Logo
Getu Temesgen
የነርቭ ዘንግ ክፍተትና ፎሊክ አሲድ ላይ ለጋዜጠኞች ስልጠና ተሰጠ

📌 በየዓመቱ ከ44,000 በላይ ኢትዮጵያውያን ሕፃናት በነርቭ ዘንግ ክፍተትና በጭንቅላት ውስጥ ውሃ መከማቸት ይጠቃሉ!
#ethiopia | አሊያንስ ፎር በርዝ ዲፌክት (ABDI) ከሪች እናዘር ፋውንዴሽን እና ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ጋር በመተባበር በዛሬው እለት ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ስልጠና ሰጥቷል።

ስልጠናው ትኩረት ያደረገው በስፓይና ቢፊዳ (Spina Bifida) እና በሀይድሮሴፋለስ (Hydrocephalus) ዙሪያ ማህበረሰባዊ ግንዛቤን በመፍጠር ላይ ነው።

ምግቦችን በንጥረ-ነገር (በተለይም ፎሊክ አሲድ) በማበልጸግ የነርቭ ዘንግ ክፍተትን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ እንደሚቻል በስልጠናው መርሐግብር ላይ ተገልጿል።

ችግሩ ያለባቸው ሕፃናት ተገቢውን ቀዶ ጥገናና የረጅም ጊዜ ክትትል ካገኙ የተሻለ ሕይወት የመምራት ዕድል ያላቸው ሲሆን የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ማህበረሰቡ ስለ በሽታው መከላከልና ስለ ፈላጊዎች ድጋፍ እንዲረዳ ሚዲያ ትልቅ ሚና መጫወት እንዳለበት ተገልጿል።

የአሊያንስ ፎር በርዝ ዲፌክት መስራችና ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ነብያት ተስፋዬ እንደገለጹት፣ በጋራ በመስራት በኢትዮጵያ በእነዚህ የጤና እክሎች ምክንያት የሚመጡ አካል ጉዳቶችንና ሞትን መቀነስ እንደሚቻል ገልጸዋል።

በቀጣይ ግንቦት 8 ቀን 2018 ዓ.ም ለታቀደው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር የጋዜጠኞች ተሳትፎ እንዲጠናከር ጥሪ ቀርቧል።
#አሊያንስ_ፎር_በርዝ_ዲፌክት #ጤና #ኢትዮጵያ #spinabifida #hydrocephalus #abdi #folicacid #healthawareness #ethiopia

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.