መጠን በዝርዝር የማጣራት ሥራ በትኩረት ይከናወናል።
ሰብሳቢዋ አክለውም በማዕከሉ ውስጥ ከተመዘገበው አጠቃላይ የመራጭ ሕዝብ ቁጥር አንጻር ጸንተው የሚደመሩ፣ ዋጋ የሌላቸው እና ጥቅም ላይ ያልዋሉ የድምፅ መስጫ ወረቀቶችን የመለየት ተግባር በከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚሠራ አስታውቀዋል።
ቦርዱ ይህንን የማረጋገጥ ሒደት በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ውስጥ ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝም ሰብሳቢዋ ሜላትወርቅ ኃይሉ ገልጸዋል።
#ምርጫቦርድ #ምርጫ #የምርጫውጤት #የኢትዮጵያምርጫ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ በሰጡት መግለጫ ምን ምን ጉዳዮችን አነሱ?
**********************
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ፣ ከድምፅ መስጫ ቀን በኋላ ያለውን አጠቃላይ የምርጫ ሂደት ሁኔታና ቀጣይ ሥራዎችን አስመልክተው በሰጡት ማጠቃለያ መግለጫ በርካታ ዋና ዋና ጉዳዮችን አንስተዋል፡፡ ሰብሳቢዋ በመግለጫቸው ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፦
የድምፅ አሰጣጥ እና የቆጠራ ሂደት ወቅታዊ ሁኔታ፦ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን የተከናወነው የድምፅ መስጠት ሂደት በአብዛኛው በጥሩ ሁኔታ መከናወኑን የገለጹት ሰብሳቢዋ፣ የተወሰኑ ክልሎች በሰዓቱ አጠናቀው ወዲያውኑ ወደ ቆጠራ መግባታቸውንና አንዳንዶቹ ደግሞ ቆጠራውን አሳድረው ማከናወናቸውን ጠቅሰዋል፡፡
በተለየ ሁኔታ በአዲስ አበባ በነበረው ረጅም ሰልፍ ምክንያት ቦርዱ እስከ ሌሊቱ 6፡00 ሰዓት ድረስ የጊዜ ማራዘሚያ ማድረጉንና በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ እንዲሁም በሲዳማ፣ በጋምቤላ፣ በአማራ እና በሶማሌ ክልሎች የሚገኙ የተወሰኑ ምርጫ ጣቢያዎች አሁንም በድምፅ ቆጠራ ሥራ ላይ እንደሚገኙ አብራርተዋል፡፡
የመዘግየት ችግሮች እና የተወሰዱ የመፍትሔ እርምጃዎች፦ በአዲስ አበባ የተስተዋለውን የሰልፍ መርዘምና የመዘግየት ችግር ለመፍታት ቦርዱ በርካታ ከፍተኛ ባለሙያዎችንና ኤክስፐርቶችን ወደ ጣቢያዎች መድቦ እንደነበር ሰብሳቢዋ አስታውቀዋል፡፡
ለመዘግየቱ እንደ ምክንያት ያነሷቸው ዋና ዋና ጉዳዮች በመራጮች መዝገብ ላይ ስም የመፈለግ ሂደት መርዘም እና በአንዳንድ ጣቢያዎች የዕጩዎች ቁጥር እስከ 123 መድረሱ መራጮች በምስጢር ድምፅ መስጫ ክፍል ውስጥ የሚወስዱትን ደቂቃ ማርዘሙን ነው፡፡
ይህንን ችግር ለመቅረፍም ቦርዱ ተጨማሪ የድምፅ መስጫ ሳጥኖችንና ቡዞችን ወደ ጣቢያዎች ልኮ መፍትሔ ለመስጠት መቻሉን ገልጸዋል፡፡
ቅሬታዎችን ማስተናገድና የተወሰዱ የቅጣት እርምጃዎች፦ ቦርዱ በሕግ ክፍል፣ በፖለቲካ ፓርቲዎች የሥራ ክፍል፣ በ6412 የጥሪ ማዕከልና ከታዛቢዎች በሚደርሱት ጥቆማዎች መሠረት የርምትና የማጣራት እርምጃዎችን ሲወስድ መቆየቱን ሜላትወርቅ ኃይሉ ገልጸዋል፡፡
በአዲስ አበባ አንዳንድ ምርጫ ጣቢያዎች መግባት የሌለባቸው ሰዎች ስለመታየታቸው የቀረቡ ጥቆማዎችን ቦርዱ በሞኒተሪንግ ቡድን አጣርቶ እውነት ሆነው በተገኙት ላይ እርምጃ መውሰዱንና ሕግና ደንብ ጥሰው የተገኙ የምርጫ ጣቢያ ሠራተኞችን ማሰናበቱን አረጋግጠዋል፡፡
የውጤት አሰጣጥ እና የማረጋገጥ ቀጣይ ሥራዎች፦ በአሁኑ ወቅት የምርጫ ውጤታቸው በምርጫ ጣቢያ ደረጃ ተደምሮ ያለቀላቸው ውጤቶች በየጣቢያዎቹ ተለጥፈው ለሕዝብ ይፋ መደረጋቸውን የጠቀሱት ሰብሳቢዋ፣ ቀጥሎም ውጤቶቹ ወደ ምርጫ ክልል ሄደው የማዳመር ሥራ እንደሚሠራ አስረድተዋል፡፡
በመጨረሻም ውጤቶቹ ወደ ዋናው መሥሪያ ቤት የማረጋገጫ ማዕከል ከመጡ በኋላ፣ ከተመዘገበው የመራጭ ቁጥር አንጻር ዋጋ ያላቸው እና የሌላቸው የድምፅ መስጫ ወረቀቶች ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ተለይተው የማረጋገጥ ሥራው በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ እንዲጠናቀቅ ቦርዱ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡
#ኢትዮጵያ_መርጣለች #ኢትዮጵያ_አሸንፋለች

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በአራቱ ክልሎች በሚገኙ አንዳንድ ጣቢያዎች አሁንም የድምጽ ቆጠራው አለመጠናቀቁን ገለጸ
ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በሲዳማ፣ በአማራ፣ በጋምቤላ እና በሶማሌ ክልሎች የድምጽ ቆጠራ ሂደት እስካሁን አለመጠናቀቁን የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ሃይሉ ተናግረዋል።
በምርጫው እለት የቀረቡ ቅሬታዎችን በመከታተል ቦርዱ እርምጃ መውሰዱን ሰብሳቢዋ ገልጸዋል። በዚህም በተደረጉ ማጣራቶች ሁለት ሰዎች ከስራቸው መባረራቸውን ጠቁመዋል። በምርጫ ጣቢያዎች ስም የመፈለግ ሂደት ችግር የነበረበት መሆኑ እና ሂደቱን ማጓተቱም ተገልጿል።
በክትትል ክፍተት የተገኘባቸው እና ጠዋት ላይ ተቋርጠው የነበሩ ጣቢያዎች ከማጣራት በኋላ በድጋሜ ሂደቱን እንዲቀጥሉ ተደርጓል ብለዋል።
አሁን ላይ ውጤትን ከጣቢያ ወደ ምርጫ ክልል በመውሰድ የማዳመር እና የመቁጠር ስራው እየተጠናቀቀ መሆኑን ጠቁመዋል። ውጤቱንም ይፋ ለማድረግ ወደ ዋናው ማእከል የመሰብሰብ ስራ በቀጣይ የሚጠበቅ መሆኑን አስረድተዋል።
ሰብሳቢዋ አክለውም በአዲስ አበባ ከ1 ሺህ በላይ የሚሆኑ ጣቢያዎች የውጤት ማዳመር ስራን ገና አላጠናቀቁም ብለዋል።
ቦርዱ ባደረገው ማጣራት ከ50 ሺህ በላይ ጣቢያዎች በሰአቱ ተከፍተው የምርጫ ሂደቱን ማከናወናቸውን ገልጸዋል። የአለም አቀፍ ታዛቢዎችን ተሳትፎ በተመለከተም ከመጀመሪያው ሰአት እና ቀን ጀምሮ ተገኝተው ሚናቸውን መወጣታቸውን ጠቁመዋል።
ቦርዱ በነበረው ሂደት ካጋጠሙት ዋና ዋና ተግዳሮቶች መካከል በጸጥታ ምክንያት የተቋረጡ የምርጫ ጣቢያዎች መኖር፣ የምርጫ ወረቀት እና የቁሳቁስ እጥረት ማጋጠማቸው መሆናቸውን ሰብሳቢዋ አመላክተዋል።

የአሜሪካ መንግሥት ከአፍሪካ ቪዛ አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን መካከል ኢትዮጵያን አልቀነሳትም
#ethiopia | የአሜሪካ መንግሥት በአፍሪካ አህጉሉአንዳ የሚሰጠውን የቪዛ አገልግሎት በከፍተኛ ደረጃ ለማሻሻል እየተዘጋጀ ነው።
በዚህ መሠረት በአፍሪካ ውስጥ የቪዛ አገልግሎት የሚሰጡ የአሜሪካ ኤምባሲዎችና ቆንስላዎች ቁጥር ከ50 ወደ 20 ብቻ ለመቀነስ ወስኗል። ይህ ለውጥ በቅርብ ጊዜያት ይጀመራል ተብሏል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ያጸደቁት ይህ አዲስ እቅድ፣ በአፍሪካ 20 ዋና የክልል ማዕከላት (Regional Hubs) በመሾም፣ ሌሎች ቦታዎችን የቪዛ ሙሉ አገልግሎት እንዳይሰጡ ለመዝጋት ያቀደ ነው።
እነዚህ የ20 ዋና ማዕከላት የትኞቹ ናቸው ፦
° አዲስ አበባ (ኢትዮጵያ) 🇪🇹
° አክራ (ጋና) 🇬🇭
° ዳካር (ሴኔጋል) 🇸🇳
° ጅቡቲ (ጅቡቲ) 🇩🇯
° ካምፓላ (ኡጋንዳ) 🇺🇬
° ኪጋሊ (ሩዋንዳ) 🇷🇼
° ኪንሻሳ (ኮንጎ) 🇨🇩
° ላጎስ (ናይጄሪያ) 🇳🇬
° ናይሮቢ (ኬንያ) 🇰🇪
° አቢጃን (አይቮሪ ኮስት) 🇨🇮
° ዳሬሰላም (ታንዛኒያ) 🇹🇿
° ሎሜ (ቶጎ) 🇹🇬
° ሉዋአንዳ (አንጎላ) 🇦🇴
° ማላቦ (ኢኳቶሪያል ጊኒ) 🇬🇶
° ሞንሮቪያ (ላይቤሪያ) 🇱🇷
° ፖርት ሉዊስ (ሞሪሸስ) 🇲🇺
° ፕራያ (ኬፕ ቨርዴ) 🇻🇪
° ያውንዴ (ካሜሩን) 🇨🇲
° ኬፕ ታውን (ደቡብ አፍሪካ) 🇿🇦
° ጆሃንስበርግ (ደቡብ አፍሪካ) 🇿🇦
ከእንግዲህ ወዲያ በእነዚህ 20 ማዕከላት ያልተካተቱ ሀገራት ዜጎች የቪዛ ቃለ መጠይቅ፣ የጣት አሻራ እና ሌሎች ሂደቶችን ለማጠናቀቅ በራሳቸው ወጪ ወደ ቅርብ ማዕከል መጓዝ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል ያለው ቲክቫህ ነው።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#ethiopia | የአሜሪካ መንግሥት በአፍሪካ አህጉሉአንዳ የሚሰጠውን የቪዛ አገልግሎት በከፍተኛ ደረጃ ለማሻሻል እየተዘጋጀ ነው።
በዚህ መሠረት በአፍሪካ ውስጥ የቪዛ አገልግሎት የሚሰጡ የአሜሪካ ኤምባሲዎችና ቆንስላዎች ቁጥር ከ50 ወደ 20 ብቻ ለመቀነስ ወስኗል። ይህ ለውጥ በቅርብ ጊዜያት ይጀመራል ተብሏል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ያጸደቁት ይህ አዲስ እቅድ፣ በአፍሪካ 20 ዋና የክልል ማዕከላት (Regional Hubs) በመሾም፣ ሌሎች ቦታዎችን የቪዛ ሙሉ አገልግሎት እንዳይሰጡ ለመዝጋት ያቀደ ነው።
እነዚህ የ20 ዋና ማዕከላት የትኞቹ ናቸው ፦
° አዲስ አበባ (ኢትዮጵያ) 🇪🇹
° አክራ (ጋና) 🇬🇭
° ዳካር (ሴኔጋል) 🇸🇳
° ጅቡቲ (ጅቡቲ) 🇩🇯
° ካምፓላ (ኡጋንዳ) 🇺🇬
° ኪጋሊ (ሩዋንዳ) 🇷🇼
° ኪንሻሳ (ኮንጎ) 🇨🇩
° ላጎስ (ናይጄሪያ) 🇳🇬
° ናይሮቢ (ኬንያ) 🇰🇪
° አቢጃን (አይቮሪ ኮስት) 🇨🇮
° ዳሬሰላም (ታንዛኒያ) 🇹🇿
° ሎሜ (ቶጎ) 🇹🇬
° ሉዋአንዳ (አንጎላ) 🇦🇴
° ማላቦ (ኢኳቶሪያል ጊኒ) 🇬🇶
° ሞንሮቪያ (ላይቤሪያ) 🇱🇷
° ፖርት ሉዊስ (ሞሪሸስ) 🇲🇺
° ፕራያ (ኬፕ ቨርዴ) 🇻🇪
° ያውንዴ (ካሜሩን) 🇨🇲
° ኬፕ ታውን (ደቡብ አፍሪካ) 🇿🇦
° ጆሃንስበርግ (ደቡብ አፍሪካ) 🇿🇦
ከእንግዲህ ወዲያ በእነዚህ 20 ማዕከላት ያልተካተቱ ሀገራት ዜጎች የቪዛ ቃለ መጠይቅ፣ የጣት አሻራ እና ሌሎች ሂደቶችን ለማጠናቀቅ በራሳቸው ወጪ ወደ ቅርብ ማዕከል መጓዝ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል ያለው ቲክቫህ ነው።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
2 days ago
ቢቢሲ በአርሲ በደረሰው ጥቃት ላይ መረጃ ለመጠየቅ ለኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ እና የክልሉ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አራርሳ መርዳሳ በተደጋጋሚ ቢደውልም ስልካቸው ባለመነሳቱ ምላሽ ማግኘት አልቻለም።
ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ የአርሲ ዞን ኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑትን አቶ ሶሪ ወጊን ስለተፈጸመው ጥቃት ማክሰኞ አመሻሽ ላይ ላቀረበላቸው ጥያቄ "እስከአሁን የደረሰን መረጃ የለም፤ እናጣራለን" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ጥቃቱ ከተፈጸመባቸው አካበቢዎች አንዱ የሆነው የሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ አስተዳዳሪ ሐሰን መሐመድም ሰዎች ስለሞቱበት እና ንብረት ስለወደመበት ክስተት "መረጃ የለንም" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ የአርሲ ዞን ኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑትን አቶ ሶሪ ወጊን ስለተፈጸመው ጥቃት ማክሰኞ አመሻሽ ላይ ላቀረበላቸው ጥያቄ "እስከአሁን የደረሰን መረጃ የለም፤ እናጣራለን" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ጥቃቱ ከተፈጸመባቸው አካበቢዎች አንዱ የሆነው የሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ አስተዳዳሪ ሐሰን መሐመድም ሰዎች ስለሞቱበት እና ንብረት ስለወደመበት ክስተት "መረጃ የለንም" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
Sponsored by
Surafel
2 days ago
በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ የመስጠት ሂደት በስኬት ተጠናቅቋል - ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ የመስጠት ሂደት በስኬት ተጠናቅቋል አለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ።
የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ÷ በግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ድምጽ ሲሰጥ የዋለው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ የመስጠት ሂደት በስኬት ተጠናቅቋል ብለዋል።
በድምጽ ምስጫ ሂደት በአዲስ አበባ ከተማ በጣም ረጃጅም ሰልፎች እንደነበሩ አንስተው÷ በዚህም በሲዳማ፣ ጋምቤላ፣ አማራ፣ ሶማሌ ክልሎች እና በአዲስ አበባ የድምጽ ቆጠራ አለመጠናቀቁን ገልጸዋል።
በዚህም የመራጮች ቁጥር እስካሁን ተጠቃልሎ አለመግባቱን ተናግረዋል።
ቦርዱ የተለያዩ ቅሬታዎች በተለያየ መንገድ ሲያስተናግድ መቆየቱን አንስተው÷ በሕግ ክፍል በኩል በቀጥታ እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲ የስራ ክፍል አማካይኝነትና በቅድመ ማስጠንቀቂያ 6412 ስልክ ቁጥር የመጡ ጥቆማና ቅሬታዎች እንደነበሩ አመልክተዋል።
በዚህም ቦርዱ ጥቆማውን በመከተል ከስር ከስር አስፈላጊውን የእርምት ርምጃ ሲሰጥ መቆየቱን እንዲሁም የማጣራት፣ የማረጋገጥና ማስረጃ ማጠናቀር በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በተለያዩ ቦታዎች የምርጫ ውጤት በምርጫ ጣቢያ ደረጃ ተደምሮ ያለቁት ለሕዝብ በይፋ መለጠፉን ገልጸው÷ ወደ ምርጫ ክልል የመጡ ውጤቶችን የመደመር ስራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል።
በቀጣይ ውጤቱን ለማረጋገጥና ይፋ ለማድረግ ወደ ዋናው መስሪያ ቤት እንዲመጣ ይደረጋልም ነው ያሉት።
ከመጣ በኋላም እያንዳንዱን የምርጫ ክልል በመለየትና በማየት ተወዳዳሪዎች ያገኙትን ድምጽ በዝርዝር በመመልከት ከመራጭ ሕዝብ ብዛት አንጻር ዋጋ ያላቸውንና የሌላቸውን በመለየት ጥንቃቄ በሞላበት የማጣራት ሂደቱን በማጠናቀቅ የማረጋገጡ ስራ እንደሚሰራ አመልክተዋል።
የማረጋገጡ ሥራም በተወሰነ የጊዜ ገደብ መከናወን እንዳለበት በመጥቀስ÷ በጊዜ ገደቡ ውስጥ ለማጠናቀቅ ቦርዱ ጥረት እያደረገና እየሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
በአድማሱ አራጋው

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በአሁኑ ወቅት ወደ ሩብ (25 በመቶ) የሚጠጋው የኢትዮጵያ መሬት ለጉዳት እና ለመራቆት መዳረጉን አንድ አዲስ የጥናት ሪፖርት አመለከተ። ይህንን ችግር ለመቅረፍ ማህበረሰቡን ያሳተፉ እና አነስተኛ ወጪ የሚጠይቁ መፍትሔዎች ተስፋ ሰጪ ውጤት እያሳዩ መሆኑ ተገልጿል።
ከ25 ዓመታት በላይ ልምድ ባላቸው ከፍተኛ ተመራማሪ ወልዴ መኩሪያ የቀረበው ይህ ጽሁፍ እንደሚያመለክተው፣ መሬቱ ሰብል የማብቀል፣ ዕፅዋትን የመሸከም እና ውሃ የመያዝ ጥራቱን እያጣ ይገኛል። ለዚህ ችግር በዋነኛነት የደን መጨፍጨፍ፣ ከመጠን በላይ መጠቀም እና ደካማ የመሬት አያያዝ የመሳሰሉ የሰው ሰራሽ ጫናዎች በምክንያትነት ይጠቀሳሉ። በተጨማሪም ከባድ ዝናብ የሚያስከትለው የአፈር መሸርሸር እና የአየር ንብረት መለዋወጥ የመሳሰሉ ተፈጥሯዊ ምክንያቶች ከፍተኛ አስተዋጽኦ አላቸው። የዚህ መዘዝ የግብርና ምርታማነትን ከመቀነስ ባለፈ፣ የከርሰ ምድር ውሃ መጠን እንዲቀንስ እና የተከማቸ ካርበን ወደ አየር በመለቀቅ የአየር ንብረት ለውጥን እንዲያባብስ አድርጓል።
ጥናቱ ሁለት ተፈጥሮን መሠረት ያደረጉ አነስተኛ ወጪ የሚጠይቁ መፍትሔዎችን በአማራጭነት አቅርቧል። የመጀመሪያው የተጎዱ መሬቶችን አጥሮ ከሰው እና ከእንስሳት ንክኪ ነፃ ማድረግ ሲሆን፣ ይህም መሬቱ በአምስት ዓመታት አጭር ጊዜ ውስጥ በተፈጥሮው እራሱን መልሶ እንዲያድን ያስችለዋል። ይህ አሰራር የአፈር መሸርሸርን የሚቀንስ፣ የካርበን ክምችትን በመጨመር ብዝሃ ሕይወትን የሚያጎለብት እና ማህበረሰቡን ከድርቅ እና ከጎርፍ የሚጠብቅ ነው። በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል በተደረገ ጥናት፣ ለ20 ዓመታት በታጠሩ መሬቶች ላይ ከፍተኛ የካርበን ክምችት መጨመሩ ተረጋግጧል።
ሁለተኛው መፍትሔ የጎርፍ መፋሰሻዎችን እና ስምጥ ሸለቆዎችን መልሶ ማልማት ነው። በደቡብ ኢትዮጵያ በተደረገ ሙከራ፣ ጥልቅ የጎርፍ መፋሰሻዎችን በአካባቢው በሚገኙ አፈር፣ ድንጋይ፣ ሣር እና ዛፎች በመጠቀም በአነስተኛ ወጪ መሙላት ተችሏል። በውሃ መፋሰሻዎቹ ላይ የውሃውን ፍጥነት የሚቀንሱ ትናንሽ ግድቦችን መስራት ሌላኛው ውጤታማ ዘዴ መሆኑ ታይቷል። ይህ አሰራር ውድ የሆኑ ማሽነሪዎችን የማይጠይቅ ሲሆን፣ አብዛኛው ስራ በዶማ እና በሜንጫ ብቻ የሚሰራ በመሆኑ አንድ ሄክታር መሬት ለማልማት ከ600 እስከ 800 የአሜሪካ ዶላር ብቻ ወጪ ይጠይቃል።
በኢትዮጵያ ውስጥ 90 በመቶ የሚሆነውን የሀገሪቱን ሰብል የሚያመርቱ ከ15 ሚሊዮን በላይ አነስተኛ አርሶ አደሮች ይገኛሉ። መሬትን መልሶ የማልማቱ ስራ ውጤታማ የሚሆነው ማህበረሰቡ በጋራ ሲያቅድ፣ አካላዊ ስራውን ሲሰራ እና የረጅም ጊዜ ቁርጠኝነት ሲኖረው ብቻ መሆኑን የጥናቱ ውጤት አረጋግጧል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2011 በገባችው ቃል መሠረት እስከ 2030 ድረስ 7 ሚሊዮን ሄክታር የተጎዳ መሬት መልሶ ለማልማት አቅዳ እስካሁን 4.2 ሚሊዮን ሄክታር ማልማት ችላለች። በተጨማሪም እንደ ሀገራዊ የአየር ንብረት ስትራቴጂ አካል ተጨማሪ 15 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ለማልማት ቃል መግባቷን ሪፖርቱ አትቷል። ትክክለኛ ፖሊሲዎች እና ተከታታይ የፋይናንስ ድጋፍ ካለ እነዚህ አካሄዶች መሬትን ከመታደግ ባለፈ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ትልቅ አቅም እንደሚፈጥሩ ተመላክቷል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ‹‹አለም አቀፍ ሚዲያዎች በምርጫው ዙሪያ ያልተመጣጠነ አሉታዊ ትረካ እያቀረቡ ነው›› ሲሉ የኢዜማ መሪ ገለፁ፡፡ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ መሪ የሆኑት አቶ እዮብ መሳፍንት አለም አቀፍ ሚዲያዎች ከምርጫው በፊት ያልተመጣጠነ አሉታዊ ትርክት እያቀረቡ መሆኑን በመግለፅ ወቀሱ፡፡
እኚህ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ሚዲያዎቹ ‹‹የአገር ውስጥ እድገትንና የመራጮችን ተስፋ ችላ በማለት በአሉታዊ ዘገባዎች ላይ ተጠምደዋል›› በማለትም ገልፀዋል፡፡ አቶ እዮብ ከራይዝ ኤንድ ሻይን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ምርጫው በግጭት የተሸፈነ፣ አነስተኛ ተሳትፎ ያለበትና ተአማኒነት እንደሚያንሰው በስፋት በአለም አቀፍ ሚዲያዎች የተዘገበውን አጣጥለውታል፡፡
በአንዳንድ አካባቢዎች በተለይም በትግራይ ክልልና በአማራ ክልል ውስጥ ባለው አለመረጋጋት ምርጫ አለመካሄዱን ያረጋገጡት መሪው ይሁንና እነዚህ አካባቢዎች ከአጠቃላይ ምርጫው የተወሰነ ክፍል እንደሚሸፍኑ ገልፀዋል፡፡ በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍል ምርጫው በመካሄዱ የምርጫው ውጤት በመንግስት ምስረታ ላይ ተፅእኖ እንደማይፈጥር መናገራቸውን ቻናል አፍሪካ ካቀረበው ዘገባ ተመልክተናል፡፡

የሟቾቹ ቁጥር 13 ደርሷል‼️
ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የአርሲና ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት 13 ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውን፣ ከ280 በላይ ምእመናን መፈናቀላቸውንና የ101 ዓመት ቤተ ክርስቲያን መቃጠሉን አሳወቁ።
ከግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ:ም ጀምሮ በአርሲ ሀገረ ስብከት በአሰኮ ወረዳ; በሺርካ ወረዳና ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ 13 ኦርቶዶክሳውያን ሲገደሉ የ101 ዓመት እድሜ ያለው የጠላታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሙሉ በሙሉ በእሳት ወድሟል።
የካራ ኩፍተና መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ላይም ዘረፋ የተካሄደ ሲሆን ምእመናን ጽላቱን ይዘው ተሰደዋል፤ መኖሪያ ቤታቸውም ተቃጥሏል።
የተገደሉ ሰዎች ስም ዝርዝርም
1. አቶ ደምረው አበራ የ70 ዓመት
2. ከፈለኝ ልክየለው የ56ዓመት
3. ሐይሉ ንጉሴ የ70 ዓመት
4. እሸቴ ዳመና የ42 ዓመት
5. አበባየሁ ዳኜ የ42 ዓመት
6. ሰሙ አባይነህ የ70 ዓመት
7. 1 ሚሊሻ
8. አማረ በላይነህ የ80 ዓመት
9. ተሬ ደሴ የ25 ዓመት
10. ወጣት ገነነ ጥላሁን በሽርካ ወረዳ
11. ሙርቴሳ ጥላሁን በሽርካ ወረዳ
12. አቶ ንጉሱ ማንደፍሮ በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ
13. አቶ በቀለ ኃ/ሚካኤል በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ
በአጠቃላይ የ13 ሰዎች ህይወት አልፈዋል።
በተጨማሪ በአሰኮ ወረዳ ከ280 ሰው በላይ ተፈናቅለዋል::
በመሆኑም ኦርቶዶክሳውያኑ ተወልደው ካደጉበት፣ ወልደው ከሳሙበት ቀያቸው በሃይማኖታቸው ብቻ ቤታቸው እየተለየ ተቃጥሏል፤ ንብረታቸውና ከብቶቻቸው ተዘርፈዋል።
ከጥቃቱ የተረፉት ነዋሪዎችም ይዘውት የሸሹት እምነታቸውንና ማንነታቸውን ብቻ በመሆኑ አሁን ላይ ሜዳ ላይ ወድቀው ይገኛሉ።

የሀዘን መግለጫ
እስመ በእንቲአከ ይቀትሉነ ኩሎ አሚረ::
ወኮነ ከመ አባግዕ ዘይጠብሑ መዝ 43:22
"ስለ አንተ ሁልጊዜም ተገድለናል እንደሚታረዱም በጎች ሆነናል። መዝ 43:22
Waa'ee Keetif Yeroo Hunda Duuna, Akka Hoolota qalamaniis Taane. Far 43:22
ከግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ:ም ጀምሮ በአርሲ ሀገረ ስብከት በአሰኮ ወረዳ; በሺርካ ወረዳና ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ 13 ኦርቶዶክሳውያን ሲገደሉ
የ101 ዓመት እድሜ ያለው የጠላታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሙሉ በሙሉ በእሳት ወድሟል።

በመሆኑም ኦርቶዶክሳውያኑ ተወልደው ካደጉበት፣ ወልደው ከሳሙበት ቀያቸው በሃይማኖታቸው ብቻ ቤታቸው እየተለየ ተቃጥሏል፤ ንብረታቸውና ከብቶቻቸው ተዘርፈዋል። ከጥቃቱ የተረፉት ነዋሪዎችም ይዘውት የሸሹት እምነታቸውንና ማንነታቸውን ብቻ በመሆኑ አሁን ላይ ሜዳ ላይ ወድቀው ይገኛሉ
ስለዚህ በተፈጸመው ጥቃት የተሰማነን ጥልቅ ሐዘን እየገለጽን የሞቱትን ወገኖቻችን (ልጆቻችን) እግዚአብሔር አምላክ ነፍሳቸውን ይማርልን (በመንግሥተ ሰማያት ያሳርፍልን) የዘኑትን እና የተፈናቀሉትን ወገኖቻችን(ልጆቻችን)
እግዚአብሔር ያጽናናልን።
ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የአርሲና ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል።
© Arsi Diocese Public Relations Department
© Biyya Lallaba Arsiitti Kutaa Sab-Qunnamtii
© የአርሲ ሀገረ ስብከት ህዝብ ግንኙነት ክፍል
© የአርሲ ሀገረ ስብከት ሚድያ Miidiyaa Biyya Lallaba Arsii ...✍️
👉 Liinkii Gadii Kana Hordofuudhan Gara Chaanaaliiwwan Miidiyaa Keenyatti Dabalamaa
👉 ከታች ያሉትን ሊንክ በመጫን ወደ ቻናሎቻችን ተቀላቀሉ
👉 FACEBOOK👇👇👇👇👇ፌስቡክ
https://www.facebook.com/s...
👉 TIKTOK👇👇👇👇👇ቲክቶት
tiktok.com/miidiyaa.ku.la.arsii
WhatsApp 👇👇👇👇👇ዋትሳፕ
https://whatsapp.com/chann...
Inistagram👇👇👇👇👇ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/...
Telegram Chanal 👇👇👇👇👇ቴሌግራም
https://t.me/Arsi21
Telegram Group👇👇👇የግሩፕ ቴሌግራም
https://t.me/+do8_6-C5_ek4...
Telegram Cominicate
BIYYALALLABAARSII
IMO👇👇👇👇👇ኢሞ
https://call.imo.im/BiyyaL...

በቅርቡ ወደ ሥራ የተመለሠው የትግራይ ክልል ምክር ቤት አዳዲስ ሹመቶች አፀደቀ
ከጦርነቱ በፊት ተቃቁሞ የነበረውና በቅርቡ ወደ ሥራ የተመለሠው የትግራይ ክልል ምክር ቤት ሕወሃት ያቀረባቸውን የአዲስ የካቢኔ አባላት፣ የዞን አስተዳዳሪዎችና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሹመት ዛሬ ማምሻውን አጸደቀ።
የሕወሃት ምክትል ሊቀመንበር አማኑኤል አሠፋ የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንትና የፍትሕ ቢሮ ኃላፊ ኾነው እንደተሾሙ የክልሉ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።
70 በመቶ ያህሉ የካቢኔ አባላት ከሕወሃት የተውጣጡ ሲሆኑ፣ 30 በመቶዎቹ ከተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችና ከምሁራን የተውጣጡ እንደሆኑ ተገልጧል።
በተመሳሳይ፣ ወልደአብርሃ ገብረጻዲቅ የሰሜን ምዕራብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ ሺሻይ ግርማይ የማዕከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ ዝናቡ ገብረመድኅን የደቡባዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ ግዴይ አዘናው የምዕራብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ ፍስሃ ኃይላይ የምሥራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እንዲሁም ከለሊ ሐጋዚ የደቡብ ምስራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኾነው እንደተሾሙ ዘገባዎቹ ጠቅሠዋል።

ተፈጸመ
#ethiopia | በተለያዩ የጥበብ ዘርፎች በስፋት የሚታወቀው አርቲስት ኪዳኔ ምስጋናው ባደረበት ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
የአርቲስቱ የቀብር ስነ ስርዓት ዛሬ፣ ማክሰኞ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም በደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል ( አማኑኤል አጂፕ ) ከቀኑ 6:00 ሰዓት ተፈጽሟል።
ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ በሙያ ህይወቱ በታማኝነት ባገለገለበት ታሪካዊው ሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት የሽኝት እና የሻማ ማብራት መርሃ ግብር ተከናወናል።
***
የሁለገቡ አርቲስት ኪዳኔ ምስጋናው
አጭር የህይወት ታሪክ
የመድረኩ እንዝርት ሁለገቡ የጥበብ ሰው አርቲስት ኪዳኔ ምስጋናው ከእናቱ ከወ/ሮ ብዙነሽ ጓንጉል እና ከአባቱ ከአቶ ምስጋናው ደርኬሮ ሰኔ 15/ 1958 ዓ.ም አዲስ አበባ ከተማ ልዩ ስሙ አማኑኤል አጂፕ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ተወለደ፡፡ ለአቅመ ፊደል ሲደርስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በደጃዝማች ኃይሉ ተስፋዬ ትምህርት ቤት እንዲሁም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በአዲስ ከተማ ትምሀርት ቤት እስከ 12ኛ ክፍል ተምሮ አጠናቋል።
ከውዝዋዜ ጋር ገና ተማሪ እያለ የተወዳጀው ሁለገቡ ከያኒ ኪዳኔ ምስጋናው የጥበብ ጉዞውን በቀበሌ ኪነትና በከፍተኛ ኪነት ውስጥ አድርጎ መዳረሻውን በአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ በማድረግ በ1977 ዓ.ም በውዝዋዜ ሙያ ለመቀጠር በቅቷል፡፡ የአርቲስት ኪዳኔ የሙያ ፍቅር፣ ችሎታና ስነምግባር ያስደመማቸው የውዝዋዜ ክፍል አሰልጣኞችና ኃላፊዎች ከተወዛዋዥነት ወደ ረዳት አሰልጣኝነት እንዲያድግ በማድረጋቸው ከ1983-1990 ዓ.ም ድረስ በረዳት አሰልጣኝነት ሙያ ሲያገለግል ቆይቷል፡፡ ጥበበኛው ኪዳኒ በረዳትነት የጀመረውን የአሰልጣኝነት ስራውን ከፍ በማድረግ ከ1991 እሰከ 1992 በቋሚ አሰልጣኝነት ተመድቦ በርካታ ባለሙያዎችን በክህሎት፣ በስነምግባርና በጥበብ አሰልጥኖ ለውዝዋዜ ሙያ መስፋፋትና አድገት የበኩሉን ድርሻ አበርክቷል፡፡
በውዝዋዜ ጥበብ በማለዳው የተነደፈው ኪዳኔ በእውቀት፣ በልምድና በፈጠራ እየጎመራና አንቱታን እያተረፈ ሲመጣ አድማሱን በማስፋት በአንጋፋው ሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ተዛውሮ ከ1992 እሰከ 2007 ዓ.ም በዋና አሰልጣኝነትና በኬሮጋራፈርነት በርካታ በሀገር አቀፍና በአለም አቀፍ ደረጃ ግዘፍ የነሱ መድረኮች ላይ የቀረቡ የውዝዋዜ ስራዎችን በማዘጋጀት፣ በማማከርና በመምራት ከሰው ልብና አእምሮ የማይጠፉ ደማቅ ኪነጥበባዊ ስራዎችን ሰርቷል፡፡
አርቲስት ኪዳኔ ፈጣን የፈጠራ፣ የማደራጀትና የመምራት አቅም የነበረው ብርቱ የጥበብ ሰው ነበር፡፡ በርካታ ተወዛዋዦች የሚገኙበት የጥበብ መድረክ ካለ እዛ የጥበብ መድረክ ላይ ኪዳኔ መኖሩ ሳይታለም የተፈታ ህልም ነበር፡፡ የኪዳኔ የፈጠራ፣ የውዝዋዜ ችሎታና የውዝዋዜ ዝግጅት ጥበብ የታየባቸው አያሌ የውዝዋዜ ጥበብ ስራዎች ህያው መስክሮቹ ናቸው፡፡ በፋሽስት ጣሊያን የተዘረፈው የአክሱም ሀውልት ወደ ሀገሩ ሲመለስ ለነበረው አቀባበል በተዘጋጀው የኪነጥበብ መድረክ ላይ በአዲስ አበባና በአክሱም ከተማ ግዙፍ የውዝዋዜ ዝግጅት፣ በህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ በተዘጋጀው የጥበብ መድረክ፣ በሚሊኒዬም አዳራሽ፣ በባህዳር ጣና ሐይቅ ላይ የውዝዋዜ የጀልባ ላይ ትርኢት፣ የአዲስ ዓመት የበዓል ዝግጅቶች ላይ ጥበብ፣ ባህል፣ ፈጠራና ውበት የተመላባቸው በርካታ ተወዛዋዦች የተሳተፉባቸውን የጥበብ ስራዎች በማዘጋጀት የጥበብና የሀገር ባለውለታነቱን አስመስክሯል፡፡
በአንጋፋው ሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ከአስራ አምስት ዓመት በላይ በአሰልጣኝነት ሲሰራ ከቆየ በኋላ ከ2007 እስከ 2017 ዓ.ም ድረስ ወደ ቀድሞ የሙያ ቤቱ የአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አደራሽ ተዛውሮ በአሰልጣኝነትና በኬሮግራፈርነት ሲሰራ ቆይቷል፡፡
አርቲስት ኪዳኔ ምስጋናው ከተወዛዋዠነት፣ አሰልጣኝነት፣ አዘጋጅነትና አማካሪነት ባሻገር በድምጻዊነትና በቴአትርና ፊልም ተዋናይነትም በመሳተፍ ሁለገብ ከያኒነቱን ያስመሰከረ ድንቅ ጥበበኛ ነበር፡፡ በርካታ የሙዚቃ ቪዲዮ ስራዎች ላይ የኪዳኔ ደማቅ የፈጠራና የጥበብ አሻራ ያረፈባቸው ውዝዋዜዎችና ዝግጅቶች ዛሬም፣ ነገም ህያው ምስክሮች ናቸው፡፡
አሰልጣኝና ኬሮግራፍር እንዲሁም የውዝዋዜ አማካሪ አርቲስት ኪዳኔ ምስጋናው በሞያው በሰራባቸው አመታት በርካታ
1. ባለሙያዎች ወደ ሙያው እንዲገቡና የሙያው ስነምግባር እንዲኖራቸው አደርጓል፡፡
2. የባህል ውዝዋዜ ትምህርት ቤት በሌለበት ዘመን በቴአትር ቤቶችና ከቴአትር ቤቶች ውጪ የነበሩ ወጣቶችን አሰልጥናል፤
3. ከከተማ ውጪ በመሄድ ቱባ ባህሎችን በማጥናትና በማምጣት የተለያዩ የባህል ጭፈራዎችንና አለባበሶችን አስተዋውቋል፡፡
4. የውዝዋዜ ሙያ እንደሙያ እንዲታይና አሁን የደረሰበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ የተለያዩ መድረኮች ላይ እና ጥናቶች ላይ በመሳተፍ አስተዋኦ አበርክቷል፡፡
5. በአዲስ አበባ ከተማ በተዘጋጁ በርካታ የኪነ ጥበብ ፌስቲቫሎች ላይ በመጋበዝ በዳኝነትና በአማካሪነት ሰርቷል፡፡
6. ከአዲስ አበባ ውጪ በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ ወጣቶችን ከማሰልጠን አልፎ በደቡብ ክልል ውስጥ የባህል ባንድ ለማቋቋም በቅቷል፡፡
7. በከተማችንና በተለያዩ ከተሞች በተከበሩ የብሄሔር ብሄረሰቦች ክብረ በዓላት ላይ የጥበብ ስራዎችን አቅርባል፡፡
8. በተለያዩ ጊዜ የተከበሩ የአደባበይ በአላት አድዋና የካቲት12 የመሳሰሉት ላይ ስራዋችን አቅርባል፡፡
9. በታላቁ ህዳሴ ግድብ ድረስ በመሄድና ታስቦ በሚከበርበት ጊዜም ስራዎችን አቅርቧል፡፡
10. በመንግስት መስረታና በበአለ ሲመቱ ዝግጅት ላይ ታላቅ የውዝዋዜ ትርኢት በኬሮግራፈርነት ሰርቷል፡፡
11. ሀገራችን የጦርነትና የተፈጥሮ ችግር በገጠማት ጊዜ ከኪነ ጥበብ ስራው ጋር ቀዳሚ በመሆን በርካታ አነቃቂ ስራዎችን ሰርቷል፡፡
12. የተለያዩ የሀገር መሪዎች፣ አንባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ሲመጡና ሲሸኙ በአየር መንገድና በከንቲባ ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ደማቅ አቀባበል በማደረግ እና ትርኢቶችን በማቅረብ ባህላችንን አስተዋውቋል፡፡
13. በከተማ ደረጃ የሚዘጋጁ ትላልቅ ሴሚናሮች፤ጉባኤዋችና ሲንፖዚየሞች ላይ የተለያዩ የኬሮግራፈር ስራዎችን ሰርቷል፡፡
ሁለገቡ አርቲስት ኪዳኔ ምስጋናው ላበረከታቸው ኪነጥበባዊ ስራዎች የምስጋናና የእውቅና የምስክር ወረቀቶችን፡-
Ø ከኢፌድሪ ፊዴሬሽን ምክር ቤት
Ø ከኢፌድሪ ባህልና ቱሪዝም ሚንስቴር
Ø አዲስ አበባ ዩንቪርስቲ
Ø ከአዲስ አበባ ባህል ኪነ የጥበብና ቱሪዝም ቢሮ
Ø ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት
Ø ከሀገር ፍቅር፤ከቴአትርና ባህል አደራሽ፤ከራስ ቴአትር፤ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአተር እና ሌሎችም በርካታ ተቋማት በክብር ተቀብሏል፡፡
አሰልጣኝ፣ ኬሮግራፍርና የውዝዋዜ አማካሪ አርቲስት ኪዳኔ ምስጋናው ሙያው እንዲያድግና ባለሙያውም እንዲጠቀም በነበረው ፍላጎትና ቁጭት ምክንያት ሙያው በተለያዩ ትልልቅ ሆቴሎችና የባህል ምሽቶች እንዲሰራና ባህላችን የበለጠ እንዲተዋወቅ በማማከርና በመደገፍ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል፡፡
አርቲስት ኪዳኔ ከበርካታ የሀገራችን ታዋቂና ተወዳጅ ሙዚቀኞች ጋር ትላልቅ መድረኮችና በከተማ ደረጃ በቀረቡ ታላላቅ ህዝባዊ በአላትና የሙዚቃ ኮንሰርቶች ላይ የኪሮግራፈር ስራዋችን
Ø በሸራተን አዲስ ሆቴል
Ø በሚሊንየም አዳራሽ
Ø በኢግዚብሽን ማዕከል
Ø በመስቀል አደባባይ
Ø በአዲስ አበባ ስቴድየም
Ø በጊዮን ሆቴል
Ø በሂልተን ሆቴል
Ø በስካይላት ሆቴል በመገኘት ጥበባዊ ስራዎችን ያቀረበ ሲሆን ትልልቅ የቀጥታ የቴሌብዥን ስርጭ የነበራቸውን ግዙፍ መድረኮችም ላይ ልዩ የኬሮግራፈርነት ሙያውን ድንቅ ብቃት አስመስክሯል፡፡
አርቲስት ኪዳኔ ምስጋናው በተለያዩ ቴአትርና ሙዚቃዊ ቴአትሮች ላይ በትወናና በዝግጅት ሰርቷል፡፡ በትወና የተሳተፈባቸው ስራዎች፦
Ø ጤና ያጣ ፍቅር
Ø ሮሚዮና ጁሌት
Ø የቀለጠው መንድር
Ø ሊስትሮ ኦፔራ
Ø ከልሺን አውልቂ
Ø ፎርፌ
Ø ኦቴሎ
Ø ቴዎድሮስ
በሙዚቃዊ ድራማ ኬሮግራፈር ዝግጅት፡-
Ø ፎርፌ
Ø ኢትዮጵያዊነት ጥልቅ ነው
Ø ከልሽን አውልቂ
Ø ሊስትሮ ኦፔራ
Ø ሉሲ
Ø ሀገር ማለት ሰው ነው እና ሌሎችም የጠቀሳሉ፡፡
በፊልም ትወና፡-
Ø በህይወት ዙሪያ
Ø ሔሮሽማ
አርቲስት ኪዳኔ ምስጋናው ከመድረክ ስራዎቹ በተጨማሪም በተላያዩ ታዋቂና አንጋፍ እንዲሁም ወጣት ድምጻውያን የሙዚቃ ቪዲዮ ስራዎች ላይ በኬሮግራፈርነትና በአማካሪነት ሰርቷል፡፡
Ø ለክብር ዳ/ር ጥላሁን ገሠሠ
Ø ለድምፃዊ ኤፍሬም ታምሩ የሰራቸው ስራዎች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
አርቲስት ኪዳኔ በተለያዩ የቴሌቪዥን ዝግጅቶችና የበዓል ፕሮግራሞች ላይ ባቀረባቸው የጥበብ ስራዎች ውበትና ድምቀት የነበረ ሲሆን በፋና ቴሌቭዥን ፋና ሰማንያ የውዝዋዜና ዳንስ ተሰጥኦ ውድድር ላይ በአማካሪነት በመስራት ሙያዊ አስተዋፅዎ አድርጓል፡፡
ሁለገቡ አርቲስት ኪዳኔ በሙያው አድማስ ተሸግሮ በዱባይ እና በታይላንድ ኢትዮጰያንና ባህሏን ያስተዋወቀ ብርቱ የጥበብ ሰው ሰሆን በቅርብ በሀገራችን እና በአለም ህዝቦች ዘንድ አንድ ጊዜ ተሰርቶ ያልተደገመውን የህዝብ ለህዝብ ተጓዥ የሙዚቃ የባህል ቡድንን የሚያስታውስ የሀገረሰብ ሙዚቃዎችን፣ ጭፈራዎችንና ባህላችንን የሚያስተዋውቅ ሉሲ ድንቅነሽ ኢትዮጵያ በሚል በመላው ሀገር ተዟዙሮ የቀረበውን ትርኢት ከባህል ሚንስቴር ኃላፊነት ተሰጥቶት በዋና አዘጋጅነት የውዝዋዜውን ዝግጅት መምራት የቻለ ድንቅ ጥበበኛ ነበር፡፡
ሁለገቡ ከያኒ አርቲስት ኪዳኔ ምስጋናው ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ ህይወቱ እስካለፈበት ግንቦት 23/2018 ዓ.ም ድረስ በአንጋፋው ሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ተዛውሮ በሙያው ወገኑን፣ ሀገሩንና ሙያውን በጥበብ፣ በታማኝነትና በትጋት ሲያገለግል የኖረ፣ በጥበብ ስራዎቹ ስሙን ከመቃብር በላይ ማኖር የቻለ ታላቅ ጥበበኛ ነበር፡፡
አርቲስት ኪዳኔ ምስጋናዉ የጋብቻ ህይወቱን ከረዥም ጊዜ ፍቅረኛዉ ከወ/ት አይናለም ተፈራ ጋር የካቲት 2 /2018 በክብር ፈፅሟል። ይሁንና ይህ ታላቅ ጥበበኛ ባጋጠመው የጤና እክል ሳቢያ በአዲስ ህይወት አጠቃላይ ሆስፒታል እና በሆፕ ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ግንቦት 23/2018 ዓ.ም በተወለደ በ60 ዓመቱ ከዚህ ዓለም ድካም አርፏል፡፡
የአርቲስት ኪዳኔ ምስጋናው የሽኝትና የጧፍ ማብራት ፕሮግራም ቤተሰቦቹ፣ ጓደኞቹ፣ የሙያ አጋሮቹና አድናቂዎቹ በተገኙበት ለረዥም ዓመታት በሙያው ባገለገለበት አንጋፋው ሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ግንቦት 25/ 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት ላይ ከተከናወነ በኋላ የቀብር ሰነ ስርዓቱ በአማኑኤል ካቴድራል ቤተክርስቲያን ይፈፀማል።
የአዲስ አበባ ቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት በመላው ሰራተኞቹና የሙያ አጋሮቹ ስም በሁለገቡ አርቲስት ኪዳኔ ምስጋናው ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ፈጣሪ ነፍሱን በመዓዛ ገነት እንዲያሳርፍ ይመኛል፡፡ እንዲሁም ለውድ ቤተሰቦቹ፣ ለዘመዶቹ፣ ለጓደኞቹ፣ ለስራ ባልደረቦቹ፣ ለሙያ አጋሮቹና አድናቂዎቹ በሙሉ ፈጣሪ ልባዊ መጽናናትን እንዲሰጣቸው ይመኛል፡፡
የአዲስ አበባ ቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት-ኮምኒኬሽን
#ኪዳኔምስጋናው #ሀገርፍቅርቴአትር #የጥበብሰው #ሀዘን #ኪነጥበብ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa