17 days ago
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) በዳሬሰላም፣ ታንዛኒያ እየተካሄደ በሚገኘው የ2027 የቶታል ኢነርጂስ ካፍ ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ውድድር፣ ወደ ግማሽ ፍጻሜው የተቀላቀሉት አራቱ ብሔራዊ ቡድኖች ታውቀዋል።
ባለፈው ቅዳሜ በተደረጉ ጨዋታዎች ታንዛኒያ፣ ዩጋንዳ እና ሱዳን ወደ ግማሽ ፍጻሜው ማለፋቸውን ሲያረጋግጡ፣ ከሁለት ቀናት በፊት ማለፏን ካረጋገጠችው ብሩንዲ ጋር ተቀላቅለዋል።
በታንዛኒያ ኡሁሩ ስታዲየም በተደረገው የምድብ ሐ (ግሩፕ ሲ) የመጀመሪያ ጨዋታ፣ ኬንያ ከደቡብ ሱዳን ጋር ተጫውታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይታለች። በ26ኛው ደቂቃ ላይ ጆናታን አጁንግ ደቡብ ሱዳንን ቀዳሚ ቢያደርግም፣ ብራይተን ናቼሪ በጭማሪ ሰዓት ባስቆጠራት ግብ ኬንያን ከአቻ ውጤት ታድጓል። ይሁን እንጂ ሁለቱም ቡድኖች በምድባቸው አንድ አንድ ነጥብ ብቻ ይዘው በማጠናቀቃቸው ከውድድሩ ተሰናብተዋል።
የዚህ የመጀመሪያ ጨዋታ በአቻ ውጤት መጠናቀቅ እያንዳንዳቸው ሦስት ነጥብ ይዘው የነበሩትን እና ቀጣዩን ጨዋታ ሊያደርጉ የነበሩትን ዩጋንዳን እና ሱዳንን ኳስ ሳይነኩ በቀጥታ ወደ ግማሽ ፍጻሜው እንዲያልፉ አድርጓቸዋል። ቆየት ብሎ በተደረገው የእርስ በእርስ ጨዋታ፣ ዩጋንዳ ሱዳንን 1 ለ 0 በማሸነፍ በአሰልጣኝ ላርዬ ኪንግስተን የሚመራው ቡድን መቶ በመቶ የማሸነፍ ክብረ ወሰኑን ጠብቆ ምድቡን በአንደኝነት አጠናቋል። ለዩጋንዳ ብቸኛዋን የማሸነፊያ ግብ ተቀይሮ የገባው አሙር ሙኖጌራ አስቆጥሯል።
በዕለቱ የመጨረሻ ጨዋታ አዘጋጇ ታንዛኒያ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ቡድን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፋለች። ባሺሪ ሳሉም ኪባይላ በመጀመሪያው አጋማሽ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር፣ ጁማ ሳግዌ ደግሞ በሁለተኛው አጋማሽ ተጨማሪ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር 'ንጎሮንጎሮ ቦይስ' የተሰኘውን የታንዛኒያ ቡድን አሸናፊ አድርገዋል።
ከፍተኛ ፉክክር እንደሚታይባቸው የሚጠበቁት የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ማክሰኞ የሚካሄዱ ሲሆን፣ ዩጋንዳ ከሱዳን እንዲሁም ታንዛኒያ ከብሩንዲ ይፋለማሉ። ለፍጻሜ የሚያልፉት ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች በ2027ቱ የቶታል ኢነርጂስ ካፍ ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ (AFCON) ላይ በቀጥታ የሚሳተፉ ይሆናል።

20 days ago
ኮቺ (Kochi / Cochin)
- የሕንድ “የአረቢያ ባሕር ንግሥት”
(Queen of the Arabian Sea)
የጉዞ ማስታወሻ ( ክፍል 16 )
— ኮቺ፣ ሕንድ
#ethiopia | በደቡብ ምዕራብ ሕንድ በኬረላ (Kerala) ግዛት የምትገኘው ኮቺ (Kochi)—በቀደመው መጠሪያዋ ኮቺን (Cochin)—በታሪክ፣ በባህል፣ በንግድ እና በዘመናዊ የቴክኖሎጂ ዕድገቷ የምትታወቅ የሕንድ ቁልፍ የባሕር በርና የወደብ ከተማ ናት።
“የአረቢያ ባሕር ንግሥት” (Queen of the Arabian Sea) በሚል የክብር ስም የምትጠራው ይህች ከተማ ለዘመናት የቅመማ ቅመም ንግድ ማዕከል በመሆን ዓለም አቀፍ ነጋዴዎችን ስትስብ ቆይታለች።
ኮቺን ለመጎብኘት የመጣ ተጓዥ አንድ ከተማ ብቻ እንዳልጎበኘ ይሰማዋል። እዚህ ታሪክና ዘመናዊነት፣ ባህልና ንግድ፣ ባሕርና የውሃ መንገዶች፣ የቅኝ ግዛት ዘመን ሕንፃዎችና የዘመኑ የከተማ ሕይወት በአንድ ላይ ተዋህደው ይታያሉ።
ኮቺ (Kochi) ወይም ኮቺን (Cochin) በሕንድ ኬራላ ግዛት የምትገኝ ታሪካዊ የወደብ ከተማ ስትሆን፣ የኬራላ የንግድ ማዕከል በመሆን ትታወቃለች። “የአረቢያ ባሕር ንግሥት” በሚል ስያሜም ትጠራለች። ለዘመናት ከእስያና ከአውሮፓ የመጡ ነጋዴዎችና መርከቦች ወደዚህ ወደብ ይመጡ ነበር።
የቅመማ ቅመም ንግድ ከተማ
ኮቺን ለመረዳት የኬራላን የቅመማ ቅመም ታሪክ ማወቅ ያስፈልጋል። ኬራላ በበርበሬ፣ ካርዳሞም፣ ቅርንፉድ፣ ቀረፋ፣ ዝንጅብልና ሌሎች ቅመማ ቅመሞች ትታወቃለች። ኮቺ ደግሞ በዚህ የቅመማ ቅመም ንግድ ውስጥ ዋና የማሰባሰቢያና የመላኪያ ማዕከል ሆና ቆይታለች።
በተለይ Mattancherry የቅመማ ቅመም ንግድ የተጠናከረበት ታሪካዊ ስፍራ ነው። አይሁዶች፣ ጉጃራቲዎች፣ ኮንካኒዎች፣ ጄይኖች፣ ማራቲዎችና ሌሎች ማኅበረሰቦች በዚህ አካባቢ ሰፍረው የከተማዋን ባህላዊ ብዝሃነት አበልጽገዋል።
ማታንቼሪ ቤተ መንግሥት (Mattancherry Palace)፦ በ1555 በፖርቹጋሎች ተገንብቶ በኋላ በደች የተጠናከረው ይህ ቤተ መንግሥት የኬረላን ባሕላዊ ሥዕሎችና የታሪክ ቅርሶች አቃፊ ነው።
ኮቺ የኬረላ ግዛት የኢኮኖሚ፣ የንግድ እና የኢንዱስትሪ ማዕከል ናት።
Fort Kochi — ታሪክ በጎዳናዎች ላይ
ከኮቺ ታሪካዊ ስፍራዎች መካከል Fort Kochi ልዩ ቦታ አላት። ፖርቱጋሎች፣ ደች እና ብሪታኒያውያን በተለያዩ ዘመናት በአካባቢው ተጽዕኖ አሳድረዋል። የድሮ የአውሮፓ የሕንፃ ቅርጾች ከባህላዊ የኬራላ አርክቴክቸር ጋር ተቀላቅለው የሚታዩበት አካባቢ ነው።
በFort Kochi የሚገኙት St. Francis Church፣ Dutch Cemetery፣ Vasco House፣ Santa Cruz Basilica እና ሌሎች ታሪካዊ ሕንፃዎች ኮቺ በተለያዩ የታሪክ ዘመናት ያሳለፈችውን ሂደት ይናገራሉ።
ቅዱስ ፍራንሲስ ቤተክርስቲያን (St. Francis CSI Church)፦ በ1503 የተገነባችው ይህች ቤተክርስቲያን በሕንድ የመጀመሪያዋ የአውሮፓውያን ቤተክርስቲያን ስትሆን፣ ታዋቂው ፖርቹጋላዊ አሰሳዊ ቫስኮ ዳ ጋማ (Vasco da Gama) መጀመሪያ የተቀበረበት ቦታ በመሆኗ ይታወቃል።
የቻይና የዓሣ ማጥመጃ መረቦች
— የኮቺ ምልክት
Fort Kochiን ከሌሎች የዓለም ከተሞች የሚለየው አንዱ ድንቅ ነገር Chinese Fishing Nets — Cheenavala ነው።
እነዚህ ግዙፍ መረቦች በእንጨትና በቀርከሃ ምሰሶዎች ላይ ተደግፈው፣ በክብደት ሚዛን መርህ የሚሰሩ የዓሣ ማጥመጃ መሳሪያዎች ናቸው።
የኬራላ ቱሪዝም መረጃ እንደሚገልጸው ይህ የማጥመድ ዘዴ በኮቺ ዳርቻ ከ1350–1450 ዓ.ም. አካባቢ መታየቱ ይታመናል።
በፀሐይ መጥለቂያ ሰዓት የሚታዩት መረቦች በባሕሩ ላይ ግዙፍ ሥዕል ይመስላሉ። እንጨቶቹ ወደ ሰማይ ተዘርግተው፣ መረቦቹ ወደ ውሃው ሲወርዱና ሲወጡ መመልከት የኮቺ ጉዞ ልዩ ትውስታ ይሆናል።
የይሁዲ ምኩራብ (Paradesi Synagogue)
በማታንቼሪ 'Jew Town' በሚባለው አካባቢ የሚገኘው ይህ ምኩራብ በ1568 የተገነባ ሲሆን በደቡብ ኤሺያ ከሚገኙ የቆዩ ምኩራቦች አንዱ ነው።
የኮቺ የውሃ ዓለም
ኮቺ የምትታወቀው በባሕር ብቻ አይደለም። በዙሪያዋ የተዘረጉ የውሃ መስመሮች፣ ደሴቶች፣ ጀልባዎችና አረንጓዴ ዳርቻዎች የከተማዋን ሌላ ፊት ያሳያሉ። በጀልባ ሲጓዙ ከተማዋ ከሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎች ወደ ባህላዊ ቤቶችና የዓሣ አጥማጆች መንደሮች ስትቀየር ይታያል።
የባሕር ንግድና ወደብ፦
ኮቺ በሕንድ ውቅያኖስ የንግድ መስመር ላይ የምትገኝ ተፈጥሯዊ የባሕር በር በመሆኗ የዓለም አቀፍ መርከቦች ማረፊያና የመርከብ ጥገና (Shipbuilding) ማዕከል ናት።
Kochi Water Metro — ዘመናዊ ኮቺ
እኔ በኮቺ ያለኝ ጉዞ ከታሪካዊው የFort Kochi ዓለም ብቻ አይደለም፤ የከተማዋን ዘመናዊ የውሃ መጓጓዣም ለማየት እድል አግኝቻለሁ።
Kochi Water Metro የከተማዋን የተለያዩ ክፍሎች በውሃ መስመሮች የሚያገናኝ ዘመናዊ የመጓጓዣ ሥርዓት ነው። የፕሮጀክቱ ኦፊሴላዊ መረጃ 75+ ኤሌክትሪክ ጀልባዎች፣ 15 መስመሮችና 75+ ኪሎሜትር የሚደርስ አውታረ መስመር እንዳለው ያሳያል።
ይህ ማለት ኮቺ የድሮ የጀልባ ባህልን ብቻ አትጠብቅም፤ ውሃውን እንደ ዘመናዊ የከተማ መጓጓዣ መሠረተ ልማትም ትጠቀማለች።
ከተማዋ የሜትሮ ባቡር (Kochi Metro) እና በባሕር ላይ የሚንቀሳቀስ የውኃ ሜትሮ (Kochi Water Metro) አቀናጅታ በመጠቀም የትራፊክ ፍሰቷን የዘመነ አድርጋለች።
የባህልና የሃይማኖት ብዝሃነት
ኮቺ የተለያዩ ሕዝቦችና ባህሎች ለዘመናት የተገናኙባት ከተማ ናት። በMattancherry አካባቢ ቤተ ክርስቲያናት፣ መስጊዶች፣ ምኩራቦች እና የተለያዩ የማኅበረሰብ መኖሪያዎች በአንድ ቦታ ይገኛሉ።
ይህ ብዝሃነት ኮቺን ከቱሪስት መዳረሻ በላይ ያደርጋታል፤ ከተማዋ የንግድ፣ የፍልሰት፣ የሃይማኖትና የባህል መገናኛ ቦታ እንደነበረች የሚያሳይ ሕያው ማስረጃ ናት።
ማሪን ድራይቭ (Marine Drive)፦
በከተማዋ መሐል የሚገኝ፣ የባሕርና የዘመናዊ ሕንፃዎችን ውበት የሚያሳይ ረጅም የእግር መንገድና የንግድ ማዕከል ነው።
የኬራላ ጣዕም
ኮቺን ማየት ብቻ ሳይሆን መቅመስም ነው። የኬራላ ምግብ በኮኮናት፣ በቅመማ ቅመም፣ በዓሣና በባህላዊ የምግብ አዘገጃጀት የተለየ ጣዕም አለው። በቅመማ ቅመም ገበያዎች ውስጥ ሲዘዋወሩ የበርበሬ፣ የካርዳሞም፣ የቀረፋና የዝንጅብል ሽታ የጉዞውን ልምድ ያሟላዋል።
ኮቺን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ (Cochin International Airport - CIAL)፦ ሙሉ በሙሉ በፀሐይ ኃይል (Solar Power) በመሥራት በዓለም የመጀመሪያው አውሮፕላን ማረፊያ በመሆን የዓለም አቀፍ አካባቢ ጥበቃ ሽልማት አሸናፊ ሆኗል።
ቱሪዝምና ተፈጥሮአዊ ውበት
(Tourism & Environment)
ኮቺ በዓለም አቀፍ ቱሪስቶች ዘንድ በብዛት ከሚጎበኙ የሕንድ ከተሞች አንዷ ናት።
ቸራይ የባሕር ዳርቻ (Cherai Beach)፦ ለዋና፣ ለእግር ጉዞ እና ለዶልፊን እይታ ተስማሚ የሆነ ውብ የባሕር ዳርቻ ነው።
የባሕርና የሐይቅ ትስስር (Backwaters)፦
በቦይ እና በሐይቆች የተከበቡት አካባቢዎች በቤት-መርከቦች (Houseboats) የሚደረጉ ጉዞዎችን ያቀርባሉ።
ባሕላዊ ኪነ-ጥበብ፦
የኬረላ ባህላዊ የውዝዋዜና የትያትር ጥበብ የሆነው ካታካሊ (Kathakali) የቀጥታ ትርኢቶች በየቀኑ ለጎብኚዎች ይቀርባሉ።
ማጠቃለያ
ኮቺ በጥንታዊ የታሪክ ቅርስ እና በዘመናዊ የአረንጓዴ ቴክኖሎጂ ልማት መካከል ፍጹም ሚዛን የጠበቀች፣ በደቡብ ኤሺያ ፈጣን ዕድገት እያስመዘገቡ ካሉ ማረፊያዎች አንዷ ናት።
ኮቺን ሲለዩ...
ኮቺ እንደ አንድ መዳረሻ ብቻ አትታይም። በአንድ በኩል የቻይና የዓሣ መረቦች የቆየውን የባሕር ታሪክ ይነግራሉ፤ በሌላ በኩል የWater Metro ጀልባዎች የዘመናዊ ሕንድን ገጽታ ያሳያሉ። Fort Kochi ያለፈውን ዘመን ያስታውሳል፤ የዘመኑ ከተማ ደግሞ ወደፊት የምትጓዝ ኮቺን ያሳያል።
ኮቺ ታሪክን በሙዚየም ውስጥ ብቻ የማታስቀምጥ፣ በጎዳናዎቿ፣ በባሕሯ፣ በውሃ መንገዶቿ፣ በገበያዎቿ እና በሰዎቿ ውስጥ በየቀኑ የምትኖር ከተማ ናት።
ለእኔም የኮቺ ጉዞ የአንድ ከተማ ጉብኝት ብቻ ሳይሆን፣ የባሕር ታሪክን፣ የቅመማ ቅመም ንግድን፣ የኬራላን ባህልና የዘመናዊ ሕንድን ፈጠራ በአንድ ጉዞ የመመልከት ተሞክሮ ሆኖ ይቀራል።
ኮቺ — ያለፈው ታሪክ ከወደፊቱ ጋር የሚገናኝባት ከተማ!
የጉዞ ማስታወሻ — ክፍል 17
ይቀጥላል...
Getu Temesgen — ጌጡ ተመስገን
#india in Ethiopia (Embassy of India, Addis Ababa) #indiaethiopia #brics #financialcooperation #banking #economiccooperation #ministry of External Affairs, #government of IndiaIndia in Ethiopia (Embassy of India, #addis Ababa)Press Information Bureau - PIB, #government of IndiaDiaspora India ConnectMinistry of Information & Broadcasting, #government of #indiamygovindiaddnewsliveasian News #international (ANI)All India Radio News #india in ethiopia (embassy of india addis ababa) #manohar Lal #ethiopian Airlines #ministry of External Affairs
Government of India
# India - External Publicity & Public Diplomacy Division External Language Media Section #mr . Amit Raghav, Publicity Officer (XLM) #unesco #brics #bricssummit #india #newdelhi #diplomacy #economy #putin #modi #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababaindiainethiopia #indiaethiopia #brics #kumarakom #kerala #vembanadlake #kottayam #india #newdelhi #traveldiary #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa #kerala #shaikhhassankhan #sevensummits #mountaineering #everest #india #travelstory

27 days ago
4 months ago
በኪነጥበብ የታጀበ ደግነት🙏
ኮሜዲያን አስረስ በቀለ (ቼሪ) የመጽሐፉን ገቢ ሙሉ ለሙሉ ለበጎ አድራጎት አበረከተ
የሕፃናት መጻሕፍት ደራሲና የልጆች ፕሮግራም አዘጋጅ በመሆን፣ በተለይም “ቼሪ” የተሰኘውን ተወዳጅ የልጆች ካራክተር (ገጸ-ባህሪ) በመፍጠር በሕፃናት መዝናኛና ትምህርት ዘርፍ ጉልህ አሻራ ያሳረፈው ታዋቂው ኮሜዲያን አስረስ በቀለ፣ በድጋሚ የደግነት ተምሳሌትነቱን አሳይቷል።
ሰሞኑን በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) ካስመረቃቸው ሁለት አዳዲስ የሕፃናት መጻሕፍት መካከል የመጀመሪያውን መጽሐፍ ሽያጭ ገቢ ሙሉ ለሙሉ ለሙዳይ በጎ አድራጎት ድርጅት በስጦታ አበርክቷል።
ከ15 በላይ የልጆች ተረት መጻሕፍትን ለንባብ ያበቃው ደራሲ አስረስ በቀለ፣ ለሕፃናት ሥነ-ጽሑፍ ባበረከተው ከፍተኛ አስተዋፅኦ እ.ኤ.አ በ2022 በተካሄደው Ethiopia Reads Children’s Reading Summit ላይ እውቅና የተቸረው አንጋፋ ባለሙያ ነው።
ይህ የሰሞኑን ስጦታውም ጥበብን ከሕዝብ ወገንተኝነት ጋር አጣምሮ የመጓዙ ማረጋገጫ ሆኗል።
ይህንን ታላቅ የበጎ አድራጎት ስጦታ የተቀበለው የሙዳይ በጎ አድራጎት ድርጅት፣ ለረጅም ዓመታት በችግር ውስጥ ያሉ ሕፃናትን፣ እናቶችንና አረጋውያንን በመደገፍና ተስፋ በመሆን የሚታወቅ ተቋም ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በአቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 2 አድራሻውን አድርጎ ሰብአዊ አገልግሎቱን በስፋት እየሰጠ ይገኛል።
የድርጅቱ መሥራች ወይዘሮ ሙዳይ ምትኩ የተደረገላቸውን ድጋፍ አስመልክተው ባስተላለፉት ልባዊ መልእክት፦
"አስረስ በቀለ (ቼሪ) የምንግዜም የልብ አጋራችንና ታማኝ ደጋፊያችን ነው። ዛሬም ይህንን የመጽሐፉን ገቢ ሙሉ ለሙሉ ለእኛ በማበርከት ያደረገልንን ታላቅ በጎ ተግባር ስንመለከት ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እናቀርባለን።"
በማለት አክለውም ለመላው የሀገራችንን ሕዝብ ጥሪ አቅርበዋል፦
"ሁሌም ከጎናችን የማትለዩ ደጋግ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፤ ይህንን ጠቃሚ የሕፃናት መጽሐፍ በመግዛት፣ በአንድ በኩል የልጆቻችሁን የዕውቀት አድማስ እንድታሰፉ፣ በሌላ በኩል ደግሞ የሽያጩን ገቢ በቀጥታ ለሙዳይ በማዋል አቅመ-ደካሞችንና ሕፃናትን እንድትደግፉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።"
ይህንን መጽሐፍ በመግዛት የዕውቀትና የቸርነት አጋር እንሁን!

ኮሜዲያን አስረስ በቀለ (ቼሪ) አዲሱን የልጆች መጽሐፍ ሊያስመርቅ ነው
#ethiopia | አዲስ አበባ፦ ኮሜዲያን፣ የህፃናት መጽሐፍት ደራሲ እና የልጆች ፕሮግራም አዘጋጅ አስረስ በቀለ (ቼሪ) “ኮሚኩ ሙዝ” የተሰኘውን አዲስ የልጆች መጽሐፍ ለማስመረቅ ዝግጅት ማድረጉ ተገለጸ።
የመጽሐፉ ምርቃት እሁድ፣ ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 8:00 ሰዓት ጀምሮ በኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጽሐፍት አገልግሎት ይካሄዳል።
አስረስ በቀለ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የልጆች ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት የሚታወቅ ሲሆን፣ “ቼሪ” የተሰኘውን የልጆች ካራክተር በመፍጠር በህፃናት መዝናኛና ትምህርት ዘርፍ ጉልህ አስተዋፅኦ አበርክቷል።
ደራሲው ከ15 በላይ የልጆች ተረት መጻሕፍትን የጻፈ ሲሆን፣ በ2022 እ.ኤ.አ በEthiopia Reads Children’s Reading Summit ላይ ለህፃናት ሥነ-ጽሑፍ ያበረከተው አስተዋፅኦ እውቅና አግኝቷል።
አዘጋጆቹ ምርቃቱ ለሁሉም ክፍት መሆኑን ገልጸው፣ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር በመገኘት የልጆችን የንባብ ባህል ለማበረታታት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።
✍️ ጌጡ ተመስገን
#getu #getutemesgen #ጌጡ #ጌጡተመስገን #አስረስበቀለ #ቼሪ #ኮሚኩሙዝ #ethiopiareads #የልጆችመጽሐፍ #ንባብ

Sponsored by
Surafel
4 months ago
እንኳን ወደ የ10000 ሀይቅ ባለቤቷና ወደ የምንኮራባት ቤታችን ሚኒሶታ በሰላም መጡ ።
በዶ/ር ሲራክ ሀይሉ።
የሚኒሶታ ትውልደ ኢትዮጵያን ሆይ፤ የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን የእስፖርት ፌዴሬሽን (ESFNA) ለመታደም ወደ ሚኒሶታ የሚመጡ እንግዶችን እንቀበል።
ይህ አመት ለኛ ኮሙኒቲ እጅግ በጣም የተለየ ነው። ምክንያቱም በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን የእስፖርት ፌዴሬሽን(ESFNA) የሚያዘጋጀው አመታዊ ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሚኒሶታ መንታ ከተሞቻችን ሚኒያፖሊስ እና ቅዱስ ጳውሎስ (ሴንት ፖል) ከተሞች ይመጣል።
ESFNA እንደሚታወቀው በሰሜን አሜሪካ ብዙ ዲያስፖራ ለስፖርት እና ለባህል አከባበር የሚሰበሰብበት ዝግጅት ነው። በርከት ያሉ ከመላው ዩናይትድ ስቴትስ እና ከዚያ ውጪም የሚመጡ ጓደኞቻችን ፣ ዘመዶቻችን እንዲሁም ሌሎች ጎብኚዎች ወደዚህ ይተማሉ። ይህም እንደ ሚኒሶታ ኮሙኒቲ አባልነታችን እንግዶቹን ሞቅ ባለ ሁኔታ፣ በኩሩና ጨዋ የእንግዳ ተቀባይነት መንፈስ የመቀበል እድል እንዲኖረን ያደርጋል።
እንደሚታወቀው ሚኒሶታ ለብዙዎቻችን ቤታችን ናት። በተለይ ለኔ እንደ አንድ ግለሰብ ላለፉት 30 አመታት መልካም ቤቴ ሆና ቆይታለች። በትጋት የምንሰራባት፣ ቤተሰብ የምናፈራባት፣ ቢዝነስ የምንገነባበት እና እርስ በርስ የምንደጋገፍበት ከተማችን ነች። ባለፉት አመታት ውስጥ የሚኒሶታ የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ ጠንካራና ንቁ ሆኖ ለማገል ባሉው ሁሉ አቅም ሳይሰለች እየለፍ እንደሆነ አግኝቸዋለሁ።
ማየት ያለብን ከESFNA ዝግጅት ወደዚህ መምጣት የምናገኘዉ የእስፓርት ዝግጅቱን የመሳተፍ እና የማህበረሰባችንን በአንድ ላይ ተሰብስቦ የማየትን ዕድል ብቻ ሳይሆን የመንታ ከተሞቻችንን ውበት፣ ባሕልና ደማቅ መንፈስ ለእንግዶቻችን የምናሳይበት ነው። ሚኒሶታ የባለ10000 ሐይቆች ስቴት ናት። በእርግጥ የስቴቷ ሀይቆች ብዛት ከ11000 በላይ ነው ይባላል። ለዚህ ነው ተፈጥሮ፣ ውሃ እንዲሁም የተዋበ ከባቢ በሚኒሶታዊያን ዘንድ ወሳኝ የህይወት አካል የሚሆኑት ።
እንግዲህ የምትቀበሏቸው ጓደኞች፣ ዘመዶች ወይም የኮሚኒቲ አባለት ካሉ ዞር ዞር አርጋችሁ ብታሣዩአቸው መልካም ይሆናል። መንታ ከተሞቻችን ሊጎበኙ የሚገቡ ብዙ ውብ ቦታዎች አሉዋቸው። ከሁሉም እጅጉን ተመራጭ የሚሆነው የጉብኝት ስፍራ የሚንሀሀ ገራሚ ፏፏቴ እና ፖርክ ሲሆን ለጉዞ፣ ሰውነት ለማፍታታት እና ቆንጆ ቆንጆ ፎቶግራፎችን ለመነሳት ይመቻል ። በተጨማሪም ጎብኚዎች ታሪካዊውን የስቶን አርክ ድልድይ አቋርጦ መሄድ ሊያስደስታቸው ይችላል። ምክንያቱም ይህ ጉዞ የሚሲሲፒን ወንዝ ማራኪ ገፅታ እና የሚኒያፖሊስን እስካይላይን ለማየት ስለሚያስችላቸው ነው። አካባቢንና ጥበብን ለሚያደንቁት ደግሞ የሚኒያፖሊስ የቅርፃቅርፅ ጋርደን መታየት የሚገባው ስፍራ ነው። ይህ ቦታ ዝነኛዉ ስፑንብሪጅ ኤንድ ቼሪ የሚገኝበት ሲሆን በእግር እየተጋዙ ለመጎብኘት በጣም ተመራጭ ስፍራ ነዉ፡፡
ሸመታና መዝናናትን ለሚሹ ደግሞ በአሜሪካ ትልቁ የገበያ አዳራሽ የሆነዉን ሞል ኦፍ አሜሪካን ብናሳያቸዉ በጣም ይደሰታሉ፡፡ ሞል ኦፍ አሜሪካን በሬስቶራንቶች ፣ በመደብሮች እንዲሁም በቤት ዉስጥ የመዝናነኛ ፓርኮች የታደለ ስፍራ ነዉ፡፡ በእግር በቢስኪሊት የሚኒሶታን የተፈጥሮ ዉበት ለማድነቅ ደግሞ ቅጥልጥል ሀይቆቿ በተለይም በደ ማካ ሳካ እና ሀሪየት ሃይቅን ማይት መንፈስን ያድሳል፡፡
በእርግጥ እናዉራ ካልን ከእንግዶቻችን ጋር የሚኒሶታ ቆይታን የማይረሳ ለማድረግ ከቤት ዉጭ ያሉ አማራጮች ይመከራሉ፡፡ በእግር እንጓዝ ቢባል፣ በቢስክሊት ብንል ወይ ደሞ በአካባባዉ ያሉ ትናንሽ ጅልባዎችን ተከራይትን ለመናፈስ ብናስብ የመንታ ከተሞቹን የሚመስጥ ዉበት እናደንቅበታለን፡፡
የእንግዶችዎ ምርጫ ደግሞ ቅዱስ ጳዉሎስ ከሆነ ወደ ሚያምረዉና ከቤተሰብ ጋር ሆኖ ለመዝናናት ወደ ሚመቸዉ ወደ ኮሞ ፓርክ አና የእንስሳት መጠበቂያ ወይንም ታሪካዊዉንና በሃገሪቱ ካሉ ቤተ እምነቶች ሁሉ በጣም ተደናቂ የሆነዉን የቅዱስ ጳዉሎስ ካቴድራል ልናስጎበኛቸዉ እንችላለን፡፡ እዛዉ አቅራቢያ የሚገኘዉም የሚኒሶታ ስቴት ካፒቶልም የሚኒሶታን ታሪክና ቅርጻ ቅርጽ ለመመልከት ያስችላል፡፡
ታሪክና ባህልን የሚያደንቁ ጎብኚዎች ካጋጠሞትም አይጨነቁ በሚሲሲፒ ወንዝ ዳርቻ ላይ ወደሚገኘዉ የሚል ሲቲ ሙዚየም አሊያም በአለም ትልቅ ደረጃ ያለዉ የሚኒያፖሊስ ኢኒስቲትዩት ኦፍ አርትን ታስጎበኙዋቸዋላችሁ፡፡
ለኮሚኒቲያችን ሌላ ጠቃሚ ሃሳብ የሚሆነዉ ደግሞ እንግዶችን ስንቀበልም ሆነ ስናስተናግድ በተቀናጀ መልኩ ቢሆን ይመረጣል፡፡ በሚኒሶታ የምንገኝ ኢትዮጵያዉያን በየአካባቢዉ በቡድን በቡድን ተደራጅተን ብንሰራ ዉጤታማ የምንሆን ይመስለኛል፡፡ ለምሳሌ አንዳችን የሌሎቻችንን እንግዶቻች ወደ የጋራ ዝግጅቶች ፒክኒክ ባርቢክዩ ወደ ሃይቅ ዳር ጉዞ እና ወደ ጥቃቅን ስብስቦች መጋበዝ እንችላለን፡፡ ከተለያየ አካባቢ የመጡ እንግዶች አንድ ላይ ሲገኛኙ ትዉስታዉ ህይወት ያለዉ እና የላቀ ይሆናል፡፡ ይህም ሰዎች ቀጣይ የሆነ ወዳጅነት እንዲያጎለብቱ እና የኛን የሚኒሶታ ኮሚኒቲ የአንድነት ስሜት ይበልጥ እንዲረዱት ያደርጋል፡፡
ESFNA ከስፖርት ዝግጅትነት ያለፈ ነዉ ኮሚኒቲን ባህልን እና አንድነትን የምናከብርበት ነዉ፡፡ እስቲ እንግዶቻችንን በኩራትና በደግነት እንቀበላቸዉ፤ ዉብ ከተሞቻችንን እናሳያቸዉ ከድንቁ ማህበረሰባችን ጋር እናስተዋዉቃቸዉ እና የሚኒሶታ ቆይታቸዉን የማይረሳ እናድርግላቸዉ፡፡ በዚህ አጋጣሚ የኒያላ ስፓርት ክለብ የኢትዬጵያ መሀበር በሚኔሶታ ባጠቃላይ ሚናሶታ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ሊመሰገኑ ይገግባል፣፣
መልካም ቆይታ።
ዶ/ር ሲራክ ኃይሉ ከሚኔሶታ
የካሪዮፕራክቲክ ሐኪም

5 months ago
የአሜሪካ የቻይና መኪናዎች እገዳ በአፍሪካ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል ተጠቆመ
በአሜሪካ ምክር ቤት በሁለቱም የፖለቲካ ፓርቲዎች ድጋፍ የቀረበውና በቻይና የተሰሩ መኪናዎች እንዲሁም የመኪና መለዋወጫዎች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ የሚከለክለው አዲስ የህግ ረቂቅ፣ በአፍሪካ እያደገ ባለው የመኪና መገጣጠም ዘርፍ ላይ ከፍተኛ አንድምታ ሊኖረው እንደሚችል ተገለጸ።
የአሜሪካ የደህንነትና የኢኮኖሚ ስጋቶችን መሰረት ያደረገው ይህ እገዳ፣ የቻይና የመኪና አምራቾች ፊታቸውን በስፋት ወደ አፍሪካ ገበያ እንዲያዞሩና ምርቶቻቸውን ወደ አህጉሪቱ እንዲያፈሱ የሚያስገድድ እንደሆነ ተመልክቷል።
በአሁኑ ወቅት አፍሪካ ከዓለም አቀፍ የመኪና ምርት ውስጥ የምታበረክተው ድርሻ ከሁለት በመቶ በታች ቢሆንም፣ እንደ ቢ.ዋይ.ዲ (BYD) እና ቼሪ (Chery) ያሉ የቻይና ኩባንያዎች በአህጉሪቱ ያላቸውን የተሽከርካሪ ሽያጭና የመገጣጠም አጋርነት በከፍተኛ ሁኔታ እያሰፉ ይገኛሉ።
ይህ የቻይና ኩባንያዎች ወደ አፍሪካ በስፋት መተምመም፣ እንደ ደቡብ አፍሪካ እና ሞሮኮ ያሉ ግዙፍ አምራቾችን ብቻ ሳይሆን እንደ ኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያ እና ኬንያ ያሉ የአገር ውስጥ መኪና መገጣጠም ኢንዱስትሪን ለማሳደግ የሚጥሩ ሀገራትን ፈተና ላይ ሊጥል እንደሚችል ተገምቷል።
በአሜሪካ ገበያ የተገደቡት ምርቶች ወደ አፍሪካ በብዛት መፍሰሳቸው ለአገር ውስጥ አነስተኛ መገጣጠሚያዎች የገበያ ፉክክርን የሚያከብድ ሲሆን፣ ይህም በአገር ውስጥ የሚመረቱ መኪናዎችን ተወዳዳሪነት ሊቀንስ እንደሚችል ባለሙያዎች ያስጠነቅቃሉ።
seledadotio

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በካናዳ ቶሮንቶ ከተማ (ስካርቦሮ አካባቢ) ያደገችው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የ'አልት-አር ኤንድ ቢ' አቀንቃኝ ሊዲያ ሀብተማርያም፣ በሙዚቃው ዓለም የምትታወቅበትን 'ቼሪ' (Chxrry) የተሰኘ ስሟን ይዛ የዓለምን የሙዚቃ መድረክ ለመቆጣጠር ተነስታለች። በቅርቡ በትውልድ ከተማዋ ለምታደርገው ትልቅ የሙዚቃ ድግስ ዝግጅቷን እያጠናቀቀች የምትገኘው ይህች ወጣት፣ ራዕይዋ ከቶሮንቶ ከተማ የዘለለ መሆኑን በልበ ሙሉነት ትናገራለች። የሰፈሯ ጀግና መሆን ብቻ እንደማትፈልግ የምታስረዳው ቼሪ፣ "እናንተ ከተማዋን ውሰዱ፣ እኔ ግን ዓለምን ነው የምፈልገው፤ ከሁሉም የላቅኩ መሆን ነው ህልሜ" በማለት ሰፊውን አላማዋን ታጋራለች።
የቼሪ ይህ ግዙፍ ህልም በአየር ላይ የተንጠለጠለ የከንቱ ምኞት አይደለም፤ በዓለማችን ላይ ካሉ እጅግ ታዋቂ የሙዚቃ ከዋክብት አንዱ በሆነው ትውልደ ኢትዮጵያዊው አቤል ተስፋዬ ሙሉ ድጋፍ ታጅቧል። ቼሪ አቤል ተስፋዬ በመሰረተው ታዋቂው የሙዚቃ ኩባንያ 'XO Records' ውስጥ ለመፈረም የበቃች የመጀመሪያዋ ሴት አርቲስት በመሆን ታሪክ ሰርታለች። የሁለቱ አርቲስቶች ግንኙነት በሙዚቃ ብቻ የተገደበ አይደለም፤ ሁለቱም ኢትዮጵያዊ ስረ-መሰረት ያላቸው ሲሆኑ፣ ያደጉትም በአንድ ሰፈር ውስጥ ነው። እናቶቻቸውም የቅርብ ጓደኛሞች እንደነበሩ ቼሪ ታስታውሳለች። አቤል በ2011 የመጀመሪያውን የሙዚቃ ስራውን ባቀረበበት ታሪካዊው 'Mod Club' መድረክ ላይ፣ ቼሪም በበኩሏ ቅዳሜ ዕለት ስራዋን ልታቀርብ መሆኑ የትውልድ ሽግግርን የሚያሳይ ተምሳሌታዊ ክስተት ሆኖላታል። አቤልም "የራስሽን መንገድ ፍጠሪ" የሚል ወርቃማ ምክር እንደለገሳት በኩራት ትገልጻለች።
ግንቦት 21 (May 29) ለህዝብ ጆሮ የሚደርሰው "U, Me & My Ego" የተሰኘው የመጀመሪያው ሙሉ አልበሟ፣ የቼሪን የሙዚቃ ብስለት እና ጥልቅ ሀሳብ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። የአልበሙ ርዕስ ሶስት የተለያዩ ማንነቶችን የሚወክል ሲሆን፤ "Me" ተጋላጭ የሆነችውን ሊዲያን፣ "U" በህይወቷ ውስጥ ያለን ወንድ፣ እንዲሁም "My Ego" ደግሞ ደፋር እና ሀይለኛ የሆነውን የቼሪን ማንነት ይወክላል። በአዘጋጁ 'ቢሊቭ' የተቀነባበረው ይህ አልበም፣ ከለዘብተኛ የፍቅር ሙዚቃዎች እስከ ሀይለኛ የሴቶች አቅም ማጎልበቻ ዜማዎችን ያካተተ ሲሆን፣ አርቲስቷ ምንም አይነት ድምጿን ከፍ ሳታደርግ ሀሳቧን በስለታም እና በማራኪ ሁኔታ የምትገልጽበት ልዩ የሙዚቃ ስልት ታይቶበታል።
የቼሪ የሙዚቃ ጉዞ መሰረት የተጣለው ገና በልጅነቷ ነበር። ኢትዮጵያውያን ስደተኛ የሆኑት ወላጆቿ በቤተክርስቲያን መዘምራን የነበሩ ሲሆን፣ እሷም በቤተክርስቲያን ዝግጅቶች እና በሰርግ ስነ-ስርዓቶች ላይ ትዘፍን ነበር። ነገር ግን ሙዚቃን እንደ ዋና የህይወት መስመር ለመያዝ ያሰበችው ያልተጠበቀ አጋጣሚ ከተፈጠረ በኋላ ነው።
በዮርክ ዩኒቨርሲቲ ትምህርቷን እየተከታተለች ባለችበት ወቅት፣ በ2018 የሪሃናን "Work" የተሰኘ ዘፈን ስትዘፍን በጓደኛዋ በስልክ ካሜራ ተቀርጻ ኢንስታግራም ላይ ከተለቀቀ በኋላ፣ ቪዲዮው በአንድ ጀምበር በመላው ዓለም ተሰራጨ። ይህ ክስተት ህይወቷን የቀየረ ሲሆን፣ አባቷን በደስታ "ስራህን አቁም፣ ጓዝህን ጠቅልል ወደ ሆሊውድ ልንሄድ ነው" እስከማለት አድርሷት ነበር። ብዙም ሳይቆይ የመጀመሪያዋን "My Love" የተሰኘች ዜማዋን እንድታወጣ እና የበርካታ ታዋቂ የሙዚቃ ኩባንያዎችን ቀልብ እንድትስብ መንገድ ከፈተላት። የ 'XO' ተባባሪ መስራች የሆነው አሚር (ካሽ) ኢስማኢልያን መልዕክት ልኮላት ወደ ኩባንያው እንድትቀላቀል ያደረጋትም በዚሁ ወቅት ነበር።
አሁን ላይ በሙዚቃው ዓለም የራሷን ጽኑ መሰረት እየጣለች የምትገኘው ቼሪ፣ በ'XO Records' ስር ሆና በመስራቷ ሙሉ ነጻነት እንዳገኘች ትናገራለች። አብዛኛውን ጊዜ ከትላልቅ ኩባንያዎች ጋር ሲፈረም የሚመጣውን ጫና እና የሚጠበቅ ግዴታ ወደ ጎን በመተው፣ ኩባንያውም ሆነ አቤል የራሷን የፈጠራ መንገድ እንድትከተል ሰፊ ሜዳ ትተውላታል። በአሁኑ ወቅት ራሷን ይበልጥ እያወቀች እና እያደነቀች የመጣችው ይህች ወጣት አርቲስት፣ የካናዳን እና የቶሮንቶን ሴት አርቲስቶች አዲስ ማዕበል የመፍጠር ግዙፍ ራዕይ ሰንቃ ጉዞዋን ቀጥላለች።

6 months ago
አርሰናል በኢምሬትስ ተደናቀፈ!
#ethiopia | መድፈኞቹ በገዛ ሜዳቸው ያልተጠበቀ ሽንፈት አስተናግደዋል። በ32ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ-ግብር ቦርንማውዝን ያስተናገደው አርሰናል 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ተሸንፎ ወጥቷል።
የጨዋታው ድምቀቶች
ክሩፒ እና አሌክስ ስኮት የቼሪዎቹን የማሸነፊያ ግቦች አስቆጥረዋል።
አዲሱ አጥቂ ቪክቶር ዮኮሬሽ በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ ቢያሳርፍም፣ ቡድኑን ከሽንፈት ሊታደገው አልቻለም።
ይህ ሽንፈት አርሰናል ለዋንጫ በሚያደርገው ትንቅንቅ ላይ ከፍተኛ ጫና የሚፈጥር ሲሆን፣ ቀጣይ ጨዋታዎች ላይ ስህተት የመስራት ዕድሉን አጥብቦበታል።
መድፈኞቹ ዋንጫውን ለማንሳት ያላቸው ተስፋ አደጋ ላይ ይወድቅ ይሆን?
አስተያያታችሁን አጋሩን
#getu #arsenal #premierleague #afc #bournemouth #footballnews #emiratesstadium #gyokeres #sportsupdate #addisababa #አርሰናል #እንግሊዝፕሪሚየርሊግ #ስፖርት #ጌጡተመስገን #getutemesgen
በሮቤ ከተማ በጤና ባለሙያው ላይ ጥቃት የፈጸሙ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
በሮቤ ከተማ አስተዳደር በጤና ባለሙያው ከዲር ዋቆ ላይ የድብደባ ወንጀል ፈጽሞ የተሰወረው ተጠርጣሪ እና ግብረ-አበሮቹ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሮቤ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።
ተጠርጣሪው በሐሰት "የእጅ ስልኬን ወስዶብኛል" በማለት፤ ጓደኞቹን በማስተባበር ግለሰቡን ያስደበደበ ሲሆን፣ ድርጊቱንም ትክክለኛ አስመስሎ ለማቅረብ የተጎጂውን ምስል በካሜራ ሲቀዳ እንደነበር ተገልጿል።
የሮቤ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ገመዳ ቱሊቻ ለ'ኦቢኤን ሳይበር ሚዲያ' እንደገለጹት፣ በሕግ አካላት በተደረገ ክትትል ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።
ድብደባውን የፈፀሙ ግብረ-አበሮችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታውቋል።
ኮማንደር ገመዳ አክለውም፣ የወንጀል ድርጊትን የማጣራትም ሆነ ውሳኔ የመስጠት ስልጣን የፍትህ አካላት ሆኖ ሳለ፣ በቡድን ተደራጅቶ ሰውን መደብደብ ወንጀል መሆኑን ህዝቡ ሊገነዘብ እንደሚገባ አሳስበዋል።
#ethiopia #security #police

7 months ago
ትራምፕ የጃፓኑን ጠቅላይ ሚኒስትር በ"ፐርል ሃርበር" ቀልድ አስደነገጡ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አዲሷን የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሳናኤ ታካይቺን በኋይት ሃውስ ባስተናገዱበት ወቅት፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል የነበረውን ታሪካዊ ቁስል የሚነካ ቀልድ በመሰንዘር መነጋገሪያ ሆነዋል።
ትራምፕ በስብሰባው ወቅት፣ በቅርቡ አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ስለሰነዘሩት ጥቃት ሲናገሩ እ.ኤ.አ. በታህሳስ 1941 ጃፓን በፐርል ሃርበር ላይ የፈጸመችውን ጥቃት እንደ ማጣቀሻ አንስተዋል።
ጋዜጠኞች "አሜሪካ በኢራን ላይ የሰነዘረችውን ጥቃት ለምን ለጃፓን ቀድማ አላሳወቀችም?" ብለው ሲጠይቁ፣ ትራምፕ ሲመልሱ፦ "ስለ ፐርል ሃርበር እናንተስ ለምን ቀድማችሁ አልነገራችሁኝም?" በማለት በቀልድ መልክ ምላሽ ሰጥተዋል።
ይህ ንግግር በስፍራው የነበሩትን ጃፓናውያን ቢያስደነግጥም፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ታካይቺ ግን ሁኔታውን በዲፕሎማሲያዊ ብልሃት ለማለፍ ሞክረዋል። የትራምፕን ልጅ ባሮንን የልደት ቀን በመመኘትና 250 የቼሪ ዛፎችን (ሳኩራ) ለአሜሪካ በስጦታ በመስጠት ግንኙነቱን ለማለስለስ ጥረዋል።
ሆኖም ከጀርባው የቻይና ተፅዕኖ እና የሆርሙዝ ቦይ የደህንነት ስጋቶች አሁንም በሁለቱ ሀገራት መካከል ውጥረት ፈጥረዋል።

9 months ago
አዲስ የፈጠራ ውጤት፡ በመኪና ወንበር ላይ የሚገጠም የሄልሜት ቅርጽ ያለው ኤርባግ (Airbag) ይፋ ሆነ
አንድ የቻይና የመኪና መለዋወጫ አምራች ኩባንያ የተለመደውን የኤርባግ አሰራር በመቀየር በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነና በመኪና ወንበሮች ላይ የሚገጠም የራስ ቁር(ሄልሜት) ቅርጽ ያለው የደህንነት ከረጢት ይፋ አደረገ። ይህ አዲስ ቴክኖሎጂ በትራፊክ አደጋ ወቅት የተሳፋሪዎችን ደህንነት በከፍተኛ ደረጃ ለማሻሻል ያለመ ሲሆን አሰራሩም ካለው የተለመደ የኤርባግ ቴክኖሎጂ በእጅጉ የተለየ ነው።
ይህ የኤርባግ ስርዓት በአደጋ ወቅት የተሳፋሪውን ራስ፣ አንገት፣ ትከሻ እና የአከርካሪ አጥንትን ሙሉ በሙሉ በመሸፈን የሚከፈት ሲሆን ከጎን በኩል ካሉ ኤርባጎች ጋር በመቀናጀት ተሳፋሪውን እንደ ሄልሜት ከበው በመያዝ ከከባድ ጉዳት ይከላከላል። ይህም በአንድ አቅጣጫ ብቻ ከሚሰነዘር ግጭት ይልቅ ተሳፋሪውን በአራት አቅጣጫዎች በመደገፍ የተሻለ ጥበቃ እንዲያገኝ ያስችለዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ስርዓቱ ከመኪናው አሽከርካሪ ረዳት ቴክኖሎጂ ጋር የተገናኙ ዘመናዊ ሴንሰሮች ያሉት ሲሆን እነዚህም ሴንሰሮች አደጋ በሚከሰትበት ቅጽበት የተሳፋሪው ወንበር ተኝቶ እንደሆነ በመለየት በጥቂት ሚሊሰከንዶች ውስጥ ወንበሩን ወደ ትክክለኛ አቀማመጥ በራሱ የመመለስ ብቃት አላቸው።
ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት ይህ ቴክኖሎጂ ለመጀመሪያ ጊዜ በሁዋዌ እና በቼሪ ኩባንያዎች የጋራ ፕሮጀክት በሆነው ሉክሲድ ቪ9 (Luxeed V9) ሞዴል መኪና ላይ ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ይህ ፈጠራ በመኪና ደህንነት ዘርፍ ላይ አዲስ ምዕራፍ ይከፍታል ተብሎ የታመነ ሲሆን በተለይም የራስና የአንገት ጉዳቶችን በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል።

10 months ago
ሴኔጋል 3-0 ቦትስዋና
ለሴኔጋል ቀኑ ብሩህ ነበር። የዛሬውን አቋም ከደገሙት ምድብ 4ን በአንደኝነት ያጠናቅቃሉ።
የሙኒኩ ኒኮላስ ጃክሰን በሁለቱም አጋማሽ ግቦችን ሲያስቆጥር፣ ቼሪፍ ንዲያዬ ማሳረጊያውን ግብ አስቆጥሯል።
ለሴኔጋል ቀኑ ብሩህ ነበር። የዛሬውን አቋም ከደገሙት ምድብ 4ን በአንደኝነት ያጠናቅቃሉ።
የሙኒኩ ኒኮላስ ጃክሰን በሁለቱም አጋማሽ ግቦችን ሲያስቆጥር፣ ቼሪፍ ንዲያዬ ማሳረጊያውን ግብ አስቆጥሯል።
Sponsored by
Surafel
12 months ago
ተወዳጁ “ልዩ ዓለሜ” ፊልም በሲኒማ ቤቶች በመታየት ላይ ነዉ
ቅዳሜና እሁድ በሁሉም ሲኒማ ቤቶች ይታያል
አለም ሲኒማ
መገናኛ አለም ሲኒማ-
አዶት ሲኒማ
ቫምዳስ ሲኒማ
ሴንቼሪ ሲኒማ
አድዋ ሲኒማ
አምባሳደር ሲኒማ
አምፔር ሲኒማ
ኢትዮጵያ ሲኒማ
“ልዩ ዓለሜ” ፊልም በኢል ሶፊ ፊልም ፕሮዳክሽን የቀረበ
ቅዳሜና እሁድ በሁሉም ሲኒማ ቤቶች ይታያል
አለም ሲኒማ
መገናኛ አለም ሲኒማ-
አዶት ሲኒማ
ቫምዳስ ሲኒማ
ሴንቼሪ ሲኒማ
አድዋ ሲኒማ
አምባሳደር ሲኒማ
አምፔር ሲኒማ
ኢትዮጵያ ሲኒማ
“ልዩ ዓለሜ” ፊልም በኢል ሶፊ ፊልም ፕሮዳክሽን የቀረበ
1 year ago
ስለ ቡና አምስት አስገራሚ እውነታዎች እነሆ!!!
🔹. ቡና ፍሬ ሳይሆን የቤሪ ዝርያ ነው
ብዙ ሰዎች የቡና ፍሬን እንደ እህል ቢቆጥሩም፣ በእውነቱ የቡና ተክል ላይ የሚበቅል የቤሪ ዝርያ ነው። ቡና አብዛኛው ጊዜ “ቼሪ” ተብሎ ይጠራል። በውስጡ ያሉት ሁለቱ ጥራጥሬዎች ደግሞ “የቡና ፍሬ” ተብለው ይጠራሉ፤ የሚጠበሱትና የሚፈጩትም እነዚህ ናቸው።
🔹. ቡና ከውሃ ቀጥሎ በዓለም ላይ በብዛት የሚጠጣ መጠጥ ነው
ከውሃ በስተቀር፣ ቡና በዓለም ዙሪያ በየቀኑ በብዙ ቢሊዮን ሊትር የሚጠጣ መጠጥ ነው። ይህ የሚያሳየው ቡና በብዙ ባህሎች እና ማህበረሰቦች ውስጥ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ነው።
🔹. ቡናን የገዙ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች የኢትዮጵያ ፍየል እረኞች ናቸው
የቡና አመጣጥ ወደ ኢትዮጵያ እና ወደ ቅዱስ ካፋ ክልል ይወሰዳል። አፈ ታሪኮች እንደሚገልጹት፣ ቡናን መጀመሪያ ያገኙት ፍየል እረኞች ናቸው። እረኞቹ የቡና ተክልን ከበሉ በኋላ ፍየሎቻቸው የበለጠ ንቁና ብርቱ እንደሆኑ አስተውለዋል። እረኞቹም ይህን ተክል ለራሳቸው በመጠቀም የቡና መጠጥ መፍጠር ጀመሩ።
🔹. ቡና በካፌይን መጠኑ ሊለያይ ይችላል
ሁሉም ቡና አንድ አይነት የካፌይን መጠን የለውም። ለምሳሌ፣ ቡናው የፈረንሳይ ቡና ከሆነ፣ ጥብስ ቡና ስለሆነ የካፌይን መጠኑ አነስተኛ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን፣ ቀላል እና ቀዝቃዛ ቡና ከሆነ፣ የካፌይን መጠኑ ከፍተኛ ሊሆን ይችላል።
🔹. ቡና ወደ ጠፈር ተጉዟል
የጠፈር ተመራማሪዎች በህዋ ውስጥ ኃይል እንዲኖራቸው ቡና ይዘው ይጓዛሉ። ለጠፈር ጉዞ የሚዘጋጀው ቡና በልዩ ሁኔታ ተጭኖ ወደ ህዋ ይላካል።

Comments