3 months ago
በኢትዮጵያ በየዓመቱ 41 ሺህ ህጻናት ከአፈጣጠር ችግር ጋር እንደሚወለዱ ተገለጸ፤ መፍትሄውስ ምን ይሆን?
#ethiopia | በኢትዮጵያ በየዓመቱ 41 ሺህ የሚጠጉ ህጻናት ከተለያዩ የአፈጣጠር የጤና ችግሮች ጋር እንደሚወለዱ የጤና ባለሙያዎች አስታወቁ። ከእነዚህ ችግሮች መካከል «ስፓይና ቢፊዳ» (Spina Bifida) እና ተያያዥነት ያለው የጭንቅላት ውስጥ ፈሳሽ መከማቸት ወይም «ሃይድሮሴፋለስ» (Hydrocephalus) በዋናነት ይጠቀሳሉ።
የሴንትራል መላ ሮተሪ ክለብ፣ ሪችአናዘር ፋውንዴሽን፣ አሊያንስ ፎር በርዝ ዲፌክት እና የጤና ሚኒስቴር በመተባበር «የአፈጣጠር ችግሮችን መቆጣጠርና መንከባከብ» በሚል ርዕስ ባዘጋጁት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ እንደተገለጸው፥ እነዚህ የጤና እክሎች ሕጻናትን ለዕድሜ ልክ የአካል ጉዳትና ብሎም ለሞት ያጋልጧቸዋል።
የችግሩ ዋነኛ መንስኤ ምንድነው?
ጥናቶች እንደሚያመለክቱት እስከ 70 በመቶ የሚሆነው የስፓይና ቢፊዳ (የአከርካሪ አጥንትና የህብለ ሰረሰር ክፍተት) ችግር የሚከሰተው በእናቶች የፎሊክ አሲድ (Folic Acid) እጥረት፣ በሌሎች ተጓዳኝ የጤና ችግሮች፣ እንዲሁም እናቶች በሚጠቀሟቸው አንዳንድ መድኃኒቶች ምክንያት ነው።
እንዴት መከላከል ይቻላል?
በመድረኩ ላይ የተገኙት የጤና ባለሙያዎች እና ፖሊሲ አውጪዎች የሚከተሉትን የመፍትሄ አቅጣጫዎች አስቀምጠዋል
* የአመጋገብ ዘይቤ፡ እድሜያቸው ከ15 እስከ 49 ዓመት የሆኑ ሴቶች በተፈጥሮ ፎሊክ አሲድ ያላቸውን ምግቦች ማዘውተር አለባቸው።
* ቅድመ ዝግጅት፡ እርግዝና ከማቀድ 3 ወራት በፊት ጀምሮ እና በእርግዝና ወቅት የፎሊክ አሲድ እንክብሎችን መውሰድ እጅግ አስፈላጊ ነው።
* የበለፀጉ ምግቦች፡ በፎሊክ አሲድ የበለፀጉ የስንዴ ዱቄቶችን እና ዘይቶችን መጠቀም ችግሩን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሰዋል።
ይህ አገር አቀፍ መድረክ፤ ከአፈጣጠር ችግር ጋር የሚኖሩ ህጻናትን የህይወት ጥራት ለማሻሻል የሚያስችሉ ስልቶች ላይ ጥልቅ ውይይት በማድረግ ተጠናቋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ethiopia #healthnews #ethiopianhealth #ministryofhealth #spinabifidaawareness #folicacid #healthypregnancy #addisababa #የጤናመረጃ #ኢትዮጵያ

4 months ago
በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ44 ሺህ በላይ ሕፃናት በነርቭ ዘንግ ክፍተትና በጭንቅላት ውስጥ ውሃ መከማቸት እንደሚጠቁ ተገለጸ
አሊያንስ ፎር በርዝ ዲፌክት (ABDI) ከሪች እናዘር ፋውንዴሽን እና ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ጋር በመተባበር ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
በስልጠናው ላይ እንደተገለጸው፣ በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ 44,000 በላይ ሕፃናት በነርቭ ዘንግ ክፍተት (Spina Bifida) እና በጭንቅላት ውስጥ ውሃ መከማቸት (Hydrocephalus) ተጠቂ ይሆናሉ።
የመከላከያ መንገዶች፡ እንደ ዱቄትና ዘይት ያሉ የምግብ ምርቶችን በፎሊክ አሲድ (Folic Acid) በማበልጸግ የነርቭ ዘንግ ክፍተትን እስከ 70% መቀነስ እንደሚቻል ተጠቁሟል።
የሕክምና ዕድል፡ ችግሩ ያለባቸው ሕፃናት በወቅቱ የቀዶ ጥገና ሕክምናና የረጅም ጊዜ ክትትል ካገኙ፣ የተሻለና ውጤታማ ሕይወት የመምራት ዕድል እንዳላቸው ተመላክቷል።
የሚዲያ ሚና፡ ጋዜጠኞች ስለ በሽታው መከላከልና ፈላጊዎች ሊያገኙት ስለሚገባው ድጋፍ ለህዝቡ ግንዛቤ በመፍጠር ረገድ ትልቅ ሚና እንዲጫወቱ ጥሪ ቀርቧል።
ዶ/ር ነብያት ተስፋዬ ምን አሉ?
የአሊያንስ ፎር በርዝ ዲፌክት መስራችና ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ነብያት ተስፋዬ እንደገለጹት፣ በቅንጅት በመስራት በእነዚህ የጤና እክሎች ምክንያት የሚመጡ አካል ጉዳቶችንና የጨቅላ ሕፃናትን ሞት መቀነስ ይቻላል።
ስለ ፎሊክ አሲድ ጠቃሚ መረጃዎች
ፎሊክ አሲድ ለሴሎች እድገትና ለፅንስ የነርቭ ሥርዓት ግንባታ ወሳኝ የሆነ የቢ-ቪታሚን (B9) አይነት ነው። አንዲት ሴት እርግዝና ከመከሰቱ ቢያንስ 3 ወራት በፊትና በእርግዝና የመጀመሪያዎቹ ወራት መውሰድ ይኖርባታል። እንደ አረንጓዴ ቅጠላቅጠል፣ ባቄላ፣ አተርና ብርቱካን ያሉ ምግቦች ተፈጥሯዊ የፎሊክ አሲድ ምንጮች ናቸው።
የገቢ ማሰባሰቢያ ጥሪ
ድርጅቱ በቀጣይ ግንቦት 8 ቀን 2018 ዓ.ም ለታቀደው ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችና መላው ማህበረሰብ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪውን አስተላልፏል።

የነርቭ ዘንግ ክፍተትና ፎሊክ አሲድ ላይ ለጋዜጠኞች ስልጠና ተሰጠ
📌 በየዓመቱ ከ44,000 በላይ ኢትዮጵያውያን ሕፃናት በነርቭ ዘንግ ክፍተትና በጭንቅላት ውስጥ ውሃ መከማቸት ይጠቃሉ!
#ethiopia | አሊያንስ ፎር በርዝ ዲፌክት (ABDI) ከሪች እናዘር ፋውንዴሽን እና ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ጋር በመተባበር በዛሬው እለት ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ስልጠና ሰጥቷል።
ስልጠናው ትኩረት ያደረገው በስፓይና ቢፊዳ (Spina Bifida) እና በሀይድሮሴፋለስ (Hydrocephalus) ዙሪያ ማህበረሰባዊ ግንዛቤን በመፍጠር ላይ ነው።
ምግቦችን በንጥረ-ነገር (በተለይም ፎሊክ አሲድ) በማበልጸግ የነርቭ ዘንግ ክፍተትን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ እንደሚቻል በስልጠናው መርሐግብር ላይ ተገልጿል።
ችግሩ ያለባቸው ሕፃናት ተገቢውን ቀዶ ጥገናና የረጅም ጊዜ ክትትል ካገኙ የተሻለ ሕይወት የመምራት ዕድል ያላቸው ሲሆን የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ማህበረሰቡ ስለ በሽታው መከላከልና ስለ ፈላጊዎች ድጋፍ እንዲረዳ ሚዲያ ትልቅ ሚና መጫወት እንዳለበት ተገልጿል።
የአሊያንስ ፎር በርዝ ዲፌክት መስራችና ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ነብያት ተስፋዬ እንደገለጹት፣ በጋራ በመስራት በኢትዮጵያ በእነዚህ የጤና እክሎች ምክንያት የሚመጡ አካል ጉዳቶችንና ሞትን መቀነስ እንደሚቻል ገልጸዋል።
በቀጣይ ግንቦት 8 ቀን 2018 ዓ.ም ለታቀደው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር የጋዜጠኞች ተሳትፎ እንዲጠናከር ጥሪ ቀርቧል።
#አሊያንስ_ፎር_በርዝ_ዲፌክት #ጤና #ኢትዮጵያ #spinabifida #hydrocephalus #abdi #folicacid #healthawareness #ethiopia

7 months ago
ፎሊክ አሲድ የነርቭ ዘንግ ክፍተትንና የጭንቅላት ውሃ ክምችትን እንደሚከላከል ተገለጸ
የነርቭ ዘንግ ክፍተት እና የጭንቅላት ውሃ ክምችት ህመሞችን በቂ የቫይታሚን B9 ወይም ፎሊክ አሲድ ከእርግዝና በፊት እንዲሁም በእርግዝና ወቅት በእናቲቱ ውስጥ እንዲኖር በማድረግ መከላከል ይቻላል ተባለ።
ሪች አናዘር ፋውንዴሽን፣ ከሮተሪ ሴንትራል መላ ክለብ፣ ከአሊያንስ ፎር በርዝ ዲፌክት እና ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የነርቭ ዘንግ ክፍተት እና ከልክ ያለፈ የጭንቅላት ውሃ ክምችት ቀንን አስመልክቶ በግዮን ሆቴል በተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐግብር በዛሬው እለት ተከብሯል።
የነርቭ ዘንግ ክፍተት ህመምን ለመከላከል ከሁሉ በፊት እርግዝናን ማቀድ ወሳኝ መሆኑ በመድረኩ የተገለጸ ሲሆን የፅንሱ የነርቭ ዘንግ እድገት የሚፈጠረው ፅንስ ከተፈጠረበት ቀን ጀምሮ እስከ 28ኛው ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ ስለሆነ፣ በዚህ ጊዜ ውስጥ በቂ የፎሊክ አሲድ ክምችት በእናት ደም ውስጥ መኖር እንዳለባት ተገልጿል።
“አክስለሬት አክሽን ፎር ስፓይና ቢፊዳ እና ሀይድሮሴፋለስ” በሚል በሚከበረው አለም አቀፍ በዓል ላይ ከተለያዩ የህክምና ተቋማት ከተውጣጡ በእናቶች እና ህፃናት ጤና ዙሪያ እያገለገሉ የሚገኙ 80 ባለሙያዎችን የሁለት ቀን የሙያ ማጎልበቻ ስልጠና በመስጠት የተጀመረ ሲሆን በዛሬውም እለት የሚዲያ አካላት አጋር ድርጅቶች እንዲሁም በችግሩ የተጠቁ ህፃናትና ወላጆቻቸው በተገኙበት ለባለሙያዎቹ የሰርትፍኬት አሰጣጥ ስነስርአት ተካሂዷል።
ሪች አናዘር ፋዉንዴሽን ፣ መሠል ስራወች ቀጣይ ትውልድ ጤናማ በመሆን ምርታማነቱን ለማረጋገጥ እ ንደሃገር የተያዘውን ራዕይ ለማሳካት የምናደርገውን ጥረት በእጅጉ ይደግፋል ብዬ አምናለሁ። በጋራ በመሆን በኢትዮጵያ ውስጥ የነርቭ ዘንግ ክፍተት እና የጭንቅላት ውሃ ክምችት በሽታን በመከላከል ላይ ዘላቂ ተጽእኖ መፍጠር እንደሚቻል በመርሐግብሩ ላይ ተገልጿል።

Sponsored by
Surafel
7 months ago
ፎሊክ አሲድን ከእርግዝና በፊት በመውሰድ የአከርካሪ አጥንት እና ሌሎች የነርቭ ዘንግ የአፈጣጠር ችግሮችን መከላከል ይገባል ተባለ
#fastmereja I “አክስለሬት አክሽን ፎር ስፓይና ቢፊዳ እና ሀይድሮሴፋለስ” በሚል መሪ ቃል የአለም አቀፍ ስፓይና ቢፊዳ እና ሀይድሮሴፋለስ ቀንን አስመልክቶ ሪች አናዘር ፋውንዴሽን፣ ከሮተሪ ሴንትራል መላ ክለብ፣ ከአሊያንስ ፎር በርዝ ዲፌክት እና ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለነርቭ ዘንግ ክፍተት ተጋላጭነታቸው ሰፊ የሆኑ እናቶችን ለይቶ ቀጣይ እርግዝናቸው የታቀደ በማድረግ ፎሊክ አሲድ መድሃኒትን ከእርግዝና በፊት እንዲያገኙ ተደራሽነቱን በማስፋት እና በማጠናከር ላይ ትኩረት በማድረግ የተሰሩ ስራዎችን ለመዳሰስ እንዲሁም በመከላከያ መንገዶች ዙሪያ ግንዛቤ ለማስጨበጥ እና ቀጣይነት ያለቸው ጅማሮችን ለማሳደግ ያለመ ፕሮግራም በጊዮን ሆቴል ተካሂዷል።
ይህ ዝግጅት የተለያዩ ከችግሩ ጋር ግንኙነት ያላቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የተካሄደ ሲሆን ንቅናቄው ከተለያዩ የህክምና ተቋማት ከተውጣጡ በእናቶች እና ህፃናት ጤና ዙሪያ እያገለገሉ የሚገኙ 80 ባለሙያዎችን የሁለት ቀን የሙያ ማጎልበቻ ስልጠና በመስጠት የተጀመረ ሲሆን በዛሬውም እለት የሚዲያ አካላት አጋር ድርጅቶች እንዲሁም በችግሩ የተጠቁ ህፃናትና ወላጆቻቸው በተገኙበት ለባለሙያዎቹ የሰርትፍኬት አሰጣጥ ስነስርአት ተካሂዷል::
ስፓይና ቢፊዳ የአከርካሪ አጥንት እና የነርቭ ዘንግ አፈጣጠር ጋር ተያይዞ የሚከሰት ችግር ሲሆን የአካል እና የአእምሮ እድገት ውስንነቶችን ጨምሮ የዕድሜ ልክ አካል ጉዳተኝነትን ሊያስከትል ይችላል። በሽታው በሺዎች የሚቆጠሩ ህጻናትን በየዓመቱ የሚጎዳ ሲሆን ቅድመ መከላከል ለነገ የማይተው አስፈላጊ ስራ ነው::
ፎሊክ አሲድን በእንክብል መልክ ከእርግዝና በፊት መውሰድ የአከርካሪ አጥንት እና ሌሎች የነርቭ ዘንግ እንዲሁም ተያያዣነት ያላቸውን የአፈጣጠር ችግሮችን ለመቀነስ የተረጋገጠ ሳይንሳዊ መፍትሄ ሲሆን በርካታ ሃገራት ይህንን በመተግበር የአፈጣጠር ችግሮችን በእጅጉ ቀንሰዋል።
#ጤና