Logo
Getu Temesgen
ኢትዮጵያ : የሰው ልጅ መገኛነቷን ዳግም ለዓለም አረጋገጠች
#ethiopia | ​ኢትዮጵያ አሁንም "የሰው ዘር መገኛ" መሆኗን በሳይንስ ዳግም አረጋገጠች።

በአፋር ስምጥ ሸለቆ በመካከለኛው አዋሽ (ሀሊቢ) አካባቢ በተደረገ የምርምር ፕሮጀክት፣ ከ100 ሺህ ዓመታት በፊት ይኖሩ የነበሩ የጥንታዊ ሆሞ ሳፒየንስ (Homo sapiens) ቅሪተ አካላት እና የድንጋይ መሣሪያዎች መገኘታቸውን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ይፋ አድርጓል።

ግኝቱ በአፍሪካ የሰው ዘር አመጣጥ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ክፍተት የነበረበትን ከ900,000 እስከ 200,000 ዓመታት ያለውን ጊዜ የሚዘክሩ አዳዲስ መረጃዎችን ይዟል።

ጥናቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ባለው የአሜሪካ የሳይንስ ጆርናል (PNAS) ላይ ዛሬ ታትሞ ወጥቷል።

በሺዎች የሚቆጠሩ የድንጋይ መሣሪያዎች መገኘታቸው፣ የሰው ልጅ የቴክኖሎጂ እድገት በወቅቱ ምን ይመስል እንደነበር ትልቅ ማሳያ ሆኗል።

​ በጥናቱ የተገኙ የእንስሳት ቅሪቶች (ጉሬዛ፣ ዝንጀሮ...) አፋር በወቅቱ ዛሬ እንደምናየው በረሃማ ሳይሆን ለምለምና ጫካማ እንደነበር ያረጋግጣሉ።

​በዶ/ር ዮናስ በየነ የተመራውና ከ24 ሀገራት የተውጣጡ ሳይንቲስቶች የተሳተፉበት ይህ ምርምር፣ ለሀገራችን የቱሪዝም ዘርፍና ለታሪክ ጥናት ትልቅ ግብዓት ነው።

​ኢትዮጵያ - የሰው ዘር ሁሉ ቤት!

​#getu #humanorigins #ethiopiacradleofmankind #archaeologynews #afardepression #homosapiens #scientificdiscovery #yonasbeyene #ethiopianheritage #አፋር #አርኪዮሎጂ #ኢትዮጵያ #የሰውዘርመገኛ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.