2 months ago
ኢትዮጵያ : የሰው ልጅ መገኛነቷን ዳግም ለዓለም አረጋገጠች
#ethiopia | ኢትዮጵያ አሁንም "የሰው ዘር መገኛ" መሆኗን በሳይንስ ዳግም አረጋገጠች።
በአፋር ስምጥ ሸለቆ በመካከለኛው አዋሽ (ሀሊቢ) አካባቢ በተደረገ የምርምር ፕሮጀክት፣ ከ100 ሺህ ዓመታት በፊት ይኖሩ የነበሩ የጥንታዊ ሆሞ ሳፒየንስ (Homo sapiens) ቅሪተ አካላት እና የድንጋይ መሣሪያዎች መገኘታቸውን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ይፋ አድርጓል።
ግኝቱ በአፍሪካ የሰው ዘር አመጣጥ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ክፍተት የነበረበትን ከ900,000 እስከ 200,000 ዓመታት ያለውን ጊዜ የሚዘክሩ አዳዲስ መረጃዎችን ይዟል።
ጥናቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ባለው የአሜሪካ የሳይንስ ጆርናል (PNAS) ላይ ዛሬ ታትሞ ወጥቷል።
በሺዎች የሚቆጠሩ የድንጋይ መሣሪያዎች መገኘታቸው፣ የሰው ልጅ የቴክኖሎጂ እድገት በወቅቱ ምን ይመስል እንደነበር ትልቅ ማሳያ ሆኗል።
በጥናቱ የተገኙ የእንስሳት ቅሪቶች (ጉሬዛ፣ ዝንጀሮ...) አፋር በወቅቱ ዛሬ እንደምናየው በረሃማ ሳይሆን ለምለምና ጫካማ እንደነበር ያረጋግጣሉ።
በዶ/ር ዮናስ በየነ የተመራውና ከ24 ሀገራት የተውጣጡ ሳይንቲስቶች የተሳተፉበት ይህ ምርምር፣ ለሀገራችን የቱሪዝም ዘርፍና ለታሪክ ጥናት ትልቅ ግብዓት ነው።
ኢትዮጵያ - የሰው ዘር ሁሉ ቤት!
#getu #humanorigins #ethiopiacradleofmankind #archaeologynews #afardepression #homosapiens #scientificdiscovery #yonasbeyene #ethiopianheritage #አፋር #አርኪዮሎጂ #ኢትዮጵያ #የሰውዘርመገኛ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

በፖላንድ በመቶዎች የሚቆጠሩ አስከሬኖች ያሉበት "የቫምፓየር መቃብር" ተገኘ
በፖላንድ ፒየን በተባለ ስፍራ በ17ኛው ክፍለ ዘመን እንደነበረ የሚታመንና በመቶዎች የሚቆጠሩ አስከሬኖችን የያዘ መቃብር በአርኪዮሎጂስቶች ተገኘ።
NTK እንደዘገበው ፣ በመቃብሩ ውስጥ ከ100 በላይ አስከሬኖች የተገኙ ሲሆን፣ አንዳንዶቹ አስከሬኖች "ተመልሰው እንዳይነሱ" በሚል እምነት በአንገታቸው ላይ ማጭድ ተደግኖባቸው፣ በእግራቸው ላይ ቁልፍ ታስሮባቸው ወይም በላያቸው ላይ ከባድ ድንጋይ ተጭኖባቸው ተገኝተዋል።
በተለይም "ቫምፓየር ዞሲያ" የተሰኘችው ወጣት እና አንዲት ነፍሰ ጡር ሴት መቃብር የአርኪዮሎጂስቶቹን ትኩረት ስቧል።
ለ20 ዓመታት በቦታው ጥናት ያደረጉት ፕሮፌሰር ዳርዩስ ፖሊንስኪ እንደገለጹት፣ እነዚህ ሰዎች በወቅቱ በነበረው ጦርነትና በሽታ ምክንያት በህብረተሰቡ ዘንድ እንደ ስጋት የሚታዩና የተገለሉ ነበሩ።
ይህ ግኝት በወቅቱ በነበረው የሰው ልጅ ስነ-ልቦና ውስጥ የነበረውን ጥልቅ የሞት ፍርሃት እና ከተፈጥሮ በላይ የሆኑ እምነቶችን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው ተብሏል።
ምንጮች፦ Niezależna Telewizja Kablowa

6 months ago
ህንድ እና ህንዳውያን:- የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ወዳጆች!!
በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን)
"... የጥንታዊት ታሪክና ገናና ሥልጣኔ ባለቤት፤ የአፍሪካና የጥቁር ሕዝብ ታላቅ የነጻነት ተጋድሎ ምልክት ከሆነች አገር- ኢትዮጵያ ይሄ የክብር ኒሻን ስለተበረከተልኝ ደስታዬ እጥፍ ድርብ ነው፤ በ1.4 ቢሊዮን በሚሆነው የአገሬ የህንድ ሕዝብ ስም ምስጋናዬን ለመግለጽ እወዳለሁኝ...፤"
በአገራችን ኢትዮጵያ ይፋዊ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት የህንዱ ጠቅላይ ሚ/ር ናኔድራ ሞዲ- በጠቅላይ ሚ/ር ዐብይ አሕመድ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ኒሻን በተበረከተላቸው ጊዜ ከላይ በመግቢያዬ ላይ ከጠቀስኩት ንግግራቸው ባሻገር በንግግራቸው - ህንድና ህንዳውያን አገራችን ኢትዮጵያ በፋስሽት በተወረረች ወቅት ከጎናችን መቆማቸውን ታሪክ አጣቅስው ተናግረዋል።
ህንድ እና ህንዳውያን:- የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ወዳጆች!!
የቅኝ ገዥዎችን ቅስም ካነካከተውና መላው አውሮፓንና ነጮችን በድንጋጤ እጃቸውን በአፋቸው ላይ እንዲጭኑ ያደረጋቸውን፤ አንፀባራቂውን የዐድዋውን ድል- ለመበቀል ፋሽስት ኢጣልያ ከ40 ዓመታት ዝግጅት በኋላ በአየርና በምድር የጦር መሳሪያ እስከ አፍንጫው ታጥቆና እንዲሁም በዓለም አቀፍ የሕግ የተከለከለ የመርዝ ቦምብ ሳይቀር ተሽክሞ ነበር የመጣው።
"... ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያን በዓለም ፊት የሚኮሩበት ነጻነታችውና ሉዓላዊነታቸው በቅኝ ግዛት ቀምበር ስር እንዲወድቅና ኢትዮጵያውያን ዳግመኛ አንገታቸውን ቀና አድርገው እንዳይሄዱ ለአፍሪካና ለመላው ጥቁር ሕዝብ መቀጣጫ ሊሆኑ ይገባል!!" በሚል እብሪትና ትእቢት ፋስሽቱ ቤኒቶ ሞሶሎኒ የበቀልና የጭካኔ ሰይፉን በኢትዮጵያውያን ላይ መዘዘብን።
በዛ የመከራና የጭንቅ ዘመን ህንድና ህንዳውያን ከኢትዮጵያ ጋር ቆመዋል፤ በዓለም መድረክ ድምፅ ሆነውናል። ታሪክን ምስክር እናድርግ፤ በወቅቱ የህንድ ጠቅላይ ሚ/ር የነበሩት ጃኋራል ኔህሩ በህንድ ፓርላማ ባሰሙት ንግግራቸው እንዲህ ነበር ያሉት፤
"We in India can do nothing to help our brethren in distress in Ethiopia… But we can at least send them sympathy… in the hour of their trial. We stand with them today in their sorrow…" (quoted in Indian government records and MEA speeches).
"... ምንም እንኳን ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ለጊዜው ምንም ማድረግ ባንችልም- ለነጻነታቸው በሚያደርጉት ተጋድሎአቸው ከጎናቸው መሆናችን የሚገልጽ ልባዊ መልእክታችንን ልንልክላቸው እንወዳለን፤ በዓለም አቀፍ መድረክ ለኢትዮጵያውያን የፀረ-ፋሽስት እና የፀረ-ቅኝ ግዛት ተጋድሎ የጋራ ድምፅ እንሆናቸዋለን...፤"
ኢትዮጵያ እና ህንድ በቀደመው ዘመን
ጥንታዊት፤ የገናና ታሪክና የግዙፍ የሥልጣኔ ባለቤት የሆነችው አገራችን ኢትዮጵያ- እንደ አገራችን ሁሉ የሺህ ዘመናት ታሪክና የሥልጣኔ ባለቤት ከሆነችው ህንድ ጋር ለ2000 ሺህ ዓመታት በፊት በህንድ ውቅያኖስ እና በቀይ ባሕር አማካኝነት የአፍሪካን ድንበር የተሻገረ የንግድ ግንኙነት/Martime Trade እንደነበረን የታሪክ ድርሳናት የአርኪዮሎጂ ሳይንስ ግኝቶች ይመሰክራሉ።
ወጌን ፈር ለማስያዝ ይረዳኝ ዘንድ ከታሪክ ድርሳናት በጥቂቱ ላጣቅስ፤
Neville Chittick, የተባለ ምሁር፤ "Indian Relations with East Africa before the Arrival of the Portuguese" በሚል በጻፈው መጽሐፍ በህንድ በኩሻን ሥርወ-መንግሥት ዘመን መገበያያ የነበሩ የወርቅ ሳንቲሞች በአርኪዮሎጂ ጥናት በአክሱምና በደብረዳሞ መገኘታቸውን ተጽፏል። ይኸው ምሁር፤ የህንድ የጉፕታ ዘመነ መንግሥት አሻራ የሆኑ ቁሳቁሶች፤ የከበሩ ጌጣጌጦችና ጨሌዎች በጥንታዊቷ አክሱም ከተማና የኢትዮጵያ ወደብ በሆነችው አዶሊስ መገኘቱን አትቷል።
በተጨማሪም በኢትዮጵያ/በአክሱም ታሪክና ሥልጣኔ ላይ የተጻፉ በርካታ የታሪክ ድርሳናትና የጉዞ ማስታወሻዎች እንደሚጠቁሙት፤ አክሱማውያን የዝሆን ጥርስ፣ ወርቅ፣ ዕንቁ፣ ሃርና የከበሩ ማዕድናትን... ወዘተ. በቀይ ባሕርና በህንድ ውቅያኖስ አማካኝነት ከህንድና ከመካከለኛው ምሥራቅ አጋራት ጋር የንግድ ልውውጥ ያደርጉ ነበር።
የግሪክ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መነኩሴና ተጓዥ የነበሩት አባ ኮስሞስ ኢንዲክሎፕተስ፤ "the Periplus of Eritrean Sea" በሚል አርእስት ከ 1500 ዓመታት ገደማ በፊት በጻፉት የጉዞ ማስታወሻቸው፤
"... ኢትዮጵያውያን/አክሱማውያን በጥንት ዘመን በቀይ ባሕር በኩል- ከመካከለኛው ምሥራቅ፣ ከዐረቢያ፣ ከቻይና ከህንድ ጋር የጠበቀ የባሕር ላይ የንግድ ግንኙነት እንደነበርን፤" ጽፈዋል።
እንደ ማጠቃለያ፤
የህንድና የኢትዮጵያ ግንኙነት ሺሕ ዘመንን የተሻገረ ጠንካራ የታሪክና የሥልጣኔን እሤቶችን የሚጋራ ነው። በግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት የኢትዮጵያና የህንድ ዲፕሎማሲ ግንኙነት ጠንካራ መሠረትን ይዞ ተጀመረ። በደርግም ሆነ በዘመነ ኢሕአዴግ መንግሥታት ቢቀያየሩም የሁለቱ አገራት ግንኙነት ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው።
ኢትዮጵያና ህንድ በትምህርት፣ በጤና፣ በግብርና፣ በኢንቨስትመንት፣ በቴክኖሎጂ... ወዘተ. ረገድ የጠበቀ ትስስር አላቸው። በዓለም ዙሪያ በሰላም ማስከበር ዘመቻ ሁለቱ አገራት- ኢትዮጵያና ህንድ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ አገራት ናቸው። በብሪክስ አገራትና በደቡብ ደቡብ ትብብር መድረክ ህንድና ኢትዮጵያ የጎላ ሚናን እየተጫወቱ የሚገኙ ሀገራት ናቸው።
የዛሬውን ኢትዮጵያንና ህንድን የተመለከተውን ወጌን- በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና የዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር/ፕሮፌሰር፤ በአንድ ወቅትም በህንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉት አምባሳደር ዶ/ር ትዝታ ሙሉጌታ አባባል ለመቋጨት ወደድኹ፤
"የኢትዮጵያና የህንድ ግንኙነት በማይናወጽ ጠንካራ የታሪክ መሠረትና የእርስበርስ ትብብር ላይ የቆመ ነው፤"
የኢትዮጵያና የህንድ ግንኙነት ይለምልም!!

የኢትዮጵያን የሰው ዘር መገኛነት ያጠናከረ ግኝት ይፋ ሆነ
የኢትዮጵያን የሰው ዘር መገኛነት ያጠናከረ ግኝት በአፋር ክልል በጎና መካነ ቅርስ ሥፍራ መገኘቱ ይፋ ሆኗል፡፡
አዲሱ ግኝት በኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን የጎና የአርኪዮሎጂ የምርምር ጥናት ተመራማሪ በሆኑት በስለሺ ሰማው (ዶ/ር) እና ሮጀርስ ማይክል (ዶ/ር) መሪነት የተገኘ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ግኝቱን አስመልክተው የጎና የቅርስ መካነ ጥናት መሪ እንዲሁም በስፒን የሰው ዘር አመጣጥ ማዕከል ከፍተኛ ተመራማሪና ሳይንቲስት የሆኑት ስለሺ ሰማው (ዶ/ር) ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫቸውም፤ በጎና መካነ ጥናት የተገኘው 1.5 ሚሊዮን ዓመታት እንደሚደርስ የተገመተው ሆሞ ኢሬክተስ በመባል የሚታወቀው የቅድመ ሰው ዝርያ ጭንቅላትና ፊት በቨርቹዋል ዲጂታል ሪኮንስትራክሽን በሳይንቲስቶች መጠናቱን አስታውቀዋል፡፡
በዚህም ቀደምት የሰው ዝርያዎች ከአፍሪካ ወደ አውሮፓ እና እስያ አህጉራት ያደረጉትን እንቅስቃሴና ኦልድዋን እና አሹሊያ በመባል በሚታወቁ የድንጋይ መሳሪያ መጠቀማቸውን በተመለከተ አዲስ መረጃ ማግኘታቸውን ገልፀዋል፡፡
አዲሱ ግኝት በአፍሪካ እስካሁን ይፋ ከሆኑ ተቀራራቢ እድሜ ካላቸው ግኝቶች የመጀመሪያው የራስ ቅል እና የፊት አጥንቶችን (ጥርሶችን ጨምሮ) የሚያሳይ መሆኑን በቨርቹዋል ዲጂታል ሪኮንስትራክሽን ዘዴ ለማየት ተችሏል ነው ያሉት፡፡
የጥናቱን ውጤት አስመልክተውም የራስ ቅሉና የፊቱ ቅርፅ ከ300 ሺህ ዓመታት በፊት እድሚያቸው 1.8 ሚሊዮን ዓመታት የሚገመቱና ለመጀመሪያ ጊዜ አፍሪካን ለቀው ወደ አውሮፓና እስያ ከፈለሱት የቅድመ ሰው ዝርያዎች የጭንቅላትና የፊት ገፅታ ጋር ተመሳሳይነት እንዳለውም ተናግረዋል ፡፡
አዲሱ ግኝት ሳይንቲስቶች ከ1.8 ሚሊዮን ዓመታት በፊት ወደ አውሮፓና እስያ የፈለሰውን የቅድመ ሰው ዝርያ ከጊዜ በኋላ ከኤስያ ወደ አፍሪካ ተመልሷል የሚለውን መላምት ውድቅ ደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ሆሞ ኢሬክተስ በአፍሪካ ውስጥ በአዝጋሚ ለውጥ የአሁኑ የሰው ዘር ግንድ መሆኑን ያሳየና ኢትዮጵያም የሰው ዘር መገኛ መሆኗን የሚያጠናክር ግኝት መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ሳይንቲስቱ አክለውም የሆሞ ኢሬክተስ ዝርያ ቀደምት የሆነና ኦልድዋን እና አሹሊያ በመባል በሚታወቁ የድንጋይ መሳሪያ መጠቀሙ ዝርያውን ልዩ እንደሚያደርገውና የነዚህ የሁለቱ የድንጋይ መሳሪያዎች ከሆሞ ኢሬክተስ ጋር ባንድ ላይ መገኘታቸው በአርኪዎሎጂ ጥናት እምብዛም ያልተለመደ በመሆኑ የጎናውን ግኝት አስደናቂ እንደሚያደርገው ተናግረዋል፡፡
የቨርቹዋል ሪኮንስትራክሽን ስራ ከዓመት በላይ ጊዜ እንደወሰደባቸው፣ የተገኘው የራስ ቅልና ፊት ከሌሎች ተመሳሳይ እድሜ ካላቸው የቅድመ ሰው ዝርያዎች የአንጎሉ መጠን አነስተኛ መሆኑን እንዲሁም በጥናቱ ከ300 ሺህ ዓመታት በፊት ከነበሩ ሆሞ ሀቢሊስ በመባል ከሚታወቁት የቅድመ ሰው ዘር ዝርያ ጋር መመሳሰሉን ጠቅሰዋል፡፡
ይህም ከአፍሪካ ቀደም ሲል ከ1.8 ሚሊዮን ዓመታት በፊት ከፈለሱት የቅድመ ሰው ዝርያዎች የፊት ገፅታን ይዞ ሳይለወጥ መቆየቱን ገልፀዋል፡፡
እስካሁን በጎና እና በመካከለኛው አዋሽ የጥናት ፕሮጀክቶች የተገኙ የቅድመ ግኝት የሰው ልጅ ዝርያዎች፣ ኢትዮጵያ ለዓለም ካበረከተቻቸው ቅርሶች ቀዳሚ አድርጓታል ተብሏል፡፡
ይህም ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ ለመሆኗ ጉልህ ማረጋገጫ እንደሆነም ተጠቅሷል፡፡
#ebc

የቀይ ባህር እንቁ አሥመራ ሽኮሪና
የአለማችን የመጀመርያዋ የቅርስ ከተማ!
( በታዴ የማመይ ልጅ )
#ethiopia | በእርግጥም በምስራቅ በፅሎትና ቤተ ጊዮርጊስ ፣ በምዕራብ በፀራራት ፣በሰሜን በአክሪያና ባዕታ አስመራ፣ በደቡብ አዲ ጓእዳ ኮረብታዎች ደጀን የሆኗት በፅዳቷ ፣ በእርጋታዋ ፣ እንደሚፈርጥ እንቁላል በጥንቃቄ በተደረደሩት እፁብ ህንፃዎቿ በተንዠረገጉት ዘንባባዎቿ፣ የአፍሪካ ዘመናዊ ከተማ ፣የቀይ ባህር እንቁ ትመስላለች ።
በዛሬዉ የአፍታ ቱሪዝም ጉብኝታችን ባለፉት ሦስት አስርት አመታት ክፉ ክፉዉን አግዝፈው የሚነግሩን ቤኒቶ ሙሶሊኒም “ፒኮላ ሮማ” ወይም “ትንሿ ሮም” ሲል ያሞካሻት የኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ገብተናል ።
በቆይታችን ደግነትና ባህል አክባሪነት መገለጫው ሰዉን ያለልዩነት የሚወደው ቸርነት ከባህሪዉ የሆነው የአስመራ ህዝብ አለና ወደኋላም ከመነሻዋ ወደፊትም ከገፅታዋ መለስ ቀለስ እያልን በጎዳናዎቿ ሸር ብትን እንላለንና አብራችሁን ዝለቁ ።
ጥንት ከሁለት ሺህ ዓመት በላይ ታሪክ ያለዉ አዶሊስ በዝያን ጊዜ ከነበሩ ከታወቁ የተለያዩ ሃገሮች ጋር ትልቅ የንግድ ግንኙነት የነበረዉ፤ አዶላዉያን በዝያን ጊዜ እስከ ሕንድ አልፈዉ እስከ ቻይና ግንኙነት ያደርጉባት የነበረዉ የወደብ ከተማ ናት የሰሜን ፈርጧ አስመራ።
በአሥመራ በሠምበል አካባቢ የተገኘው የአርኪዮሎጂ ማስረጃ ከተማዋ ስያሜ በ 800 ዓ.ዓ. ይወስደናል ።
የኦና ባህል ተብሎ የሚጠራውን የአሥመራ ታሪክ በ 800 ዓ.ዓ. እና በኤርትራ ትግሪኛ ቃል ባሕላዊ ታሪክ መሠረት፣ በቀበሳ አምባ ላይ በአስመራ አካባቢ አራት ጎሳዎች ይኖሩ ነበር።
በዘመኑ ተበታትነው የነበሩት ገዛ ጉርቶም። ገዛ ሽሌሌ፣ ገዛ ሴሬንሰር እና ገዛ አስመኤ የተባሉ ግዛቶች ጎሳዎች በአንድነት በመሆን ከተማ በመመስረት "አርባተ አስመራ" የሚል ስም ሰጧት ይባላል ይህም አርባተ አስመራ ማለት በትግርኛ ቋንቋ 'አራቱ ጎሳዎች' ማለት ነው።
ከባህር ጠለል በላይ ከ2,300 ሜትር በላይ ከፍታ ላይ የምትገኝ ሲሆን ከአካባቢው ዝቅተኛ ቦታዎች ሙቀት ጋር የሚቃረን መለስተኛ የአየር ንብረት ያላት አስመራ ግብፆች፤ ቱርኮች፤ጣልያኖች እንጊሊዞች ተዋግተዉባታል። ከተማዋን የጎዳ ማንም ኃይል ግን አልነበረም ወዘናዋ ዛሬም በእርጋታ ተዉቦ ይገኛል ።
ከተማዋና ዙርያዋ ታሪክ ከ 2000 ዓመት ወደኋላ ይወስደናል 2000 አመታት በላይ ስልጣኔ የነበረዉ ታሪካዉ" መጠራ በለዉ ከለዉ" የተባለ በአፍሪቃዉ ቀንድ ላይ ለሚገኙ ሁለቱም ሃገሮች የሥነ-ጽሑፍ የተከሰተበት ታሪካዊ ቦታ ሲሆን በሃዉልቱ ላይ አናባቢ የሌለዉ የግዕዝ ጽሑፍ ሰፍሮ ይገኛል ።
ሰፊ ከተማ የነበረችዉ 17 ኪሎሜትር ስፋት የነበራት ቆሃይቶ እስከ ትልቅ የአፍሪቃ ከተማ ያደርጋታል። ከዚህም ባሻገር በአፍሪቃ እስልምናን ከተቀበሉት አካባቢዎች የመጀመርያዉ የሆነው ዳህላክኬሪስ
ጥንታዊ መቃብሮች ጥንታዊ የዉኃ ማጠራቀምያ ገንዳዎች መገልገያዎች አስመራና ዙርያዋ የረጂም ታሪክ እንዳላት ህያው እማኝ ይሆናሉ ።
ይሁንና የዛሬውን ገፅታ የያዘችው በጎርጎረሳዉያኑ 1930ዎቹ በቅኝ ግዛት ኤርትራን የያዘዉ ኢጣልያዊዉ ፋሺስት ሞሶሎኒ በምስራቅ አፍሪቃ ለሚያካሂደዉ የቅኝ ግዛት ዘመቻ ማዕከል እና መነሻ እንድትሆነዉ ዓይኑን ከጣለባት በኋላ ነበር ።
የጣልያንን መምጣት ተከትሎም አስመራ የምትባለዉ ትንሽ መንደር ሞቅ ደምቅ ማለት ጀመረች ። በአፍሪካ የመጀመሪያው የቴሌቪዥን ስርጭት ፣ የመጀመሪያው Am FM አጭር መካከለኛ ረጂም ሞገድ ራዲዮ ፣
የኤርትራ የባቡር መስመር በጊንዳ ከተማ በኩል በካርሎ ካቫና መሪነት ወደ ምጽዋ የባህር ዳርቻ የሚያመራ ሀዲድ ፣ ሲኒማ
ፋብሪካዎች በብዛት ተገንብተው በአፍሪካ ምድር ላይ የአውሮፓ ዘመናዊነት እውነተኛ ማሳያ ያደርጋታል ።
ሲኒማ ኢምፔሮ፣ የፊያት ታግሊየሮ አገልግሎት ጣቢያ እና የቅዱስ ጆሴፍ ካቴድራል ያሉ ታዋቂ ሕንፃዎች ለዚህ የፈጠራ ኃይል ምስክር ናቸው። ፊያት ታግሊየሮ፣ እንደ አውሮፕላን ለመነሳት ዝግጁ የሆነ አውሮፕላን ቅርጽ ያላቸው የተጠናከረ የኮንክሪት ክንፎቹ ያሉት፣ የዘመኑን የቴክኖሎጂ፣ የእድገት እና የፍጥነት ውበት ያለውን ማራኪነት መገለጫዎች ናቸው ።
ጋዜጠኛ ጆን ጉንተር እ.ኤ.አ. በ 1955 እንደገለጸው "ጣሊያኖች [አስመራን] እንደ ትሪፖሊ በጥሩ ሁኔታ እንደገነቧት ጽፏል።
በሚያማምሩ ሰፊ ጎዳናዎች ፣ ያጌጡ የህዝብ መገልገያ ሕንፃዎች እና የሥልጣኔ ምልክት የሆነው በከተማዋ የተገነባው ዘመናዊ የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓት ... የጣልያኖች የስራ ውጤት መሆኑን ጽፏል።
የኢጣሊያ መንግሥት በአስመራ እና በአስመራ ዙሪያ ባሉ አካባቢዎች በኢንዱስትሪ ልማት ላይ ኢንቨስት አድርጓል ።
ከሥነ ሕንፃዋ ባሻገር፣የጂኦሜትሪክ ዲሲፕሊን እና የሜዲትራኒያን ጸጋ ድብልቅ አሰራሯ አስመራን ልዩ ውበት ይሰጣታል ።
አስመራ ሙሉ በሙሉ በዘመናዊነት ሀሳብ ዙሪያ ለተቀረፀ የከተማ ፕላን ትታወቃለች፤ ሰፊ አውራ ጎዳናዎች፣ ሥርዓታማ ሰፈሮች፣ ለጋስ የሕዝብ ቦታዎች እና ቀልጣፋ መሠረተ ልማቶች የጣልያኖች የስራ ዉጤት የተመለከተው ፋሽስት ሞሶሎኒም በዝያን ጊዜ አስመራን አፍሪቃዊትዋ ትንሽዋ የሮም ከተማ ሲል አንቆለጳጽሷታል።
ሲኒማ ቤቶቹ ራሳቸዉ ድንቅ ናቸዉ ሲኒማ ኤንፔሮ፤ ሲኒማ ዳንቴ፤ ሲኒማ ካፒቶል፤ ሲኒማ ሮማ፤ ሲኒማ ኦዲዎን የሚባሉ ሲኒማ ቤቶች አሉ።ሁሉም ሲኒማ ቤቶች የተሰሩት በአዉሮጳ ደረጃ ነዉ። ሌሎቹ ሕንጻዎች ቡናማ ሰማያዊ አረንጓዴ ቀለም ያላቸዉ ሲሆኑ የአስመራ ቅድስተ ማርያም ቤተ ክርስትያን ዉብ ቪላ ቤቶች ፤ ፋብሪካዎች አስመራ የሚገኘዉ ትልቁ መስጊድ የመሳሰሉት ሁሉ የሚያማልሉ ናቸዉ።
ከተማዋ እድለኛ ከተማም ናት 30 እና 40 ዓመት ጦርነት ተካሂዶ ከተማዋ ምንም አልተጎዳችም ከተማዋን የጎዳ ኃይል የለም። በመጀመርያ ከተማ አስመራን በኦቶማን ኤምፓየር በሚባለዉ ዘመን ቱርኩች ያዙ፤ ከዝያ በኋላ ግብጾች ያዙ ከዝያ በኋላ ጣልያኖች ያዙ ከዝያ በኋላ እንጊሊዞች ያዙ። ይህ ሁሉ ትርምስ ሲካሄድ ግን ከተማዋ አልተጎዳችም ።
የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስ እና የባህል ድርጅት አስመራ የዓለም ቅርስ ሆና እንድትመዘገብ በፖላንድ ዋርሶ ባካሔደው ጉባዔ ላይ የአለማችን የመጀመርያዋ የቅርስ ከተማ ክብር መዝገብ አስፍሯታል ።
በአስመራ የሚገኙትና ቅኝ ግዛቱ ዘመን የተሰሩት ከ 50 በላይ ሕንፃዎች በሙሉ በዓለሙ መንግሥታት የቅርስ መዝገብ በመስፈራቸዉ ኤርትራ ጥንታዊና የባህል ቅሪቶች በሙሉ የተመዘገበላት ቀዳሚዋ የዓለም ሀገር ያደርጋታል ።
UNESCO ስለ ከተማዋ ሲገልፅ
«አስመራ በጣም ዉብ የሆነች ከተማ ናት። ከሁሉ ደግሞ ሕዝብዋ በዉስጥዋ እየኖረ ባህሉን እየጠበቀ ሥነ ሕንጻዉን እየጠበቀ በመሆኑ ነዉ። የአስመራ ሕንጻዎች ለየት ያለ ንድፍና ቅርስ የያዙ ናቸዉ። ጣልያኖቹ በቅኝ ግዛት ወቅት ሃገራቸዉ ዉስጥ የሌለ ነጻነት አስመራ ዉስጥ፤ ቅኝ ሃገር ዉስጥ ነጻነት ተሰምቶአቸዉ ፤ በምህንድስናዉ ረገድ አብዮት ያካሄዱ ይመስላል። ምክንያቱም ኢጣልያ ዉስጥ የማይገኘዉ ሕንጻ አስመራ ዉስጥ አለ።» ሲል ገልጿል ።
አስመራ ከተማ በኪነ ሕንጻ ብቻ ሳይሆን በጽዳትዋ ፤ በአየር ፀባይዋና በተለያዩ ሁኔታዎች ከአፍሪቃ የታወቁ ከተማ በመሆንዋ አስመራ በዓለሙ የቅርስ መዝገብ መመዝገብዋ ለኛ ለኢትዮጵያዉያን ለዓለም ሕዝብ ሁሉ ኩራት ነዉ ሲሉ የወቅቱ የበኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ገልጿል ።
አስመራ ሕያው ሙዚየም እና ሕያው የስልጣኔ ከተማ የአፍሪካን ዘመናዊነት ማሳያ የተረጋጋች እጅግ ማራኪ ብትሆንም ከተማዋ ከቱሪዝም ዘርፉ ተጠቃሚ አልሆነችም።
ሜሳረጊያዉን የባለቅኔዉን የሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ግጥም እንገባበዝና ለዛሬው ይብቃን ።
አስመራ
ምነው ሁሉ እንዳንቺ አስመራ
እንደ ከተሞች መዲና አቀያየሱ ቢጠራ
ያውራ ጎዳናሽ ጠለላ ፡
ሁሉን በአክናፉ እየጠራ
አስር ሰዓት ላይ ሲደራ
ለመንገደኛሽ መዝናኛ ፣ሲያጠላ ሲያብብ ሲያፈራ
ምነው ሁሉ እንዳንቺ አስመራ
አደባባይ ሲያነጥፉ
አድባራትና መስኪዱን ፣ ካቴድራሉን በየረድፉ
ገበያውን በየመልኩ ፣ እንደ አውታር እያሰለፉ
በወግ እየደረደሩ ፣በስምረት እያሰመሩ
በውበት እያዳበሩ ፣እያሳመሩ ቢያደሩ
በየክፍሉ በየበሩ በየመልኩ በየተራ
ፋኖሱን እንደ ደመራ
ቡና ቤቱን እንደ ሦራ
ምነው ሁሉ እንደ አንቺ አስመራ
እንደ ከተሞች መዲና አቀያየሱ ቢጠራ፡፡
እሳት ወይ አበባ (ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን )

Sponsored by
Surafel
8 months ago
በተራዘመዉ ጦርነት የፍልስጤም ክርስትያኖች 800 ብቻ ቀርተዋል !
ግብፅ በፍልስጤም የወደሙ መሳጂዶችን ዳግም ለመገንባት አዲስ አረብ ሀገራት የሚሳተፉበት የገቢ ማሰባሰብያ ለማዘጋጀት ቃል መግባቷ ተሰምቷል አብያተክርስቲያናቱን ግን እስካሁን ዳግም ለመስራት አልተገኘም ።
በአንድ ወቅት አለምአቀፋዊው ጳጳሳዊ ፋውንዴሽን በዓለማች 38 አገሮች ውስጥ ክርስቲያኖች ስቃይና በደል እንዲሁም መገለል እንደሚደርስባቸው ከሰባቱ መካከል አንዱ ስቃይ መከራና ስደት እንደሚዳረግ
በጥናት አረጋግጧል ። ጥናቱ እንደገለፀው ከሆነ ደግሞ ክርስቲያኖች የሚገፉት የእምነቱ መፍለቂያ ከተባለው መካከለኛው ምስራቅ ነዉ ከቀዳሚዎቹ ደግሞ ፍልስጤም ትጠቀሳለች ።
እስኪ ለዛሬው እንደሌሉ ተቆጥረው ልሳን ቸግሯቸዉ በሁለት ጉልበተኞች መሃል ተገኝተው ህልዉናቸዉ አደጋ ላይ ስለሚገኘው የፍልስጤም ክርስትያኖችና አብያተክርስቲያናት ጥቂት ልበል ።
ፍልስጤም በጥንታዊ እና በዘመናዊው የመካከለኛው ምስራቅ ታሪክ ውስጥ ታላቅ ሚና ያለው አንድ አነስተኛ ክልል ነው። ለበርካታ የዓለማችን ዋና ዋና እምነቶች ካለው ጠቀሜታ እና በአፍሪካ እና እስያ መካከል ጠቃሚ የሆነ አገናኝ ድልድይ የሆነ መልከዓ ምድራዊ አቀማመጥ ያለው በመሆኑ የፍልስጤም ታሪክ ተደጋጋሚ በሆነ ፖለቲካዊ ግጭት እና በአደገኛ የመሬት ወረራ የተሞላ ነው።
ይህ ሰርጥ ከግጭቱ በፊት በነበረ ቁጥራዊ መረጃ ከሆነ ሰፊውን ቁጥር የሚይዙት አረቦች ከዚህም ውስጥ በአብዛኛው የሱኒ ሙስሊም ሀይማኖት ተከታይ ቢሆንም ቅሉ ቀላል የማይባል አናሳ ክርስቲያኖች ይገኙበት ነበር።
የጋዛ ክርስቲያኖች ቁጥራቸው እምብዛም ባይሆንም እኒህ የጋዛ ክርስቲያኖች በቤተ-ክርስቲያኑ ዙሪያ ካለው መሬት ጋር ትልቅ ቁርኝት ስላላቸው ከጥንት እስከዛሬ እምነታቸው አስጠብቀው መዝለቅ ችለዉ ነበር ። ነገር ግን ከሁለት አመት በፊት አይ.ሁ..ዳዊ መሰረት ባላት እስራኤልና ከስሙ መነሻ ጀምሮ ለእስልምና እንደሚታገል የሚገልጸው ሃማስ ጦርነቱ ተቀሰቀሰ ።
በሀማስና እስራኤል በተራዘመ ጦርነት ምክንያት በ365 ስኩዌር ኪሎሜትር በ40 ኪሎሜትር የባህር እርዝማኔ ክልል ዉስጥ የምትገኘውን 2 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ይኖሩባታል የተባለችዉን ጋዛ ሰርጥ የምድር ገሀነም ሆነች ሁለቱም ፅንፍ በመያዝ አፀፋ በሚመላለሱበት ወቅት በሁለቱም ዘንድ በሰላይነት የተፈረጁ እነዚህን ክርስትያኖች እና የእምነት ተቋማት ከቁብ የሚቆጥር ጠፋ ።
እስራኤል " የሐማስን መሪዎች ላይ ያነጣጠረ " እያለች በምትፈፅማቸዉ ንፁሃንን ከታጣቂዎች ያለየ ጥቃትና በሰማይ የቦንብ ዶፍም ሆነ ሃማስ ሰላይ ናችሁ በማለት በሚያደርስባቸዉ ማህበራዊ መገለል መፈጠራቸውን እስኪጠሉ መከራ ገጠማቸው ።
በዓለም ላይ ካሉት ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናት አንዱ በዓለም ላይ ካሉት ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናት አንዱ እንደሆነ የሚታመነዉ በ400 ዓ.ም አካባቢ በቅዱስ ፖርፊየስ እራሱ ባሰራው ቤተክርስትያን መሰረት ላይ እንደታነፀ የሚነገርለት በአለም ላይ ካሉ ጥንታዊ አብያተ ክርስትያናት አንዱ የሆነዉ በአለም ሶስተኛው ጥንታዊ ቤተክርስትያን ወደመ ።
የክርስቶስ የልደት ስፍራ በሆነችው የፍልስጥኤም ግዛት የዌስት ባንክ ከተማ ቤቴልሄም እና በጋዛ ሰርጥ የሚገኙ ክርስቲያኖች የልደቱን በዓል እንዲያከብሩ ተከለከሉ ሌሎችም አብያተክርስቲያናት እንዳልነበሩ ሆኑ ።
ምንድነው ማስረጃዎችህ ከተባልኩ አለምአቀፋዊ ሚዲያዎችን መጥቀስና ዘገባዎችን ማስታወስ ይቻላል ።
ለአለም አቀፍ የወንጀል ችሎት (ICC) የወንጀል ምርመራ ሪፖርት እንደገለፁት ከአምስት በላይ አብያተ ክርስቲያናት የ150 ዓመታት ታሪክን መዛግብትን ጨምሮ ተጎድተዋል ወይም ወድመዋል። ሲል ገልፆታል ።
በጋዛ የባህል ዘርፍ መጥፋት፣ ቤተመጻሕፍት እና የባህል ቅርሶች በመውደማቸው እንዳስደነገጣቸው ባለሙያዎቹ ተናግረዋል። "የፍልስጤም ማህበረሰብ መሰረቱ ወደ ፍርስራሽነት እየተቀየረ ነው፣ እናም ታሪካቸው እየጠፋ ነው።" ብለዉታል ።
በአለፉት ሁለት ዓመታት የጋዛ አነስተኛ ክርስቲያኖች መካከል 550 የሚጠጉ ሰዎች ከቤታቸዉ ከቤተክርስቲያን ተፈናቅለው
የመቃብር ሥፍራዎች ለመኖር ተገደዋል. ሲል ፎክስ ኒዉስ ዘግቧል ።
በጋዛ የሚኖሩ ክርስቲያኖች እስራኤል የምትፈፅመው ሞትና ውድመት እንዲያበቃ በመጸለይ የገናን በዓል አክብረዋል። በዌስት ባንክ ከተማ ቤተልሔም የኢየሱስ የትውልድ ቦታ በርካቶች ጸሎታቸውን ያቀረቡ ሲሆን በእስራኤል “የዘር ማጥፋት” ሰለባዎችን በማስታወስ ፀሎት አድርገዋል። የሚለው ዘገባ የ ዋሽንግተን ፖስት ነዉ ።
በ2024 እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ከሚገኙት ሶስት አብያተ ክርስቲያናትን ሙሉ በሙሉ አፍርሳለች ሲል የግዛቱ ኢንዶውመንት ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ለአናዶሉ ተናግሯል።
ኢክራሚ አል ሙዳላል እንዳሉት የእስራኤል ጦር ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር ግንኙነት ያላቸውን 255 የሀይማኖት አባቶች እና መግደሉን እና ሌሎች 26 ሰዎችን ማሰሩን ተናግረዋል። ብሏል የአናዶሉ ዘገባ
" የአምልኮ ቦታዎች ላይ በፀጥታ ሃይሎች ላይ የሚፈፀመው ጥቃት ሁሉንም ቅድስናዎች፣አለም አቀፍ ህጎች እና የሰብአዊ መብት ህጎችን መጣስ ነው"ብለዋል።
በአውሮፓውያኑ 2024 ጥቅምት 19 አመሻሽ ገደማ ከእስራኤል የተወነጨፈ ሚሳዔል አንዱን የቤተ-ክርስቲያኑን ሕንፃ መታው። በጥቃቱ 18 ሰዎች ተገደሉ፤ በርካቶች ቆሰሉ።
ማሪያን እንደምትለው የ34 ዓመቱ የባሏ ወንድም ሶሊማን ልጆቹን ከሕንፃው ፍርስራሽ ሲከላከል ሕይወቱ አልፏል።
“በጣም አስፈሪ ነው። የሞተ ሰው አይቼ አላውቅም። ምን ማለት እንዳለበኝ አላውቅም። በጣም ፈጣን ሞት ነበር።”
ራሚ ታራዚ ደግሞ ሕንፃው በሚሳዔል ሲመታ በሥፍራው የነበረውን ሁኔታ ሲያስታውስ “ከባድ ሚሳዔል ነው። በጣም ትልቅ ከመሆኑ የተነሳ በሌላኛው ሕንፃ ውስጥ የነበሩ ሰዎች አቧሯ ለብሰው ነው የወጡት” ይላል።
የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ቤተ-ክርስቲያኑ በአቅራቢያው በነበረ የሐማስ ይዞታ ላይ በተሰነዘረ ጥቃት እንደተጎዳ አምኗል። የቢቢሲ ዘገባ ነበር ።
በቀድሞው ትዊተር በአሁኑ ኤክስ ላይ የተለጠፈ ቪድዮ፣ አንድ የእስራኤል ወታደር የወደቀ ሃይማኖታዊ ሕንፃን በእብራይስጥ ቋንቋ ሲያቆሽሽ አስመልክቷል።
ቢቢሲ ለእስራኤል መከላከያ ይህን ቪድዮ ልኮ አስተያየት ቢጠይቅም ምላሽ አላገኘም።
የለንደን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የአርኪዮሎጂ ተቋም ፕሮፌሰር የሆኑት ጆርጂያ አንድሪው፣ በጋዛ ሰርጥ ጉዳት የደረሰባቸውን ሕንፃዎች ሲያጠኑ ቆይተዋል።
ፕሮፌሰሯ እኒህ ሃይማኖታዊ ሥፍራዎች በጣም ትልቅ ታሪካዊ ጠቀሜታ አላቸው ይላሉ።
“[ጥቃቱ] ሰዎች ከእነዚህ ሕንፃዎች ጋር ያላቸውን ቁርኝት ለማጥፋት እንደተደረገ ሙከራ ነው መታየት ያለበት” የሚሉት ምሑሯ መሰል ውድመት አይተው እንደማያውቁ ይናገራሉ።
በአለም ሶስተኛው ጥንታዊ ቤተክርስትያን ነው ተብሎ የሚታሰበው በዉስጡ የያዛቸውን ታሪኮቹ ቅርስና መዛግብቶችን እንደያዘ ወደ አመድነት መቀየሩን ተከትሎም ።
የቤተ ክርስቲያኒቱ መሪዎችም ጉዳዩን በተመለከተ መግለጫ ያወጡ ሲሆን “የጋዛ ሕዝብ፣ በአያቶቻቸው ምድር ለትውልድ የኖሩ ቤተሰቦች፣ በግዞት መገደድ የለባቸውም፣ የተረፈውን ቤታቸውን፣ ቅርሶቻቸውን፣ እና የማንነታቸው መገለጫ በሆነው ምድር ላይ የመቆየት መብታቸውን ሊነጠቁ አይገባም” ሲሉ መናገራቸውን አልጀዚራ ዘገባ ያሳያል ።
የኢየሩሳሌም አብያተ ክርስቲያናት እንደ ክርስቲያን በጋዛ ሕዝብ ለሚደርስባቸው መከራ ግድየለሾች ሊሆኑ እንደማይችሉ "ወንጌል የሰውን ልጅ ሁሉ ክብር እንድንጠብቅ ያዘናልና።"
የአለም አቀፉ ማህበረሰብ በጋዛ ያለውን ሰብአዊ አደጋ ለመግታት አፋጣኝ እና ቆራጥ እርምጃ እንዲወስዱ ያሳስባሉ።
የሰው ልጅ ሕይወት ቅድስና እና መከላከያ የሌላቸውን የመጠበቅ የሞራል ግዴታ ከጥፋት እና ተስፋ መቁረጥ ይበልጡ። ተስፋ የቆረጡ ሰዎች አፋጣኝ ያልተገደበ ሰብዓዊ እርዳታ እንዲደረግ እንጠይቃለን።"ያሉት ኩስቶስ ብፁዕ አቡነ ፍራንቸስኮ ፓተን
"ልመናቸውን በእምነት እና በተስፋ መልእክት ሲያጠቃልሉ፣ የኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለሐዘን መጽናናት፣ ለቆሰሉት ፈውስ እና መከራ ቢደርስባቸውም በአገራቸው ለሚቀሩት ጽናትን ለማግኘት እንደሚፀልዩ ተናግረዋል ። በማለት የዘገበው ጀሩሳሌም ፖስት ነበር ።
እነዚህና ምናልባት በዝርዝር ብፅፋቸዉ አንባቢያን እንዳይሰለቹ የተዉኳቸዉ በሁለቱም ወገኖች በሀማስና እስራኤል በተራዘመ ጦርነት ምክንያት በ365 ስኩዌር ኪሎሜትር በ40 ኪሎሜትር የባህር እርዝማኔ ክልል ዉስጥ የምትገኘውን ጋዛ ሰርጥ ይኖሩ በነበሩ ክርስትያኖች ላይ የደረሱ ግፎች ናቸው ። ከዚህ ምስቅልቅል በኋላ ለወትሮው ጥቂት የነበረው የፍልስጤማውያን ክርስትያኖች ቁጥር አሽቆልቁሎ 800 ብቻ ቀርቷል ። እነዚህም የማምለኪያ ስፍራዎች ስለወደሙባቸዉ መቀጠላቸው ያጠራጥራል ሲል ያስነበበው ደግሞ አለምአቀፋዊ የክርስቲያን ህብረት ነዉ ።
( ታዴ የማመይ ልጅ በየኔታ ትዩብ )

9 months ago
አርኪዮሎጂስቶች በኢራቅ ጥንታዊ ከተማ አገኙ
የቅርስ ጥናት ባለሙያዎች በኢራቅ ኩርዲስታን ክልል ውስጥ ዕድሜው አምስት ሺህ ዓመት የሚገመት ጥንታዊ ከተማ አግኝተዋል።
የዱሆክ ገዥነት ቅርስና ቅርሶች ዳይሬክቶሬት ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ከሞሱል ግድብ የውሃ መጠን መቀነስ በኋላ ከተማይቱ በግልፅ ታይታለች።
ስፍራው የሄሌናዊው ዘመን (ከክርስቶስ ልደት በፊት 300 ዓመት) የሸክላ ሳጥኖች ያሉት ትልቁ የቀብር ቦታን አካቷል።
በአሁኑ ወቅትም የጥንት መቃብሮችን እና ታሪካዊ ቅርሶችን ለመታደግ አፋጣኝ የአርኪኦሎጂ ቁፋሮ እየተካሄደ ነው።
በተደረገው የመጀመሪያ ፍተሻ፣ ከነነዌ አምስተኛው ዘመን፣ ከቅድመ እና መካከለኛው የነሐስ ዘመን፣ ከሚታኒ እና ከኒዮ-አሦራውያን ዘመን የተገኙ የሸክላ ሥራዎች ተገኝተዋል።
በተጨማሪም ከሄሌናዊው ዘመን ጀምሮ እስከ እስላማዊው ዘመን ድረስ ያሉ ብዙ የሸክላ ስብርባሪዎች ተገኝተዋል።
ይህ ስፍራ በ1978 ዓ.ም የተከፈተው የሞሱል ግድብ ከተገነባ በኋላ በውሃ የተሸፈነ ሲሆን፣ በዚህ ዓመት የግድቡ የውሃ መጠን በእጅጉ በመቀነሱ ምክንያት እንደገና ታይቷል።
EBC

10 months ago
የፖላንድ ተመራማሪዎች በትግራይ በጥንታዊቷ የነጋሽ ከተማ የአርኪዮሎጂ ሥራቸውን ዳግም ጀመሩ
ስራው በጥንታዊው የነጋሽ ሰፈራ ላይ የሚያተኩር ሲሆን የአክሱም ፣አዲግራት እና የመቐለ ዩንቨርስቲ ተመራማሪዎችም በተበባሪነት ይሰራሉ።
የተወሰነ ሥራዎች ከተጀመሩ በኋላ ይህ ስራ በኮሮና ምክንያት መቋረጡ ይታወሳል።

11 months ago
ኦዛና ምኒልክ መፅሐፍ ተመረቀ
#ethiopia | በደራሲ ንጉሤ አየለ ተካ የተፃፈው፣ ከፍተኛ ምርምር የተደረገበት "ኦዛና ምኒልክ" የተሰኘ ድንቅ መፅሐፍ የ ቅዳሜ ሰኔ 28 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት በወመዘክር አዳራሽ ተመርቋል፡፡
ከዚህ ቀደም "ታላቁ ጥቁር" የተሰኘውን ከፍተኛ ተነባቢነትን ያገኘ በዳግማዊ ምኒልክ ዙሪያ ላይ ያተኰረ መፅሐፍ ፅፎ ለንባብ ያቀረበው ንጉሤ አየለ አሁን ደግሞ ከፍተኛ ምርምር በማድረግ "ኦዛና ምኒልክን" ለንባብ አብቅቷል፡፡
"ኦዛና ምኒልክ" ስለ ዳግማዊ ምኒልክ ያልተነገሩ ዕውነታዎችን በዝርዝር የሚያስረዳ ጥልቅ የምርምር ሥራ ሲሆን 460 ገፆችንም ይዟል፡፡ መፅሐፉ፣ ኢትዮጵያ ከ 125 ዐመት በፊት በአሜሪካ ጋዜጦች መልካም ገፅታ የያዘች አገር እንደነበረች የሚያስረዳ ሲሆን ሀጂ አብዱላሂን የመሰሉ የምኒልክ ተወካዮች ደብዳቤ ይዘው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ቴዎዶር ሩዝቬልት ዘንድ መቅረባቸውን ተንትኖ የሚያስረዳ ነው።
በዕለቱ የሥነ ሂስ አቅራቢ ደመላሽ አማረ በኦዛና ምኒልክ ላይ የመፅሐፍ ዳሰሳ ያቀረበ ሲሆን ስለ ዳግማዊ አፄ ምኒሊክም አጭር የድምፅ ዶኪመንተሪ ቀርቧል፡፡
የስታትስቲክስ ባለሙያ ወግ አዋቂው በኃይሉ ገብረመድኅንም ለዛ ባለው አቀራረብ የምኒሊክ ዘመን ላይ አጭር ዲስኩር አቅርቧል፡፡
የዕለቱ የክብር እንግዶች ጄነራል ካሣዬ ጨመዳ፣የሰው ዘር አመጣጥ ተመራማሪዎች ዶክተር ብርሀኔ አስፋው እና ዶክተር ዮናስ በየነ ሲሆኑ በተለይ የአርኪዮሎጂ አጥኚዎቹ ዶክተር ዮናስ እና ዶክተር ብርሀኔ ልዩ ክብር የተሰጣቸው ከመሆኑም በላይ በሙያቸው ላይም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ደራሲ ንጉሥ አየለ ተካ፣ ከተወዳጅ ሚድያ "ታላላቆችን እናክብር" የተሰኘውን ሽልማት በዕለቱ የተበረከተለት ሲሆን በመፅሀፍ ምረቃው እና ዝግጅቱ ላይ አስተዋፅዖ ላደረጉም ዕውቅና ተሰጥቷል፡፡
ደራሲ ንጉሤ አየለ ተካ ፣በታላላቅ ቤተ መፅሐፍት ውስጥ ጊዜውን በማሳለፍ አዳዲስ የታሪክ ዕውነቶችን ለመጀመሪያ ጊዜ ለአንባቢ ፅፎ ያቀረበ ሲሆን መኖሪያውንም በአሜሪካን አገር ያደረገ ነው።
ንጉሤ አየለ ተካ፣ ከዚህ ቀደም ሐኖስ ፣የገራዶ ዋሽንት፣ ጣዝማ እና ሌሎች 7 መፅሐፍትን ለንባብ ያበቃ ሲሆን በ1970ዎቹ አጋማሽ ከኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ- ፅሑፍ ክፍልም የተመረቀ ነው፡፡
የመፅሐፍ ምረቃ ሁነት ዝግጅቱ በተወዳጅ ሚድያና ኮምዩኒኬሽን እና በአቶ መሳፍንት አወቀ አስተባባሪነት የተሰናዳ ሲሆን መድረክ መሪውም ዕዝራ እጅጉ ነው።

ቁንጅና ከ 10,500 ዓመታት በፊት ቀረ !
ከዛሬ አስር ሽህ አምስት መቶ አመት በፊት ይኖሩ የነበረ የሴቶች ከዚህ ዘመን በተሻለ ዉብና ቆንጆ እንደነበሩ ታወቀ ።
በምዕራብ አውሮፓ ውስጥ በአሁኗ ቤልጂየም በሜሶሊቲክ ዘመን ከዛሬ 10,500 ዓመታት በፊት ትኖር ከነበረች ሴት አስከሬን አፅም ጥንታዊውን ዲኤንኤ በመጠቀም ፊቷን እንደገና በመገንባት ያጠኑት ተመራማሪዎች በሜሶሊቲክ ዘመን የነበሩት አብዛኞቹ ሰዎች ከዚህ ዘመን በበለጠ ቆንጆዎች እንደነበሩና ሲበዛ ጌጣጌጥ ተጠቃሚ ንቅሳት የሚነቀሱ ዉብ ቆዳ ሰማያዊ አይኖች እና ትንሽ ቀለል ያለ ቆዳ እንደነበራቸው ማረጋገጥ ችለናል ።ብለዋል
በዚህ በዲናንት በሚገኘው ማርጋውዝ ዋሻ ውስጥ በ1988-1989 በተደረገው የአርኪኦሎጂ ቁፋሮ ወቅት
የተገኘውን በዘመኑ የነበረች ሴት አስከሬን ዲኤንኤ በዘመናዊ መልኩ በቴክኖሎጂ እገዛ ባደረጉት ምርምር የጥንት ሴቶች የቆዳ ቀለም "በጣም የሚያስደንቅ ነበር" በጣም ጥሩ ጥራት ያለው አይን ጠንካራ የቅንድብ ሸንተረሮች ማራኪ ገፅታ እንደነበራቸዉ አረጋግጠናል ሲሉ እንደነገሩት የዘገበዉ CNN የዜና ወኪል ነዉ ።
በ1988-1989 በተደረገው የአርኪኦሎጂ ቁፋሮ ወቅት የተገኘውን የሴት የራስ ቅል በመነሳት ከ35 እስከ 60 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ እንደነበረች አረጋግጠናል ያሉት ተመራማሪዎች የቆዳ ቀለሟ፣የፀጉሯ ቀለም እና የአይን ቀለሟ በጥንታዊ ዲኤንኤ ላይ የተመሰረተ ሲሆን ሌሎች እንደ ጌጣጌጥነቷ እና ንቅሳትዋ ያሉ ንጥረ ነገሮች በሜኡዝ ወንዝ ተፋሰስ ውስጥ በተደረጉ ሌሎች ቁፋሮዎች በተገኙ የአርኪዮሎጂ መረጃዎች ላይ የተመሰረቱ ናቸው ይህም ገፅታዋን የእለት ተእለት ህይወቷን ምስል እንዲገነቡ እንዳስቻላቸዉ አስረድተዋል ።
የሜሶሊቲክ የመቃብር ቦታዎች በተመለከተም "አብዛኞቹ አፅሞች ከሥነ-ሥርዓት ወይም ተምሳሌታዊ ባህሪ ጋር በተቆራኘው መልኩ የተቀበሩ እንደነበሩ የገለፁት አርኪኦሎጂስት ኢዛቤል ደ ግሩቴ በዘመኑ አስከሬኖች በኦቾሎኒ ይታጠቡና ይረጭ ነበር" ሲል ተናግሯል ።
አክሎም "እነዚህ ግኝቶች ውስብስብ የቀብር ልማዶችን እናም ጥልቅ ማህበራዊ መዋቅር እና ባህላዊ ልምዶች እንደነበራቸው ያሳያል ይህም ለዚህ ዘመን የአኗኗር ልማድ ጥያቄዎችን ያስነሳል " ብሏል ።

Comments