1 month ago
አርጀንቲና ኬፕቨርዴን በማሸነፍ ወደ 16ቱ ጥሎ ማለፍ ተሸጋገረች
*********
በ23ኛው ዓለም ዋንጫ የ32 ሀገራት ጥሎ ማለፍ መርኃ ግብር አፍሪካዊቷን ደሴት ኬፕቨርዴን የገጠመችው አርጀንቲና 3 ለ 2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ቀጣዩን የ16 ሀገራት ጥሎ ማለፍ ዙር ተቀላቅላለች።
ሊዮኔል ሜሲ ለአርጀንቲና ዳንኤል ዱዋርቴ ደግሞ ለኬፕቨርዴ 1 አቻ በተጠናቀቀው መደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ግቦቹን ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው።
አሸናፊውን ለመለየት በተጨመሩት 90 ደቂቃዎች፤ የአርጀንቲናን የማሸነፊያ ግቦች ያስቆጠሩት ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ እና ዲኔይ ቦርገስ(በራሱ መረብ ላይ) ሲሆን የኬፕ ቨሮዴን ግብ ሲድኒ ካብራል ከመረብ አሳርፏል።
ሻምፒዮኗ አርጀንቲና በቀጣዩ የጥሎ ማለፍ መርኃ ግብር ግብፅን የምትገጥም ይሆናል።
#worldcup #fifaworldcup #argentina #caboverde #lionelmessi #football #sports

ሊዮኔል ስካሎኒ በአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነት 100ኛ ጨዋታውን ያደርጋል
**************************
የ“አልበ ሰልስቴ”ዎቹ ወርቃማ ትውልድ ታሪክ መስራቱን ቀጥሏል። ለሌላ የዓለም ሻምፒዮንነት የጀመረውን መንገድ በአስገራሚ ሁኔታ እየተጓዘ ነው። የ48 ዓመቱ ሰው በሊዮኔል ሜሲ ዙሪያ የተገነባውን ቡድን በአህጉር እና ዓለም አቀፍ ደረጃ ወደ ስኬታማነት እያመላለሰው ነው።
ከ2018ቱ ዓለም ዋንጫ በኋላ ስካሎኒ የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድንን አሰልጣኝነት ሲረከብ በዓለም እግር ኳስ በጉልህ የሚጠራ ስም አልነበረውም። ሆኖም አሰልጣኙ የጎላ የአሰልጣኝነት ልምድ ሳይኖረው የኳታሩን ዓለም ዋንጫ ጨምሮ ሁለት የኮፓ አሜሪካ ክብሮችን አሳክቷል። የፋይናሊዝማ ዋንጫም የስኬቱ አካል ነው።
ያኔ ከስምንት ዓመታት በፊት ስካሎኒ የሆርጌ ሳምፓውሊን መንበር ሲረከብ ታላቁን ማራዶና ጨምሮ ብዙዎች በጥርጣሬ ነበር የተመለከቱት። ልምዱ ታላቋን የእግር ኳስ ሀገር በአሰልጣኝነት ለመምራት ብቁ አይደለም የሚለው የጥርጣሬው መነሻ ነበር።
ማራዶና ኃይለ ቃላትን ጭምር ተጠቅሞ ስካሎኒን የተቸው ጄራርዶ ማርቲኖ ወደ ቀድሞ አሰልጣኝነታቸው መመለሳቸውን በመሻትም ጭምር ነው።
የቀድሞ የዲፖርቲቮ ላካሮኛ እና ላዚዮ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ለብሔራዊ ቡድንም ቢሆን ከሰባት ኢንተርናሽናል ጨዋታዎች ውጭ ኣላሸነፈም። ከሊዮኔል ሜሲ ጋር አብረው የተጫወቱበት የ2006 የጀርመን ዓለም ዋንጫ በተጫዋችነት ትልቁ ዓለም አቀፍ ተሳትፎው ነው።
የአሰልጣኝነት ትልቁ ልምዱ ግን በ2018 ዓለም ዋንጫ በ16ቱ ጥሎ ማለፍ በተሰናበተው የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን የሆርጌ ሳምፖሊ ረዳት ሆኖ ሲሰራ ይጀምራል። የሳምፖሊ መሰናበት ደግሞ ለስካሎኒ አዲስ ዕድል ይዞለት መጣ።
“አልበ ሰልስቴ”ዎቹን በዋና አሰልጣኝነት የመምራት ዕድል። በዚህም ጊዜያዊ አሰልጣኝ በኋላም ዋና አሰልጣኝ ሆኖ በቅርብ ዓመታት ከታዩ ውብ እግር ኳስ ከሚጫወቱ ብሔራዊ ቡድኖች አንዱን አሳየ።
“ስካሎኒታ” አሁን በተጫዋችነት ዘመኑ ያላገኘውን ክብር በአሰልጣኝነት ተቀዳጅቷል። ስካሎኒ ብሔራዊ ቡድኑን እየመራ ካደረጋቸው 99 ጨዋታዎች 72 አሸንፏል፣ በ18 አቻ ተለያይቷል፣ በ9 ጨዋታዎች ደግሞ ተሸንፏል። ከ2019 – 2022 የተጓዘበት በ36 ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ጉዞውም የመንገዱ አካል ነው።
ነገ ሚያሚ ላይ የሚደረገው የ32ቱ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ለሊዮኔል ስካሎኒ 100ኛ መርኃ ግብር ሆኖ ይመዘገባል። አርጀንቲና ሲሆን አስከ ሻምፒዮንነት ካልሆነ ግን እስከ ፍፃሜ ትጓዛለች ተብላ በምትጠበቅበት በዚህ ዓለም ዋንጫ መሃል ስለ 100ኛ ጨዋታው ተጠይቆ፤ ያኔ 100ኛ ጨዋታው ላይ እደርሳለሁ ብሎ አስቦ እንዳልነበር ነው የተናገረው።
ሆኖም ይህ በህይወቱ አስቦት የማያውቀው ደረጃ ቢሆንም ዋነኛ ትኩረቱ የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድንን ለተከታታይ የዓለም ሻምፒዮንነት ማብቃት መሆኑን ገልጿል።
ይህን በዓለም እግር ኳስ የስኬታማነት ምሳሌ የሆነ ታሪካዊ ቡድንን መምራት እና ይህን ያህል ርቀት መጓዝ ልዩ ስሜት እንደሚፈጥር ግን አልሸሸገም።
ትሁቱ ሰው የ21ኛው ክፍለ ዘመን የእግር ኳስ ክስተት ሜሲንም ሆነ ብሔራዊ ቡድኑን ውጤታማ በሚያደርግ አግባብ በእርሱ ዙሪያ የገነባው ቡድን ለስኬታማነቱ በምክኒያትነት የሚጠቀስ ዋነኛ ጉዳይ ነው።
የዓለም ዋንጫውን ኮከብ ግብ አስቆጣሪነት ከኪሊያን ምባፔ ጋር በስድስት ግቦች እየመራ የሚገኘው ሊዮኔል ሜሲ በብሔራዊ ቡድን ደረጃ የዘመኑን ውጤታማ ጊዜያት በስካሎኒ አሰልጣኝነት ስር ነው ያሳለፈው።
በ74 ጨዋታዎች 58 ጊዜ ኳስና መረብን አገናኝቷል። በ128 ጨዋታዎች 65 ግቦች ካስቆጠረበት የቀደመው ጊዜ ጋር ተነፃፅሮ በጨዋታዎች ብዛት ሲሳላ በእጅጉ ያነሰ ነው።
በመጀመሪያው 0.51 በሁለተኛው ደግሞ 0.78 በአማካይ በየጨዋታው ያስቆጠራቸው ግቦች ናቸው። ይህ ቁጥር ስካሎኒ በሜሲ ዙሪያ የሚያጠነጥን ቡድን ለመገንባቱ ጉልህ ማሳያ ነው።
የአሰልጣኙ ውል በቀጣይ ዓመት ታህሳስ ወር ላይ ያበቃል። የአርጀንቲና እግር ኳስ ፌደሬሽንም የአሰልጣኙን ውል ለተጨማሪ አምስት ዓመታት ለማራዘም እንቅስቃሴ መጀመሩ ታውቋል።
የ48 ዓመቱ ሊዮኔል ስካሎኒ በአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነት 100ኛ ጨዋታውን የዓለም ዋንጫው ክስተት ከሆነችው ኬፕቨርዴ ጋር ነገ ሌሊት 7፡00 ሰዓት በሚያሚው ሃርድ ሮክ ስታዲየም ያደርጋል።
በእድሪስ አህመድ
Ethiopian Broadcasting Corporation EBC-መዝናኛ EBC SPORT ኢቢሲ ስፖርት #messi #argentina #football

የ32ቱ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ እየተካሄደ በሚገኘው የ2026 የዓለም ዋንጫ የምድብ ጨዋታዎች ተጠናቅቀዋል።
ከየምድቦቻቸው 1ኛ እና 2ኛ በመሆን 24 ሀገራት በቀጥታ እንዲሁም ተጨማሪ 8 ሀገራት ምርጥ 3ኛ በመሆን የ32ቱን ጥሎ ማለፍ ተቀላቅለዋል።
በዚህም መሰረት የ32ቱ የጥሎ ማለፍ መርሐ ግብር ከምድብ 1 እና 2 ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቁት ደቡብ አፍሪካ እና አዘጋጇ ሀገር ካናዳ ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀምራል።
ምድብ ሦስትን በበላይነት ያጠናቀቀችው ብራዚል ከጃፓን እንዲሁም የምድብ 5 አሸናፊዋ ጀርመን ከፓራጓይ ተደልድለዋል።
ኔዘርላንድስ ከሞሮኮ፣ ኮትዲቯር ከኖርዌይ፣ ፈረንሳይ ከስዊድን፣ ሜክሲኮ ከኢኳዶር፣ እንግሊዝ ከዲሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክ እንዲሁም ቤልጂዬም ከሴኔጋል ይገናኛሉ።
አሜሪካ ከቦሲኒያ ሄርዞጎቪና፣ ስፔን ከኦስትሪያ፣ ፖርቹጋል ከክሮሺያ፣ ስዊዘርላንድ ከአልጄሪያ፣ አውስትራሊያ ከግብጽ፣ አርጀንቲና ከኬፕቨርዴ እንዲሁም ኮሎምቢያ ከጋና ተደልድለዋል።

2 months ago
ስፔን ከሳዑዲ አረቢያ…
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሜሪካ፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ አዘጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የ2026 የዓለም ዋንጫ የምድብ 2ኛ ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው ይደረጋሉ፡፡
በምድብ 8 የምትገኘው ስፔን ምሽት 1 ሰዓት ላይ ከሳዑዲ አረቢያ ጋር የምድብ ሁለተኛ ጨዋታዋን ታደርጋለች፡፡
በ2026 የዓለም ዋንጫ ለሻምፒዮንነት ቅድመ ግምት የተሰጣት ስፔን በውድድሩ የመጀመሪያ ሦስት ነጥብ ለማሳካት ወደ ሜዳ የምትገባ ይሆናል፡፡
ተጋጣሚዋ ሳዑዲ አረቢያም በተመሳሳይ በውድድሩ ሦስት ነጥብ ለማሳካት የምታደርገው ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡
በዚሁ ምድብ የሚገኙት ዩራጋይ እና ኬፕቨርዴ ሌሊት 7 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
በምድብ-7 ቤልጂየም ከኢራን ምሽት 4 ሰዓት ላይ እንዲሁም ኒውዚላንድ ከግብጽ ሌሊት 10 ሰዓት ላይ ይገናኛሉ፡፡

ቮዚኒያ : የኬፕቨርዴው ግብ ጠባቂ
#ethiopia | በዓለም ዋንጫ መድረክ ኬፕቨርዴ ከኃያሏ ስፔን ጋር ነጥብ እንድትጋራ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከተው ግብ ጠባቂው ቮዚኒያ በአሁኑ ወቅት ሰፊ አድናቆትን እያገኘ ይገኛል።
ይህ ድንቅ ብቃቱ ማኅበራዊ ገጹ ላይም ትልቅ ተፅዕኖ የፈጠረ ሲሆን ከጨዋታው በኋላ የኢንስታግራም ተከታዮቹ ቁጥር ከ56 ሺህ ተነስቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ 3 ሚሊዮን አድጓል።
ዕድሜው 40 ዓመት የሞላው ይህ ግብ ጠባቂ በዓለም ዋንጫ ታሪክ ውስጥ ጨዋታ በማድረግ ሁለተኛው በእድሜ አንጋፋ ተጨዋች በመሆን አዲስ ታሪክ አስመዝግቧል።
ከእርሱ ቀድሞ የሚገኘው በ45 ዓመቱ ሜዳ ውስጥ የገባው ግብፃዊው ግብ ጠባቂ ኢሳም ኤል ሀዳሪ ብቻ ነው።
ትክክለኛ ስሙ ጆሲማር ሆሴ ኤቮራ ዲያስ ቢሆንም በይበልጥ የሚታወቀው ግን ቮዚኒያ በሚለው የቅፅል ስሙ ነው።
ጆሲማር የሚለውን ስም ያወጣለት አባቱ ሲሆን በ1986 የዓለም ዋንጫ ወቅት አባቱ በወታደራዊ አገልግሎት ላይ እያለ ብራዚላዊው ተጫዋች ጆሲማር ባሳየው አስደናቂ ብቃት ተማርኮ አዲስ የተወለደ ልጁን በእርሱ ስም ሰይሞታል።
ቮዚኒያ የሚለው የቅፅል ስሙ ደግሞ በፖርቹጋልኛ ቋንቋ አያቴ ማለት ነው። ይህን ስም ሊያገኝ የቻለው ከአያቱ ጋር ስላደገ እና በጣም ይቀራረብ ስለነበር ነው። በልጅነቱ ሰፈር ውስጥ ኳስ ሲጫወት በተጎዳ ቁጥር በቀጥታ ወደ አያቱ ይሮጥ ስለነበር የሰፈሩ ልጆች ይህንን ስም አውጥተውለታል።
ይህ አንጋፋ ግብ ጠባቂ በዕለቱ ለምን እንደአለቀሰ ሲያስረዳ ከአያቱ ጋር እንዳደገ ገልጾ እርሷ በቅርብ ዓመት ማለፏንና እናቱ ደግሞ በቪዛ ምክንያት እንዲሁም ከፍተኛ የገንዘብ ማስያዣ በመጠየቋ ወደ ስፍራው ልትመጣ ስላልቻለች መሆኑን በሀዘን ተናግሯል።
ቢረፍድም ለሀገሩ ታሪክ የሰራው ቮዚኒያ በደስታ ዕንባ ታጥቧል። በአትላንታ ስታዲየም የስፔን የፊት መስመር አጥቂዎች ወደ ግብ በደረሱባቸው አጋጣሚዎች ሁሉ በፖርቹጋል ሁለተኛ ዲቪዚዮን ለቻቬስ ክለብ የሚጫወተው ይህ ባለተሰጥኦ ግብ ጠባቂ እንደ ብረት የጠነከረ ግንብ በመሆን ወደ መረብ የተመቱ ኳሶችን በሚገርም ብቃት መልሷል።
በተለይም ፌራን ቶሬስ እና አሜሪክ ላፖርቴ ያደረጓቸውን ተደጋጋሚ እና አደገኛ ሙከራዎች ማክሸፍ የቻለ ሲሆን ቶሬስ ያገኘውን ወርቃማ የግብ ዕድል በቮዚኒያ ጫና ምክንያት አግድም ብረት ላይ መትቶታል።
በጨዋታው ማጠናቀቂያ ላይ ሚኬል ኦያርዛባል የሞከረውን ኳስ ደግሞ ሮቤርቶ ሎፔስ ባደረገው አስደናቂ መከላከል ሊያድን ችሏል።
ስፔን በጨዋታው በአጠቃላይ 27 የግብ ሙከራዎችን ያደረገች ቢሆንም ኢላማውን የጠበቀው ግን ሰባቱ ብቻ ነበር። ከዚህም በተጨማሪ የኒኮ ዊሊያምስ በቋሚነት አለመሰለፍ የስፔንን የማጥቃት ጥንካሬ በእጅጉ ቀንሶታል ተብሏል።
የቀድሞው የቶተንሃም አሰልጣኝ አንጅ ፖስቴኮግሉ በእንግሊዙ አይቲቪ ስፖርት በሰጡት ትንታኔ ይህ የእግር ኳስ ውበትና ታላቅነት ነው ካሉ በኋላ የኬፕ ቨርዴ ተጫዋቾች በውስጣቸው የነበረው ወኔና ተነሳሽነት እጅግ አስደናቂ ነበር ብለዋል።
ጨዋታው ሲጠናቀቅም አንጋፋው ግብ ጠባቂ ቮዚኒያ በቡድን አጋሮቹ ታቅፎ የደስታ ዕንባውን ሲያብስ ታይቷል።
ስፔን እ.አ.አ በ2010 የዓለም ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታ በስዊዘርላንድ ብትሸነፍም በመጨረሻ ዋንጫውን ማንሳቷ ለዘንድሮው ጉዞዋ እንደ ተስፋ የሚቆጠር ታሪካዊ ማስታወሻ ሲሆን ኬፕ ቨርዴ ግን ከጋና የ2006 ጉዞ በኋላ ወደ ቀጣዩ ዙር የምታልፍ የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ሀገር የመሆን ዕድሏን በከፍተኛ ደረጃ አሳድጋለች።
#football #worldcup #capeverde #spain #sportsnews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

ኬፕ ቨርዴ ከስፔን ጋር ያለ ጎል አቻ በመለያየት ታሪክ ሰራች
#ethiopia | በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ እስካሁን ከተመዘገቡት ኩነቶች ሁሉ እጅግ አስገራሚና ታላቅ የተባለው ታሪክ በአትላንታ ሜዳ ላይ ተከስቷል።
በዓለማችን በቆዳ ስፋቷ በሦስተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው አነስተኛዋ አገር እና በፊፋ የደረጃ ሰንጠረዥ 67ኛ ላይ የምትገኘው ኬፕ ቨርዴ የአውሮፓ ሻምፒዮንና በዓለም እግር ኳስ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘውን ጠንካራዋን ስፔንን ያለ ምንም ጎል 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት በመግታት ነጥብ ማስጣል ችላለች።
የእግር ኳስ ተንታኞችና ብዙኃኑ ተመልካቾች ይህ ጨዋታ ለስፔን ብሔራዊ ቡድን ቀላል የግብ ማግቢያ ልምምድ እንደሚሆን ቅድመ ግምት ሰጥተው የነበረ ቢሆንም በሜዳ ላይ የታየው እውነታ ግን የዓለም ዋንጫ ሁልጊዜም አስቀድሞ ለመተንበይ አስቸጋሪ መሆኑን ዳግም አስመስክሯል።
የስፔን ተጫዋቾች በጨዋታው ላይ ለረጅም ሰዓታት ኳስን ተቆጣጥረው ቢጫወቱም የኬፕ ቨርዴን የተከላካይ መስመር ሰብረው ለመግባት ግን በእጅጉ ተፈትነዋል።
የስፔን የፊት መስመር አጥቂዎች ወደ ግብ በደረሱባቸው አጋጣሚዎች ሁሉ በፖርቹጋል ሁለተኛ ዲቪዚዮን ለቻቬስ ክለብ የሚጫወተው የ40 ዓመቱ አንጋፋ የኬፕ ቨርዴ ግብ ጠባቂ ቮዚንሃ እንደ ብረት የጠነከረ ግንብ ሆኖ አግዷቸዋል።
ይህ ግብ ጠባቂ ፌራን ቶሬስ እና አሜሪክ ላፖርቴ ያደረጓቸውን ተደጋጋሚና አደገኛ ሙከራዎች በሚያስደንቅ ብቃት አድኗል።
ቶሬስ በጨዋታው ያገኘውን ወርቃማ የግብ ዕድል በቮዚንሃ ጫና ምክንያት አግድም ብረት ሲመታበት በጨዋታው ማጠናቀቂያ ላይ ሚኬል ኦያርዛባል የሞከረውን ኳስ ደግሞ ሮቤርቶ ሎፔስ ባደረገው አስደናቂ መከላከል ሊከሽፍ ችሏል።
ስፔን በጨዋታው በአጠቃላይ 27 የግብ ሙከራዎችን ያደረገች ቢሆንም ኢላማውን የጠበቀው ግን ሰባቱ ብቻ ነበር።
የአሰልጣኝ ሉዊስ ዴ ላ ፉየንቴ ስብስብ የጨዋታውን አካሄድ ለመቀየር በማሰብ ከጉዳት ገና ያገገመውን የባርሴሎናውን ታዳጊ ላሚን ያማልን በሁለተኛው አጋማሽ ቀይረው ቢያስገቡም የያማል መግባት ስታዲየሙን ከማሞቅ ባለፈ ከስምንት ሳምንታት የጉዳት እረፍት በኋላ የተመለሰ በመሆኑ የስፔንን የማጥቃት ድክመት ሙሉ በሙሉ ሊፈታ አልቻለም።
ከዚህም በተጨማሪ የኒኮ ዊሊያምስ በቋሚነት አለመሰለፍ የስፔንን የማጥቃት ጥንካሬ በእጅጉ ቀንሶት ታይቷል።
የስፔኑ ታዋቂ ጋዜጣ ማርካ ሁኔታውን ሲገልጽ በአትላንታ ድንገተኛ አደጋ ተከሰተ ስፔን መጫወቻ መንገድና መፍትሔ አጥታ ተቸገረች በማለት በትችት ጽፏል።
በሌላ በኩል የቀድሞው የቶተንሃም አሰልጣኝ አንጅ ፖስቴኮግሉ በእንግሊዙ አይቲቪ ስፖርት በሰጡት ትንታኔ ይህ የእግር ኳስ ውበትና ታላቅነት ነው የኬፕ ቨርዴ ተጫዋቾች በውስጣቸው የነበራቸው ወኔና ተነሳሽነት እጅግ አስደናቂ ነበር። አሁን የዚህች ትንንሽ አገር ዜጎች በማንነታቸው በኩራት ይናገራሉ መላው ዓለምም አውቆላቸዋል በማለት አወድሰዋል።
የመጨረሻው ዳኛ ፊሽካ ሲነፋ የኬፕ ቨርዴ ተጫዋቾችና ደጋፊዎች የዓለም ዋንጫውን በራሱ ያሸነፉ ያህል ስታዲየሙን በደስታ ድምፅ አናውጠውታል።
አንጋፋው ግብ ጠባቂ ቮዚንሃ በቡድን አጋሮቹ ታቅፎ የደስታ ዕንባውን ሲያብስ ታይቷል።
ስፔን እ.አ.አ በ2010 የዓለም ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታ በስዊዘርላንድ ብትሸነፍም በመጨረሻ ዋንጫውን ማንሳቷ ለዘንድሮው ጉዞዋ እንደ ተስፋ የሚቆጠር ታሪካዊ ማስታወሻ ሲሆን ኬፕ ቨርዴ ግን ከጋና የ2006 ጉዞ በኋላ ወደ ቀጣዩ ዙር የምታልፍ የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት አገር የመሆን ዕድሏን በከፍተኛ ደረጃ አሳድጋለች።
#የዓለምዋንጫ #ኬፕቨርዴ #ስፔን #እግርኳስ #ስፖርት #አፍሪካ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Sponsored by
Surafel
Comments