Logo
FIDEL POST NEWS
በፖላንድ በመቶዎች የሚቆጠሩ አስከሬኖች ያሉበት "የቫምፓየር መቃብር" ተገኘ

​በፖላንድ ፒየን በተባለ ስፍራ በ17ኛው ክፍለ ዘመን እንደነበረ የሚታመንና በመቶዎች የሚቆጠሩ አስከሬኖችን የያዘ መቃብር በአርኪዮሎጂስቶች ተገኘ።

NTK እንደዘገበው ፣ በመቃብሩ ውስጥ ከ100 በላይ አስከሬኖች የተገኙ ሲሆን፣ አንዳንዶቹ አስከሬኖች "ተመልሰው እንዳይነሱ" በሚል እምነት በአንገታቸው ላይ ማጭድ ተደግኖባቸው፣ በእግራቸው ላይ ቁልፍ ታስሮባቸው ወይም በላያቸው ላይ ከባድ ድንጋይ ተጭኖባቸው ተገኝተዋል።

​በተለይም "ቫምፓየር ዞሲያ" የተሰኘችው ወጣት እና አንዲት ነፍሰ ጡር ሴት መቃብር የአርኪዮሎጂስቶቹን ትኩረት ስቧል።

ለ20 ዓመታት በቦታው ጥናት ያደረጉት ፕሮፌሰር ዳርዩስ ፖሊንስኪ እንደገለጹት፣ እነዚህ ሰዎች በወቅቱ በነበረው ጦርነትና በሽታ ምክንያት በህብረተሰቡ ዘንድ እንደ ስጋት የሚታዩና የተገለሉ ነበሩ።

​ይህ ግኝት በወቅቱ በነበረው የሰው ልጅ ስነ-ልቦና ውስጥ የነበረውን ጥልቅ የሞት ፍርሃት እና ከተፈጥሮ በላይ የሆኑ እምነቶችን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው ተብሏል።

​ምንጮች፦ Niezależna Telewizja Kablowa
2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.