Logo
Getu Temesgen
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በድል መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገለጸ
#ethiopia | ከፍተኛ የዕጩ ተወዳዳሪዎች ቁጥር የተመዘገበበት ሰባተኛው አገራዊ ምርጫ በስኬታማ ሁኔታ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ እንደገለጹት በአሁኑ ወቅት በየምርጫ ጣቢያዎቹ የተሰጡ ድምጾችን የማደመርና ውጤቱን ይፋ የማድረግ ተግባር በመከናወን ላይ ይገኛል።

በየምርጫ ጣቢያው የተሰበሰበው ድምፅ በይፋ ከተለጠፈ በኋላ ውጤቱ ተጠቃሎ ወደ የምርጫ ክልሉ ይላካል። በምርጫ ክልል ደረጃም የድምፅ ማጠቃለል ሥራው ከተከናወነ በኋላ ውጤቱን በይፋ ለማወጅና ለማረጋገጥ ወደ ዋናው መሥሪያ ቤት የማረጋገጫ ማዕከል እንዲመጣ ይደረጋል።

ውጤቶቹ ወደ ማረጋገጫ ማዕከሉ በሚደርሱበት ወቅት የእያንዳንዱ ምርጫ ክልል መረጃ በተናጠል ተለይቶ የሚታይ ሲሆን ተወዳዳሪዎች ያገኙት የድምፅ መጠን በዝርዝር የማጣራት ሥራ በትኩረት ይከናወናል።

ሰብሳቢዋ አክለውም በማዕከሉ ውስጥ ከተመዘገበው አጠቃላይ የመራጭ ሕዝብ ቁጥር አንጻር ጸንተው የሚደመሩ፣ ዋጋ የሌላቸው እና ጥቅም ላይ ያልዋሉ የድምፅ መስጫ ወረቀቶችን የመለየት ተግባር በከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚሠራ አስታውቀዋል።

ቦርዱ ይህንን የማረጋገጥ ሒደት በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ውስጥ ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝም ሰብሳቢዋ ሜላትወርቅ ኃይሉ ገልጸዋል።
#ምርጫቦርድ #ምርጫ #የምርጫውጤት #የኢትዮጵያምርጫ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.