2 days ago
“ሕልሜ አውሮፕላኑን ቴል አቪቭ ላይ መከስከስ ነበር!”
የፍላይዱባይ ረዳት አብራሪ ሃማም አል-ሃማሚ ወደ እስራኤል የሚበር አውሮፕላን ለመጥለፍና ለመከስከስ አስቀድሞ በጥንቃቄ ያቀደ መሆኑን በምርመራ ወቅት ማመኑን የጄሩሳሌም ፖስት ዘገባ አመልክቷል።
የ30 ዓመቱ ኦማናዊ ረዳት አብራሪ ወደ ቴል አቪቭ የሚበሩ አየር መንገድ ኩባንያዎችን አስቀድሞ በማጥናት ፍላይዱባይን እንደመረጠ ገልጾ፣ "ትልቁ ሕልሜ አውሮፕላኑን በቤን ጉሪዮን አውሮፕላን ማረፊያ ወይም በቴል አቪቭ ረጅም ሕንፃዎች ላይ መከስከስ ነበር" ብሏል።
ለዚሁ ጥቃት መረጃ ለመሰብሰብም ቀደም ብሎ በሥራ አጋጣሚ ወደ እስራኤል ተደጋጋሚ ጉዞ ያደርግ ነበር።
የጥቃት ዕቅዱ የጦር ጄቶች ደርሰው ሳይከለክሉት በፍጥነት የሚፈጸም ነበር።
ረዳት አብራሪው ዋና አብራሪውን በምሳር መትቶ እጁን ከባድ አደጋ ካደረሰበት በኋላ፣ የአውሮፕላኑን ሞተሮች በማጥፋት ለመከስከስ ሞክሯል።
ሆኖም ዋና አብራሪው ከባድ ጉዳት ቢደርስበትም ከተሳፋሪዎች ጋር በመተባበር ረዳት አብራሪውን በቁጥጥር ስር በማዋል አውሮፕላኑን በሳዑዲ ዓረቢያ በሰላም ማሳረፍ ችለዋል።
የእስራኤል ባለስልጣናት ግለሰቡ ጥቃቱን የፈጸመው በራሱ ተነሳሽነት እንጂ ከሽብር ቡድን ታዝዞ እንዳልሆነ ገልጸዋል።
አል-ሃማሚ ቀደም ሲል በኦማን አየር መንገድ ይሰራ የነበረ ቢሆንም በአክራሪነት አስተሳሰቡ ምክንያት ከስራ የተባረረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የአውስትራሊያ ፖሊስና የደህንነት ተቋማት ግለሰቡ በአውስትራሊያ በነበረበት ወቅት እንዴት ወደ ፅንፈኝነት እንደገባ መረጃዎችን በማሰባሰብ ሰፊ ምርመራ እያደረጉበት ይገኛሉ።
Seledadotio

5 days ago
የደቡብ አትላንቲክ የዓሣ ነባሪ መጠለያ ሀሳብ ዳግም ውድቅ ሆነ
ዓሣ ነባሪዎችን ከአደንና ከተለያዩ የባሕር አደጋዎች ለመጠበቅ የቀረበው የደቡብ አትላንቲክ የጥበቃ ቀጣና ሀሳብ ዳግም ሳይፀድቅ ቀርቷል። ሀሳቡ በአርጀንቲና፣ ብራዚልና ኡራጓይ የቀረበ ሲሆን፣ በአውስትራሊያ ሆባርት ከተማ በተካሄደው 70ኛው የዓለም አቀፉ የዓሣ ነባሪ ኮሚሽን ስብሰባ ላይ ተወያይቶበታል።
ሀሳቡ ቢፀድቅ በደቡብ አትላንቲክ ሰፊ የባሕር አካባቢ ከንግድ ዓሣ ነባሪ አደን የተጠበቀ ቀጣና ይፈጠር ነበር። የመጠለያው ዓላማም ዓሣ ነባሪዎችን ከአደን በተጨማሪ በባሕር ላይ ለሚያጋጥሟቸው ሌሎች ስጋቶች ጥበቃ ማጠናከር ነው። ዓሣ ነባሪዎች በባሕር ሥነ-ምህዳር ውስጥ ጠቃሚ ሚና ስላላቸው፣ የሚኖሩበትንና የሚፈልሱበትን አካባቢ መጠበቅ የባሕር ሥነ-ምህዳሩን ጤና ለመጠበቅ እንደሚያግዝ ተገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪም፣ ዓሣ ነባሪዎች በረጅም ርቀት ስለሚፈልሱ ከትላልቅ መርከቦች ጋር መጋጨት ለእነሱ ከሚያጋጥሙ አደጋዎች አንዱ ነው። ሰፊና በተገቢው የሚተዳደር የባሕር ጥበቃ ቀጣና መፍጠር እንደ መርከብ ግጭት ያሉ ስጋቶችን ለመቀነስ ሊያግዝ ይችላል።
ይሁንና ሀሳቡ ለመፅደቅ ከሚያስፈልገው የሦስት አራተኛ ድምፅ ድጋፍ በታች በማግኘቱ ሳይፀድቅ ቀርቷል። የጀርመን የዜና ወኪል epd እንደዘገበው፣ ይህ ለደቡብ አትላንቲክ የዓሣ ነባሪ መጠለያ ለመመስረት የቀረበው ሀሳብ ዳግም ለወደፊት ውይይት እንዲተላለፍ አድርጓል። የጀርመን መንግሥት በበኩሉ ለሀሳቡ ድጋፍ መስጠቱን ገልጿል።
ቤዛዊት አራጌ
#ዳጉ_ጆርናል

12 days ago
ኦፕንኤአይ የሰራው ኤአይ ኤጀንት የአውስትራሊያ መንግስት ድረ-ገጽን ጥሶ መግባቱን ጠቅላይ ሚኒስትሩገለፁ
በኦፕንኤአይ (OpenAI) የበለፀገ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ኤጀንት ባለፈው ሰኔ ወር የፈቃድ ወሰኑን አልፎ ወደ አውስትራሊያ መንግስት ድረ-ገጽ በመግባት ይፋዊ እና ሚስጥራዊ የሆኑ መረጃዎችን ማግኘት መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኔዝ አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድርጊቱን በኤአይ ኤጀንት የመንግስት ስርዓት የተሰበረበት የመጀመሪያው የሚታወቅ አጋጣሚ ሲሉ ገልፀውታል።
ራሱን ችሎ የሚሰራው የኦፕንኤአይ ፕሮግራም ባለፈው ሰኔ ወር የአውስትራሊያ መንግስት የጤና ድረ-ገጽን ጥሶ የገባው ተቀባይነት የሌለው በሆነ መንገድ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኔዝ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ረቡዕ ዕለት በኒውዮርክ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፣ ይህ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ኤጀንት የጤና ስታቲስቲክስ አገልግሎቱን ይፋዊ እና ሚስጥራዊ ፋይሎች ማግኘት ችሏል።
ኦፕንኤአይ ስለ ሁኔታው ለአውስትራሊያ መንግስት ጥቆማ የሰጠው እስከ መስከረም ወር ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ሲሆን፣ ያንንም ያደረገው ክስተቱን የሚያብራራ ኢሜይል ለማንኛውም ሰው ክፍት ወደሆነ አጠቃላይ የኢሜይል አድራሻ በመላክ ነበር። ዛሬ ከኦፕንኤአይ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሳም ኦልትማን ጋር በመነጋገር አውስትራሊያ በዚህ ክስተት ላይ ያላትን ከፍተኛ ስጋት ገልጬላቸዋለሁ ብለዋል አልባኔዝ።
አክለውም ኩባንያው የሂደቱን ዝርዝር ለስርዓታችን ለማሳወቅ ይህን ያህል ረጅም ጊዜ በመውሰዱ የተሰማኝን ቅሬታ ገልጫለሁ ብለዋል። ምንም ዓይነት ማሳወቂያ ከመደረጉ በፊት እስከ መስከረም 10 ድረስ ፈጅቷል፤ የተደረገውም ማሳወቂያ ቢሆን ለሕዝብ ክፍት ወደሆነ የኢሜይል ሳጥን የተላከ ኢሜይል ብቻ ነበር።
ከኦፕንኤአይ እና ከተፎካካሪው አንትሮፒክ ኤአይ ሞዴሎች ጋር በተያያዙ ተከታታይ የሳይበር ጥቃቶች ምክንያት፣ በላቀ የኤአይ መሳሪያዎች ኃይል ላይ ያለው ዓለም አቀፋዊ ስጋት እየጨመረ መጥቷል። የኦፕንኤአይ መሳሪያው የተከለከሉ መረጃዎችን ለማግኘት ሲሞክር የጤና ምርምር እያካሄደ እንደነበር አልባኔዝ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም መረጃውን እንዳያገኝ በተከለከለ ጊዜ፣ እገዳውን ያልፍ ዘንድ ሌሎች መንገዶችን ፈልጓል ብለዋል።ኦፕንኤአይ የተሻሉ የአሰራር ደንቦች ሊኖሩት እንደሚገባ የሚያውቅ ይመስለኛል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህ መግባት ወደሌለበት ቦታዎች የገባ የምርምር ፕሮጀክት ነው ሲሉ አብራርተዋል።
ሰላማዊ ነጋሲ

13 days ago
የዜጎቿን የጤና መረጃ በያዘ የኤአይ ወኪል ተቋም ላይ የደህንነት ጥሰት መፈፀሙን አውስትራሊያ አስታወቀች
የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኔዝ በሰዉ ሰራሽ አስተውሎት ዙሪያ “አፋጣኝ ዓለም አቀፍ የጥበቃ ማዕቀፎች” እንዲዘጋጁ የሚጠይቅ የጋራ ጥሪ ላይ ከፈረሙ ከአንድ ቀን ባነሰ ጊዜ ውስጥ፣ የአውስትራሊያ ዜጎችን የጤና መረጃ በያዘ የመንግስት ድረ-ገጽ ላይ በአንድ “የኤአይ ወኪል ተቋም ላይ” የደህንነት ጥሰት መፈጸሙን ይፋ አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማክሰኞ ዕለት በኒው ዮርክ እየተካሄደ ካለው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን፣ ካናዳ፣ ስፔን እና ጀርመንን ጨምሮ ከ21 ፈራሚዎች ጋር በመሆን “የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሞዴሎችን ለመቆጣጠር የቀረበ ጥሪ” በሚል መግለጫ ላይ በጋራ ፈርመዋል።
ረቡዕ ዕለት ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት አልባኔዝ፣ በ ኦፕን AI የበለጸገው ይህ ተቋም በሰኔ ወር በመንግስት የሜዲኬር ወደብ ላይ የሚገኙ ህዝባዊ እና ህዝባዊ ያልሆኑ መረጃዎችን ሰብሮ መግባቱን ተናግረዋል።
አልባኔዝ አያይዘውም ኩባንያው የደህንነት ጥሰቱን አምኖ ለመቀበል ሶስት ወራት መውሰዱ እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል።
ከጋዜጣዊ መግለጫው ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ምላሽ የሰጠው ተቋሙ ጉዳዩን አሁንም እያጣራ መሆኑን ቢገልጽም፣ የታካሚዎች የህክምና ታሪክ መረጃዎች መወሰዳቸውን የሚያሳይ ምንም ዓይነት ማስረጃ እንደሌለ አስታውቋል።
በሚኪያስ ጸሐዬ

የዓለም የሜትሮሎጂ ድርጅት 2027 ዓ.ም. እጅግ ሞቃታማው ዓመት ሊሆን እንደሚችል አስጠነቀቀ።
የዓለም የሜትሮሎጂ ድርጅት ይፋ ባደረገው አዲስ መረጃ፣ የፓስፊክ ውቅያኖስ ሙቀት መጨመርን ተከትሎ የተፈጠረው የኤል ኒኖ ክስተት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ በመምጣት እስከ እ.ኤ.አ. የካቲት 2027 ድረስ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የመድረስ እድሉ ከፍተኛ መሆኑን አስታወቀ።
ድርጅቱ በአየር ንብረት እና በውቅያኖስ ጥናቶች ላይ በመመስረት ባወጣው መግለጫ፣ ይህ ክስተት ከታሪክ አኳያ ከታዩት እጅግ ኃይለኛ የኤል ኒኖ አዝማሚያዎች አንዱ ሊሆን እንደሚችል ገልጿል።
የድርጅቱ ዋና ጸሐፊ "ይህ ክስተት በዓለም አቀፍ ደረጃ በሙቀት መጠን ላይ ከፍተኛ ጭማሪ እንዲመዘገብ ምክንያት ይሆናል" ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ በዝናብ ስርጭት፣ በሙቀት መጠን እና በሁኔታዎች ላይ ከፍተኛ መዋዠቅ እንደሚያስከትል የተጠበቀው ይህ የኤል ኒኖ ክስተት፤ በተለይ በደቡብ አፍሪካ፣ በደቡብ አሜሪካ እና በአውስትራሊያ ከባድ ድርቅ፣ የሙቀት ማዕበል እና የደን እሳት አደጋዎችን ሊያባብሰው እንደሚችል ተመልክቷል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በበኩሉ፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሊደርስ የሚችለውን ሰብአዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ለመቀነስ አስቸኳይ ቅድመ-ዝግጅትና የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓቶችን ማጠናከር እንዳለበት አሳስቧል።
@TikvahethMagazine

22 days ago
በህልሙ ባያቸው ቁጥሮች 8 ሚሊዮን ዶላር አሸናፊ የሆነው ግለሰብ!
#ethiopia | በሕልሙ ያያቸውን ቁጥሮች ላለፉት 5 ዓመታት ሲቆርጥ የነበረው ግለሰብ የሎተሪ አሸናፊ መሆኑ ተገለፀ።
አውስትራሊያ ነዋሪነቱን ያደረገው ይህ ግለሰብ በሕልሙ የተመለከታቸውን ቁጥሮች ባለመተው ላለፉት አምስት ዓመታት በተደጋጋሚ ሲቆርጥ እንደነበረ ተገልጿል።
ግለሰቡ ከ5 ዓመታት በፊት በሕልሙ ባያቸው 6 ልዩ ቁጥሮች ተስፋ ሳይቆርጥ በእያንዳንዱ የሎተሪ ዕጣ ወቅት እነዚሁኑ ቁጥሮች ብቻ በመምረጥ ይገዛ እንደነበር ታውቋል።
በርካቶች የዕድል ቁጥራቸውን በየጊዜው ሲቀይሩ እሱ ግን በሕልሙ ያየውን ምልክት እንደ ተራ ነገር ሳይቆጥር በጽናትና በትዕግስት ተመሳሳይ ቁጥሮችን መቁረጡን ቀጥሎበታል።
በቅርቡ በወጣው ይፋዊ የሎተሪ ዕጣ መውጫ ላይ በሕልሙ ያያቸው ሁሉም 6 ቁጥሮች ሙሉ በሙሉ በመውጣታቸው የ8 ሚሊዮን ዶላር ባለቤት ለመሆን በቅቷል።
ግለሰቡ ስለ ዕድሉ ሲናገር ብዙዎች ሕልምን እንደ ተራ ቅዠት ይቆጥሩታል እኔ ግን ሕልሜን አልናቅኩትም ነበር ሲል ተናግሯል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #lotterywinner #dreamtoreality #australianews #inspirationalstory #luckynumbers

Sponsored by
Surafel
24 days ago
ኢትዮጵያዊያኖች የድህነትን ተራራ በሩጫ ደርምሶ በመጣል ወደ ሀብት ማማ ወይም ወደ ሚሊየነሮች ተርታ የተሠለፉበት ታሪካዊ ድልና ሽልማት በሀንጋሪ ቡዳፔስት
🔴አትሌት ልቅና አምባው 150,000 ዶላር ወይም ከ26 ሚሊየን ብር በላይ ያሸነፈች የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊ አትሌት ሆና ስሟን በታሪክ መዝገብ አፅፋለች
ኢትዮጵያዊያን ለሽልማት ከተወጋጀው 10ሚሊየን ውስጥ 377ሺ ዶላር ወይም ከ65 ሚሊየን ብር በላይ ወደ ሀገሪቱ ኢኮኖሚ ይጨምራሉ
ኢትዮጵያዊቷ ልቅና አምባው በሀንጋሪ ቡዳፔስት በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ አልቲሜት ሻምፒዮና (World Athletics Ultimate Championship)የሴቶች የ5000 ሜትር ውድድርን 14:30:36 በሆነ ጊዜ በመግባት በአስገራሚ የአጨራረስ ብቃት ቀማሸነፍ አዲስ ታሪክ አፃፈች።
አትሌት ልቅና አምባው አውስትራሊያዊቷን ጄስ ኸልን እና የሀገሯን ልጅ ፋንታዬ በላይነህን በመቅደም የ5000 ሜትር የሴቶች የአልቲሜት ሻምፒዮና የወርቅ ሜዳሊያ እና የ150,000 ዶላር ወይም ከ26 ሚሊየን ብር በላይ ያሸነፈች የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊ አትሌትም በመሆን ስሟን በታሪክ መዝገብ ላይ በወርቅ ቀለም በደማቁ አፅፏለች።
🔴የአትሌት ልቅና አምባው የቅርብ ጊዜ ድሏ
አትሌት ልቅና አምባው የአልቲሜት ሻምፒዮንሺፕ የ5ሺ ሜትር አሸናፊ መሆኗን ዛሬ ከማወጇ በፊት የሮም ዳይመንድ ሊግን ሰኔ 2026 መጀመሪያ ላይ 14:18:41 በሆነና በወቅቱ የዓለም ፈጣኑ በሆነ ጊዜ በመሮጥ የመጀመሪያውን የዳይመንድ ሊግ ድል አስመዘግባለች።
አትሌት ልቅና አምባው መጋቢት 2026 በተካሄደው 45ኛው የበርሊን ግማሽ ማራቶን 1:05:07 በሆነ ጊዜ አሸናፊ በመሆንም በታሪክ ላይ ታሪክ ማፃፏንም ቀጥላለች።
አውስትራሊያዊቷ ጄሲካ ኸል (በግል ምርጥ ሰዓቷ 14:32.39 በማስመዝገብ የጨረሰች ሲሆን ከሁለት ሰከንድ በላይ በሆነ ልዩነት በመቅደም አሸንፋለች። ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊ ፋንታዬ በላይነህ 14:32:62 በሆነ ሰዓት ሦስተኛ ደረጃን የያዘች ሲሆን ይህም ከሀገርዋ ልጆች አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ እና አለሺኝ ባወቀ ቀድማ እንድትጨርስ አስችሏታል።
🔴በ5ሺ ሜ ሴቶች ያሸነፉበት ሠዓቴና ያገኙት ሽልማት
1.
አትሌት ልቅና አምባው ⏰14:30:36
💰150,000(usd)
2.
ጄሲካ ኸል ⏰14:32:39(PB)
💰75,000(usd)
3.
አትሌት ፋንታዬ በላይነህ ⏰14:32:62
💰40,000(usd)
4.
አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ ⏰14:32:76
💰25,000(usd)
5.
አትሌት አለሽኝ ባወቀ ⏰14:32:95
💰16,000(usd)
6.
ሮስ ዴቪስ ⏰14:35:64
💰14,000(usd)
7.
አትሌት ሠናይት ጌታቸው ⏰14:38:65
💰12,000(usd)
8.
ማውረን ኮስትር ⏰14:38:78
💰10,000(usd)
9.
አትሌት ሂሩት መሸሻ ⏰14:42:49
💰9,000(usd)
10.
ሀናህ ኑታል ⏰15:00:04
💰8,000(usd
11.
ሼልቢ ሁሊኸን ⏰15:18:65
🔴ኢትዮጵያዊያን አትሌቶችምን ያህል ዶላር ወደ ካዝናቸው ከተቱ
የዓለማችን ከዋክብት ብቻ የተሠባሠቡበትና ውዱ ሽልማት 10ሚሊየን ዶላር በተበጀተለት በታሪካዊው የአልቲሜት ሻምፒዮና ኢትዮጵያዊያን አቴሌቶች ምን ያህል ዶላር ወደ ካዝናቸው ከተቱ?የሚል ጥያቄ መመዘዙ አይቀርም ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ቢኒያም መሐሪና ፍሬወይኒ ሐይሉ ቴናንት 4ተኛ በመውጣት ያገኙትን 50ሸመ ዶላር እና ዛሬ የተገኘውን ዳጎስ ያለ ዶላር ጨምሮ 377,000 የአሜሪካን ዶላር ወይም በወቅታዊ ምንዛሪ ከ65 ሚሊየን የኢትዮጵያ ብር በላይ ወደ ሀገሪቱ ኢኮኖሚ ይጨምራሉ
።
🔴ከዚህ ውስጥ ከፍተኛውን ያገኘችው አትሌት ልቅናው አምባው 150ሺ ዶላር ወይም በወቅታዊ ምንዛሪ ከ26 ሚሊየን ብሩን ለብቻዋ ስታገኝ አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ 50ሺ ዶላር ለብቻዋ ያገኘች አትሌትም ናት።
🔴ይህ ገንዘብ የድህነትን ተራራ በሩጫ ደርምሶ በመጣል ወደ ሀብት ማማ ወይም ወደሚሊየነሮች ተርታ የሚያሠልፍ ታሪካዊ ድልና ሽልማት ነው።
✍️✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርትጰኦፊሺያል)
🔴አትሌት ልቅና አምባው 150,000 ዶላር ወይም ከ26 ሚሊየን ብር በላይ ያሸነፈች የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊ አትሌት ሆና ስሟን በታሪክ መዝገብ አፅፋለች
ኢትዮጵያዊቷ ልቅና አምባው በሀንጋሪ ቡዳፔስት በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ አልቲሜት ሻምፒዮና (World Athletics Ultimate Championship)የሴቶች የ5000 ሜትር ውድድርን 14:30:36 በሆነ ጊዜ በመግባት በአስገራሚ የአጨራረስ ብቃት ቀማሸነፍ አዲስ ታሪክ አፃፈች።
አትሌት ልቅና አምባው አውስትራሊያዊቷን ጄስ ኸልን እና የሀገሯን ልጅ ፋንታዬ በላይነህን በመቅደም የ5000 ሜትር የሴቶች የአልቲሜት ሻምፒዮና የወርቅ ሜዳሊያ እና የ150,000 ዶላር ወይም ከ26 ሚሊየን ብር በላይ ያሸነፈች የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊ አትሌትም በመሆን ስሟን በታሪክ መዝገብ ላይ በወርቅ ቀለም በደማቁ አፅፏለች።
🔴የአትሌት ልቅና አምባው የቅርብ ጊዜ ድሏ
አትሌት ልቅና አምባው የአልቲሜት ሻምፒዮንሺፕ የ5ሺ ሜትር አሸናፊ መሆኗን ዛሬ ከማወጇ በፊት የሮም ዳይመንድ ሊግን ሰኔ 2026 መጀመሪያ ላይ 14:18:41 በሆነና በወቅቱ የዓለም ፈጣኑ በሆነ ጊዜ በመሮጥ የመጀመሪያውን የዳይመንድ ሊግ ድል አስመዘግባለች።
አትሌት ልቅና አምባው መጋቢት 2026 በተካሄደው 45ኛው የበርሊን ግማሽ ማራቶን 1:05:07 በሆነ ጊዜ አሸናፊ በመሆንም በታሪክ ላይ ታሪክ ማፃፏንም ቀጥላለች።
አውስትራሊያዊቷ ጄሲካ ኸል (በግል ምርጥ ሰዓቷ 14:32.39 በማስመዝገብ የጨረሰች ሲሆን ከሁለት ሰከንድ በላይ በሆነ ልዩነት በመቅደም አሸንፋለች። ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊ ፋንታዬ በላይነህ 14:32:62 በሆነ ሰዓት ሦስተኛ ደረጃን የያዘች ሲሆን ይህም ከሀገርዋ ልጆች አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ እና አለሺኝ ባወቀ ቀድማ እንድትጨርስ አስችሏታል።
🔴በ5ሺ ሜ ሴቶች ያሸነፉበት ሠዓቴና ያገኙት ሽልማት
1.
💰150,000(usd)
2.
💰75,000(usd)
3.
💰40,000(usd)
4.
💰25,000(usd)
5.
💰16,000(usd)
6.
💰14,000(usd)
7.
💰12,000(usd)
8.
💰10,000(usd)
9.
💰9,000(usd)
10.
💰8,000(usd
11.
🔴ኢትዮጵያዊያን አትሌቶችምን ያህል ዶላር ወደ ካዝናቸው ከተቱ
የዓለማችን ከዋክብት ብቻ የተሠባሠቡበትና ውዱ ሽልማት 10ሚሊየን ዶላር በተበጀተለት በታሪካዊው የአልቲሜት ሻምፒዮና ኢትዮጵያዊያን አቴሌቶች ምን ያህል ዶላር ወደ ካዝናቸው ከተቱ?የሚል ጥያቄ መመዘዙ አይቀርም ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ቢኒያም መሐሪና ፍሬወይኒ ሐይሉ ቴናንት 4ተኛ በመውጣት ያገኙትን 50ሸመ ዶላር እና ዛሬ የተገኘውን ዳጎስ ያለ ዶላር ጨምሮ 377,000 የአሜሪካን ዶላር ወይም በወቅታዊ ምንዛሪ ከ65 ሚሊየን የኢትዮጵያ ብር በላይ ወደ ሀገሪቱ ኢኮኖሚ ይጨምራሉ
።
🔴ከዚህ ውስጥ ከፍተኛውን ያገኘችው አትሌት ልቅናው አምባው 150ሺ ዶላር ወይም በወቅታዊ ምንዛሪ ከ26 ሚሊየን ብሩን ለብቻዋ ስታገኝ አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ 50ሺ ዶላር ለብቻዋ ያገኘች አትሌትም ናት።
🔴ይህ ገንዘብ የድህነትን ተራራ በሩጫ ደርምሶ በመጣል ወደ ሀብት ማማ ወይም ወደሚሊየነሮች ተርታ የሚያሠልፍ ታሪካዊ ድልና ሽልማት ነው።
✍️✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርትጰኦፊሺያል)
24 days ago
ልቅና አምባው በቡዳፔስት ድቅድቅ አየር ውስጥ የዓለም አልቲሜት ሻምፒዮን ሆነች!
#ethiopia | በሃንጋሪ ቡዳፔስት በተካሄደው የዓለም አልቲሜት ሻምፒዮና የሴቶች 5,000 ሜትር ፍፃሜ፣ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ልቅና አምባው አስደናቂ የበላይነት በማሳየት የውድድሩ አሸናፊ ሆናለች ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።
ልቅና ሩጫው በተጀመረ በመጀመሪያዎቹ ዙሮች ከዋናው ተፎካካሪ ቡድን በድፍረት ተነጥላ ፈጣን ሩጫ በማድረግ፤ ርቀቱን በ14 ደቂቃ ከ30.36 ሴኮንድ በማጠናቀቅ የሻምፒዮንሺፑን የክብር ዋንጫ ማንሳት ችላለች።
ይህ ድሏ በአትሌቲክስ ታሪክ ከፍተኛው የሽልማት ገንዘብ የሆነውን የ150 ሺህ ዶላር ባለቤት አድርጓታል።
በዚሁ አወዛጋቢና ብርቱ ፉክክር በተደረገበት ውድድር አውስትራሊያዊቷ ጄሲካ ሃል የግል ምርጥ ሰዓቷን በማሻሻል ሁለተኛ ደረጃን ስትይዝ፣ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ፋንታዬ በላይነህ በ14 ደቂቃ ከ32.62 ሴኮንድ ሦስተኛ በመውጣት የነሐስ ሜዳሊያ አግኝታለች።
በተጨማሪም አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ 4ኛ፣ አለሽኝ ባወቀ 5ኛ እንዲሁም ሰናይት ጌታቸው 7ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

አትሌት ልቅና አምባው የ5 ሺህ ሜትር የአልቲሜት ሻምፒዮና አሸናፊ ሆነች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በአልቲሜት ሻምፒዮና የመጨረሻ ቀን በተካሄደው የሴቶች 5 ሺህ ሜትር የፍፃሜ ውድድር አትሌት ልቅና አምባው ውድድሩን በበላይነት በማጠናቀቅ የሻምፒዮናው አሸናፊ ሆናለች።
አትሌቷ ርቀቱን 14 ደቂቃ፣ 30 ሰከንድ፣ 36 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ጊዜ በቀዳሚነት በማጠናቀቅ የወርቅ ሜዳሊያ ማሸነፍ ችላለች።
ሌላኛው አትሌት ፋንታዬ በላይነህ 3ኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቅ የነሐስ ሜዳሊያ አሸንፋለች።
አትሌት ፍሬወይኒ ሀይሉ 4ኛ፣ አትሌት አለሺኝ ባወቀ 5ኛ እንዲሁም አትሌት ሰናይት ጌታቸው 7ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል።
አውስትራሊያዊቷ አትሌት ጄሲካ ሂል በሁለተኛነት ውድድሯን አጠናቃለች።

26 days ago
የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ ማን ምን አለ?
#ethiopia | የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ የተለያዩ የውጭ ሀገራት መሪዎች የዲፕሎማቲክ መሪዎችና እና አምባሳደሮች የመልካም ምኞት መልእክት አስተላልፈዋል።
የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዝ ለአዲሱ ዓመት ባስተላለፉት የአዲስ አመት መልእክት ለኢትዮጵያውያን እና አውስትራሊያውያ ውስጥ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን አዲሱ አመት የሰላም የብልጽግና እና የደስታ ዓመት እንዲሆን ተመኝተዋል።
በተመሳሳይ የአውስትራሊያ የተቃዋሚ መሪ የሆኑት አንገስ ቴለር በበኩላቸው እንኳን ለ2019 የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
በአዲስ አበባ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ሶፊ ፍሮም ኤመሰበርገር
አውሮፓ ህብረት ከኢትዮጵያ ጎን እንዳለ በመግለፅ የሰላምና የደስታ ዘመን እንዲሆን ተመኝተዋል።
የካሜሩን አምባሳደር ኤዉምቡዌ ሞኖኖ አዲሱ ዓመት የተስፋ እና የእድገት እንዲሆን ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።
የእስራኤል አምባሳደር አቭራሃም ንጉሴ የዕንቁጣጣሽ እና የእስራኤል "ሮሽ ሀሻናህ" አዲስ ዓመት በተመሳሳይ ወቅት መዋላቸውን በመጥቀስ "መልካም አዲስ ዓመት ዕንቁጣጣሽ" ብለዋል።
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (UAE) አምባሳደር አብደላ ሀሰን አልሻምሲ
የሀገራቸውን እና የኢትዮጵያን ጠንካራ ወዳጅነት በማንሳት የሰላምና የፍቅር ዘመን እንዲሆን ተመኝተዋል።
የጀርመን፣ ፊንላንድ፣ ዴንማርክ፣ ስሪላንካ፣ የየመን እና ማሌዥያ ዲፕሎማቶች እና ኤምባሲዎችም በተመሳሳይ ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #ethiopiannewyear #enkutatash #ethiopia #newyear2019 #peaceandunity #diplomacy

1 month ago
በኢትዮጵያ የአምልኮ መርሐግብር ሊካሄድ ነው
#ethiopia | በኢትዮጵያ ዮጎ ቸርች ታላቅ የአምልኮ መርሀግብር ሊካሄድ መሆኑ ተነገረ።
ሙዚቀኛና የአምልኮ መድረኮች አዘጋጅ የሆነው ዮሐንስ ዋጋሪ በኢትዮጵያ የአምልኮ ፕሮግራም ለማዘጋጀት ዝግጅቱን መጨረሱን አስታወቀ።
በአሜሪካ 18 ግዛቶች እንዲሁም በአውስትራሊያና በሌሎች የዓለም ክፍሎች ተመሳሳይ የወንጌል ስርጭትና የአምልኮ መድረኮችን ሲያዘጋጅ መቆየቱን ገልጿል።
ሙዚቀኛው ዮሐንስ ዋጋሪ ይህንን ልምዱን በመጠቀም በኢትዮጵያ ከተለያዩ አንጋፋና አዳዲስ ዘማሪዎች ጋር በመቀናጀት ፕሮግራሙን አዘጋጅቷል።
ቦሌ ብራስ አካባቢ በሚገኘው ዩጎ ሲቲ ቸርች የሚካሄደው ይህ መድረክ ከከፍተኛ ጥራትና የላቀ አዘጋጀጀት ጋር የሚቀርብ ነው ተብሏል።
በዕለቱ ከአምልኮ ፕሮግራሙ በተጨማሪ የቃል አገልግሎት እንደሚሰጥ ተገልጿል።
ከ10 ዓመታት በላይ አገልግሎት ላይ የሚገኘው "የዜማ ዮሐንስ ፕሮጀክት" ዕድሉ የሌላቸውን አዳዲስ ባለጸጋዎችን በስቱዲዮ በማስተናገድና በመደገፍ የሚታወቅ ነው።
መርሐግብሩ የሚካሄድበትን ቀን በቅርብ ጊዜ በሚዲያ ይፋ እንደሚደረግ በመግለጫው ላይ ተገልጿል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #yohanneswagari #zemayohannesproject#elbethesministry

ዩጎ ሲቲ ቸርች ቦሌ አጥቢያ ላይ ትልቅ የአምልኮ ፕሮግራም ሊካሄድ ነው!
#fastmereja I ሙዚቀኛውና የአምልኮ ፕሮግራም አዘጋጁ ዮሐንስ ዋጋሪ ከአሜሪካና ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የአምልኮ መድረኮች ቆይታ በኋላ፣ በኢትዮጵያ ታላቅ የአምልኮ ፕሮግራም ለማዘጋጀት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን በዛሬዉ እለት በተሰጠ መግለጫ ተገልጿል።
በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ እንደተገለጸው፣ ይህ ፕሮግራም ከአንጋፋና ከአዳዲስ ዘማሪዎች ጋር በመቀናጀት የተዘጋጀ ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም የወንጌል ስርጭትን ማስፋፋትና አምልኮን ማቅረብ መሆኑ ተገልጿል።
ዮሐንስ ዋጋሪ ቀደም ሲል በአሜሪካ 18 ስቴቶች እንዲሁም በአውስትራሊያና በሌሎች ሀገራት ተመሳሳይ ፕሮግራሞችን ሲያዘጋጅ የቆየ ሲሆን እድሉ የሌላቸውን አዳዲስ ዘማሪዎችና ባለጸጋዎችን በነፃ በስቱዲዮ በማስተናገድና በመደገፍ ይታወቃል።
ይህ የአምልኮ መድረክ በከፍተኛ ጥራትና የላቀ ዝግጅት (Excellence) የሚቀርብ ሲሆን፣ የቃሉን አገልግሎት የሚያካፍሉ አገልጋዮችም አብረው እንደሚሳተፉም ነዉ የተገለፀዉ።
የዜማ ዮሐንስ ፕሮጀክት (Zema Yohannes Project) ከተጀመረ ከ10 ዓመታት በላይ እንሆነዉ የተገለፀ ሲሆን በወጣቶች ላይ ትኩረት አድርጎ አዳዲስ ዘማሪዎችን እንደሚያበራታ እና የወንጌል ስርጭት ስራዎችን እንደሚሰራ ገልጿል።
#ኹነት

ሜታ በልጆች የሶሻል ሚዲያ ሱሰኝነት የቀረበበትን ክሶች በስምምነት ለመፍታት እስከ 18 ቢሊዮን ዶላር ለመክፈል ተስማማ
#ethiopia | ኦክላንድ፣ ካሊፎርኒያ — ሜታ ፕላትፎርምስ (Meta Platforms) ፌስቡክንና ኢንስታግራምን ወጣቶች ሱስ እንዲይዙ አድርጎ ነድፈዋል በሚል ከቀረቡበት ክሶች ጋር በተያያዘ ከሞላ ጎደል ከሁሉም የአሜሪካ ግዛቶች ጋር ስምምነት ላይ ደርሷል።
በስምምነቱ መሠረት ሜታ ታዳጊዎች ፌስቡክን እና ኢንስታግራምን የሚጠቀሙበትን ጊዜ እና መንገድ ይገድባል።
ስምምነቱ ኩባንያው የልጆችን ደህንነት አስመልክቶ ህዝብን አሳስቷል እና ምርቶቹም በህጻናት ላይ ጉዳት አድርሰዋል በሚል የቀጠለውን የፌዴራል ፍርድ ሂደት ያቋርጠዋል ተብሏል።
ካሊፎርኒያ፣ ኮሎራዶ፣ ኬንታኪ እና ኒው ጀርሲ የተባሉት አራት ግዛቶች በክሱ ሂደት ወደ 200 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የሲቪል ቅጣት ለመጠየቅ አቅደው ነበር።
የታዳጊዎች የሶሻል ሚዲያ አጠቃቀም ይገደባል
ሜታ በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ታዳጊዎች ፌስቡክን እና ኢንስታግራምን በቀን ከሁለት ሰዓት በላይ እንዳይጠቀሙ የሚያደርግ ገደብ ይጥላል። የወላጅ ፈቃድ ከሌለ ደግሞ ከእኩለ ሌሊት 6፡00 ሰዓት ድረስ አጠቃቀም ይታገዳል።
በተጨማሪም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 9፡00 ሰዓት ባለው የትምህርት ጊዜ አብዛኛዎቹ የገፊ የሆኑ መልዕክቶች ለታዳጊዎች እንዳይላኩ ይደረጋል። ህጻናት የእድሜ ገደብ ያላቸው ይዘቶችን እንዳያገኙም ተጨማሪ የደህንነት ርምጃዎች ይጠናከራሉ።
እነዚህ ገደቦች ስናፕቻት፣ ቲክቶክ እና ዩቲዩብ ተመሳሳይ የህጻናት ጥበቃ ርምጃዎችን ከወሰዱ የበለጠ ሊጠናከሩ ይችላሉ።
እስከ 18 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ክፍያ ሜታ ለ47 የአሜሪካ ግዛቶች፣ ለዋሺንግተን ዲሲ፣ ለፖርቶ ሪኮ፣ ለአሜሪካን ሳሞአ እና ለኖርዘርን ማሪያና ደሴቶች በአጠቃላይ እስከ 16.7 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ክፍያ ለመፈጸም ተስማምቷል።
ከዚህ ውስጥ 12.7 ቢሊዮን ዶላር የተረጋገጠ ክፍያ ሲሆን፣ ተጨማሪ 5 ቢሊዮን ዶላር ደግሞ ስናፕ፣ ቲክቶክ እና ዩቲዩብ ተመሳሳይ የህጻናት ጥበቃ ርምጃዎችን የሚወስዱበት ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ነው።
ካሊፎርኒያ ወደ 2.2 ቢሊዮን ዶላር የሚያገኝ ሲሆን፣ ኒው ዮርክ ደግሞ 1.1 ቢሊዮን ዶላር ያህል ሊያገኝ ይችላል። ቴክሳስ በበኩሉ ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጣ የተለየ ስምምነት አድርጓል።
ከግዛቶቹ መካከል አንዳንዶቹ የሚቀበሉትን ገንዘብ በአጠቃላይ የመንግሥት ሂሳብ ላይ ለማስገባት ሲያቅዱ፣ ሌሎች ደግሞ የተወሰነውን ገንዘብ የህጻናት የአእምሮ ጤናን ለመደገፍ ለመጠቀም አቅደዋል።
የሜታ አሠራር ላይ የሚኖረው ለውጥ
የሰሜን ዌስተርን ዩኒቨርሲቲ የሕግ ፕሮፌሰር ጄምስ ስፔታ ስምምነቱ “ትልቅ ጉዳይ” መሆኑን ገልጸዋል።
እሳቸው እንደገለጹት፣ ሜታ እና ሌሎች ኩባንያዎች ክሱን ቢያሸንፉም ቢሸነፉም የንግድ አሠራራቸውን እንዲቀይሩ ከሕዝብ፣ ከኮንግረስ እና ከግዛት ሕግ አውጪዎች ጫና እየደረሰባቸው ነበር።
ሆኖም ስምምነቱ ሜታ የግል ምርጫዎችን የሚከተሉ የይዘት ምክረ ሃሳቦችን (personalized recommendations) ወይም የታለመ ማስታወቂያን (targeted advertising) እንዲያቆም አያስገድደውም።
በተጨማሪም ተመራማሪዎቹ በተለይ አሳሳቢ ናቸው ብለው የጠቀሷቸውን እንደ የሰውነት ቅርጽ ላይ አሉታዊ ስሜት የሚፈጥሩ የኢንስታግራም ጽሑፎች ያሉ አንዳንድ ይዘቶችን አይመለከትም።
ሜታ በክሱ ላይ ከስምምነትላይ ቢደርስም ጥፋት መፈጸሙን ግን አልተቀበለም። ኩባንያው የሚከፍለው ጠቅላላ ገንዘብ ከሜታ የሶስት እስከ አራት ወራት ትርፍ እና ወደ አንድ ወር ገቢ ያህል እንደሚሆን ገልጿል።
የካምብሪጅ አናሊቲካ የዳታ ጥሰት
በተለየ ጉዳይ ሜታ ከካምብሪጅ አናሊቲካ ቅሌት ጋር በተያያዙ የግላዊነት ክሶች ለመፍታት 459 ሚሊዮን ዶላር ለመክፈልም ተስማምቷል። ጉዳዩ የብዙ ሚሊዮን የፌስቡክ ተጠቃሚዎች የግል መረጃ ያለፈቃዳቸው መሰብሰቡን ይመለከታል።
የአሜሪካ የወረዳ ዳኛ ዮቮን ጎንዛሌዝ ሮጀርስ ዋናውን የስምምነት ሰነድ ረቡዕ ምሽት አጽድቀዋል። ዳኛዋ ከኦገስት 18 ጀምሮ የቀጠለውን የፍርድ ሂደት መርተው ነበር።
ተመሳሳይ ክሶች በመላው አሜሪካ ቀጥለዋል
ሜታ ላይ ከተመሰረቱት ክሶች በተጨማሪ በፌዴራል እና በግዛት ፍርድ ቤቶች በሺዎች የሚቆጠሩ ክሶች በሶሻል ሚዲያ ኩባንያዎች ላይ ቀጥለዋል።
እነዚህ ክሶች ኩባንያዎቹ ልጆችን ሆን ብለው ወደ ሱሰኝነት የሚያመሩ ምርቶችን ነድፈዋል እና በዚህም ከጭንቀትና ከድብርት እስከ ራስን ማጥፋት የሚደርስ የአእምሮ ጤና ቀውስ አባብሰዋል የሚል ክስን ያካትታሉ።
በተጨማሪም 29 ግዛቶች ሜታ የልጆችን የግል መረጃ ያለወላጆች ፈቃድ በማሰባሰብ እና መረጃውን የጄኔሬቲቭ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ለማሰልጠን በመጠቀም በህጻናት የማኅበራዊ ሚዲያ አካውንቶች ላይ ግላዊነት ጥበቃ ሕግን ጥሷል ብለው ከሰዋል።
ኒው ሜክሲኮ እና ፍሎሪዳ ከስምምነቱ ውጭ ናቸው
ኒው ሜክሲኮ በረቡዕ በተደረገው ስምምነት አልተካተተችም። የግዛቱ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ራውል ቶሬዝ ስምምነቱ አዋቂዎች ህጻናትን ላይ እንዳያነጣጥሩ የሚደረጉ ጥበቃዎችን እና ከልጆች ጋር የጾታዊ ይዘት ያለው የAI ቻትቦት ግንኙነትን ለመከልከል የሚደረጉ ርምጃዎችን አልያዘም ብለዋል።
ፍሎሪዳም ስምምነቱን አልተቀበለችም እና ክሱን በፍርድ ቤት ለመቀጠል ወስናለች። የፍሎሪዳ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ጄምስ ኡዝሜየር፣ ለግዛቶች የሚከፈለው ገንዘብ ሜታ በልጆች ላይ ካደረሰው ከባድ ጉዳት ጋር ሲነጻጸር “በጣም ትንሽ” ነው በማለት ክሱን በፍርድ ቤት እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
ስምምነቱ በዓለም ዙሪያ ካሉ ሌሎች ሺዎች የሚቆጠሩ በማህበራዊ ሚዲያ ኩባንያዎች ላይ ለቀረቡ ክሶች እንደ አብነት ሊያገለግል ይችላል ተብሏል፤ መንግስታት ደግሞ ህጻናት ጎጂ የማኅበራዊ ሚዲያ አካውንቶች ላይ ይዘቶችን እንዳያገኙ ለመግታት እየሰሩ ነው፤ ከእነዚህም መካከል አውስትራሊያ ከ16 ዓመት በታች ላሉ ህጻናት ማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምን ማገዷ ይታወሳል።
https://www.reuters.com/bu...

2 months ago
ጋና አሜሪካን በመበለጥ በዓለም 6ኛዋ ከፍተኛ የወርቅ አምራች ሀገር ሆነች
ጋና አሜሪካን በመብለጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስድስተኛዋ ከፍተኛ የወርቅ አምራች ሀገር ሆናለች።
ሀገሪቱ በ2025 እ.ኤ.አ ሪኮርድ የሆነ 185 ቶን (ወደ 5.94 ሚሊዮን አውንስ ገደማ) ወርቅ ያመረተች ሲሆን፣ ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ23 በመቶ ዕድገት በማሳየት ከአሜሪካ በላይ እንድትሰለፍ አድርጓታል።
የጋና ማዕድን ምክር ቤት ባልደረባ ክሪስቶፈር ኛርኮ እንደገለጹት፦ "አሁን ከፔሩ ቀጥሎ 6ኛ ደረጃ ላይ እንገኛለን። ስለዚህ ቅደም ተከተሉ ቻይና፣ ሩሲያ፣ አውስትራሊያ፣ ካናዳ፣ ፔሩ፣ ከዚያም ጋና... በመቀጠል አሜሪካ ይሆናሉ" ብለዋል።
ለዚህ የደረጃ ለውጥ አበይት ምክንያቶች ሁለት ናቸው። የጋና ምርት ያደገ ሲሆን፣ በአንጻሩ የአሜሪካ ምርት በኔቫዳ በሚገኙ የማዕድን ማውጫዎች ላይ ባጋጠሙ ቴክኒካዊ ችግሮች ምክንያት ቅናሽ አሳይቷል።
በጋና የ100 ዓመታት የንግድ ማዕድን ቁፋሮ ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ አነስተኛ አምራቾች ከሀገሪቱ ጠቅላላ የወርቅ ምርት ከ52 በመቶ በላይ የሚሆነውን አቅርበዋል።
በአንጻሩ ትልልቅ የማዕድን ኩባንያዎች ያመረቱት መጠን ካለፈው ዓመት በጥቂቱ ዝቅ ብሏል።
ለዚህ ስኬት ደግሞ በቅርቡ የተቋቋመው የጋና ወርቅ ቦርድ (GoldBod) ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል።
ቦርዱ የኮንትሮባንድ ንግድን በመቀነስ ምርቱ በህጋዊ መንገድ ወደ ስርዓቱ እንዲገባ በማድረጉ፣ የአነስተኛ አምራቾች ወርቅ በመደበኛ መስመር ሊሰበሰብ ችሏል።
ጋና ከአፍሪካ አንደኛ የወርቅ አምራችነቷን ያስጠበቀች ሲሆን፣ ወርቅ አሁንም ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ከሚያስገኙ ዋና ዋና ምርቶች መካከል ይጠቀሳል።
ይህ ለሀገሪቱ ትልቅና ታሪካዊ ክስተት ተደርጎ ተወስዷል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የሃይማኖት ጉዳዮች ላይ የተመካከረው የሥራ ቡድን፣ ከመንግስት እና ሃይማኖት መስተጋብር እስከ ማህበራዊ ቀውሶች መፍትሔ ድረስ የተዘረጉ በርካታ አነጋጋሪ እና መሰረታዊ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ምክረ ሀሳቦችን አቅርቧል። እነዚህ ሃሳቦች በሀገሪቱ የረጅም ጊዜ የሴኩላሪዝም (የመንግስት እና ሃይማኖት መለያየት) ፖሊሲ ላይ አዲስ የክርክር በር የሚከፍቱ ከመሆናቸውም በላይ፣ መንግስት በሃይማኖት ተቋማት ላይ ሊኖረው ስለሚገባው የቁጥጥር ልክ አዲስ አቅጣጫን የሚያመላክቱ ናቸው።
በስራ ቡድኑ ከቀረቡት አበይት ምክረ ሀሳቦች መካከል የሃይማኖት ጉዳዮችን በበላይነት የሚከታተል የሃይማኖት ኮሚሽን ማቋቋም የሚለው ይገኝበታል። ከዚህ ጋር ተያይዞ ተቋማት የጁምዓ ጸሎትን ታሳቢ በማድረግ ዓርብ ዕለት ከ5 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት ያለውን ጊዜ መደበኛ የዕረፍት ሰዓት እንዲያደርጉ፣ የጰንጠቆስጤ አማኞች የሚያከብሩት በዓለ ሀምሳ በብሔራዊ የዘመን መቁጠሪያ ላይ ዕውቅና እንዲሰጠው፣ እና የአዳዲስ ሃይማኖቶች ምዝገባ እጅግ ጥብቅ እንዲሆን ጥያቄ ቀርቧል። የጎዳና ላይ ሃይማኖታዊ ተግባራት ሚዛናዊ በሆነ መመሪያ እንዲመሩ፣ የሃይማኖት ተቋማት የመሬት አሰጣጥ ፍትሃዊ እና ቦታ ቆጣቢ እንዲሆን፣ እንዲሁም የሃይማኖት አባቶች ተገቢው ክብር እንዲሰጣቸው ተጠይቋል።
በሌላ በኩል ተቋማዊ አሰራርን እና ደህንነትን በሚመለከት፣ የሃይማኖት ተቋማት የፋይናንስ ግልጸኝነትን ለማረጋገጥ ኦዲት እንዲደረጉ፣ እንዲሁም ሃይማኖትን ሽፋን ያደረገ የሰው እና የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመግታት ጥብቅ እርምጃ እንዲወሰድ ሃሳብ ቀርቧል። ከሃይማኖት ርዕሰ ጉዳይ ውጪ ያሉ ነገር ግን በማህበረሰብ ደህንነት ስር የተካተቱት ማህበራዊ ጉዳዮችን በሚመለከት ደግሞ፣ ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕጻናት ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ ገደብ መጣል እና የአደንዛዥ ዕጽ እርሻን በሌሎች አምራች ምርቶች ለመተካት ሀገራዊ ንቅናቄ መፍጠር የሚሉት ተካተዋል።
እነዚህ ምክረ ሀሳቦች ወደ ትግበራ ከተሸጋገሩ በህግ እና በአፈጻጸም ደረጃ ትልቅ ትርጉም አላቸው። የሌሎች ሀገራትን ተሞክሮ ስንመለከት፣ ሩዋንዳ አዳዲስ የሃይማኖት ተቋማት ላይ እጅግ ጥብቅ የሆነ የምዝገባ መስፈርት በማውጣት እና ሰባኪዎች የሥነ-መለኮት ዲግሪ እንዲኖራቸው በማስገደድ በቅርቡ በሺዎች የሚቆጠሩ አብያተ ክርስቲያናትን ዘግታለች። በእንግሊዝ (ዩናይትድ ኪንግደም) ደግሞ የሃይማኖት ተቋማት እንደ ማንኛውም የበጎ አድራጎት ድርጅት በቻሪቲ ኮሚሽን በኩል ጥብቅ የፋይናንስ ኦዲት እና ክትትል ይደረግባቸዋል። የኢትዮጵያው የፋይናንስ ግልጸኝነት እና ጥብቅ የምዝገባ ጥያቄም ተመሳሳይ አሰራርን ለመከተል ያለመ ይመስላል። የጁምዓ ጸሎትን የሥራ ዕረፍት ሰዓት ማድረግ በመካከለኛው ምስራቅ የተለመደ ቢሆንም፣ ሙሉ በሙሉ ሴኩላር በሆኑ ሀገራት ግን ይህን በህግ ማስገደድ የህገ-መንግስት ማሻሻያን ሊጠይቅ የሚችል ጉዳይ ነው።
የማህበራዊ ሚዲያ ዕድሜ ገደብን በተመለከተም አውስትራሊያ፣ ብሪታንያ እና የአሜሪካ ግዛቶች (እንደ ዩታህ ያሉት) ከ16 ዓመት በታች ለሆኑ ታዳጊዎች ክልከላ ለማድረግ ህግ ቢያወጡም፣ ቴክኖሎጂውን በመጠቀም ዕድሜን የማጣራት (Age verification) ከፍተኛ የተግባር ፈተና ገጥሟቸዋል።
የምክረ ሀሳቦቹን ቀጣይ ሂደት በተመለከተ፣ አንድ መቶ ሃያዎቹ የጋራ ማረጋገጫ ቡድን አባላት ከተመካካሪዎች በተሰበሰቡ አስተያየቶች ያዳበሩትን የመጨረሻ ሰነድ ነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ለምክክሩ ጠቅላላ ጉባኤ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ በማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1265/2014 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በጠቅላላ ጉባኤው የሚጸድቁትን አጀንዳዎች ተቀብሎ፣ በተግባር ሊውሉ የሚችሉበትን ስልት የሚገልጽ ሰነድ በማዘጋጀት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለአስፈጻሚ አካሉ እና ለሚመለከታቸው ተቋማት ያቀርባል። ይሁን እንጂ የህግ እና የአፈጻጸም ውስብስብነት ያላቸው፣ እንዲሁም የመንግስት አስተዳደርን መርህ የሚጋፉ አንዳንዶቹ ምክረ ሀሳቦች በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ቀጣዩ የማስፈጸም ሂደት ላያልፉ እንደሚችሉ መረጃዎች ያመለክታሉ።

በፈረንሳይ ከ15 ዓመት በታች ለሆኑ ታዳጊዎች የተጣለው የማኅበራዊ ሚዲያ ክልከላ በፍርድ ቤት ታገደ
የፈረንሳይ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ላይ የተጣለውን የማኅበራዊ ሚዲያ እገዳ "ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን ይጥሳል" ሲል ውድቅ አደረገ።
የአገሪቱ ሕግ አውጭዎች ባለፈው ሐምሌ ወር ነበር ማኅበራዊ ሚዲያ በሕፃናት የአዕምሮ ጤና ላይ ጎጂ ተፅዕኖ ያስከትላል የሚሉ ስጋቶች መነሳታቸውን ተከትሎ ለሕጉ ድጋፋቸውን የሰጡት።
ይህም ፈረንሳይ ታዳጊዎች ማኅበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ በመከልከል የመጀመሪያዋ አውሮፓዊት አገር እንድትሆን አድርጓት ነበር።
ሆኖም አርብ ዕለት የሕገ መንግሥታዊ ምክር ቤት ባስተላለፈው ውሳኔ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከመስከረም ጀምሮ ደረጃ በደረጃ እንደሚተገበር ቃል የገቡለትን እገዳ ውድቅ አድርጎታል።
ፕሬዚደንቱ ለፍርድ ቤቱ ውሳኔ ምላሽ የሰጡ ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ሴባስቲን ሌኮርኑን የምክር ቤቱን ሁሉንም ነጥቦች ግምት ውስጥ የሚያስገባ አዲስ ረቂቅ እንዲያዘጋጁ ጠይቀዋል።
ባለፈው ወር ሕግ አውጭዎች በሕጉ ላይ ድምጽ ከሰጡ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕጉን የተወሰኑ ክፍሎች ዘጠኝ አባላት ላሉት እና የሚወጡ ሕጎች ሕገ መንግሥቱን ያከበሩ እንደሆኑ ለሚያረጋግጠው ምክር ቤት ልከው ነበር።
ሕገ መንግሥታዊው ምክር ቤቱም ሕጉ "የሐሳብ ልውውጥን እና የመናገር ነፃነትን የሚጥስ" መሆኑን እንዳረጋገጠ ገልጿል።
ከዚህም በተጨማሪ የኦንላየን አገልግሎት ለማግኘት የዕድሜ ማረጋገጫ ማቅረብ እንዳለባቸው በሚጠይቀው መስፈርት ላይ ያለውን ስጋት አንስቷል። " ሕጉ አስፈላጊ የሆኑ የሕግ ከለላዎችን አላዘጋጀም" ብሏል።
የፕሬዚዳንት ማክሮን ቢሮ በበኩሉ ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ካሳለፈ በኋላ " መንግሥት አዲስ ረቂቅ ለማዘጋጀት በሚቻለው ፍጥነት እንደሚሰራ" ጠቅሶ፣ ፕሬዚደንቱ ማሻሻያውን በ2027 መጀመሪያ ላይ ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጿል።
ከመስከረም ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ የነበረው ሕግ ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች የማኅበራዊ ሚዲያ አካውንት መክፈት እንዳይችሉ የሚከለክል ሲሆን ለሁሉም አዲስ አካውንቶች ማረጋገጫዎች እንዲቀርቡም ይጠይቃል።
ይህም ከጥር ወር ጀምሮ ቀድሞ በተከፈቱ ሁሉም አካውንቶች ላይ ተግባራዊ መሆን እንደሚጀምር ይገልጻል።
ተቃዋሚዎች የሕጉ ተጨባጭነት ላይ ጥያቄ ሲያነሱ የነበረ ሲሆን ግላዊነትን በመጠበቅ ረገድ እንዲሁም የእድሜ ማረጋገጫ መንገዶች ውጤታማነት፣ ታዳጊዎች ሕጉን የመጣስ አደጋዎች እና ሕጉ የተዘጋጀበት እና ተግባራዊ ለማድረግ የታሰበበት ጊዜ ፍጥነት ላይ ስጋታቸውን ገልጸዋል።
አውስትራሊያ ታኅሳስ ወር ላይ ማኅበራዊ ሚዲያን ከ16 ዓመት በታች ላሉ ታዳጊዎች በመከልከል የመጀመሪያዋ አገር ሆናለች። ሆኖም በርካቶች አሁንም የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮችን መጠቀማቸውን እንደቀጠሉ በስፋት ይታወቃል።
ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥም ታዳጊዎች ማኅበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ የሚከለክል ሕግ በአውሮፓ እየተስፋፋ መጥቷል።
ግንቦት ወር ላይ የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ፕሬዚደንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን፣ በኅብረቱ አባል አገራት ውስጥ ላሉ ታዳጊዎች "ማኅበራዊ ሚዲያን ማዘግየት" የሚል ሃሳብ ያቀረቡ ሲሆን አዲስ ሕግ በወራት ውስጥ ሊወጣ እንደሚችል ተናግረዋል።
በዩናይትድ ኪንግደምም የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ኪር ስታርመር፣ ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት ከጥር 2027 ጀምሮ ማኅበራዊ ሚዲያ መጠቀም እንደሚከለከሉ ሰኔ ወር ላይ አስታውቀው ነበር።
BBC

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በኢንዶኔዥያ ፍሎሬስ ደሴት የባህር ዳርቻ ላይ የተከሰተው 7.7 ማግኒቲዩድ የሆነ ጠንካራ የመሬት መንቀጥቀጥ የሁለት ሰዎችን ህይወት አጠፋ። የሀገሪቱ የብሔራዊ አደጋ መከላከል ኤጀንሲ እንዳስታወቀው፣ በማውሜሬ ወደብ አካባቢ አንድ ወንድ እና አንዲት ሴት ህይወታቸውን ሲያጡ ሌላ አንድ ሰው ላይ ደግሞ ጉዳት ደርሷል። በተጨማሪም በአካባቢው በሚገኙ ሕንፃዎች እና ወደቡ ላይ ከፍተኛ የንብረት ውድመት መድረሱን የአካባቢው መገናኛ ብዙሃን ዘገባዎች አሳይተዋል።
የአሜሪካ የጂኦሎጂካል ጥናት ተቋም መረጃ እንደሚያሳየው፣ የመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተው ቅዳሜ ማለዳ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር 11፡58 ላይ ነው። የንዝረቱ መነሻ የምስራቅ ኑሳ ተንጋራ ግዛት በሆነችው ኢንዴ ከተማ 68 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እና 10 ኪሎ ሜትር ጥልቀት ውስጥ መሆኑ ተገልጿል። ከዋናው የመሬት መንቀጥቀጥ በኋላ በግማሽ ሰዓት ጊዜ ውስጥ 5.9፣ 5.6 እና 6.1 ማግኒቲዩድ ያላቸው ሶስት ተከታታይ አነስተኛ ንዝረቶች ተከስተዋል።
አደጋውን ተከትሎ የኢንዶኔዥያ የሚቲዎሮሎጂ፣ ክላይማቶሎጂ እና ጂኦፊዚክስ ኤጀንሲ የሱናሚ (የባህር ላይ ማዕበል) ማስጠንቀቂያ አውጥቷል። ነዋሪዎች ከባህር ዳርቻዎች እና ወንዞች አካባቢ ርቀው ወደ ከፍተኛ ቦታዎች እንዲሸሹ አሳስቧል። የብሔራዊ አደጋ መከላከል ኤጀንሲ ኃላፊ የሆኑት አብዱል ሙሃሪ ህብረተሰቡ ከባህር ዳርቻ ቢያንስ ሁለት ኪሎ ሜትር ወደ ውስጥ እንዲገባ ወይም ከ10 ሜትር በላይ ከፍታ ወዳላቸው ተራራማ ቦታዎች በመሄድ ራሱን እንዲያድን ጥሪ አቅርበዋል። በአንጻሩ የአውስትራሊያ የሱናሚ ማስጠንቀቂያ ማዕከል አደጋው በአውስትራሊያ ላይ ምንም አይነት ስጋት እንደማይፈጥር አረጋግጧል።
ከዚህም በተጨማሪ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአካባቢው ነዋሪዎች ከፍተኛ የሆነ ንዝረት እንደተሰማቸው ተገምቷል። የአደጋው ሙሉ ገጽታ ገና እየወጣ ሲሆን፣ አንዳንድ ክፉኛ የተጎዱ አካባቢዎች መንገድ በመዘጋቱ ምክንያት ለነፍስ አድን ሰራተኞች አስቸጋሪ ሆነው እንደሚገኙ ተዘግቧል።
ከ270 ሚሊዮን በላይ ህዝብ እና ወደ 17,000 የሚጠጉ ደሴቶች ያሏት ኢንዶኔዥያ፣ ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ በሚታይበት የፓሲፊክ የእሳት ቀለበት (Ring of Fire) በሚባለው አካባቢ ላይ ትገኛለች። በተመሳሳይ የባህር ዳርቻ ላይ እ.ኤ.አ. በታህሳስ 1992 ዓ.ም. ተከስቶ በነበረ የመሬት መንቀጥቀጥ እና ሱናሚ ከ2,500 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ማጣታቸው ይታወሳል። አካባቢው አሁንም በተጠንቀቅ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ የአካባቢው ባለስልጣናት ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተሉ ይገኛሉ።

😆አውስትራሊያ ለሥራ አጥ ዜጎቿ በየሁለት ሳምንቱ ከ91,000 ብር በላይ ትከፍላለች
# ይህን ግን ያውቁ ኖሯል⁉
አውስትራሊያ ለሥራ አጥ ዜጎቿ የምታደርገው የገንዘብ ድጋፍ
#አውስትራሊያ "JobSeeker Payment" በተሰኘው የመንግሥት የማህበራዊ ዋስትና ፕሮግራም አማካኝነት፣ ሥራ አጥ ለሆኑና መስፈርቱን ለሚያሟሉ ዜጎቿ በየሁለት ሳምንቱ የፋይናንስ ድጋፍ ታደርጋለች።
* እንደ እ.ኤ.አ 2026 መረጃ መስረት ልጅ የሌለው/ላት አንድ ነጠላ ግለሰብ በየሁለት ሳምንቱ እስከ 808.70 የአውስትራሊያ ዶላር (A$808.70) ማግኘት ይችላል/ትችላለች።
ወደ ብር ስንመነዝረው በየሁለት ሳምንቱ 91 ሺህ 335 ብር ከ87 ሳንቲም ይሆናል፤ ማለትም በወር 182 ሺህ 671 ብር ከ74 ሳንቲም ይደርሳል።
* የሚከፈለው የገንዘብ መጠን እንደ ግለሰቡ የኑሮ ሁኔታ (ልጅ መኖር፣ የትዳር አጋር መኖር ወይም ሌላ የገቢ ምንጭ መኖር) ይወሰናል።
ሥራ አጥ የሆነ ሰው ሁሉ ክፍያው በቀጥታ አይሰጠውም። አመልካቾች የነዋሪነት ሁኔታን፣ የገቢና የንብረት መጠን ምርመራን ማለፍ እንዲሁም በንቃት ሥራ የመፈለግ ግዴታ አለባቸው።
በዓለም ዙሪያ ያሉ አገራት ሥራ አጥ ዜጎቻቸውን ለመደገፍ የተለያዩ አሰራሮችን የሚከተሉ ሲሆን፣ የአውስትራሊያ "JobSeeker" ፕሮግራም የመንግሥት የማህበራዊ ዋስትና (Social Safety Net) አንዱ ማሳያ ነው።

የዩኒቨርስቲ ዲግሪ ማግኘት ከዕውቀት በላይ ከፍተኛ የፋይናንስ አቅም የሚጠይቅ ሆኗል
#ethiopia | የትምህርት ክፍያቸው እጅግ ከፍተኛ የሆኑ ሀገራት ደረጃ ሲወጣ አሜሪካ እና እንግሊዝ አሁንም የደረጃውን አናት ይዘው ይገኛሉ።
በአሜሪካ የሚገኙ ታዋቂ የግል ዩኒቨርሲቲዎች ለአንድ ተማሪ በአመት እስከ 60,000 ዶላር እና ከዚያ በላይ የሚያስከፍሉ ሲሆን ይህም የመኖሪያ እና የምግብ ወጪዎችን ሳይጨምር ነው።
በአንፃሩ እንደ ጀርመን እና ኖርዌይ ያሉ ሀገራት ዩኒቨርሲቲዎቻቸው ትምህርትን በነፃ ወይም እጅግ አነስተኛ በሆነ ክፍያ በማቅረብ የተለያየ የትምህርት ፖሊሲ አቀራረብ እያሳዩ ይገኛሉ።
አውስትራሊያ ለአለም አቀፍ ተማሪዎች በጣም ውድ ከሆኑ ሀገራት አንዷ ስትሆን የመኖሪያ ወጪዎችን ጨምሮ አንድ ተማሪ በአመት እስከ 40,000 ዶላር ታስከፍላለች።
በትምህርት ጥራት አለምን እየመራች ያለችው ካናዳ ለአካባቢው ተማሪዎች የትምህርት ክፍያ በአንፃራዊነት ተመጣጣኝ ክፍያ ቢሆንም ለአለም አቀፍ ተማሪዎች ግን ክፍያው በየዓመቱ እየጨመረ ይገኛል።
በዚህም አንድ ተማሪ በአመት እስከ 36,000 ዶላር ክፍያ ይከፍላል።
ይህ ከፍተኛ የትምህርት ወጪ ተማሪዎችን ከምረቃ በኋላ ለከፍተኛ የብድር ዕዳ እየዳረጋቸው ሲሆን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዋጋ ንረት አሁንም በዓለም አቀፍ ደረጃ አልቀመስ ብሏል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #worldwide #costeducation #university #expenses #students #income

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ረጅም ርቀት መጓዝ የሚችሉ አውሮፕላኖች ግዢ እየተከናወነ ነው
አየር መንገዱ ወደ አውስትራሊያ በረራ የመጀመር ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለውና ገበያውም እንዳለ መረዳቱን የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል።
ነገር ግን አሁን ላይ ወደ አውስትራልያ በረራ ለመጀመር " አውሮፕላን የለንም " ብለዋል።
ለዚህም ረጅም ርቀት መጓዝ የሚችሉ አዳዲስ አውሮፕላኖች ግዢ እየተከናወነ መሆኑን ተጠቁሟል።
አየር መንገዱ ከጥር 2020 ዓ.ም ጀምሮ ከቦይንግ እና ኤርባስ ኩባንያዎች የሚረከባቸው በርከት ያሉ አዳዲስ አውሮፕላኖች በመኖራቸው ለአውስትራሊያው መስመር በረራ መጀመር ዝግጅት እንደሚደረግ ገልጸዋል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙሉ የራስ ገዝነት መብቱን ለመተግበር ባደረገው የመዋቅር ማስተካከያ ምክንያት ከ500 በላይ አስተዳደራዊ ሰራተኞች እና 50 መምህራን ያለመደብ መቅረታቸውን ኤስቢኤስ ራድዮ ከአውስትራሊያ ዘግበ። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ማንም ሰራተኛ እንዳልተባረረ ገልጸው፤ የተጎዱት በጡረታ፣ በካሳ ወይም በቅርቡ በሚጀመረው የንግድ እንቅስቃሴ እንደሚካተቱ ተናግረዋል።
ፎርቹን ጋዜጣ እንደዘገበው ደግሞ ምደባው ለአስተዳደር ሰራተኞች በፈተና፣ ለመምህራን ደግሞ በትምህርት ዝግጅት አግባብነት ላይ ተመስርቶ እየተከናወነ ነው። በሀገሪቱ ከሚገኙ 46 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች መካከል የመጀመሪያው ሞዴል የሆነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሪፎርም እርምጃ፣ ቀጣይ ተመሳሳይ እርምጃ ለመውሰድ ለሚዘጋጁት እንደ ጅማ፣ ባህር ዳር፣ ጎንደር፣ መቀሌ እና መሰል ታላላቅ ዩኒቨርሲቲዎች ማሳያ ይሆናል ተብሏል።
ፎርቹን ጋዜጣ እንደዘገበው ደግሞ ምደባው ለአስተዳደር ሰራተኞች በፈተና፣ ለመምህራን ደግሞ በትምህርት ዝግጅት አግባብነት ላይ ተመስርቶ እየተከናወነ ነው። በሀገሪቱ ከሚገኙ 46 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች መካከል የመጀመሪያው ሞዴል የሆነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሪፎርም እርምጃ፣ ቀጣይ ተመሳሳይ እርምጃ ለመውሰድ ለሚዘጋጁት እንደ ጅማ፣ ባህር ዳር፣ ጎንደር፣ መቀሌ እና መሰል ታላላቅ ዩኒቨርሲቲዎች ማሳያ ይሆናል ተብሏል።
Sponsored by
Surafel
2 months ago
የሐሰት የኦንላይን የሥራ ማስታወቂያዎች ዓለም አቀፍ የሰዎች ዝውውርና የሳይበር ማጭበርበር መረቦችን እያጠናከሩ ነው
#ethiopia | በውጭ አገራት የሚገኙ ከፍተኛ ደመወዝ ያላቸውን የሥራ ዕድሎች በማስታወቅ የሚያታልሉ የኦንላይን የሥራ ማስታወቂያዎች፣ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ወደ የሳይበር ማጭበርበር መረቦች በማስገባት የዘመናዊ ባርነትና የሰዎች ዝውውር ችግርን እያባባሱ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት አስጠንቅቋል።
(IOM) እንደገለጸው፣ የወንጀለኛ መረቦች በማኅበራዊ ሚዲያ፣ በድረ-ገጾች እና በሌሎች የኦንላይን መድረኮች ላይ የሐሰት የሥራ ማስታወቂያዎችን በማሰራጨት ተጎጂዎችን ወደ ውጭ አገራት ያጓጉዛሉ።
በዚያ ከደረሱ በኋላ ፓስፖርታቸውና የጉዞ ሰነዶቻቸው ይወሰድባቸዋል፤ ከዚያም በዛቻ፣ በአካላዊ ጥቃት፣ በዕዳ እገታ እና በእስራት በመጠቀም በኦንላይን የገንዘብ ማጭበርበር ሥራዎች ላይ እንዲሳተፉ ይገደዳሉ።
የIOM ዋና ዳይሬክተር በጄኔቫ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ እነዚህ ወንጀሎች በፍጥነት እየተስፋፉ መሆናቸውን ገልጸው፣ ከ80 በላይ አገራት የመጡ ዜጎች የእነዚህ መረቦች ሰለባ እየሆኑ መሆኑን አስታውቀዋል።
በተለይም እንግሊዝኛ በደንብ የሚናገሩ፣ የዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎችና ሙያዊ ክህሎት ያላቸው ወጣቶች በዋናነት ኢላማ እየሆኑ መሆኑንም ገልጸዋል።
ድርጅቱ እንደሚለው፣ የማጭበርበር ማዕከላቱ በተለይ በደቡብ ምስራቅ እስያ በስፋት የተስፋፉ ሲሆን፣ ተጎጂዎች በፍቅር ማጭበርበር (Romance Scams)፣ በሐሰተኛ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች፣ በክሪፕቶ ማጭበርበር እና በሌሎች የኦንላይን የገንዘብ ማጭበርበር ዘዴዎች ላይ እንዲሠሩ ይገደዳሉ።
(UNODC) ባወጣው ግምገማ መሠረት፣ እነዚህ የሳይበር ማጭበርበር መረቦች በ2024 ብቻ በምስራቅ እስያ፣ በአውስትራሊያ እና በኒውዚላንድ 114 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የገንዘብ ኪሳራ አስከትለዋል።
በቀጣናው የሚገኙ የማጭበርበር ካምፖችም በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ በማታለል ወይም በግዳጅ የተወሰዱ ሰዎችን ይዘው ሊያሰሩ እንደሚችሉ ተገልጿል።
IOM እንደገለጸው፣ ከ2022 እስከ 2025 ባለው ጊዜ ውስጥ ከ40 በላይ አገራት የመጡ 3,500 በላይ ተጎጂዎችን መታደግ ችሏል።
በእነዚህ መካከል ከኢንዶኔዥያ፣ ከሕንድ፣ ከስሪላንካ፣ ከኢትዮጵያ፣ ከኬንያ እና ከባንግላዴሽ የመጡ ዜጎች በብዛት ይገኙበታል።
ባለሙያዎች ዜጎች በማኅበራዊ ሚዲያ የሚወጡ የሥራ ማስታወቂያዎችን ከመቀበላቸው በፊት የቀጣሪውን ተቋም ሕጋዊነት እንዲያረጋግጡ፣ የጉዞ ሰነዶቻቸውን ለማንም እንዳይሰጡ እና አጠራጣሪ የሥራ ቅጥር ጥሪዎችን ለሚመለከታቸው ባለሥልጣናት እንዲያሳውቁ ያሳስባሉ።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በጸጥታ እና ጂኦፖለቲካዊ ቀውሶች ምክንያት ከ6 እስከ 7 ዓመታት ገደማ ተጓትቶ የነበረው የኬፊ ጎልድ ኤንድ ኮፐር ኩባንያ 'የቱሉ ካፒ' የወርቅ ማዕድን ፕሮጀክት በመጨረሻም ወደ ግንባታ ምዕራፍ መግባቱ ተገለጸ።
ከአዲስ አበባ 360 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኘው ይህ ፕሮጀክት፣ ከ400 ሚሊዮን ዶላር በላይ የፋይናንስ ፓኬጅ የተመደበለት ሲሆን (የኢትዮጵያ መንግስት 20 ሚሊዮን ዶላር በማዋጣት የ17 በመቶ ድርሻ ይዟል)፣ በዓመት 166 ሺህ አውንስ ወርቅ የማምረት አቅም ይኖረዋል። ማዕድን ማውጣቱ ክፍት እና ከመሬት በታች የማውጣት ዘዴዎችን አጣምሮ የሚጠቀም ሲሆን፣ በ2027 መገባደጃ ላይ ስራ ጀምሮ በ2028 ሙሉ የማምረት አቅሙ ላይ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።
የኩባንያው ስራ አስፈፃሚ ሃሪ አናግኖስታራስ-አዳምስ እንዳሉት፤ ይህ "ስትራቴጂካዊ የኢትዮጵያ ፕሮጀክት" አሁን ላይ 1 በመቶ ብቻ ያለውን የማዕድን ዘርፉን የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) አስተዋፅኦ በቀጣዩ አስርት ዓመት ውስጥ ወደ 10 በመቶ ለማሳደግ ለታለመው የመንግስት ዕቅድ ትልቅ ሚና ይጫወታል።
ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ይህንን እጅግ ከፍተኛ ሆነ የኢኮኖሚ ዕቅድ ለማሳካትና ማዕድን ዘርፉን እንደ አውስትራሊያ ለማሳደግ፣ እንደ ቱሉ ካፒ ፕሮጀክት ያጋጠማቸው ዓይነት የጸጥታ መደፍረስና የዓመታት መጓተት ዳግም እንዳይከሰት አስተማማኝ ሰላም ማረጋገጥ ዋነኛ ፈተናዋ ሆኖ ይቀጥላል። ፕሮጀክቱ ትርፋማነቱ (በተለይ አሁን ባለው የዓለም የወርቅ ዋጋ መጨመር) እጅግ አጓጊ ቢሆንም፣ ቀጣይነቱ የሚወሰነው በመሬት ላይ ባለው ፖለቲካዊ እና የጸጥታ መረጋጋት ላይ መሆኑን ባለሙያዎች ለዘ-ሐበሻ ተናግረዋል።

"የተሰደድኩበትን ቂም ትቼ ልመካከር መጥቻለሁ" - ፓስተር ፖች ኦኩዌር
******************
ከ22 ዓመታት በፊት በጋምቤላ በደረሰው አሳዛኝ ግጭት አባታቸውን፣ አጎታቸውንና የቅርብ ቤተሰቦቻቸውን በአንድ ቀን ያጡት ፓስተር ፖች ኦኮዌር፤ ለዓመታት የዘለቀውን የልብ ስቃይና ቁስል በበቀል ሳይሆን በይቅርታ ለመፈወስ የወሰኑበትን ታሪክ ያካፍላሉ።
ያ ከባድ ሀዘን እና ቁርሾ ውስጣቸውን ለዘመናት ሲያንገበግበው ቢኖርም፤ "ያኔ ብንመክር ይህ አይፈጠርም ነበር፤ ዛሬ መክረን መጠፋፋት በእኛ ይብቃ ልንል ይገባል" በማለት ቂማቸውን ወደ ይቅርታ በመቀየር በሀገራዊ ምክክሩ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ከአውስትራሊያ በመምጣት በዚሁ ታሪካዊ የምክክር መድረክ ላይ የተገኙት ፓስተር ፖች፣ ሀገራዊ መግባባት የሚጀምረው ከግል ይቅርታ እንደሆነ ይመሰክራሉ።
ፓስተር ፖች፤ ላለፉት በርካታ ዘመናት በኢትዮጵያ ውስጥ የተከማቹ በርካታ ቁስሎችና አለመግባባቶች ዋናው ምክንያት አለመነጋገርና አለመመካከር መሆኑን ይናገራሉ።
ሰዎች በግልጽ በሚነጋገሩበት ወቅት አንዱ የሌላውን ሕመም የመረዳት አቅም ያገኛል፤ ይህ ደግሞ በቂም የተዘጉ በሮችን በመክፈት የጠፉ ፍቅሮችንና የቤተሰባዊነት ስሜትን ይመልሳል ይላሉ።
የቤተሰብ አባልን በግፍ ማጣት ከፍተኛ የልብ ስቃይ የሚያስከትል ቢሆንም፣ በበቀል ስሜት የሚወሰድ እርምጃ ግን ጥፋቱን ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚያስተላልፍ ተጨማሪ ቁስል ከመፍጠር እንደማይዘል ፓስተር ፖች ይገልፃሉ።
ይቅርታ ማድረግ የደረሰውን በደል መካድ ሳይሆን፣ የበቀልን ከባድ ሸክም አውርዶ በማስቀመጥ ለተሻለና ለሰላማዊ ነገ መንገድ የመክፈት ጥበብ መሆኑንም ይናገራሉ።
ዛሬ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ሰፊና አካታች መክክር ለሀገሪቱ ትንሣኤ ትልቅ ጅምር መሆኑን በመጥቀስ፤ በተለይም አዲሱ ትውልድ ከቂም፣ ከጥላቻና ከመገዳደል አዙሪት ወጥቶ በፍቅርና በመቻቻል እንዲኖር ትልቅ በር እንደሚከፍት ይገልጻሉ።
ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የመጡ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች በእኩልነት የሚሳተፉበት መድረክ መፈጠሩ ለነገዋ ኢትዮጵያ ትልቅ ተስፋ እንደሆነም ይጠቁማሉ።
በእውነትና በይቅርታ ላይ የተመሰረተ ውይይት ሀገራችንን ወደ ተሻለች ከፍታ እንደሚያሸጋግራት ፓስተር ፖች ያላቸውን ፅኑ እምነት ገልፀዋል።
#ebc #ethiopia #ethiopiannationaldialogue #nationalconsensus
ሙሉ ታሪኩን በአስተያየት መስጫው ላይ ያገኙታል፡-

ዘማሪት ኢየሩሳሌም አየለ «የጄሪ ጩኮ»ን ጨምሮ ባህላዊ ምግቦችን ለኤክስፖርት አቀረበች!
#fastmereja I ታዋቂዋ ዘማሪ ኢየሩሳሌም አየለ (ጄሪ) የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግቦችን(ጩኮ) እና የቅመማ ቅመም ምርቶችን ለውጭ ሀገር ገበያ (Export) ለማቅረብ ያዘጋጀችውን አዲስ የንግድ ስራ እና የምርት አይነቶች በይፋ አስተዋወቀች።
በእናትና አባቷ የሼፍነት ሙያ እና በቤተሰብ የሙያ ውርስ ላይ ተመስርቶ የተጀመረው ይህ የንግድ ስራ፤ በዋናነት «ጄሪ»በሚል የምርት ስም የሚታወቅ ሲሆን፣ የቦቆጂን የሳር እና የጦስኝ ለጋ ቅቤ በመጠቀም የተዘጋጀውን «የጄሪ ጩኮ» ጨምሮ አነባበሮ፣ በቅቤ የታሸገ ቆሎ፣ ዳጣ እና ሚጥሚጣን ለገበያ አቅርቧል።
ዘማሪ ኢየሩሳሌም እንደገለፀችው፣ ምርቶቹ ሙሉ በሙሉ በቤት ውስጥ በከፍተኛ ንፅህና እና ጥንቃቄ በራሳቸው እጅ የሚዘጋጁ መሆናቸዉን ገልፃለች።
ዘማሪ እየሩሳሌም አክላም ምርቶቹ አለም አቀፍ የኤክስፖርት መስፈርትን (Export Standard) አሟልተው የተሰሩ በመሆናቸው ቀዝቃዛ ቦታ ላይ በመጠበቅ ከ1 ወር እስከ 1 ዓመት ድረስ ሳይበላሹ መቆየት እንደሚችሉ ገልፃ በተለይም በቅቤ የታሸገው ቆሎ የምርቱን ትኩስነት እና ጥራት ለመጠበቅ ሲባል በልዩ ትዕዛዝ ብቻ የሚዘጋጅ መሆኑ ገልፃለች።
የምርቱ"ዋና አላማ ከሀገር ውስጥ አልፎ የኢትዮጵያን ባህላዊ ጣዕሞች በዓለም አቀፍ ደረጃ ማስተዋወቅ ነው" ስትል የተናገረችው ዘማሪ ኢየሩሳሌም፤ በአሁኑ ወቅት ወደ ካናዳ፣ አሜሪካ፣ አውስትራሊያ እና ጀርመን ምርቶቹን ለመላክ የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ገልጻለች።
በአሁኑ ወቅት በቤተሰብ ደረጃ እየተከናወነ የሚገኘው ይህ ኢንተርፕራይዝ፣ ስራው ከፍተኛ ጥንቃቄ እና ድካም የሚይዝ ቢሆንም ምርቶቹን ለተጠቃሚው በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ መታቀዱ ተገልጿል።
በመጨረሻም ድርጅቱ ወደፊት አቅሙን በማስፋፋት ለበርካታ ዜጎች ተጨማሪ የሥራ ዕድል የመፍጠር እና አዳዲስ ባህላዊ ምርቶችን ወደ ገበያ የማስገባት እቅድ እንዳለው ነዉ የተገለፀዉ።

3 months ago
ከ22 ዓመት የስደት ቁስል እስከ ሀገራዊ ምክክር፣ በሕይወት ስጋት የተደረገው አውስትራሊያ ጉዞ እና የሀገራዊ ምክክሩ ተስፋ
#pastorpochokuwer #nationaldialogue #ethiopianreconciliation #ethiopiandiaspora #nationalconsensus
3 months ago
ለመኖሪያ ቤት ፈላጊዎች አዲስ ተስፋን ይዘው የመጡት ዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂዎች
**********************
የ3ዲ ኮንክሪት ሕትመት፣ ቀላል የዓረብ ብረት ግንባታ እና የኮንቴይነር መኖሪያ ቤቶች የዓለማችን የግንባታ ቴክኖሎጂ አዳዲስ ቋንቋዎች ሆነዋል።
እነዚህ ቴክኖሎጂዎች በስፋት ጥቅም ላይ መዋል የጀመሩት በቅርብ ዓመታት ቢሆንም፣ በዓለም ዙሪያ በፍጥነት እየተስፋፉ ይገኛሉ።
እንደ አሜሪካ፣ ካናዳ፣ አውስትራሊያ፣ እንግሊዝ፣ ኔዘርላንድስ እና ደቡብ ኮሪያ ያሉ ሀገራት የዜጎቻቸውን የቤት ፍላጎት በተቀላጠፈ ሁኔታ ለመፍታት እነዚህን ቴክኖሎጂዎች ቀድመው ጥቅም ላይ ካዋሉ ግንባር ቀደም ሀገራት መካከል ይጠቀሳሉ።
በዚህ ረገድ ኢትዮጵያም ፈጥናለች፣ ሀገራችን በእርግጥም ዘምናለች፤ ከሰሞኑ እነዚህን ሦስት የግንባታ ቴክኖሎጂዎች በማጣመር፣ የዜጎችን የቤት ጥያቄ ለመፍታት አንድ ብላ ጉዞ ጀምራለች!
በኢትዮጵያ የመኖሪያ ቤት ፍላጎት እጅግ መሠረታዊ ከሆኑ ጥያቄዎች አንዱ ነው። የከተሞች መስፋፋት እና የሕዝብ ቁጥር ዕድገት ይህን ፍላጎት ይበልጥ አንገብጋቢ አድርገውታል።
በተለይ በዋና ከተማችን አዲስ አበባ ያለው የቤት አቅርቦት እና ፍላጎት አለመጣጣም ለከፍተኛ የቤት ኪራይ ንረት እና ለኑሮ ውድነት ዋነኛ ምክንያት በመሆኑ አፋጣኝ መፍትሔ ይሻል።
ይህን ችግር ለመፍታት መንግሥት ባወጣው የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ፣ 4.4 ሚሊዮን ቤቶችን በተለያዩ አማራጮች ለመገንባት አቅዷል። ይህንንም ለማሳካት፦
✅ የግል ዘርፉን ማሳተፍ፦ ችግሩን ለመቅረፍ መንግሥትን ብቻ ከመጠበቅ ይልቅ፣ የግል አልሚዎች በስፋት እንዲሳተፉ የሚያስችሉ የሕግ ማዕቀፎች ተሻሽለዋል።
✅ የማኅበራት አደረጃጀት፦ በአዲስ አበባ እና በሌሎች ከተሞች ነዋሪዎች በማኅበር ተደራጅተው የቤት ችግራቸውን እንዲፈቱ የመሬት አቅርቦት እና መሰል ድጋፎች እየተደረጉ ይገኛሉ።
በሌላ በኩል ከዚህ ቀደም በተለመደው የቤት ግንባታ ሒደት ብቻ በከተሞች ያለውን የቤት አቅርቦት ችግር መፍታት ስለማይቻል፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ተግባራዊ እየተደረጉ ነው።
እነዚህ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ በርከት ያለ ነው፦
👉 የ3ዲ ሕትመት (3D Printing)፦ ልዩ የሆነ ትልቅ ፕሪንተር በመጠቀም ኮንክሪት ወይም ሌሎች የግንባታ ቁሳቁሶችን በመደርደር ግድግዳዎችን እና መዋቅሮችን ይገነባል። ይህ ቴክኖሎጂ የብረት ግብዓትን እስከ 30 በመቶ፣ ሲሚንቶን ደግሞ ከ35 እስከ 40 በመቶ መቀነስ የሚችል ወጪ ቆጣቢ አማራጭ ነው። በአሁኑ ወቅት ባለ 4 ወለል (G+4) ቤቶች በዚህ ቴክኖሎጂ እየተገነቡ ሲሆን፣ ዲዛይኑ እስከ 14 ወለል እና ከዚያ በላይ የመገንባት አቅም አለው።
👉 ቀላል የአረብ ብረት ግንባታ፦ ቀላል እና ጠንካራ የብረት ክፍሎች በፋብሪካ ተዘጋጅተው ወደ ግንባታ ቦታ ተወስደው የሚገጣጠሙበት ዘዴ ነው። ይህም የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋን የመቋቋም አቅም ያለው ሲሆን፣ ለፈጣን ግንባታ ምላሽ ከመስጠቱ ባሻገር ከእንጨት ይልቅ እጅግ ዘላቂ ነው።
👉 ተገጣጣሚ ቤቶች፦ የቅድመ-ፋብሪካ ቴክኖሎጂዎች የግንባታ ጊዜን በአጭሩ በመቅጨት ለፈጣን የቤት አቅርቦት ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ።
መንግሥት እነዚህን ጊዜ፣ ጉልበት እና ወጪ ቆጣቢ የሆኑ አዋጭ የግንባታ ዘዴዎች ወደ ተግባር እያስገባ ነው። ኢትዮጵያ በጀመረችው በዚህ የለውጥ ፍጥነት ጉዞዋን ስትቀጥል፣ ቴክኖሎጂው ደግሞ በበኩሉ ፈጥኖ ቤታችንን ይገነባልናል።
በዚህም በመጪዎቹ ጥቂት ዓመታት ውስጥ፣ የዘመናት የቤት ጥያቄያችን ዘላቂ መፍትሔ እንደሚያገኝ ታላቅ ተስፋ ተጥሏል።
በዓይናለም ሀድራ
#ethiopia #ebc #housing #3dtechnology

ግብፅ አውስትራሊያን በመለያ ምቶች አሸንፋ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈች!
#ethiopia | በጠንካራ ፉክክር የተሞላው ጨዋታ ከመደበኛ እና ከተጨማሪ ሰዓት በኋላ በመለያ ምቶች ተወስኖ፣ ግብፅ አውስትራሊያን አሸንፋ ወደ ቀጣዩ ዙር መግባቷን አረጋግጣለች።
#egypt #australia #penaltyshootout #football #caf #egyptwins

ግብፅ አውስትራሊያን በማሸነፍ 16ቱን ተቀላቀለች
**********************
በ23ኛው ዓለም ዋንጫ ግብፅ አውስትራሊያን በመርታት የ16ቱ ጥሎ ማለፍ ጉዞዋን አሳክታለች።
በጨዋታው ኢማም አሹር በ13ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ግብፅን መሪ ብታደርግም፣ በ55ኛው ደቂቃ ሞሀመድ ሀኒ በራሱ መረብ ላይ ባስቆጠራት ግብ አውስትራሊያ አቻ ሆና ነበር።
የጨዋታው መደበኛ ክፍለ ጊዜና ጭማሪው 30 ደቂቃ 1 ለ 1 ተጠናቆ ግብፅ በመለያ ምት 4 ለ 2 አሸንፋለች።
ወደ 16ቱ ጥሎ ማለፍ የተሸጋገረችው ግብፅ በቀጣይ ጨዋታዋ ከአርጀንቲና እና ኬፕ ቨርዴ አሸናፊ ጋር ትጫወታለች።
#worldcup #fifaworldcup #switzerland #algeria #embolo #football #sports #ebc

ግብጽ አውስትራሊያን በማሸነፍ 16ቱን ተቀላቀለች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በዓለም ዋንጫ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ግብጽ አውስትራሊያን በመለያ ምት በማሸነፍ 16ቱን ተቀላቅላለች።
ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች በመደበኛና ተጨማሪ ጊዜ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት በማጠናቀቃቸው ወደ መለያ ምት አምርተዋል።
አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠ የመለያ ምትም ግብጽ 4 ለ 2 በማሸነፍ 16ቱን መቀላቀል ችላለች።
ግብጽ ሞሮኮን በመከተል 16ቱን የተቀላቀለች 2ኛዋ የአፍሪካ ሀገር ሆናለች።

Comments