Logo
Tigu S Alemayew
የሀዘን መግለጫ

እስመ በእንቲአከ ይቀትሉነ ኩሎ አሚረ::
ወኮነ ከመ አባግዕ ዘይጠብሑ መዝ 43:22

"ስለ አንተ ሁልጊዜም ተገድለናል እንደሚታረዱም በጎች ሆነናል። መዝ 43:22

Waa'ee Keetif Yeroo Hunda Duuna, Akka Hoolota qalamaniis Taane. Far 43:22

ከግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ:ም ጀምሮ በአርሲ ሀገረ ስብከት በአሰኮ ወረዳ; በሺርካ ወረዳና ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ 13 ኦርቶዶክሳውያን ሲገደሉ
የ101 ዓመት እድሜ ያለው የጠላታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሙሉ በሙሉ በእሳት ወድሟል።

የካራ ኩፍተና መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ላይም ዘረፋ የተካሄደ ሲሆን ምእመናን ጽላቱን ይዘው ተሰደዋል፤ መኖሪያ ቤታቸውም ተቃጥሏል።

የተገደሉ ሰዎች ስም ዝርዝርም

1. አቶ ደምረው አበራ የ70 ዓመት
2. ከፈለኝ ልክየለው የ56ዓመት
3. ሐይሉ ንጉሴ የ70 ዓመት
4. እሸቴ ዳመና የ42 ዓመት
5. አበባየሁ ዳኜ የ42 ዓመት
6. ሰሙ አባይነህ የ70 ዓመት
7. 1 ሚሊሻ
8. አማረ በላይነህ የ80 ዓመት
9. ተሬ ደሴ የ25 ዓመት

10. ወጣት ገነነ ጥላሁን በሽርካ ወረዳ
11. ሙርቴሳ ጥላሁን በሽርካ ወረዳ

12. አቶ ንጉሱ ማንደፍሮ በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ
13. አቶ በቀለ ኃ/ሚካኤል በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ

በአጠቃላይ የ13 ሰዎች ህይወት አልፈዋል።
በተጨማሪ በአሰኮ ወረዳ ከ280 ሰው በላይ ተፈናቅለዋል::
በመሆኑም ኦርቶዶክሳውያኑ ተወልደው ካደጉበት፣ ወልደው ከሳሙበት ቀያቸው በሃይማኖታቸው ብቻ ቤታቸው እየተለየ ተቃጥሏል፤ ንብረታቸውና ከብቶቻቸው ተዘርፈዋል። ከጥቃቱ የተረፉት ነዋሪዎችም ይዘውት የሸሹት እምነታቸውንና ማንነታቸውን ብቻ በመሆኑ አሁን ላይ ሜዳ ላይ ወድቀው ይገኛሉ
ስለዚህ በተፈጸመው ጥቃት የተሰማነን ጥልቅ ሐዘን እየገለጽን የሞቱትን ወገኖቻችን (ልጆቻችን) እግዚአብሔር አምላክ ነፍሳቸውን ይማርልን (በመንግሥተ ሰማያት ያሳርፍልን) የዘኑትን እና የተፈናቀሉትን ወገኖቻችን(ልጆቻችን)
እግዚአብሔር ያጽናናልን።

ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የአርሲና ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል።

© Arsi Diocese Public Relations Department
© Biyya Lallaba Arsiitti Kutaa Sab-Qunnamtii
© የአርሲ ሀገረ ስብከት ህዝብ ግንኙነት ክፍል

© የአርሲ ሀገረ ስብከት ሚድያ Miidiyaa Biyya Lallaba Arsii ...✍️

👉 Liinkii Gadii Kana Hordofuudhan Gara Chaanaaliiwwan Miidiyaa Keenyatti Dabalamaa
👉 ከታች ያሉትን ሊንክ በመጫን ወደ ቻናሎቻችን ተቀላቀሉ

👉 FACEBOOK👇👇👇👇👇ፌስቡክ
https://www.facebook.com/s...

👉 TIKTOK👇👇👇👇👇ቲክቶት
tiktok.com/miidiyaa.ku.la.arsii

WhatsApp 👇👇👇👇👇ዋትሳፕ
https://whatsapp.com/chann...

Inistagram👇👇👇👇👇ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/...

Telegram Chanal 👇👇👇👇👇ቴሌግራም
https://t.me/Arsi21

Telegram Group👇👇👇የግሩፕ ቴሌግራም
https://t.me/+do8_6-C5_ek4...

Telegram Cominicate
BIYYALALLABAARSII

IMO👇👇👇👇👇ኢሞ
https://call.imo.im/BiyyaL...

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.