30 days ago
የስፓይና ቢፊዳ እና ሃይድሮሴፋለስ ታካሚ ህጻናትን ህይወት ለመለወጥ የሚደረግ ጥረት
#ethiopia | በኢትዮጵያ በአመት ከ14 ሺህ እስከ 50 ሺህ የሚደርሱ ህጻናት የስፓይና ቢፊዳ እና የሃይድሮሴፋለስ የፅንስ አፈጣጠር እክል ገጥሟቸው ይወለዳሉ።
ይህንን ከፍተኛ የማህበረሰብ እና የጤና ችግር ለመቅረፍ እንዲሁም የተጠቁ ህጻናትን እና ወላጆቻቸውን ለመደገፍ ሰፊ ህዝባዊ እና መንግስታዊ ንቅናቄ እንደሚያስፈልግ የዘርፉ ባለሙያዎች እና የእንቅስቃሴው መሪዎች ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
የማያ በጎ አድራጎት ድርጅት መስራችና ስራ አስኪያጅ፣ የህግ ባለሙያና ጋዜጠኛ ጠበቃ አበባው አበበ እንደሚገልፁት፣ የስፓይና ቢፊዳ እና ሃይድሮሴፋለስ ችግሮች በዋናነት እናቶች በእርግዝና ወቅት ከሚያጋጥማቸው የቫይታሚን B9 ወይም የፎሊክ አሲድ እጥረት ጋር የተያያዙ ናቸው።
ችግሩን ከስሩ ለማስቀረት እና የወደፊት ትውልድን ለመጠበቅ መንግስት የፎሊክ አሲድ እና የቫይታሚን B9 ማበልፀጊያ በምግብ ምርቶች፣ በተለይም በጨው፣ ዘይት እና ዱቄት ላይ አስገዳጅ ሆኖ እንዲካተት ህግ ማውጣቱ ትልቅ የፖሊሲ እርምጃ ነው።
ቀደም ሲል የእንግርት (ጎይተር) በሽታን በጨው ውስጥ አዮዲን በመጨመር መከላከል እንደተቻለው ሁሉ፣ አሁንም ጨውን በፎሊክ አሲድ በማበልፀግ የስፓይና ቢፊዳ በሽታን ዘላቂ በሆነ መንገድ መከላከል እንደሚቻል ጠበቃ አበባው አስረድተዋል።
በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህጻናት የነርቭ ዘንግ ህክምና ክፍል ባለሙያ እና የ"አሊያንስ ፎር ባርዝ ዲፌክትስ" ድርጅት መስራች የሆኑት ዶክተር ነቢያት ተስፋዬ በበኩላቸው፣ ራሳቸው ከስፓይና ቢፊዳ እክል ጋር ተወልደውና በህክምና አልፈው ዛሬ ላይ ሀኪም በመሆን በርካቶችን እያገለገሉ ይገኛሉ።
ዶክተር ነቢያት እንደሚሉት፣ የነርቭ ዘንግ እድገት እናት እርጉዝ መሆኗን ሳታውቅ በ28 ቀናት ውስጥ ተጠናቆ ስለሚያልፍ፣ ከእርግዝና በፊት የፎሊክ አሲድ እጥረትን መቅረፍ ወሳኝ ነው። የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጥናት እንደሚያሳየው ከ50 በመቶ በላይ የሚሆኑ በወሊድ እድሜ ላይ ያሉ ሴቶች የፎሊክ አሲድ እጥረት አለባቸው።
አሁን ላይ መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የጨው፣ የስንዴ እና የዘይት አምራቾች ምርቶቻቸውን ማበልፀግ የጀመሩ ሲሆን፣ በተለይም ከ95 በመቶ በላይ ህብረተሰብ የሚጠቀመውን ጨው በፎሊክ አሲድ የማበልፀግ ስራ በሚቀጥለው አንድ አመት ውስጥ በሰፊው ገበያ ላይ ይውላል።
ከቅድመ መከላከል ጎን ለጎን አሁን በህይወት ያሉ ህጻናት የሚያጋጥሟቸውን ሁለገብ ፈተናዎች መፍታት ሌላው ዋና ትኩረት ሊሆን እንደሚገባ ሁለቱም ባለሙያዎች ያሰምሩበታል።
እነዚህ ህጻናት የእንቅስቃሴ እክል እና የሽንትና ሰገራ የመቆጣጠር ችግር ስለሚያጋጥማቸው በትምህርት ቤቶች፣ በህክምና ተቋማት እና በመሰረተ ልማቶች አካባቢ ተገቢውን ድጋፍ አያገኙም። በአሁኑ ወቅት በርካታ ትምህርት ቤቶች ግንዛቤ በማጣታቸው እና ተንከባካቢ ባለሙያ ባለመኖሩ ምክንያት እነዚህን ህጻናት የመቀበል ፍላጎት እንደሌላቸው እናቶች አቤቱታ ያቀርባሉ።
ይህንን ችግር ለመቅረፍ የማያ በጎ አድራጎት ድርጅት ለህጻናቱ የፊዚዮቴራፒ አገልግሎት ያካተተ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመክፈት ህልም እንዳለው ጠበቃ አበባው አበበ ገልፀዋል።
ይህ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ህጻናቱ ትምህርት የሚያገኙበት እና እንቅስቃሴያቸውን የሚያሻሽሉበት ብቻ ሳይሆን፣ እናቶችም ልጆቻቸውን በታማኝ ቦታ አስቀምጠው ወደ ስራ በመሰማራት በኢኮኖሚ ራሳቸውን እንዲችሉ የሚያስችል ነው።
በተመሳሳይ መልኩ ዶክተር ነቢያት ተስፋዬ እንደሚያስረዱት፣ ከ"ፐርኪንስ ኤንድ አዘርስ ፋውንዴሽን" እና ከ"ኢፖስ" (EPOS) የመልሶ ማቋቋም ተቋማት ጋር በመተባበር ለህጻናቱ ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎችን፣ ዊልቼሮችን እና ክራንቾችን የማቅረብ ስራ እየተሰራ ይገኛል።
በመጨረሻም፣ ሁለቱም ባለሙያዎች የስፓይና ቢፊዳ እና ሃይድሮሴፋለስ ያለባቸው ህጻናት አዕምሯቸው ሙሉ በሙሉ ጤናማ እና በትምህርታቸው በጣም ጎበዞች መሆናቸውን ገልፀው፣ የትምህርት ሚኒስቴር፣ የጤና ሚኒስቴር፣ መገናኛ ብዙሃን፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ባለሀብቶች በጋራ በመቆም የህጻናቱን የመማር መብት ሊያስከብሩ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።
መገናኛ ብዙሃን ህብረተሰቡን በማንቃት ረገድ የመሪነቱን ሚና እንዲጫወቱና ችግሩ የአንድ ቤተሰብ ብቻ ሳይሆን የሀገር ችግር መሆኑ ተይዞ የተቀናጀ ድጋፍ እንዲደረግ አሳስበዋል።
ማያ የበጎ አድራጎት ድርጅት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ፣ ከኢቻ ፉድ ኮምፕሌክስ እና ከክሊን ማቴሪያልስ ጋር በመተባበር በግዮን ሆቴል ባካሄደው መርሀግብር ለ100 አባላቱ የአዲስ አመት የማዕድ ማጋራት መርሐግብር አካሂዷል።
ጌትነት ተመስገን
📷 ሲሳይ ጉዛይ
#spinabifida #hydrocephalus
#spinabifidaawareness #folicacid
#foodfortification #birthdefects#healthethiopia #mayacharity

6 months ago
ማያ በጎ አድራጎት ድርጅት በህፃናት የአፈጣጠር ችግር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ
#ethiopia | የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ከማያ የበጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር በአፈጣጠር ችግር ምክንያት በሚከሰቱ የጀርባ አጥንት ክፍተት (Spina Bifida) እና የአንጎል ውስጥ ፈሳሽ መከማቸት (Hydrocephalus) ዙሪያ ያተኮረ ልዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር በአዲስ አበባ አካሂዷል።
በመድረኩ ላይ እንደተገለጸው በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ44 ሺህ በላይ ህፃናት በእነዚህ የጤና ችግሮች ምክንያት የሚወለዱ ሲሆን፣ ለችግሩ ዋነኛው መንስኤ እናቶች በእርግዝና ወቅት የሚገጥማቸው የፎሊክ አሲድ ወይም የቫይታሚን ቢ9 እጥረት መሆኑ በሰፊው ተብራርቷል።
እነዚህ የአፈጣጠር ችግሮች በህፃናቱ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ሲሆን፣ በተለይም ለዕድሜ ልክ የሚዘልቅ የመንቀሳቀስ መገደብ እና ራስን ችሎ የመፀዳዳት ችግር እንደሚገጥማቸው ተመላክቷል።
ይህንን ችግር በዘላቂነት ለመከላከል በመንግስት የተጀመረው ምግቦችን በፎሊክ አሲድ የማበልጸግ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የተገለጸ ሲሆን፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩም ይህንን ሀገራዊ ጥረት በግለሰብ፣ በማህበረሰብ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ለማገዝ ያለመ እንደሆነ ተጠቁሟል።
በመድረኩ ላይ የአካቶ ትምህርት እና የዜጎች ተጠቃሚነት ጉዳይም በስፋት የተነሳ ሲሆን፣ በእነዚህ የጤና ችግሮች የተጠቁ ህፃናት የማህበረሰቡ አካል መሆናቸው ታምኖበት ትምህርትን ጨምሮ ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶችን የማግኘት መብታቸው ሊከበር እንደሚገባ ጥሪ ቀርቧል።
መርሃ ግብሩ በእነዚህ ህፃናት ሰብአዊ መብት እና ማህበራዊ ተሳትፎ ዙሪያ ሰፊ ውይይት ያደረገ ሲሆን፣ ህብረተሰቡ ለችግሩ ተጋላጭ የሆኑ ወገኖችን ከመገለል እንዲታደግና አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ አሳስቧል።
በዚህ መርሃ ግብር ላይ የፌዴራል ጤና ሚኒስቴር ፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ፣ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና የማያ በጎ አድራጎት ድርጅት መስራቾች አስተባባሪዎች ተገኝተዋል።
ከእነዚህም በተጨማሪ የጥበብ ባለሙያዎች፣ የሚዲያ አካላት፣ እንዲሁም የችግሩ ተጋላጭ የሆኑ ህፃናትና ወላጆቻቸው በመሳተፍ ስለ በሽታው መከላከያ መንገዶች እና ስላለው ተግዳሮት በቂ ግንዛቤ እንዲጨበጥ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ አበርክተዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#healthawareness #ethiopia #spinabifida #hydrocephalus #mayacharitableorganization #publichealth #folicacid #inclusion #addisababa

7 months ago
በኢትዮጵያ በየዓመቱ 41 ሺህ ህጻናት ከአፈጣጠር ችግር ጋር እንደሚወለዱ ተገለጸ፤ መፍትሄውስ ምን ይሆን?
#ethiopia | በኢትዮጵያ በየዓመቱ 41 ሺህ የሚጠጉ ህጻናት ከተለያዩ የአፈጣጠር የጤና ችግሮች ጋር እንደሚወለዱ የጤና ባለሙያዎች አስታወቁ። ከእነዚህ ችግሮች መካከል «ስፓይና ቢፊዳ» (Spina Bifida) እና ተያያዥነት ያለው የጭንቅላት ውስጥ ፈሳሽ መከማቸት ወይም «ሃይድሮሴፋለስ» (Hydrocephalus) በዋናነት ይጠቀሳሉ።
የሴንትራል መላ ሮተሪ ክለብ፣ ሪችአናዘር ፋውንዴሽን፣ አሊያንስ ፎር በርዝ ዲፌክት እና የጤና ሚኒስቴር በመተባበር «የአፈጣጠር ችግሮችን መቆጣጠርና መንከባከብ» በሚል ርዕስ ባዘጋጁት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ እንደተገለጸው፥ እነዚህ የጤና እክሎች ሕጻናትን ለዕድሜ ልክ የአካል ጉዳትና ብሎም ለሞት ያጋልጧቸዋል።
የችግሩ ዋነኛ መንስኤ ምንድነው?
ጥናቶች እንደሚያመለክቱት እስከ 70 በመቶ የሚሆነው የስፓይና ቢፊዳ (የአከርካሪ አጥንትና የህብለ ሰረሰር ክፍተት) ችግር የሚከሰተው በእናቶች የፎሊክ አሲድ (Folic Acid) እጥረት፣ በሌሎች ተጓዳኝ የጤና ችግሮች፣ እንዲሁም እናቶች በሚጠቀሟቸው አንዳንድ መድኃኒቶች ምክንያት ነው።
እንዴት መከላከል ይቻላል?
በመድረኩ ላይ የተገኙት የጤና ባለሙያዎች እና ፖሊሲ አውጪዎች የሚከተሉትን የመፍትሄ አቅጣጫዎች አስቀምጠዋል
* የአመጋገብ ዘይቤ፡ እድሜያቸው ከ15 እስከ 49 ዓመት የሆኑ ሴቶች በተፈጥሮ ፎሊክ አሲድ ያላቸውን ምግቦች ማዘውተር አለባቸው።
* ቅድመ ዝግጅት፡ እርግዝና ከማቀድ 3 ወራት በፊት ጀምሮ እና በእርግዝና ወቅት የፎሊክ አሲድ እንክብሎችን መውሰድ እጅግ አስፈላጊ ነው።
* የበለፀጉ ምግቦች፡ በፎሊክ አሲድ የበለፀጉ የስንዴ ዱቄቶችን እና ዘይቶችን መጠቀም ችግሩን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሰዋል።
ይህ አገር አቀፍ መድረክ፤ ከአፈጣጠር ችግር ጋር የሚኖሩ ህጻናትን የህይወት ጥራት ለማሻሻል የሚያስችሉ ስልቶች ላይ ጥልቅ ውይይት በማድረግ ተጠናቋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ethiopia #healthnews #ethiopianhealth #ministryofhealth #spinabifidaawareness #folicacid #healthypregnancy #addisababa #የጤናመረጃ #ኢትዮጵያ

8 months ago
የነርቭ ዘንግ ክፍተትና ፎሊክ አሲድ ላይ ለጋዜጠኞች ስልጠና ተሰጠ
📌 በየዓመቱ ከ44,000 በላይ ኢትዮጵያውያን ሕፃናት በነርቭ ዘንግ ክፍተትና በጭንቅላት ውስጥ ውሃ መከማቸት ይጠቃሉ!
#ethiopia | አሊያንስ ፎር በርዝ ዲፌክት (ABDI) ከሪች እናዘር ፋውንዴሽን እና ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ጋር በመተባበር በዛሬው እለት ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ስልጠና ሰጥቷል።
ስልጠናው ትኩረት ያደረገው በስፓይና ቢፊዳ (Spina Bifida) እና በሀይድሮሴፋለስ (Hydrocephalus) ዙሪያ ማህበረሰባዊ ግንዛቤን በመፍጠር ላይ ነው።
ምግቦችን በንጥረ-ነገር (በተለይም ፎሊክ አሲድ) በማበልጸግ የነርቭ ዘንግ ክፍተትን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ እንደሚቻል በስልጠናው መርሐግብር ላይ ተገልጿል።
ችግሩ ያለባቸው ሕፃናት ተገቢውን ቀዶ ጥገናና የረጅም ጊዜ ክትትል ካገኙ የተሻለ ሕይወት የመምራት ዕድል ያላቸው ሲሆን የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ማህበረሰቡ ስለ በሽታው መከላከልና ስለ ፈላጊዎች ድጋፍ እንዲረዳ ሚዲያ ትልቅ ሚና መጫወት እንዳለበት ተገልጿል።
የአሊያንስ ፎር በርዝ ዲፌክት መስራችና ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ነብያት ተስፋዬ እንደገለጹት፣ በጋራ በመስራት በኢትዮጵያ በእነዚህ የጤና እክሎች ምክንያት የሚመጡ አካል ጉዳቶችንና ሞትን መቀነስ እንደሚቻል ገልጸዋል።
በቀጣይ ግንቦት 8 ቀን 2018 ዓ.ም ለታቀደው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር የጋዜጠኞች ተሳትፎ እንዲጠናከር ጥሪ ቀርቧል።
#አሊያንስ_ፎር_በርዝ_ዲፌክት #ጤና #ኢትዮጵያ #spinabifida #hydrocephalus #abdi #folicacid #healthawareness #ethiopia

Sponsored by
Surafel
Comments