ህወሃት ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በአስቸኳይ ጣልቃ እንዲገባ ጠየቀ
#fastmereja I የሕዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ (ህወሃት) ከፍተኛ አመራር የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት የፌደራል መንግስቱ በይፋ ማፍረሱንና ክልሉን በከበባ ውስጥ ማድረጉን በመጥቀስ፣ አዲስ ሊቀሰቀስ የሚችለውን አስከፊ ጦርነት ለመግታት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በአስቸኳይ ጣልቃ እንዲገባ ጥሪ አቀረበ።
በትግራይ ክልል ያለውን የፖለቲካ የሥልጣን ክፍተት ለመሙላትና ተቋማዊ ቀጣይነትን ለማረጋገጥ ከ1 ሚሊዮን በላይ የክልሉ ነዋሪዎች የተሳተፉበት ሰፊ ውይይት መደረጉን የገለጸው የህወሃት መግለጫ፣ በዚህም መሠረት በ2012 ዓ.ም የተመረጠው የትግራይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወደ ሉዓላዊ ሥልጣኑ እንዲመለስ መወሰኑን ይፋ አድርጓል። ምክር ቤቱ ወደ ሥራው ሲመለስ አካታች የሆነ የሕግ አስፈጻሚና የዳኝነት መዋቅር እንደሚያዋቅር የተገለጸ ሲሆን፣ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች በካቢኔው ውስጥ የ33 በመቶ (አንድ ሶስተኛ) የሥልጣን ድርሻ እንዲኖራቸው ጥሪ መቅረቡም ገልጿል።
በትግራይ ክልል ያለው ሰብአዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ አሁንም እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑን የጠቀሰው ይኸው አለም አቀፍ ጥሪ፣ የፌደራል መንግስቱ በነዳጅ እና በንግድ ዕቃዎች ላይ የጣለው እገዳ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴውን ሙሉ በሙሉ ማሽመድመዱንና ከፍተኛ የዋጋ ንረትን ማስከተሉን ያብራራል። ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በትግራይ ድንበሮች ዙሪያ መጠነ-ሰፊ ወታደራዊ ዝግጅትና ከበባ እያደረገ እንደሚገኝ በመግለጽ፣ ይህ ድርጊት በሕዝቡ ላይ ከፍተኛ የስነ-ልቦና እና የማኅበራዊ ጫና እየፈጠረ መሆኑን ይከሳል።
በተመሳሳይ በምዕራብ ትግራይ የሚገኙ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዳይመለሱ በፌደራል መንግስቱና በአጋሮቹ በኩል እንቅፋት እየተፈጠረባቸው መሆኑንና ዓለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶችም ድጋፋቸውን እያቋረጡ መምጣታቸውን ሰነዱ ያስረዳል።
የቀጣናው የፖለቲካ አቅጣጫ ወደ ግትርነት፣ ወታደራዊ ኃይል አማራጭነትና አንድ ወገንተኝነት እያዘገመ በመሆኑ አዲስ ጦርነት የመቀስቀስ ስጋቱ ከአሁን በኋላ ግምታዊ ሳይሆን በተጨባጭ ከደጃፍ ላይ የደረሰ መሆኑን ሰነዱ ያስጠነቅቃል። ይህ ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኢትዮጵያ ድንበር ብቻ ሳይወሰን መላውን የአፍሪካ ቀንድ (Horn of Africa) ቀጣና ክፉኛ ሊያናጋ እንደሚችል በማመልከት፣ የጋራ ሰላምን ለማውረድ አሁንም ቢሆን የትግራይ መስተዳድር እና ህወሃት ለውይይት ዝግጁ መሆናቸውን በመግለጽ፣ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሁለቱንም ወገኖች ወደ ድርድር ጠረጴዛ ለማምጣት ዲፕሎማሲያዊ ተጽዕኖውን እንዲጠቀም ጥሪ አቅርቧል።

2 months ago