Logo
Getu Temesgen
የአሜሪካ መንግሥት ከአፍሪካ ቪዛ አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን መካከል ኢትዮጵያን አልቀነሳትም
#ethiopia | የአሜሪካ መንግሥት በአፍሪካ አህጉሉአንዳ የሚሰጠውን የቪዛ አገልግሎት በከፍተኛ ደረጃ ለማሻሻል እየተዘጋጀ ነው።

በዚህ መሠረት በአፍሪካ ውስጥ የቪዛ አገልግሎት የሚሰጡ የአሜሪካ ኤምባሲዎችና ቆንስላዎች ቁጥር ከ50 ወደ 20 ብቻ ለመቀነስ ወስኗል። ይህ ለውጥ በቅርብ ጊዜያት ይጀመራል ተብሏል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ያጸደቁት ይህ አዲስ እቅድ፣ በአፍሪካ 20 ዋና የክልል ማዕከላት (Regional Hubs) በመሾም፣ ሌሎች ቦታዎችን የቪዛ ሙሉ አገልግሎት እንዳይሰጡ ለመዝጋት ያቀደ ነው።

እነዚህ የ20 ዋና ማዕከላት የትኞቹ ናቸው ፦

° አዲስ አበባ (ኢትዮጵያ) 🇪🇹
° አክራ (ጋና) 🇬🇭
° ዳካር (ሴኔጋል) 🇸🇳
° ጅቡቲ (ጅቡቲ) 🇩🇯
° ካምፓላ (ኡጋንዳ) 🇺🇬
° ኪጋሊ (ሩዋንዳ) 🇷🇼
° ኪንሻሳ (ኮንጎ) 🇨🇩
° ላጎስ (ናይጄሪያ) 🇳🇬
° ናይሮቢ (ኬንያ) 🇰🇪
° አቢጃን (አይቮሪ ኮስት) 🇨🇮
° ዳሬሰላም (ታንዛኒያ) 🇹🇿
° ሎሜ (ቶጎ) 🇹🇬
° ሉዋአንዳ (አንጎላ) 🇦🇴
° ማላቦ (ኢኳቶሪያል ጊኒ) 🇬🇶
° ሞንሮቪያ (ላይቤሪያ) 🇱🇷
° ፖርት ሉዊስ (ሞሪሸስ) 🇲🇺
° ፕራያ (ኬፕ ቨርዴ) 🇻🇪
° ያውንዴ (ካሜሩን) 🇨🇲
° ኬፕ ታውን (ደቡብ አፍሪካ) 🇿🇦
° ጆሃንስበርግ (ደቡብ አፍሪካ) 🇿🇦

ከእንግዲህ ወዲያ በእነዚህ 20 ማዕከላት ያልተካተቱ ሀገራት ዜጎች የቪዛ ቃለ መጠይቅ፣ የጣት አሻራ እና ሌሎች ሂደቶችን ለማጠናቀቅ በራሳቸው ወጪ ወደ ቅርብ ማዕከል መጓዝ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል ያለው ቲክቫህ ነው።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.