6 hours ago
ኮሜዲያን አስረስ በቀለ (ቼሪ) አዲሱን የልጆች መጽሐፍ ሊያስመርቅ ነው
#ethiopia | አዲስ አበባ፦ ኮሜዲያን፣ የህፃናት መጽሐፍት ደራሲ እና የልጆች ፕሮግራም አዘጋጅ አስረስ በቀለ (ቼሪ) “ኮሚኩ ሙዝ” የተሰኘውን አዲስ የልጆች መጽሐፍ ለማስመረቅ ዝግጅት ማድረጉ ተገለጸ።
የመጽሐፉ ምርቃት እሁድ፣ ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 8:00 ሰዓት ጀምሮ በኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጽሐፍት አገልግሎት ይካሄዳል።
አስረስ በቀለ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የልጆች ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት የሚታወቅ ሲሆን፣ “ቼሪ” የተሰኘውን የልጆች ካራክተር በመፍጠር በህፃናት መዝናኛና ትምህርት ዘርፍ ጉልህ አስተዋፅኦ አበርክቷል።
ደራሲው ከ15 በላይ የልጆች ተረት መጻሕፍትን የጻፈ ሲሆን፣ በ2022 እ.ኤ.አ በEthiopia Reads Children’s Reading Summit ላይ ለህፃናት ሥነ-ጽሑፍ ያበረከተው አስተዋፅኦ እውቅና አግኝቷል።
አዘጋጆቹ ምርቃቱ ለሁሉም ክፍት መሆኑን ገልጸው፣ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር በመገኘት የልጆችን የንባብ ባህል ለማበረታታት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።
✍️ ጌጡ ተመስገን
#getu #getutemesgen #ጌጡ #ጌጡተመስገን #አስረስበቀለ #ቼሪ #ኮሚኩሙዝ #ethiopiareads #የልጆችመጽሐፍ #ንባብ

3 months ago
6ኛው ዓመታዊ የሕፃናት ንባብ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ
#ethiopia | በኢትዮጵያ ውስጥ ላለፉት 22 ዓመታት የንባብ ባህልን ለማስፋፋትና ትምህርትን ለመደገፍ ሲሠራ የቆየው ኢትዮጵያ ሪድስ (Ethiopia Reads)፣ ዘንድሮ ለስድስተኛ ጊዜ ያዘጋጀውን ዓመታዊ የሕፃናት ንባብ ጉባኤ በአዲስ አበባ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል።
"የንባብ ችግኝ በቀዳማይ ልጅነት መትከል" በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ይህ ጉባኤ፣ በሕፃናት የንባብ ዕድገትና በትምህርት ጥራት ዙሪያ ላይ ትኩረት በማድረግ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የሚከናወን ታላቅ መድረክ ነው።
በዚህ ጉባኤ ላይ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የፖሊሲ አውጪዎች፣ የትምህርት ዘርፍ ተመራማሪዎች፣ መምህራን፣ ደራሲያን፣ የአሳታሚ ድርጅቶች ተወካዮች እንዲሁም ከውጭ አገር የመጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
መድረኩ በዋናነት በሕፃናት የንባብ ልምድ ላይ ያተኮሩ ጥናታዊ ጽሑፎች የሚቀርቡበት፣ የፓናል ውይይቶች የሚካሄዱበትና ልምድ የሚለዋወጥበት ሰፊ ዕድል የፈጠረ ሲሆን፣ ይህም በዘርፉ ለሚታዩ ችግሮች ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣትና የንባብ ባህልን ከልጅነት ጀምሮ ለማዳበር ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል።
ኢትዮጵያ ሪድስ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ በሁሉም የአገሪቱ ክልሎች ከ70 በላይ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቤተ-መጻሕፍትን በማቋቋም ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎችና ሕፃናት የንባብ አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ ችሏል።
በተጨማሪም ድርጅቱ ከ"Open Hearts Big Dreams" ጋር በመተባበር "ሬዲ-ሴት-ሪድ" በሚል መጠሪያ የሕፃናት መጻሕፍትን በአሥር አገር በቀል ቋንቋዎች በማዘጋጀትና በማሰራጨት ሕፃናት በትምህርት ቤትም ሆነ በቤታቸው ከወላጆቻቸው ጋር ሆነው እንዲያነቡ ምቹ ሁኔታዎችን ሲፈጥር ቆይቷል።
በአሁኑ ወቅትም ድርጅቱ በደቡብና በኦሮሚያ ክልሎች ትምህርት ቤት መሄድ ለማይችሉ ከ14 ሺህ በላይ ሕፃናት በፈረስና በአህያ በታገዘ ተንቀሳቃሽ የንባብ አገልግሎት መጻሕፍትን እስከ መንደራቸው ድረስ በማድረስ አመርቂ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል።
ይህ የስድስተኛው ዓመታዊ ጉባኤም ድርጅቱ እስካሁን ያከናወናቸውን ተግባራት ከመገምገም ባለፈ፣ ለወደፊቱ የተሻለ የእውቀት ትውልድ ለመቅረጽ የሚያስችሉ ጠቃሚ ግብዓቶችና ምክረ-ሀሳቦች የሚገኙበት እንደሚሆን ታምኖበታል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#ethiopiareads #childrensliteracy #readingculture #ethiopiaeducation #earlychildhoodeducation #bookfair #literacyconference #readysetread

Comments